Ethio-Cert

Ethio-Cert We are the first Cyber Emergency Response Team in Ethiopia. Ethio-CERT helps you prevent, detect, respond.

01/09/2026
የ29 ደቂቃው የስጋት ጊዜ*******************አጭበርባሪዎች አሁን ላይ ሲስተም ሰብረው ከመግባት (Hacking) ይልቅ፣ የተሰረቁ የተጠቃሚ ስሞችን እና የይለፍ ቃላትን በመጠቀም በቀ...
01/09/2026

የ29 ደቂቃው የስጋት ጊዜ
*******************
አጭበርባሪዎች አሁን ላይ ሲስተም ሰብረው ከመግባት (Hacking) ይልቅ፣ የተሰረቁ የተጠቃሚ ስሞችን እና የይለፍ ቃላትን በመጠቀም በቀጥታ በመግባት (Logging in) እና AIን በመጠቀም ጥቃታቸውን በፍጥነት ያፋጥናሉ።

እንደ CrowdStrike Global Threat Report 2026 መረጃ፣ አጥቂዎች ወደ ኔትወርክ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ መረጃ እስከ ማሾለክ የሚያስፈልጋቸው አማካይ ጊዜ (Breakout Time) ወደ 29 ደቂቃ ዝቅ ብሏል (በ2022 ከነበረበት 84 ደቂቃ)።

አስፈላጊ የመከላከያ እርምጃዎች
የተጠቃሚ ባህሪን መከታተል (UEBA)፦ አጥቂዎች በህጋዊ ሰራተኛ ስም ስለሚገቡ በስም ብቻ ማመን አይቻልም። ያልተለመዱ ድርጊቶችን (ለምሳሌ፡ ያልተለመደ የSaaS መተግበሪያዎች አጠቃቀም፣ ያልተለመደ የፋይል ማውረድ ) ለመለየት የባህሪ ትንተና (UEBA) መጠቀም ያስፈልጋል።

የAI ድክመቶችን በፍጥነት መደፈን (Rapid Patching)፦ አጥቂዎች በስርዓቶች ላይ ያሉ አዳዲስ ድክመቶችን (Zero-days) በወራት ሳይሆን በቀናት ውስጥ ለማግኘት AI ይጠቀማሉ። ስለዚህ ለአደጋ የተጋለጡ ሲስተሞችን በፍጥነት የማዘመን (Patching) አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ነው።

የተግባር ልምምድ እና አውቶሜሽን (Response Drills)፦ በ29 ደቂቃ ውስጥ የሰው ልጅ ብቻ ተከታትሎ ጥቃትን መግታት ስለሚከብደው፣ አጠራጣሪ ድርጊቶች ሲታዩ ሲስተሙ እራሱ ወዲያውኑ ገድቦ የሚያቆምበትን አውቶሜሽን እና የልምምድ ፕሮግራሞችን መተግበር ያስፈልጋል።

‎የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት የኤክስ (X) ገፅ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመበት።‎*************‎የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት ኦፊሴላዊ የኤክስ (X) ገፅ  የሳይበር ጥቃት  እንደተደረገበት አስታወቀ...
31/08/2026

‎የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት የኤክስ (X) ገፅ የሳይበር ጥቃት ተፈጸመበት።
‎*************
‎የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት ኦፊሴላዊ የኤክስ (X) ገፅ የሳይበር ጥቃት እንደተደረገበት አስታወቀ፤ ይህም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በናይጄሪያ ወታደራዊ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት ላይ የተፈጸመ ሁለተኛው የሳይበር ጥቃት ነው።

‎ቅዳሜ ዕለት ከቀኑ 9:50 ገደማ የጦር ሰራዊቱ መለያ "memecoin" ከተሰኙት የዲጂታል ገንዘብ ዓይነቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ማሰራጨት የጀመረ ሲሆን፣ በመቀጠልም ድርጊቱ የሳይበር ደህንነት ስጋት መሆኑ ተረጋግጧል።

‎የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አፖሎኒያ አኔሌ በሰራዊቱ ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ አደጋውን አረጋግጠዋል።

