Ethiopian Enterprise Development

Ethiopian Enterprise Development ራዕያችን ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝና ሰፊ መሰረት ያለ?

" የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ለአምራች ኢንዱስትሪው መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል!" ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ : የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር==============E...
06/09/2026

" የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ለአምራች ኢንዱስትሪው መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል!"

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ : የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር
==============
EED ጳጉሜ 1/2018

በፖለቲካ አመራሩ በኩል የታየው ቁርጠኝነትና ባለቤትነት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲሻሻልና የማምረት አቅሙ እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዶክተር አለባቸው ይህንን የገለጹት፣ በዛሬው ዕለት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር እና ብሄራዊ ባንክ በመተባበር “እምርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ ቃል በጋራ እንደ ሀገር በተከበረው የእምርታ ቀን አስመልክቶ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ነው።

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አሁን ከደረሰበት ደረጃ እንዲያድግና ወደፊትም እንዲራመድ፣ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከ ክልል አመራሮች ድረስ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ ባለቤትነትና የዘርፉን መሻሻል ለማምጣት የተተገበሩየማሻሻያ ስራዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እንዲሻሻል፣ የምርት ጥራታቸው እንዲጨምር፣ በሀገር ውስጥ ገበያ ያላቸው ድርሻ እንዲያድግ እና ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል ብለዋል።





የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አመራርና ሠራተኞች ዕውቅና ተሰጠ============የኢንዱስትሪ ሚንስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 መሳካት  የላቀ አስ...
06/09/2026

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አመራርና ሠራተኞች ዕውቅና ተሰጠ
============
የኢንዱስትሪ ሚንስቴር በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 መሳካት የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ተጠሪ ተቋማት (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና የአምራች ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት): ባለድርሻ አካላት አመራሮችና ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል።







የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት"የእመርታ ቀንአባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነት...
06/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!"



የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

የፕሬስ መግለጫእመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል...
06/09/2026

የፕሬስ መግለጫ

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡ የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡ በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ጳጒሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ



የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

"የሀገር ሉዓላዊነት ከኢንዱስትሪ ምርታማነት ጋር የተቆራኘ ነው!"  (አቶ መላኩ አለበል)============================EED ነሐሴ 30/2018 ኢትዮጵያ የምትፈልገውን ሉዓላዊነ...
05/09/2026

"የሀገር ሉዓላዊነት ከኢንዱስትሪ ምርታማነት ጋር የተቆራኘ ነው!" (አቶ መላኩ አለበል)
============================
EED ነሐሴ 30/2018

ኢትዮጵያ የምትፈልገውን ሉዓላዊነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ የሀገሪቱን የማምረት አቅምና የኢንዱስትሪ ምርታማነት የበለጠና በላቀ ሁኔታ ማሳደግ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ሚኒስቴሩ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው።

አቶ መላኩ እንዳሉት 2018 በጀት ዓመት የኢንዱስትሪ ዘርፉ በተለያዩ መመዘኛዎች አበረታች አፈጻጸም ያሳየበት ዓመት ነው።

የተገኘው ውጤትም በአንድ ጀምበር የተፈጠረ ሳይሆን፣ በተከታታይ የተከናወኑ ሥራዎች፣ የተደረጉ ማሻሻያዎችና በየደረጃው የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥራዎቹን በውጤት እየለካ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ መላኩ በ2018 በጀት ዓመት በተለይም በ“ኢትዮጵያ ታምርት” እና በሪፎርም ሥራዎች የተገኙ ውጤቶች የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን የሚያመላክቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ታምርት” በ2014 ዓ.ም በትንሹ ተጀምሮ በተከታታይ እየተሻሻለና እያደገ የመጣ ተግባር መሆኑን አቶ መላኩ ገልጸዋል።

የኢንዱስትሪ ዘርፉ ዕድገት የሚለካው በቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ በማምረት አቅም፣ በምርታማነት፣ በጥራትና በተጨማሪ እሴት ፈጠራ ላይ በሚመዘገቡ ውጤቶች ጭምር መሆን አለበት ያሉት ሚኒስትሩ የሀገሪቱን የማምረት አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ከማፋጠን ባለፈ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በተጨባጭ ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

ሉዓላዊነት በፖለቲካዊ አቅም ብቻ የሚረጋገጥ ሳይሆን፣ አንድ ሀገር የራሷን ፍላጎት በራሷ የማምረት አቅም ላይ በመመስረት ማሟላት መቻሏም አንዱ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማጠናከር፣ የማምረት አቅምን ማስፋፋትና በውጭ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ ለሀገራዊ ጥንካሬ ወሳኝ እንደሆነ አብራርተዋል።

የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ለ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትምህርትና መነሻ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በቀጣይም የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና የቀሩ ችግሮችን በመፍታት የኢንዱስትሪውን አፈጻጸም ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ አመላክተዋል ።

