በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን FDRE Environment Protection Authority

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን FDRE Environment Protection Authority

በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን    FDRE Environment Protection Authority Ethiopian Environmental Protection Authority is Re-established Under Proclamation No. 1263/2021.

10/09/2026
የአካባቢ  ጥበቃ ባለሥልጣን ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።** ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ምአዲስ አበባ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በየወቅቱ በበበአለት ...
09/09/2026

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።

**
ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በየወቅቱ በበበአለት የሚያደርገውን የመደጋጋፍ በጎ ሥራን ዛሬ “ጳጉሜ 04 የኅብር ቀንን” ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ ለ48 ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እና ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 9 በቋሚነት በየበአላቱ ለሚደገፉ 7 ወላጅ ላጡ ልጆችና ቤተሰቦች ለዘመን መለወጫ በአል የሚሆን 5 ሊትር ዛይት፣20 ኪ.ግ የዳቦ ዱቄት እና 3 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና በማደገፍ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄዷል።

በወቅቱ ስጦታውን ያበረከቱት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ ጳጉሜ 4 የህብር ቀን መሆኑን በማስታወስ በልዩነት ውስጥ አንድነትን ፣ መደጋገፍንና መተሳሰብ መሠረት ያደረገው የመደመር መንግስት አንዱ መርሆ በመሆኑ እንደ ሀገርም በርካታ ሰው ተግባራት እየተሰሩ በመሆኑ የአብሮነት መንፈስ እየተጠናከረ መጥቷል በማለት
እንደተቋም በሚቀጥለው አዲስ ዓመት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዋሉ።፡በተጨማሪም ቀጣዩ ዓመት የስኬት፣ የደስታና የብልፅግና እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
የመተሳሰብና የመደጋገፍ ባህላችንን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥሉም አረጋግጠዋል።

ሦስተኛው ዙር የ"ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ"ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው የግብርና  ኢንዱስትሪ ኬሚካል አያያዝ በሚመለከት  ከባድርሻ አካላት ጋር  ምክክር ተካሄደ ፡፡‎‎ጳ...
09/09/2026

ሦስተኛው ዙር የ"ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ"ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው የግብርና ኢንዱስትሪ ኬሚካል አያያዝ በሚመለከት ከባድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሄደ ፡፡

‎ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም
‎አዲስ አበባ
‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሦስተኛው ዙር የ"ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ"ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው የግብርና ኢንዱስትሪ ኬሚካል አያያዝ በሚመለከት ከባድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሄደ ፡፡
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ባስተላለፉት መልዕክት ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ሁላችንም በጋራ በመቆም ውብ እና ጽዱ ለዘጎቿ እና ምቹ ሀገርን ለትውልድ የመስራት እንቅስቃሴ አካል ነው።
አክለውም ግብርና እና ኢንዱስሪ ለኢኮኖሚያችን፣ እና ለምግብ ዋስትናችን ወሳኝ ሚና ያለው ዘርፍ መሆኑን የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከፍ ለማድረግ የግብርና ግብዓቶች ወሳኝ ሚና አላቸው። በተለይም የሆርቲካልቸር ዘርፍ በኢኮኖሚያች ዕድገት ለውጭ ምንዛሪ ገቢ እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑና ይህንን የልማት እንቅስቃሴ ማበረታታት እና መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።
ኬሚካል ለግብርናና ለኢንዱስትሪ እንደ ግብአት የሚያገለግል ሲሆን ለዘርፉ እድገት አስፈላጊ ጠቀሜታ ያላቸውን ያህል አጠቃቀማቸው እና አያያዛቸው ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ኬሚካሎች በአካባቢና በሰው ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያስከትሉ የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን፣ ደረጃዎችንና መመሪያዎችን አፈጻጸማቸውን የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል ።

ስራውን በተሻለ ሁኔታ ለመስራት የመንግሥት ፣ የግሉ ዘርፍ፣ የአካዳሚክና የምርምር ተቋማት እና የልማት አጋሮች በጋራ በስራት እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
በመድረኩ ላይ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የምርምር ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ፣ የአበባ እርሻ ተቋማት ተገኝተዋል ።

የ'ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ  ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አካል በሆነው የአደገኛ  ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።‎‎ጳጉሜ 02/2018ዓ.ም‎አዲስ አበባ‎፨...
07/09/2026

የ'ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አካል በሆነው የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

‎ጳጉሜ 02/2018ዓ.ም
‎አዲስ አበባ
‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሦስተኛው ዙር ''የ'ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ አንዱ የትኩረት መስክ በሆነው የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በሚመለከት ከፌደራልና ክልልሎች ባድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ፡፡

ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንሶስተኛው ዙርሀገር አቀፍ የብክለት መከለከል ንቅናቄ “ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ ''በሚል መሪ ሃሳብ እያካሄደ ሲሆን ዛሬ የንቅናቄው አንዱ የትኩረት መስክ የሆነው የአደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፣ ቆሻሻን ከምንጩ ጀምሮ በኃላፊነት ማስተዳደር፣ ኬሚካሎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መጠቀም እንዲሁም የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻን ወደ ሀብት የመቀየር እና የህዝብን ጤና የመጠበቅ ስራን ያማክላል ።

ጽዱ ኢትዮጵያ በመፍጠር ረገድ በሀገራችን በገጠርም በከተማም በርካታ አርአያነት ያለው ስራዎች ተሰርተዋል። የኮሪደር ልማታችን የከተሞች መዘመን እና ጽዱነት የኢትዮጵያ ማነሰራራት አንዱ ማሳያ ነው። ጽዱ ኢትዮጵያ ለተውልድ 3ኛ ዙር ንቅናቄም ምቹ፣ የዘጎችን የኑሮ ጥራት እና ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም ተስማሚ አካባቢን የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚያጠናክር ነው። የዝህ መድረክም አጀንዳ የጽዱ ኢትየጵያ እንቅስቃሴ አካል ሆኖ ከአደገኛ ቆሻሻ ብክለት ነጻ አካባቢን መፍጠር ነው።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የአካባቢ ህግ ተከባሪነትና ተፈፃሚነት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አዲሡ ጥበቡ በበኩላቸው ኬሚካልና አደገኛ ቆሻሻዎች በአግባቡ ካልተያዙ በአካባቢና በሰው ጤና ላይ ሚያደርሱትን ተፅዕኖዎች አደገኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ በአደገኛ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ፣የመንግስት ግዥ ከአካባቢንና ሰው አንፃር እና የህምምና መድኃንት ቆሻሻን አወጋገድን በሚመለከት የጥናት ሰነድ የቀረበ ሲሆን በመድረኩም የፓናል ውይይት ተከሄዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የክልልና የፌዴራል ግዥ ባለስልጣን ኃላፊዎች፣ የመንግስትና የግል ድርጅቶች እንዲሁም የክልልና ፌዴራል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎በአሁኑ ወቅት የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተራዘመ የአምራቾች ኃላፊነት ግዴታ ተግባር ላይ እንዲውል ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌትሪክ እና የኤሌክትሮኒክ ቁሳቁሶችን የምዝገባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመታዊ የሰራተኞች አንድነት ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አከበረ።ነሐሴ 2018ዓ.ምአዲስ አበባ ===========የአካባቢ  ጥበቃ ባለስልጣን አመታዊ የሰራተኞች የአብሮነ...
03/09/2026

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመታዊ የሰራተኞች አንድነት ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አከበረ።
ነሐሴ 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ
===========
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አመታዊ የሰራተኞች የአብሮነት ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አከበረ። በበዓሉ አከባበር ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ለሊሴ ነሜ እንደገለፁት በዓሉ የባለስልጣኑን የ2018 በጀት አመት የተግባራት አፈፃፀም በአመርቂ ውጤት ማጠናቀቁን በማብሰር ሠራተኞች በመጪው በጀት አመትም በአገልጋይነት መንፈስ ኃላፊነትን በመወጣት ለተሻለ አፈፃፀምና ውጤት ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋሉ።

በበዓሉ ላይ ለረጅም አመት ተቋሙን በም/ዋና ዳይሬክተርነት ያገለገሉት ክቡር አቶ ንጉስ ለማ በቅንነት ስላገለገሉ ምስጋና በማቅረብ የመልካም ምኞት መግለጫ ከአመራሮች ብሎም ከሰራተኞች ቀርቧል።
በዕለቱም የክረምት በጎ ተግባር አካል የሆነው የማስ ስፖርትን እና የደም ልገሳን አካሂደዋል።

የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ ሙሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲ...
24/08/2026

የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ ሙሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአቅማ ደካማ ነዋሪዎች የቤቶች ግንባታ  ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ ።ነሐሴ16/2018 ዓ.ም ሰንዳፋ ==============የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣ...
22/08/2026

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለአቅማ ደካማ ነዋሪዎች የቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ ።
ነሐሴ16/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ
==============
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ተግባር መርሃ ግብርን በኦሮሚያ ክልል በሰንዳፋ በኬ ከተማ ለአምስት አቅማ ደካማ ለሆኑ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን በይፋ አስጀመሯል።

