Lafto Woreda Lebu Communication ላፍቶ ወረዳ ለቡ ኮሙኒኬሽን

Lafto Woreda Lebu Communication  ላፍቶ ወረዳ ለቡ ኮሙኒኬሽን lafto woreda lebu communication

  የማንሰራራት_ቀን"የማንሰራራት ቀን "ን አስመልክቶ የወርቃማ ሰኞ የፓናል ውይይት ተካሄደበንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ  አስተዳደር የጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን አስመ...
07/09/2026

የማንሰራራት_ቀን

"የማንሰራራት ቀን "ን አስመልክቶ የወርቃማ ሰኞ የፓናል ውይይት ተካሄደ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ አስተዳደር የጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን አስመልክቶ የወርቃማ ሰኞ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

የውይይቱ ዋና ዓላማ የማንሰራራት ቀን የሚያስተላልፈውን መልዕክት በማጉላት፣ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችንና ስኬቶችን በመገምገም ቀጣይ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።

በፓናል ውይይቱ የማንሰራራት ትርጉምና ጠቀሜታ፣ ከተሞችን በተሻለ ደረጃ ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች፣ የመንግስት ሰራተኛው የጋራ ኃላፊነት እንዲሁም የተጀመሩ መልካም ተግባራትን ወደ ዘላቂ ልማት ለማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሀሳብ ተለዋውጧል።

ተሳታፊዎችም ያለፈውን ልምድ በመገምገም የተሻለ ነገን ለመገንባት ከግለሰብ እስከ ተቋምና ማህበረሰብ ድረስ የሚጠበቀውን ሚና በተግባር መወጣት እንደሚገባ ተገልጿል።

በወረዳ ደረጃ የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል የነዋሪዎችን ኑሮና የአካባቢውን ገጽታ ለማሻሻል በትብብር መስራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የማንሠራራት ቀን ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ...
07/09/2026

የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።



Guyyaa Bayyanannaa

Itoophiyaa jecha bira darbuun milkaa'ina qabatamaadhaan dhaabbatte!

Kaleessa "Itoophiyaan Kaateetti" gaafa jennu hawwii utuu hin ta'iin dhugaa har'a qabatamaadhaan mirkaneessinedha! Ijaarsa Hidha Haaromsaa Guddicha irraa hanga misooma kooriidarii ammayyaatti, Buufata Xiyyaaraa Bishooftuu guddichaa hanga riifoormii dinagdee maakrootti dadammaqinsi biyya keenyaa gochaan dhugoomeera. Jijjiiramni kun sadarkaa jireenyaa lammiilee keenyaatiin, ammayyoomuu magaalotiifi carraa hojii uumuutiin ifa dhugaa ta'uurraayyuu, mul'ata guddaa abdii egeree ijoollee keenyatti horudha. Kana booda duubatti hin deebinu! Imala bayyanannaa seena-qabeessa eegalleen humna misoomaa keenya caalaatti saffisiisuudhaan olka'insa Itoophiyaa gara badhaadhina waaraatti ol ni kaafna.

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።ለቤተሰቦቿ ፣...
06/09/2026

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።

አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።
ለቤተሰቦቿ ፣ለወዳጅ ዘመዶቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሷን በአፀደ ገነት ያኑር

Lubbuun darbuu Artistii fi Qabsooftuu Bilisummaa Ilfinash Qannoo kanan dhagahe gadda guddaa keessatti.

Artist Ilfinash weellistuu qofa osoo hin taane qabsooftuu mirga namummaa fi wal-qixummaa turte.
Maatii ishee, firoottan ishee fi dinqisiifattoota isheef jajjabinan hawwa.
Waaqni Lubbuu ishee Jeennata haa jiraachisu

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

06/09/2026
"በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመያዝ ያለምንም ቀስቃሽ አከበቢያችንን እናፀዳለን"  ነዋሪዎች​ላፍቶ፣ ወረዳ 01 ለቡጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም.፦ "በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመያዝ ያለ...
06/09/2026

"በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመያዝ ያለምንም ቀስቃሽ አከበቢያችንን እናፀዳለን"

ነዋሪዎች

​ላፍቶ፣ ወረዳ 01 ለቡጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም.፦ "በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመያዝ ያለምንም ቀስቃሽ አከበቢያችንን እናፀዳለን" የወረዳዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

​በዛሬው ዕለት የጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀንን አስመልክቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ ለቡ አስተዳደር የፅዳት ንቅናቄ ተካሂዷል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ጽዳትና ዉበት አስተባባሪነት “በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ በመያዝ ያለምንም ቀስቃሽ አከበቢያችንን እናፀዳለን ”በሚል መሪ ሃሳብ የአንድ ማእከል የጽዳት ንቅናቄ የከተማ ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተገኙበት በክላስተር 1 በተለምዶ ተገጣጣሚ አከባቢ በሚባለዉ ሰፈር አካሄደ፡፡

ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገራት ከሚለያት ነገሮች አንዱ የራሷ የዘመን መለወጫ መኖሯ መሆኑን ገልጸው አዲሱን ዓመት ለመቀበል የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበሩ እንደሚገኙና የዛሬው የፅዳት ዘመቻም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም ለህብረተሰባችን ፅዳት፣ ለአካባቢው ውበትና ወንድማማችነት መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው አብራርተዋል።

በተለይም በበዓላት ወቅት ሁሉም ነዋሪዎች የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን በመተግበር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

​በተጨማሪም አዲሱን ዓመት በቆሸሸ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በቆሸሸ አስተሳሰብም ላለመቀበል ዝግጁ መሆን ይገባል ብለዋል።

#ወረዳ 01 ለቡ ኮሙኒኬሽን

የእመርታ ቀን አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባ...
06/09/2026

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡ የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡

በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ጳጉሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም

# የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

Addis Ababa

Telephone

+251933584761

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto Woreda Lebu Communication ላፍቶ ወረዳ ለቡ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Lafto Woreda Lebu Communication ላፍቶ ወረዳ ለቡ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share