Akaki kality woreda 7 communication-አቃቂ ቃሊቲ

Akaki kality woreda 7 communication-አቃቂ ቃሊቲ communication center for woreda 7 community
(1)

ለነዋሪው እፎይታን የሰጡ  የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላት በአዳስ አበባየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኑሮ ውድነት መባባስ መንስኤ የሆኑትን የምርት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የፍጆታ እና ...
04/09/2026

ለነዋሪው እፎይታን የሰጡ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላት በአዳስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኑሮ ውድነት መባባስ መንስኤ የሆኑትን የምርት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የፍጆታ እና የሰብል ምርቶች አቅርቦት ከአርሶ አደሮች፣ ከዮኔን እና ከባለሀብቶች ጋር በማስተሳሰር ምርት ወደ ከተማ በቀጥታ እንዲገባ በማድረግ ሸማቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላትን በተለያዩ ቦታዎች በመገንባት ለህዝብ ጥቅም እያዋለ ይገኛል፡፡

በተለይም በከተማዋ ለዋጋ ንረትና ለንግድ ሚዛን መዛባት ምክንያት የሆኑ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች እና ደላሎች ላይ ህጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በገበያው ላይ ይታይ የነበረውን የዋጋ ንረት በነዚህ የአንድ ማዕከል የገቢያ ማዕከላት አማካኝነት በማስቀረት ገቢያው እንዲረጋጋ ማድረግ ችሏል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ግንባታውን አጠናቆ ለህዝብ ክፍት ያደረገው 7ኛውን የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው ።

በለሚ የአንድ ማዕከል ገቢያ በሸማቹ እና በአምራች መሀከል የቀጥታ ግንኙነት እንዲኖር በማድረግ ማህበረሰቡ ለዕለት ፍጆታ የሚጠቀምባቸውን የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የበርበሬና የቅመማቅመም ምርቶች እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በአንድ ማዕከል መሸመት እንዲችሉ እድል ፈጥሯል ፡፡

በዚህ ሁለገብ የገቢያ ማዕከል የሚቀርቡ ምርቶች ከ15 እስከ 20 በመቶ የዋጋ ቅናሽ የሚሸጥበት፣ ዋጋ የሚያንረውን ህገ ወጥ የደላላ ሰንሰለት በመበጣጠስ ከአምራቹ ያልተቋረጠ ምርት የሚቀርብበትና የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በመረዳት ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የተቻለበት ስኬታማ ስራ ነው።

የአንድ ማእከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ::                              ነሃሴ 29/2018 ዓ/ም          የወረዳ 7 ኮሙኒኬሽንበአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ...
04/09/2026

የአንድ ማእከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ::

ነሃሴ 29/2018 ዓ/ም
የወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 7 አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ከቃሊቲ ፖሊስ መምሪያጋር በመተባበር የአንድ ማእከል የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ መዋቅር ስምሪት ተሰጠ።

በስምሪቱ ላይ የወረዳ 7 ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዝምይበሉ ወልዴን ጨምሮ የወረዳው አመራሮች፣ ፓሊሶች፣ የደንብ ኦፊሰሮችና የሰላም አምባሳደር ሰላም ሰራዊቶች ተገኝተዋል።

የሰላም ሰራዊቱ በተሰጠው ስምሪት መሰረት በአካባቢው ሰላምን በማስፈን፣ ማህበረሰቡን በማሳተፍ እና የሰላም እሴቶችን በማጠናከር ረገድ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ አፅንኦት ተሰጥቷል።

ስምሪቱም በተለያዩ የሰላም ስራዎች ላይ የሚሳተፉ አካላትን በማስተባበር ሰላማዊ እና የተቀናጀ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።



ለተጨማሪ መረጃዎችና ዜናዎች ገጾቻችንን ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇

https://linktr.ee/Akkworeda7communication_office

04/09/2026
የጥንቃቄ መልዕክት !!በዓላትን በደስታና በፍቅር እንዲጠናቀቁ የእሳት አደጋ ስጋቶችን አስቀድመን እንከላከል!ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ  የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ...
04/09/2026

የጥንቃቄ መልዕክት !!

በዓላትን በደስታና በፍቅር እንዲጠናቀቁ የእሳት አደጋ ስጋቶችን አስቀድመን እንከላከል!

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

ህብረተሰቡ አዲስ ዓመትን ሲያከብር ከምግብ ዝግጅት፣ ከኤሌክትሪክና ከሻማ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎችን ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። "ጥንቃቄ ባህላችን እናድርግ" በሚል መርህ የአደጋ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ቀድሞ በማስወገድ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በአካባቢው ማንኛውንም የአደጋ ስጋት ሲመለከት ወይም ድንገተኛ አደጋ በሚያጋጥምበት ወቅት በነፃ የስልክ መስመር 939 ላይ በመደወል ፈጣን ጥቆማ እንዲሰጥ እና ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አስተላልፏል።

የአደጋ ግዜ ስልክ ቁጥሮች

011-4-34-00-96

011-4-34-30-63
011-4-34-35-76

በነዚህ ቁጥሮች ጥሪ ማስተላለፍ ይችላሉ!