መርሃ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ ሲሆኑ፤ የበጎ ሥራ ዋና ዓላማ ዜጎች ጤናማና ምቹ የኑሮ አካባቢ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማስፋፋትና አቅመ ደካማ ወገኖችን መደገፍ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በጎ ሥራ ከግለሰቦች፣ ከመንግስትና ከመንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚጠበቅ ተግባር ብቻ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ ባህል ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንም ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብና ሌሎች ሰፊ የማህበረሰብ በጎ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።
በዚህ ዓመት በኦሮሚያ ክልል በሰንዳፋ በኬ ከተማ አቅመ ደካማ ለሆኑ እናቶች አምስት ቤቶችን በደረጃቸው መሠረት መገንባት፣ የወጣቶች የደም ልገሳ ንቅናቄን ማካሄድ፣ የአካባቢ ጽዳትና ችግኝ ተከላ ማከናወን እንዲሁም ለ285 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በመርሃ ግብሩ ተከናውኗል።

የኦሮሚያ ግብርና ምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጅሶ፣ አንድ ሀገር የምታድገው ዜጎች እርስ በርስ በመረዳዳትና አቅመ ደካማ ወገኖችን በመደገፍ መሆኑን ገልጸው፣ የበጎ ሥራ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የሰንዳፋ በኬ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ አለማየሁ ቶንኮሉ በበኩላቸው፣ በከተማው በርካታ የአቅመ ደካማ ቤቶች መገንባታቸውንና የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማትም በጥራትና በብዛት መስፋፋታቸውን ገልጸዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የክረምት በጎ ሥራውን በከተማው ማስጀመሩንም በከተማው ህዝብ ስም አመስግነዋል።
“በጎ ሥራ የአንድ ቀን ተግባር ሳይሆን የማህበረሰብ ባህል ይሁን!”

በአካባቢ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የማይባክኑ ኦርጋኒክ ባካይ ኬምካሎች (POPs)  "በህያዋን ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው ተባለ።ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ++++++++...
21/08/2026

በአካባቢ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የማይባክኑ ኦርጋኒክ ባካይ ኬምካሎች (POPs) "በህያዋን ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው ተባለ።

ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም |
አዲስ አበባ
++++++++++++++++
የስቶክሆልም የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮች (POPs) ዓለም አቀፍ ስምምነት ማስፈጸሚያ የተሻሻለ ብሔራዊ የትግበራ ዕቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ።
የውይይቱ ዋና ዓላማ፣ የተሻሻለውን የብሔራዊ የትግበራ ዕቅድ ረቂቅ በስቶክሆልም ስምምነት ሴክሬታሪያት ከመቅረቡ በፊት በጋራ መገምገም፣ መወያየትና ማጽደቅ ነው።
በውይይቱ ላይ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ እንደገለጹት፣ POPs በአካባቢ ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ፣ በሕያዋን አካላት ውስጥ የሚከማቹ፣ በረጅም ርቀት ሊጓጓዙ የሚችሉ እና በሰው ጤናና በአካባቢ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ በካዮች ናቸው።
ኢትዮጵያ የስቶክሆልም ኮንቬንሽን አባል ሀገር በመሆኗ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ስምምነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲተገበር የተሰጠውን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል። በዚህም የቆዩና ጊዜያቸው ያለፈባቸው አደገኛ ኬሚካሎችን የያዙ ቁሳቁሶችን በአካባቢና በጤና ላይ ጉዳት በማያስከትል መንገድ ማስወገድ፣ የተቋማትና የባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር፣ የመረጃና የክትትል ሥርዓትን ማሻሻል እና የሕግና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጓል።
በመድረኩ የተሻሻለው ብሔራዊ የትግበራ ዕቅድ ኢትዮጵያ እስካሁን ያስመዘገበችውን እድገት ለመገምገም፣ ያሉ ክፍተቶችና ተግዳሮቶችን ለመለየት እና በቀጣይ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት ለመወሰን የሚያግዝ ስትራቴጂካዊ ሰነድ መሆኑ ተገልጿል።
ዕቅዱ የPOPs ይዘት ያላቸው ቁሳቁሶችና ቆሻሻዎች በአካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ እንዲተዳደሩ፣ የPOPs ልቀትና ተጋላጭነት እንዲቀንስ እንዲሁም ኢትዮጵያ በስቶክሆልም ስምምነት የተጣለባትን ግዴታ በብቃት እንድትወጣ ያግዛል።
በውይይቱ ላይ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግሥት አመራሮች፣ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ተወካዮች፣ የልማት አጋሮች፣ የአካዳሚክና የሲቪል ማህበራት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የስቶክሆልም ኮንቬንሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ 185 አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን፣ ዓላማውም በሰው ጤናና በአካባቢ ላይ አደገኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቀጣይነት ያላቸው ኦርጋኒክ በካዮችን ለመቀነስና ለማስወገድ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ነው።

“ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” የአካባቢ ብክለት መከላከል  ክልል አቀፍ ንቅናቄ  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  መንግስት በሆሣዕና ከተማ ተጀመረሐምሌ 11/2018 ዓ.ም  ሆሣዕና============...
17/08/2026

“ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” የአካባቢ ብክለት መከላከል ክልል አቀፍ ንቅናቄ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሆሣዕና ከተማ ተጀመረ
ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም
ሆሣዕና
===============
ሶስተኛው ዙር የአካባቢ ብክለት መከላከል "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዘዳንት በተገኙበት በሆሣዕና ከተማ በይፋ ተጀመሯል።

በመድረኩም ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሳው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዘዳንት፣ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የጸጥታ አካላት፣ ተማሪዎችና መምህራን ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሆዕሣዕና ከተማ ነዋሪዎች በመድረኩ ተገኝተዋሉ።

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው የአካባቢ ብክለትን መከላከል ዘላቂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም መንግስታዊ፣ የግሉም ሴክተሮችና ግለሰቦች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋሉ።

“ፅዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ በሀገር አቀፍ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተግባር የሚጨበጥ ውጤት እንደተገኘ በመንሳት በክልላችን በየደረጀው በሚገኙ መዋቅሮች ሥራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

ዛሬ በክልላችን የሚናስጀምረው ሦስተኛው ዙር “ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ ለቀጣይ ሦስት ወራት የሚከናወነው የፕላስቲክ ብክለት፣ የአደገኛ ቆሻሻና ኬሚካሎች አያያዝና አወጋገድ፣ እንዲሁም የድምፅ ብክለት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን በመግለጽ በእነዚህ ዘርፎች ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ የአካባቢ ሕግን ማስከበርና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በየደረጀው የሚገኙ መዋቅሮምች ተግባራቱን በአግባቡ በመምራት፣ግልፅ መግባባትና ግንዛቤ በመፍጠር፣ ህጉን በማያከብት ላይ የህግ ማስከበር እርማጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሰስበዋል።

የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሃ ሕይወት መመናመንና የአካባቢ ብክለት ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸውን በማንሳት
ችግሮቹ የሚከሰውም ተፈጥሮን ዘላቂነት ባለው መንገድ ባለመጠቀማችን በመሆኑም ችግሮቹን ለመቅረፍ በሀገር አቀፍ ደረጀ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ሲሆን በሂደት የተገኙ ውጤቶችንና መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናቀርና በማስፋፋት፣ ለሀገራችን ዘላቂ ልማት፣ ለዜጎች ጤናማና ንጹሕ አካባቢ እንዲፈጠር እና ለመጪው ትውልድ ፅዱ ኢትዮጵያን ለማስረከብ በጋራና በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሥራው በአንድ ተቋም አቅም ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ የሚመለከታቸውን አካላት ቅንጅት የሚጠይቅ ስለሚሆን በተላይም የጸጥታ አካላትና ሌሎች ተዛማጅ ተቋማት በቅንጅትና በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ደራ ብለዋል።

ክቡር አቶ አብርሃም መጫ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ወቅት አካባቢን መጠበቅ የነገ ትውልድን ከጥፋት መታደግ መሆኑን በማንሳት፤ አስካሁን በሀገር አቀፍእና እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም የተጀመረው ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ሥራዎች ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ እንደሀገር ተጨባጭ ውጤት የተመዘገበበት፣ ሰፊ ግንዛቤም ተፈጥሯል።

የአካባቢ ብክለት በሀገራችን ብሎም በአለም አቀፍ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አላካት እና መለው ክልላችን ህዝባችን የአፈር፣ የውሃ፣ የአየርና የድምፅ ብክለትን ለመቀነስ እና የብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ እንዲቻል በሚካሄደው በፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በመሳተፍ የባኩን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋሉ፡፡

በመጨረሻም ለሆሣዕና ከተማ ነዋሪዎች በፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ የሚላውን ዓላማውንና የሚጠበቀውን ግብ የሚዲያ አካላት በተገኙበት በጀግናው ኮሎነል በዛብህ ጴጥርስ አደበባይ ግንዛቤ በመፍጠር የተጀመረው በመድረኩ ለውይይት የሚሆን መወያያ ሰነድ በቢሮው ቀርቦ ውይይት በማድረግ ሁሉም የሚመለከታቸው ባድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስተያየት በመስጠት በክልሉ በም/ርዕሰ መስተዲደር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ የሥራ አመራር በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

Address

Niger Street
Addis Ababa
12760

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን FDRE Environment Protection Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በኢፌዲሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን FDRE Environment Protection Authority:

Shortcuts

Share