ሚኒስቴሩ በቀጣይ የሚያከናውናቸው ሥራዎች ከሀገራዊ የልማት ግቦች ጋር የተጣጣሙና በተጨባጭ ውጤት የሚለኩ መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም “እያንዳንዳችን የምናስቀምጠው በጎ ሥራ ተደምሮ የሀገራችንን ዕድገት ይወስናል” በማለት፣ የሀገሪቱ ዕድገትና ሉዓላዊነት በጋራ ጥረት፣ በምርታማነትና በትጋት እንደሚጠናከር ገለልፀዋል።

በመሆኑም የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገራዊ ሉዓላዊነትን የማጠናከር ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።



የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

ሀገር ያተረፈችበት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ
04/09/2026

ሀገር ያተረፈችበት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ

#ፋና #ኢትዮጵያ

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች*** የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ...
30/08/2026

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች
***

የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ጥገኝነት ተላቅቃ የራሷን ፍላጎት በራሷ ማምረት ስትችል ነው።

የመደመር መንግሥት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የጀመራቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማነቃቃት አስደናቂ ለውጦችን ማምጣት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነት በመላቀቅ የሀገር ውስጥ አቅምን ወደ መገንባት በተኪ ምርት የተሳካ ሽግግር እያደረገ ይገኛል።

የማምረት አቅም ማደግ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሚና

ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከነበራቸው የማምረት አቅም ከግማሽ በታች (በአማካይ 47 በመቶ) ብቻ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም በኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግሮች የተተበተበ ነበር።

ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ እንዳብራሩት፣ አሁን ላይ አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።

የዚህ ከፍተኛ ለውጥ ዋነኛ ሞተር በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እየተመራ ያለው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በተለያዩ ምክንያቶች ተዘግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ፣ እንዲሁም የአምራቾችን የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት ማነቆዎች በመፍታት ምርታማነትን በእጅጉ አነቃቅቷል።

➡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ምቹ የኢንቨስትመንት መሠረተ ልማት ማቅረብ ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ነባር ከሆኑት የኮምቦልቻ፣ የመቐለ እና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ ዐሥር አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ተችሏል።

የእነዚህ ፓርኮች መስፋፋት የሀገር ውስጥ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ፣ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለመሳብ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

የውጭ ኢንቨስተሮች ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያመጡ እና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

➡ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት፦ የ5 ቢሊዮን ዶላር ስኬት

ለዘመናት የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሲፈታተን የነበረው ዋነኛ ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በገቢ ምርቶች ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነበር።

ይህንን ለመቀልበስ "የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት" ስትራቴጂ በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ከባድ እና ወሳኝ የግንባታ/የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።

መንግሥት ቀደም ሲል በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሒደት በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ፖሊሲውን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

በግብርናው (በተለይም በስንዴ ምርት) የተገኘው የገቢ ምርትን የመተካት ስኬት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍም በተጨባጭ ተሸጋግሯል።

➡ የተቀናጀ የዘርፎች ዕድገት

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ መነቃቃት በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይም አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። የኢንዱስትሪ ዕድገት ብቻውን ሊመጣ አይችልም፤ ኃይል እና የጥሬ ዕቃ ግብዓት ይፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን ዕድገት ምክንያት፦ በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20.3 በመቶ፣ እና በኢነርጂ ዘርፍ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን አብራርተዋል። እነዚህ ሦስቱ ዘርፎች (ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኢነርጂ) እርስ በርስ በመመጋገባቸው የመጣ "የተቀናጀ ዕድገት" (Synergy) መሆኑን ያሳያል።

➡ የወደፊቱ አቅጣጫ እና ራዕይ

የተገኙት ስኬቶች የጉዞው ጅማሮ እንጂ ማቆሚያ አይደሉም። ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ በመጪው ዓመት ግልጽ ዒላማዎች ተቀምጠዋል። እነዚህም፦

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ የ12.7 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እና ከኢንዱስትሪ ምርቶች ኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) የ1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ሲሆኑ ለስኬቱም በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እውነተኛ ዕምርታ እያሳየ ነው። “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ብሔራዊ ንቅናቄ በመመራት፣ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።

አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመክፈት ኢንቨስትመንትን መሳብ እና ቁልፍ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉም ሀገራችን ከሸማችነት ወጥታ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች አምራች ኢኮኖሚ ወደ መገንባት የተጨበጠ ዕርምጃ መጀመሯን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ራዕዩ ግቡን ሲመታም፣ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብልጽግናዋ ዋነኛ የጀርባ አጥንት መሆኑ አይቀርም።





የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

Address

Ras Abebe Aragay Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Telephone

+251115150333

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Enterprise Development posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Enterprise Development:

Shortcuts

Share