"ጥንቃቄን ባህላችን እናድርግ" !!!

 #በወረዳ 7 አስተዳደር የዘመን መለወጫ በአል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል!በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያዎ ይሸምቱ!
04/09/2026

#በወረዳ 7 አስተዳደር የዘመን መለወጫ በአል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል!

በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያዎ ይሸምቱ!

ለአዲስ ዓመት በቂ  የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸየአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶች...
04/09/2026

ለአዲስ ዓመት በቂ የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማዋ ነዋሪዎች መቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኮሚሽኑ የገበያ ጥናትን መሠረት በማድረግ በበዓላት ወቅት በገበያ ላይ የሚፈጠረውን ፍላጎት በመለየት በቂ የፍጆታ ምርቶች እንዲቀርቡ በስፋት መስራቱን ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሽታዬ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ ከአምራቾች፣ ከአስመጪዎች፣ ከዩኒየኖችና ከተለያዩ የኀብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመተባበር የምርት ትስስር በመፍጠር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች እንዲሁም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች በበቂ መጠን መቅረቡን አስረድተዋል።

እነዚህ ምርቶች በከተማው በሚገኙ በዘመኑ 700 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ በአዲስ ዓመት ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በ154 የኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በስፋት ለሸማቹ እየቀረቡ መሆናቸውን ኮሚሽነሯ ገልጸዋል።

ከነፃ ገበያው ጋር ሲነፃፀር በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡት እነዚህ ምርቶች የከተማዋን ነዋሪዎች የበዓል ፍላጎት በማሟላት የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና ገበያውን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በበዓሉ ወቅት 27/4 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሉካንዳ ሥጋ ቤቶች ሥጋን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ዝግጅት መደረጉን ወ/ሮ ሽታዬ ገልጸው፤ ይህም በበዓሉ ወቅት የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

ዋና ኮሚሽነሯ በመጨረሻ ህብረተሰቡ ምርቶቹን ከኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች፣ ከኤግዚቢሽንና ባዛር ማዕከላት እንዲሁም ከቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በመግዛት ከተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኮሚሽኑም በበዓላት ወቅት የምርት አቅርቦትና የገበያ መረጋጋት ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ መከታተሉን አረጋግጠዋል።

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ፣በብዙ አማራጭ በባዛር ይሸምቱ!የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲበአቃቂ ...
04/09/2026

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ፣በብዙ አማራጭ በባዛር ይሸምቱ!

የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈተው የበዓል ባዛር እና በዛሬው ዕለትም ህብረተሰቡ የግብይት ሂደቱን በደመቀ ሁኔታ እያከናወነ ይገኛል።

በዚህ ባዛር ላይ አምራቾች የህብረት ስራ ማህበራት እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ናቸው። ይህም ደንበኞች ጥራት ያላቸውን መሰረታዊ የቤት ውስጥና የበዓል ሸቀጦች በግልጽና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበዩ ዕድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም የበዓል ገበያው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና ማህበረሰቡ አዲሱን ዓመት ያለ አላስፈላጊ የኢኮኖሚ ጫና በደስታ እንዲያከብር ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ዓለም ዕውቀና የቸረው የአዲስ አበባ የትውልድ ግንባታ ተግባር ዛሬን በሰው ተኮር ተግባራቶቿ የብዙዎች የከተማው ነዋሪዎቿ እንባ ያበሰችው አዲስ አበባ፤ ነገዋን ብሩህ ለማድረግ ደግሞ በትውልድ ...
04/09/2026

ዓለም ዕውቀና የቸረው የአዲስ አበባ የትውልድ ግንባታ ተግባር

ዛሬን በሰው ተኮር ተግባራቶቿ የብዙዎች የከተማው ነዋሪዎቿ እንባ ያበሰችው አዲስ አበባ፤ ነገዋን ብሩህ ለማድረግ ደግሞ በትውልድ ግንባታ ላይ ያልተቆጠቡ ስራዎችን እያከናወነች ነው፡፡

የዛሬ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢ ናቸው በሚል መርህ ባለፉት ሶስት ዓመታት አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ የምትመች ምርጧ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ የተሰራው ስራ እና የተገኘው ውጤት ፈርጀ ብዙ ነው፡፡

የሰው ልጅ አእምሮ በህይወት ዘመኑ ከሚያሳየው አጠቃላይ እድገት ውስጥ እጅግ ፈጣኑ እና ወሳኙ ክፍል በመጀመሪያዎቹ የልጅነት ዓመታት ውስጥ የሚከናወን ነው፡፡

የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህፃናት እድገት ማዕከል እና የአለም ጤና ድርጅት ሳይንሳዊ መረጃ እንደሚያሳየው የህፃናት የአዕምሮ ዕድገት አስከ ሶስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ 80 በመቶ እንደሚጠናቀቅ ሲያረጋግጥ፤ ይህ እድገት ከ5- 6 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶ ላይ እንደሚደርስ ሳይንሳዊ ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ህፃናት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚያገኙት እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ጥሩ አመጋገብ እና ማነቃቂያ (ጨዋታ፣ ንባብ፣ የንግግር ችሎታ) የወደፊት አእምሯዊ ብቃታቸውን ይወስናል።

