Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር

Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር The Ministry of Peace established to prevent and resolve conflicts, to bring equitable development among the regions and to create stable nation.
(2)

The Ministry of Peace was established under proclamation number 1097/2011 on October 16, 2018. The office of the Ministry of Peace was created to sustain the reforms that Ethiopia is currently undergoing through peace-building measures, establishing, and strengthening the rule of law, and building the capacity of peace and security focused sectors. Additionally, the office is tasked with using alr

eady existing social customs to deepen and sustain peace-building objectives and building national consensus. The Power and Duties of the ministry include:

• Work in cooperation with concerned Federal and Regional State government organs to ensure the maintenance of public order.

• Develop strategies and undertake awareness creation and sensitization activities to ensure the peace, security and freedom of the country and its people.

• In collaboration with relevant Regional Organs, facilitate the provision of proper protection to citizens living in any part of the country.

• Work in cooperation with relevant government organs, cultural and religious organizations, and other pertinent bodies to ensure peace and mutual respect among followers of different religions and beliefs, as well as nations, nationalities, and peoples. Since its establishment more than three years ago the Ministry has carried out numerous activities and tasks.

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ  ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲጎበኙ ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
05/09/2026

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲጎበኙ

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ  ተጠናቀቀ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋዊ ...
05/09/2026

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ተጠናቀቀ

ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋዊ እውቅና አግኝተው ለሀገር ግንባታ፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለግጭት አፈታት የድርሻቸውን ሚና እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ ውይይት በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሂዷል ።

በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጸጥታ ኃላፊዎች የየራሳቸውን ልምዶች እና ተሞክሮዎች በስፋት አቅርበዋል።

መድረኩን ያጠቃለሉት በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ካሳ የዛሬ መድረክ ለቀጣይ የድህረ-ግጭት ሥራዎች፣ የሀገር ግንባታ እና የሰላም ግንባታ ተግባራት ትልቅ ሀሳብ የተገኘበት ነው ብለዋል።

ሰላም የጋራ አጀንዳ እንደመሆኑ ሁላችንም ለሀገራችን ሰላም በጋራ ልንሰራ ይገባል ያሉት አቶ መብራቱ ብዙ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮቻችን ናቸው ለውጭ ችግሮች ተጋላጭ የሚያደርጉን እና ለውስጥ ችግሮቻችን ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለሰላም ግንባታ ለማዋል፣ የሰላም ትምህርትን ለማስፋፋት፣ ሁሉም ሴክተር የሰላም ስራን የራሱ አድርጎ እንዲሰራ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ በበኩላቸው የሰላም ሚኒስቴርን እንደዚህ አይነት መድረክ በማዘጋጀቱ እና ያለውን የክልሉን ነበራዊ ሁኔታ ህዝቡ እንዲያውቁ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የተነሱ ሀሳቦች ለቀጣይ ሥራችን መሠረቶች ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ የቀጣይ የድህረ ግጭት ሥራችን ውጤታማ እንዲሆን እና ሰላምን የሚያፀኑ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

05/09/2026

ውጤት የዲሲፕሊን ፍሬ ነው!🕊

ሰላም ለኢትዮጵያችን!
-
Success is the result of discipline!🕊

Peace for our Ethiopia!

በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የአማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡ ክልሉ በአንፃራዊ ሰላ...
05/09/2026

በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የአማራ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡

ክልሉ በአንፃራዊ ሰላም ውስጥ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በክልሉ የተጀመረውን የሰላም ጥረት አጠናክሮ መቀጠል፤ የታጠቁ ሃይሎች የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ መስራት፤ የክልሉን ህግ የማስከበር አቅም ማጎልበት፤ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶችን ማጠናከር እና መጠቀም እንዲሁም ህግ ከማስከበር ጎን ለጎን ልማትን ማፋጠን እና የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የቀጣይ የክልሉ የቤት ሥራ መሆኑን ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጸጥታ ኃላፊዎች የየራሳቸውን ልምዶች አቅርበዋል።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነውነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋ...
05/09/2026

ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው

ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋዊ እውቅና አግኝተው ለሀገር ግንባታ፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለግጭት አፈታት የድርሻቸውን ሚና እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ ውይይት በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ካሳ ሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች የሚገጥሟትን ፈተናዎች ሰላም ወዳድ በሆኑ ህዝቦቿ እና በመንግስት የተቀናጀ ጥረት እያሸነፈች መምጣቷ ገልፀዋል፡፡

በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው ግጭት እና አለመረጋጋት ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር ጥሎ ከማለፉም በላይ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ቀጥፏል ያሉት አቶ መብራቱ በሕዝቦች መካከል ያለው ጥልቅ የእርስ በእርስ መተሳሰር፣ የሰላም ፍላጎት እና መንግስት በወሰደው ቁረጠኝነት በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በአንፃራዊ ሰላም ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡

የዛሬው መድረክም የተፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት፣ በህብረተሰቡ መካከል መተማመንን እና ማህበራዊ መናበብን ለማጎልበት፣ የህግ የበላይነትን ከባህላዊ ዕርቅ ጋር በማቀናጀት በፍጥነት መፍትሄ ለመስጠት የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ በበኩላቸው የዛሬው መድረክ በግጭት የተጎዳውን የክልላችን ማህበረሰብ ወደ ዘላቂ ሰላም፣ መተማመን፣ እርቅ እና መልሶ መቀራረብ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎችን ለመለየት ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

መድረኩ በአማራ ክልል ያሉ የሰላም ሥራዎችን ለማጠናከር እና በሀገር ደረጃ የተቀናጀ የሰላም ግንባታ ሥርዓት ለመፍጠር እንደ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡

በቅርብ አመታታት ጊዜ ጀምሮ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከተማችን ችግር ውስጥ የነበረች ቢሆንም አሁን ላይ በተሰራው ከፍተኛ የጸጥታ ሥራ ከተማችችን በአስተማመኝ ሰላም ውስጥ ትገኛለች ያሉት ደግሞ የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ ናቸው፡፡

በመድረኩ ላይ “ማህበረ ባህላዊ ሃብቶች መጠበቅና ማጎልበት” የሚል ሰነድ በሰላም ሚኒስቴር የሀገር ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገመቺሳ ኢቲቻ እና “ሀገር በቀል ዕውቀት ለድህረ ግጭት” የሚል ሰነድ ደግሞ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ይርጋለም መንግሥቱ በኩል ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

 የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋዊ እውቅና አግኝተው ለሀገር ግንባታ፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለግጭት አፈታት የድርሻቸውን በተቀናጀ መንገድ እንዲያበረክቱ ለማስቻል...
05/09/2026



የማህበረ-ባህላዊ ሀብቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ህጋዊ እውቅና አግኝተው ለሀገር ግንባታ፣ ለሀገራዊ መግባባት እና ለግጭት አፈታት የድርሻቸውን በተቀናጀ መንገድ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ያለመ ውይይት በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰላም እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፋ ይገኛሉ።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

05/09/2026

ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን!🕊

ሰላም ለኢትዮጵያችን!
-
Ethiopia, our shared home! 🕊

Peace for our Ethiopia!

04/09/2026

ዝቅ ማለት መሸነፍ አይደለም!🕊️

ሰላም ለኢትዮጵያችን!
-
Humbling yourself is not defeat!🕊

Peace For Our Ethiopia!

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ እና ዲሞክራሲያዊ የመንግሥት አደረጃጀት ስርዓትን የምትከተል ሀገር ናት።ከተናጠል ጥረቶች ይልቅ በየእርከኑ የሚገኙ አቅሞችን በተገቢው መንገድ በማቀናጀት ዘርፈ ብዙ መንግሥታ...
04/09/2026

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ እና ዲሞክራሲያዊ የመንግሥት አደረጃጀት ስርዓትን የምትከተል ሀገር ናት።

ከተናጠል ጥረቶች ይልቅ በየእርከኑ የሚገኙ አቅሞችን በተገቢው መንገድ በማቀናጀት ዘርፈ ብዙ መንግሥታዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችሉ መደበኛ የመንግስታት ግንኙነቶችን በግልፅ ደንግጋለች፡፡

⚡️ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን
⚡️ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን
⚡️ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ
⚡️ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማትን ለማስቀጠል
⚡️ አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን ለመገንባት የመንግስታት ግንኙነት አስፈላጊ ነዉ፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊

04/09/2026

ሰላማችን የአንድነት መሠረታችን!🕊

ሰላም ለኢትዮጵያችን!
-
Our peace, the foundation of our unity! 🕊

Peace for Our Ethiopia!

Address

Ethio-Chinese Friendship Road
Addis Ababa
5608

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር:

Shortcuts

Share