‎"የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት በኦፊሴላዊ የኤክስ (ቀደም ሲል ቴሌግራም/ትዊተር) መለያው ላይ የተደረገውን ያልተፈቀደ የመግባት ሙከራ ደርሶበታል፤ አሁንም ፈጣን ምላሽ እየሰጠ ይገኛል" ብለዋል።

‎አኔሌ አክለውም፣ ገፁን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ፣ ተጨማሪ ያልተፈቀዱ Loginoችን ለመከላከል እና በገጹ የሚሰራጩ መረጃዎችን አስተማማኝነት ለመጠበቅ ወዲያውኑ ቴክኒካዊ እና የጥበቃ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

‎"የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት የተጎዳውን መለያ ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እና አስተዳደራዊ ቁጥጥሩን መልሶ ለመቆጣጠር አግባብ ያላቸው እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ለህዝቡ፣ ለብዙሃን መገናኛዎች እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ያረጋግጣል" ብለዋል።


‎የሳይበር ደህንነትን ለማጠናከር እና ወቅታዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለማግኘት የ Ethio- CERTን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ።
‎ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
‎• ድረ ገጽ፦ https://www.ethiocert.gov.et/
‎•ሊንክዲን (LinkedIn) ፦ https://www.linkedin.com/company/ethio-cert/
‎•ቲክቶክ (Tiktok) ፦ https://www.tiktok.com/
‎• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

3ቱ የUK ኤርፖርቶች የሳይበር ጥቃት ደረሰባቸው*******************በሶስት የዩናይትድ ኪንግደም (UK) ኤርፖርቶች የመኪና ማቆሚያ፣ የፋስት ትራክ (ፈጣን ማለፊያ) ቦታ ማስያዣዎችን...
28/08/2026

3ቱ የUK ኤርፖርቶች የሳይበር ጥቃት ደረሰባቸው
*******************
በሶስት የዩናይትድ ኪንግደም (UK) ኤርፖርቶች የመኪና ማቆሚያ፣ የፋስት ትራክ (ፈጣን ማለፊያ) ቦታ ማስያዣዎችን እና የኤርፖርት ውስጥ የዋይፋይ ምዝገባዎችን የሚመለከቱ የደንበኞች መረጃዎች ያልተፈቀደለት ሦስተኛ ወገን በእጁ አስገብቷል። ድርጅቱ የተሳፋሪዎች ደህንነት እና የአቪዬሽን ደህንነት አደጋ ውስጥ አለመውደቁንና የኤርፖርት ስራዎች በሙሉ ያለ ምንም እንቅፋት መቀጠላቸውን አረጋግጧል።

የተወሰደው መረጃ የደንበኞችን የኢሜይል አድራሻዎች፣ የስልክ ቁጥሮች፣ የመኪና ሰሌዳ ቁጥሮች እና የፖስታ ኮዶችን ያካትታል። ድርጅቱ (MAG) እርሱም ሆነ ጥቃቱ የደረሰበት ስርዓት የደንበኞችን የባንክ ወይም የከፈያ መረጃዎችን እንደማይይዙ አስታውቋል። ተጨማሪውን ለማንበብ ሊንኩን https://www.ethiocert.gov.et/news/%E1%8B%A8uk-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%B3%E1%8B%AD%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8C%A5%E1%89%83%E1%89%B5

የሳይበር ደህንነትን ለማጠናከር እና ወቅታዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለማግኘት የ Ethio- CERTን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ።
‎ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
‎• ድረ ገጽ፦ https://lnkd.in/e_ZNJkew
‎•ሊንክዲን (LinkedIn) ፦ https://lnkd.in/dWhnui6U
‎•ቲክቶክ (Tiktok) ፦ https://lnkd.in/dYDfNbEY
‎• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

ዋትስአፕ አዳዲስ የደህንነት ማሻሻያዎችሜታ (Meta) በዋትስአፕ (WhatsApp) ላይ ማጭበርበርን (Phishing)  የሚከላከሉ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አድርጓል!በአዲሱ ማሻሻያ የተካተቱ ...
26/08/2026

ዋትስአፕ አዳዲስ የደህንነት ማሻሻያዎች
ሜታ (Meta) በዋትስአፕ (WhatsApp) ላይ ማጭበርበርን (Phishing) የሚከላከሉ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አድርጓል!