በመሆኑም በቀዳማይ ልጅነት መረኃ ግብር ላይ መስራት ለወደፊት ትውልድ ግንባታ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመሰጠት በለፉት ዓመታት ውጤታማ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ በቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብሩ የህፃናት የተቀናጀ የጤና እና የክትትል አገልግሎት በተጨማሪ በህፃናት ማቆያ እና የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ያሉ የህፃናት ማቆያዎች 11 ብቻ ነበሩ ዛሬ 1100 ደርሰዋል፤ 20 የነበሩት የህፃናት መጨወቻዎች አሁን 5 ሺህ ደርሰዋል። ይህ መዋቅራዊ ለውጥ ነው፡፡
ቤተሰቦቻቸው መክፈል ለሚችሉ ህፃናት ብቻ ተትቶ የነበረው የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሁን በአዲስ አበባ ለሁሉም ሆኗል፤ ልጆቻቸው እስኪያድጉ ከስራ ገበታ እርቀው ለኢኮኖሚ ችግር ይጋለጡ የነበሩ እናቶች ዛሬ ላይ ግን በተዘጋጀው የህዝብ የህፃናት ማቆያ ልጆቻቸውን በማስቀመጥ አምራች ወደሚያደርጋቸው የስራ ገበታ ላይ መሰማራት እንዲችሉ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ መራኃ-ግብር በአዲስ አበባ 1.3 ሚሊዮን ህፃናት በመረኃ ግብሩ ታቅፈው ተጠቃሚ እየሆኑ ሲሆን ፕሮግራሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ እምርታዊ ለውጥ እያስመዘገባ ይገኛል፡፡

ዋና መቀመጫው በእንግሊዝ ለንድ የደረገው Act For Early Years ኢኒሼቲቭ በፈረንጆቹ 2023 በይፋ ስራውን የጀመረ ሲሆን መሰረታዊ እንክብካቤ እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት የተነፈጉ ከ350 ሚሊዮን በዓለም ላይ የሚገኙ ህፃናትን ችግር እልባት ለመስጠት የተመሰረት ኢንሼቲቭ ነው፡፡

ኢንሼቲቩ በዋናነት የመንግስታት እና ፖሊሲ አውጪዎችን ግንዛቤ በመለወጥ ከጽንሰት እስከ ስድስት ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት ጉዳይ ትኩረት እዲሰጥ ማድረግ ሲሆን ፕሮግራሙ በበርካታ ሀገራት ተግባራዊ ሲደረግ በእነዚህ ዓመታት ውስጥም አዲስ አበባ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ግንባር ቀደም ከተማ ስትባል፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤም በኢንሼቲቩ"የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን" ማዕረግን ተቀዳጅተዋል፡፡

ይህን እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

ከመኪና ሽያጭ ጋር ተያይዞ የሕግ ጥሰቶች የሚፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በመዲናዋ በመኪና አስመጪዎች እና በኮሚሽን ሠራተኞች በኩል የሚፈጸምን የታ...
04/09/2026

ከመኪና ሽያጭ ጋር ተያይዞ የሕግ ጥሰቶች የሚፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በመዲናዋ በመኪና አስመጪዎች እና በኮሚሽን ሠራተኞች በኩል የሚፈጸምን የታክስ ስወራ እና የግብር ማጭበርበር ድርጊት ለመግታት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ በርካታ የመኪና አስመጪዎች ለከተማ አስተዳደሩ የሚገባውን ወርሃዊ ቫት እና ዓመታዊ ግብር ላለመክፈል ሲሉ ሽያጮቻቸውን በኮሚሽን ሠራተኞች አማካይነት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በተጨማሪም አብዛኞቹ አስመጪዎች አድራሻቸው ሳይታወቅ ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ ከፍተኛ የግብር ስወራ ወንጀል እንደሚፈጽሙ በተካሄደው ጥናት መረጋገጡ በመግለጫው ተጠቅሷል።

በታክስ ሕጉ መሠረት በሌሎች ክልሎች የተመዘገቡ አስመጪዎች አዲስ አበባ ውስጥ ሽያጭ ለማካሄድ በሚያስችል መልኩ የክልል ንግድ ፈቃዱን ማስጠቀስ፣ የመሸጫ ቦታ መከራየት እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖቻቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።

ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት በኮሚሽን ሠራተኞች አድራሻ ሳይሆን ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ሊሆን እንደሚገባም ቢሮው አሳስቧል።

የኮሚሽን ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሠራተኞችም ቢሆኑ በኮሚሽን ፈቃድ የመኪና መሸጫ ግቢዎችን ተከራይተው ከአስመጪዎች የተረከቧቸውን መኪኖች መሸጥ በሕግ ተጠያቂ የሚያደርግ የታክስ ስወራ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።

ቢሮው ከመኪና ሽያጭ ጋር ተያይዞ የሕግ ጥሰቶችን የሚፈጸሙ አካላት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሕግ የማስከበር እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

Address

Addis Ababa

Telephone

114395928

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki kality woreda 7 communication-አቃቂ ቃሊቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share