14/03/2024
አስደሳች ዜና
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነዉን "ሰላምን " ሰርቆ ለሌላ ሀገር አሳልፎ ለመሸጥ ሲስማ አደገኛው ሌባ እጅ ከፍንጅ ተይዟል
ሰላምም ከተደበቀችበት ወጥታ ወደ ሀገሯ እንድትመለሰች ተሰማ :: ይህ የሆነዉ በሙስሊም እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያን የመረረ ፆለት እንደ ሆነ ከእምነት ቦታዎች "የፍቅር ከተማ" ከተሰኘዉ የተገኘዉ መረጃ ገልፇል ::
ሌባውም ከተደበቀበት ንብረቱንም ከሰወረበት የወጣ ሲሆን ሌባው እንዴት እንደሰረቀ ሲናገር ሁሉም በማህበራዊ ሚዲያ ተጥዶ ቢሞቅ ቢደፋ ቢጣድ ቢፈላ ግድ ባላለበት ወቅት ምቹ አጋጣሚ አግኝቶ የሰረቀ መሆኑን ተናግሮ የደበቀበት ቦታም እሚካላ እና እሾ ከበዛበት መሆኑ ተገልፇል
ሰላምም በሰላም የተመለሰች ስትሆን ደማቅ አቀባበል ተደርጎ ህዝብ እንዲጠብቅ ለሀይማኖት አባቶች ለሀገር ሽማግሌዎች ለአባ ገዳዎች ለሀደ ስንቄዎች የበላይ ጠባቂነት ሁሉም ወጣቶች እንዱጠብቁ አደራ ተሰጥቷል ::እኛም በያለንበት ሰላም ዋጋዋ ተመን የማይወጣላት ንብረትነቷም የህዝብ በህዝብ የምትጠበቅ የህዝብ በመሆኗ አደራውን ተቀብለናል ::