በአዲሱ ማሻሻያ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
በርካታ የፓስኪ (Multiple Passkeys) ድጋፍ፦ አሁን በሁለቱም iOS (iPhone) እና Android ስልኮች አንድን የዋትስአፕ መለያ በባዮሜትሪክስ (የፊት ወይም የጣት አሻራ) በመጠቀም መግባት ይቻላል።
እንዴት ማስተካከል ይቻላል? ወደ Settings > Account > Passkeys በመሄድ ማስተካከል ይችላሉ።

ጠንካራ የይለፍ ቃል (Full Password) ፦ ቀደም ሲል የነበረው ባለ 6-አሃዝ PIN አሁን ወደ ሙሉ ይለፍ ቃል ተቀይሯል። ረጅም፣ ፊደላት፣ ቁጥሮች እና ልዩ ምልክቶችን (Special Characters) በማካተት አካውንቶን ከመጠለፍ ይ ጠብቁ።

ያልታወቁ ጥሪዎች ተጨማሪ መረጃ (Call Context for Unknown Numbers)፦ በስልክዎ ያልተመዘገቡ (unknown contacts) ሲደውሉ ፣ ጥሪው ከየት እንደተደወለ፣ ከደዋዩ ጋር የጋራ ግሩፕ ካለዎት እና ደዋዩ በስልክዎ መመዝገቡን የሚገልፅ ተጨማሪ መረጃ በስክሪንዎ ላይ ያሳያል።

ምን ማድረግ አለብዎት?
የዋትስአፕ መተግበሪያዎን አሁኑኑ Update ያድርጉ።
ወደ መተግበሪያው በመግባት የፓስኪ (Passkey) እና የሁለት-ደረጃ ማረጋገጫ የይለፍ ቃልዎን ያጠናክሩ!

ከዲጂታል ማስታወቂያዎች (Digital Ads) ጀርባ ያሉ አዳዲስ የሳይበር ስጋቶች*****************በቅርቡ ካስፐርስኪ (Kaspersky) ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሳይበር ወንጀለ...
24/08/2026

ከዲጂታል ማስታወቂያዎች (Digital Ads) ጀርባ ያሉ አዳዲስ የሳይበር ስጋቶች
*****************
በቅርቡ ካስፐርስኪ (Kaspersky) ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሳይበር ወንጀለኞች ሰዎችን በግል ለይተው ጥቃት ለማድረስ የዲጂታል ማስታወቂያ ቴክኖሎጂዎችን (Digital Advertising Systems) እንደ አዲስ መሳሪያ መጠቀም ጀምረዋል።

ስጋቱ ምንድን ነው?
ለእርስዎ የሚሆኑ ማስታወቂያዎችን ለመምረጥ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን (የመቃኘት ልማድ፣ የጂኦግራፊያዊ ቦታ እና የመሳሪያ አይነት) ወንጀለኞች ተጠቅመው ሰዎችን ይከታተላሉ። በተጨማሪም በአንዳንድ አፕሊኬሽኖች እና ድህረ ገጾች ላይ የሚወጡ የውሸት ማስታወቂያዎች (Malvertising) ተጠቃሚዎችን ወደ አደገኛ ድህረ ገጾች በመምራት ማልዌር (Malware) መሳሪያዎ ላይ እንዲጫን ያደርጋሉ።

ራሷን እና ድርጅትዎን እንዴት ይጠብቃሉ?
ለግል ተጠቃሚዎች፡
አጠራጣሪ ማስታወቂያዎችን አይጫኑ፡ አፕሊኬሽን ወይም ድህረ ገጽ ላይ የሚወጡ እጅግ ማራኪ ወይም አስቸኳይ የሚመስሉ ማስታወቂያዎችን ከመጫን ይቆጠቡ።

