19/08/2026
🧅🌊🌽በሸበሌ ወንዝ ዳር፣ መሬት ከሰብል ባሻገር ተስፋ እያበቀለ ነው። በዚህ ስፍራ የተፈጠረውን የልማት ዕድል በመጠቀም፣ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ራሳቸውን ችለው የተሻለ ኑሮ ለመገንባት እየተጉ ይገኛሉ።🕊️🌿
🧅🌊🌽ይህ ለውጥ በግጭት የተጎዱና የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ከአስቸኳይ ዕርዳታ ጥገኝነት በመላቀቅ ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲገነቡ በሚያግዘው የሰብአዊ–ልማት–ሰላም (HDP) ትስስር ፕሮጀክት በኩል እየተጠናከረ ይገኛል።🕊️🌿
🧅🌊🌽በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሚተገበረውና በዴንማርክ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (DANIDA) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ፕሮጀክት፣ ሰብአዊ ዕርዳታን፣ መልሶ ማቋቋምን፣ የግብርና ልማትን፣ የገበያ ትስስርን እና ሰላም ግንባታን በማቀናጀት የተሻለና ዘላቂ የኑሮ መሠረት ለመገንባት ይሰራል።🕊️🌿
🧅🌊🌽ከ2017 ዓ.ም. እስከ 2021 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል በ12 ወረዳዎች እና በአጎራባች ኦሮሚያ ክልል በአንድ ወረዳ ይተገበራል። ፕሮጀክቱ በሰብልና በእንስሳት ኮሜርሻላይዜሽን፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ በአግሮ ቢዝነስ ልማት እና በዲጂታል ግብርና ላይ ያተኩራል።🕊️🌿
🧅🌊🌽እስካሁን በሶማሌ ክልል ብቻ ከ90,000 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ስደተኞች በተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል። ከዚህ ቁጥር በስተጀርባ ግን የራሳቸውን ኑሮ እንደገና እየገነቡ ያሉ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች አሉ።🕊️🌿
🧅🌊🌽በደባልደግ ቀበሌ በሸበሌ ወንዝ ዳር የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የአስተናጋጅ ማህበረሰብ አባላት በአርሶ አደሮች የምርት ክላስተር በመደራጀት፣ በመስኖ የሚለማ መሬትን በጋራ እያለሙ ይገኛሉ።🕊️🌿
🧅🌊🌽በHDP ፕሮጀክት የቀረበላቸውን ጥራት ያለው ዘር፣ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች፣ የምክርና የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ እንዲሁም ቴክኒካዊና የአመለካከት ለውጥ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን በመጠቀም፣ ቀደም ሲል በበቂ ሁኔታ ያልለማውን መሬት በማልማት የምግብና የገቢ ምንጫቸውን አሳድገዋል።🕊️🌿
🧅🌊🌽የሽንኩርት ምርታቸው 1,625 ኩንታል የደረሰ ሲሆን፣ ኩንታሉን በአማካይ 7,000 ብር መሸጥ ችለዋል። ከአካባቢው ገበያ በተጨማሪ ምርታቸውን ወደ ጎዴ ከተማ በማጓጓዝ የተሻለ ገበያ በማግኘት የተሻለ ገቢ ማግኘት ችለዋል።🕊️🌿
የሽንኩርት ምርት ስኬትን ተከትሎ፣ ተመሳሳይ የምርት ክላስተር አቀራረብ በበቆሎ ምርትም ተጠናክሯል።🕊️🌿
🧅🌊🌽ሰባት የአርሶ አደሮች የምርት ክላስተሮች 95 ሄክታር በመስኖ የሚለማ መሬት በማልማት 2,755 ኩንታል የበቆሎ ምርት አግኝተዋል። ከምርቱ ሽያጭም 19.28 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።
🧅🌊🌽እርዳታ ላይ በእጅጉ ጥገኛ ለነበሩና የኑሮ አማራጮቻቸው ውስን ለነበሩ ቤተሰቦች፣ እነዚህ ውጤቶች ከተሻለ ምርት መሰብሰብ በላይ ትርጉም አላቸው። መሬት፣ ቴክኖሎጂ፣ እውቀትና ክህሎት፣ የጋራ ተሳትፎ እና የገበያ ትስስር ሲጣመሩ፣ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል መሸጋገር እንደሚቻል የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው።🕊️🌿
🧅🌊🌽ጉዞው ምርታማነትን በማሻሻል ብቻ አያበቃም። የረጅም ጊዜ ዓላማው እነዚህን አርሶ አደሮች ከምርት ክላስተር ወደ ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር፣ ከዚያም በመጨረሻ ወደ አግሮ ቢዝነስ ኩባንያዎች በማሸጋገር፣ በግብርና የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ንቁ ተሳታፊና ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል ነው።🕊️🌿
📌Website: https://ati.gov.et/
📌Facebook: Ethiopian Agricultural Transformation Agency
📌Twitter or X:
📌LinkedIn: https://www.linkedin.com/posts/ethiopianata
📌YouTube: www.youtube.com/