የአፕሊኬሽን ፈቃዶችን (Permissions) ይቀንሱ፡ አፕሊኬሽኖች አስፈላጊ ካልሆነ በቀር የቦታዎን (Location) እና ሌሎች የግል መረጃዎችን የማግኘት ፈቃድ ይከልክሉ።

የማስታወቂያ ማገጃ (Ad Blocker) ይጠቀሙ፡ አስተማማኝ የማስታወቂያ ማገጃ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ተገቢ ያልሆኑ ማስታወቂያዎችን እና አደገኛ ማዞሪያዎችን (Redirects) ያግዱ።

ለድርጅቶች እና ኩባንያዎች፡
በኩባንያ ስራ ላይ በሚውሉ ኮምፒውተሮች እና ስልኮች ላይ የማስታወቂያ ማገጃዎችን (Ad Blockers) መጫን።

አደገኛ ማስታወቂያዎችን እና የሳይበር ጥቃቶችን በቅድሚያ የሚለዩ የደህንነት ሶፍትዌሮችን (እንደ EDR እና Anti-Targeted Attack Solutions) መጠቀም።

በAndroid የመኪና ስክሪኖች ላይ የሚሰራጭ አደገኛ ማልዌር ተገኘ!******************‎የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በ DoFun በተገነቡ  የመኪኖች የመረጃና መዝናኛ ስርዓት (...
22/08/2026

በAndroid የመኪና ስክሪኖች ላይ የሚሰራጭ አደገኛ ማልዌር ተገኘ!
******************
‎የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በ DoFun በተገነቡ የመኪኖች የመረጃና መዝናኛ ስርዓት (Android head unit) ሶፍትዌሮችን ለመበከል ታስቦ የተሰራ አዲስ የማልዌር አይነት (Malware Family) አግኝተዋል።

‎ስጋቱን ያገኘው ካስፐርስኪ (Kaspersky) እንዳለው፣ የማልዌሩ ዋና ዓላማ የባለብዙ-ደረጃ ማውረጃዎችን (multi-stage downloader) በመጫን የማስታወቂያ ማጭበርበር (ad fraud) መስራት እና የፕሮክሲ ቦትኔት (proxy botnet) መፍጠር ነው።

‎"ማልዌሩ የተሰራጨው በአንድሮይድ መኪና የመረጃና መዝናኛ ስርዓት ላይ በሚገኙ የውስጥ ማዘመኛዎች (built-in updaters) በኩል ነው" ሲሉ የደህንነት ተመራማሪው ዲሚትሪ ካሊኒን ተናግረዋል።

‎የመኪና መረጃና መዝናኛ ስርዓት (Head unit) መልቲሚዲያዎችን የመቆጣጠር እና የመኪናውን የተወሰኑ ክፍሎች የማስተዳደር ማዕከል ነው። ከፋብሪካው ተገጥሞ የሚወጣ ወይም አሮጌ መኪኖች ላይ በኋላ የሚገጠም (aftermarket upgrade) ሊሆን ይችላል። በአንድሮይድ የሚሰሩ ስርዓቶች በሁለቱም በኩል ተዋቂ በመሆናቸው፣ አብዛኛዎቹ መደበኛ መተግበሪያዎች እና ማልዌሮች በእነሱ ላይ መስራት ይችላሉ። ይህም የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥ የ SIM ካርድ ማስገቢያ ስላላቸው ለአጥቂዎች ምቹ ያደርጋቸዋል።

‎"የእነዚህ ማልዌሮች ማሰራጫ መንገድ በጣም የተወሳሰበ እየሆነ መጥቷል" ብለዋል ካሊኒን። "በዚህ ጥናት ወቅት የሶፍትዌር ማዘመኛዎችን ተፎካካሪ በመጠቀም የተፈጸመ የበለጠ የረቀቀ ጥቃት ተመልክተናል።"

‎ጥቃቱ የጀመረው TWCore ("com.tw.core") ከተሰኘው ህጋዊ የሲስተም መተግበሪያ ሲሆን፣ አጥቂዎቹ ይህንን የማዘመኛ መስመር ተጠቅመው JarService የተሰኘ ማልዌር ጭነዋል። ማልዌሩ የሚከተሉትን ያደርጋል:

‎የተበከለውን መሳሪያ መረጃ ወደ አጥቂዎቹ ሰርቨር ይልካል።

‎ሰርቨሩ ቀጣዩን ጎጂ ፋይል ለማውረድ የሚያስችል ሊንክ ይመልሳል።

‎ማልዌሩ ተራ መተግበሪያ መስሎ ከጀርባ ይሰራል፤ በየ 90 ደቂቃው ከቁጥጥር ሰርቨሩ (C2) ጋር ይገናኛል።

‎ሰርቨሩ ትእዛዞችን በመላክ መሳሪያውን ይቆጣጠራል።

‎ማልዌሩ ያልተፈለጉ ማስታወቂያዎችን ማሳየት፣ ተጨማሪ ጎጂ ሶፍትዌሮችን ማውረድ እና የመሳሪያውን ዝርዝር መረጃዎች (የስክሪን ጥራት፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ የ Wi-Fi መረጃ እና የ MAC አድራሻ) ለአጥቂዎች መላክ የሚያስችሉ 9 ትእዛዞችን ይደግፋል።

‎የሳይበር ደህንነትን ለማጠናከር እና ወቅታዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለማግኘት የ Ethio- CERTን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ።
‎ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
‎• ድረ ገጽ፦ https://www.ethiocert.gov.et/
‎•ሊንክዲን (LinkedIn) ፦ https://www.linkedin.com/company/ethio-cert/
‎•ቲክቶክ (Tiktok) ፦ https://www.tiktok.com/
‎• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

በማይክሮሶፍት አዙር (Azure) መረጃ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የMcDonald እና የVodafone ሰራተኞች መረጃ ተሰረቀ።*************************TheHatman በመባል የሚታወ...
17/08/2026

በማይክሮሶፍት አዙር (Azure) መረጃ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የMcDonald እና የVodafone ሰራተኞች መረጃ ተሰረቀ።
*************************
TheHatman በመባል የሚታወቀው የሳይበር ጥቃት አድራሽ በተሰረቁ የመግቢያ ምስጢራዊ መረጃዎች (credentials) በመጠቀም ከማይክሮሶፍት አዙር (Microsoft Azure) እና ኢንትራ አይዲ (Entra ID) ሥርዓቶች የወጡ የበርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሰራተኞች መረጃ ለሽያጭ ማቅረቡ ተገለጸ።

ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ዋና ዋና ተቋማት መካከል ማክዶናልድስ (McDonald’s)፣ ቮዳፎን (Vodafone)፣ ታታ ኮንሳልታንሲ ሰርቪሰስ (TCS)፣ ኤችሲኤል ቴክኖሎጂስ (HCL Technologies)፣ ኪንድሪል (Kyndryl)፣ ጋፕ (Gap Inc.)፣ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴልስ ግሩፕ (IHG)፣ ዊንድሃም ሆቴልስ (Wyndham Hotels) እና ሄክሳዌር (Hexaware) ይገኙበታል። ተጨማሪውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.ethiocert.gov.et/news/%E1%89%A0%E1%88%9B%E1%8B%AD%E1%8A%AD%E1%88%AE%E1%88%B6%E1%8D%8D%E1%89%B5-%E1%8A%A4%E1%8B%A0%E1%88%AD-azure-%E1%88%98%E1%88%A8%E1%8C%83-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8C%B8%E1%88%98-%E1%8C%A5%E1%89%83%E1%89%B5-%E1%8B%A8mcdonald-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%A8vodafone-%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%88%98%E1%88%A8%E1%8C%83-%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%88%A8%E1%89%80%E1%8D%A2

የሳይበር ደህንነትን ለማጠናከር እና ወቅታዊ የመከላከያ መረጃዎችን ለማግኘት የ Ethio- CERTን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ።
‎ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
‎• ድረ ገጽ፦ https://lnkd.in/e_ZNJkew
‎•ሊንክዲን (LinkedIn) ፦ https://lnkd.in/dWhnui6U
‎•ቲክቶክ (Tiktok) ፦ https://lnkd.in/dYDfNbEY
‎• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

የAI ምስሎችዛሬ AI ቴክኖሎጂ በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ እውነተኛ የሚመስሉ ምስሎችን መፍጠር ችሏል። ችግሩ ደግሞ እነዚህ ምስሎች ለመዝናኛ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን ለማሳሳት፣ የሐሰት መረጃ ለማሰራ...
13/08/2026

የAI ምስሎች

ዛሬ AI ቴክኖሎጂ በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ እውነተኛ የሚመስሉ ምስሎችን መፍጠር ችሏል። ችግሩ ደግሞ እነዚህ ምስሎች ለመዝናኛ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን ለማሳሳት፣ የሐሰት መረጃ ለማሰራጨት እና በDeepfake ማጭበርበር ለመፈጸም ሊውሉ ይችላሉ።

Deepfake ምንድነው?
Deepfake ማለት AI እና Machine Learning በመጠቀም የሰውን ፊት፣ ድምፅ ወይም እንቅስቃሴ በሌላ ሰው ላይ በመቀየር እውነተኛ የሚመስል የሐሰት ይዘት መፍጠር ነው።

ለምሳሌ፣ አንድ ታዋቂ ሰው ያልተናገረውን ነገር እየተናገረ የሚያሳይ ቪዲዮ ወይም አንድ ሰው በሌለበት ቦታ እንዳለ የሚያሳይ ምስል ሊፈጠር ይችላል።

በAI የተሰሩ ምስሎች ለምን አላማ ሊውል ይችላል?

- የሐሰት ዜና ለማሰራጨት
- የሰውን ስም ለማጥፋት
- ማጭበርበር ለመፈጸም
- Social Engineering እና Cybercrime ለመፈፀም

በAI የተሰራ ምስልን እንዴት እንለያለን?

1. የፊት እና የሰውነት ዝርዝሮችን ይመልከቱ

የጣቶች ቅርጽ፣ ጥርሶች፣ ጆሮዎች፣ የዓይን እንቅስቃሴ ወይም የፊት ሚዛን ከተፈጥሮ ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ። ዘመናዊ AI ግን እነዚህን ስህተቶች እየቀነሰ ስለሆነ ይህ ብቻ በቂ አይደለም።

2. ብርሃንና ጥላን ይመልከቱ

በምስሉ ውስጥ ያሉ ሰዎችና እቃዎች የተለያየ የብርሃን አቅጣጫ ካላቸው ምስሉ የተሰራ ሊሆን ይችላል።

3. የጀርባ አካባቢን ይመልከቱ

የማይነበብ ፅሁፍ፣ የተዛቡ ምልክቶች፣ የማይመስሉ ህንፃዎች ወይም እቃዎች የAI ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ።

4. የምስሉን ምንጭ ያረጋግጡ

“ይህ ምስል የት ነው የተገኘው?” ብለው ይጠይቁ። የመጀመሪያ ምንጩ ካልታወቀ በቀጥታ እውነት ብለው አይቀበሉት።

5. Reverse Image Search ይጠቀሙ

Google Lens ወይም ሌሎች Reverse Image Search መሳሪያዎችን በመጠቀም ምስሉ ቀደም ሲል የተለጠፈበትን ቦታ መፈለግ ይቻላል።

6. AI Detector ብቻ አትመኑ

AI detection tools ሊረዱ ይችላሉ፣ ግን 100% ትክክለኛ አይደሉም። ስለዚህ የTool ውጤትን ከምስሉ ምንጭ፣ ከContext እና ከሌሎች ማረጋገጫዎች ጋር ማየት ያስፈልጋል።

ከእነዚህ ሁለት ምስሎች የትኛው በAI የተሰራ ነው?” መልሶን በ Comment ያሳውቁን 👇

Address

Ethio-China Street
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Cert posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethio-Cert:

Shortcuts

Share