ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል / Kidus Petros Hospital

ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል / Kidus Petros Hospital ''We promise to provide compassionate care with a strong desire and understanding of your pain''

Exciting Publication Announcement! I am delighted to share our recently published research: "Practice of Breast Self-Exa...
12/07/2026

Exciting Publication Announcement!

I am delighted to share our recently published research:

"Practice of Breast Self-Examination and Its Associated Factors Among Women of Reproductive Age in Seven Public Health Facilities in Addis Ababa, Ethiopia: A Multi-Centre Cross-Sectional Study"

Authors: Abdurehman Seid Mohammed, Tsehaynesh Tafese, Mathewos Sileshi Menberu, Yared Nigussie, Mustofa Hassen, Zewudu Minda, and Getachew Mekete Deress.
🔗 DOI: https://doi.org/10.1177/17455057261467912
Breast cancer remains a significant public health challenge, and early detection plays a critical role in improving outcomes. This study contributes important evidence on breast self-examination practices and the factors influencing them among women of reproductive age in Addis Ababa, Ethiopia.

I extend my heartfelt appreciation to my co-authors, research participants, data collectors, supervisors, and institutional partners whose support made this work possible.

As a Public Health Specialist and Researcher, I remain committed to generating evidence that informs policy, strengthens health systems, and improves population health outcomes.

Every publication is not just an achievement—it is an opportunity to create impact.

Congratulation all KPH Team!

✍️ Abdurehman Seid

BSC,MPH,PMAE

▬▬▬▬▬▬▬▬

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"

Background Breast cancer is the leading cause of cancer-related deaths worldwide and the second most common cancer among women globally. Breast self-examination...

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ዋና ተልዕኮ ኃላፊ አቢባቱ ዋኔ በሆስፒታሉ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉአዲስ አበባ - ሐምሌ 3 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)የዓለም አቀፍ የስደተኞች ...
10/07/2026

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ዋና ተልዕኮ ኃላፊ አቢባቱ ዋኔ በሆስፒታሉ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ - ሐምሌ 3 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የኢትዮጵያ ዋና ተልዕኮ ኃላፊ የሆኑት አቢባቱ ዋኔ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ኃላፊዋ የሆስፒታሉን የልብ ሕክምና ማዕከል ፣ የዲያሊሲስ ማዕከል ፣ የቶክሲኮሎጂ ማዕከል ፣ የጥሪ ማዕከል ፣ ላብራቶሪ ፣ የድንገተኛ እና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ ባሻገር ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ የሕክምና አገልግሎቶች ቅንጅት ፣ የአገልግሎት ማሻሻያዎች ፣ የዓቅም ግንባታ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል።

በቀጣይም በሆስፒታሉና በዓለም አቀፍ ድርጅቱ መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ እንደሚጀመር በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

▬▬▬▬▬▬▬▬

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"

10/07/2026
ማስታወቂያ3/11/2018 ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው የቃልና የጽሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተፈታኞች የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ቢሮ በ6/11/2018 ዓ.ም. በመቅ...
10/07/2026

ማስታወቂያ

3/11/2018

ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው የቃልና የጽሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተፈታኞች የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ቢሮ በ6/11/2018 ዓ.ም. በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

✍️ ሆስፒታሉ

▬▬▬▬▬▬▬▬

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"

የጤናው ዘርፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለብዙ ዜጎች ተደራሽ የጤና አገልግሎትን በማቅረብ ሕይወትን እያተረፈ ይገኛልየጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒ...
10/07/2026

የጤናው ዘርፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለብዙ ዜጎች ተደራሽ የጤና አገልግሎትን በማቅረብ ሕይወትን እያተረፈ ይገኛል

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሃርት አታክ ኢትዮጵያ ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ጋር በመተባበር እየሰጠ ያለውን ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ወቅት፣ ይህ አገልግሎት የልብ ቀዶ ሕክምና በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ህሙማንን ቁጥር በመቀነስና ሕይወትን በማትረፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

በመላ ሀገሪቱ የሚካሄዱ የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎቶች ለዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ ሕክምና፣ የደም ልገሳ እና የህክምና መሳሪያዎች ጥገናን ጨምሮ አስፈላጊ አገልግሎቶችን በማድረስ የጤና አገልግሎትን ለዜጎች ይበልጥ ተደራሽ እያደረጉ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በዚሁ አጋጣሚ ዶ/ር መቅደስ፣ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ሰራተኞች እና በበጎ ፈቃድ ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና እየሰጡ ለሚገኙት የሃርት አታክ ኢትዮጵያ ቡድን አባላት ላበረከቱት አገልግሎትና ላተረፉት ሕይወት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

የቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እንደገለጹት፣ ቡድኑ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለ34 ህሙማን የልብ ቀዶ ሕክምና በማድረግ ሕይወት አድኗል።

በጉብኝቱ የጤና ሚኒስቴር አመራሮችም ከዶ/ር መቅደስ ጋር ተገኝተዋል።

✍️ ጤና ሚኒስቴር

▬▬▬▬▬▬▬▬

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"

10/07/2026

በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 90 ሺህ አደገ
03/11/2018 ዓም ኢጤመአ
በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአመት አመት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የሆስፒታሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አስተባባሪ ወይዘሮ አሰለፈች ወርቁ አስታወቁ።
እንደ አስተባባሪዋ ገለጻ፥ ባለፈው አመት 70 ሺህ የነበረው የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር በተያዘው በጀት አመት ወደ 90 ሺህ አድጓል። እነዚህ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በሪፈራል ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ መሆናቸው ተገልጿል።
ሆስፒታሉ ከማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የሚያገኘው ገቢ ለውስጥ ገቢ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። እየተገኘ ያለው ገቢ ለተከታታይ የመድሃኒት ግዢ እና ለሌሎች የህክምና ግብአቶች ማሟያነት በመዋል ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም በሆስፒታሉ የጤና መድህን ተጠቃሚዎችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም አገልግሎት ፈላጊዎች በሚያገኟቸው ህክምናዎች ላይ ቅሬታ ካላቸው፣ አቤቱታቸውን በቀላሉ ማቅረብ የሚችሉበት የተለያየ ቀልጣፋ አሰራር መዘርጋቱንም ወይዘሮ አሰለፈች ወርቁ አክለው ገልጸዋል።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

09/07/2026

የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የሕብረተሰቡን የሕክምና ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻሉ ተገለጸ
02/11/2018 ኢጤመአ
የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት መተግበሩ፣ የኅብረተሰቡን ወደ ሕክምና ተቋማት የመምጣት ልምድ በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጥራት ቁጥጥር ኃላፊ ተወካይ አቶ ኢብራሂም ኸይረዲን ገለጹ።
ቀጥተኛ የሕክምና ወጪ በማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን መሸፈኑ የሕዝቡን የሕክምና ተጠቃሚነት ያሻሻለ ሲሆን፣ ይህም ለጤና ተቋማት በርካታ ጠቀሜታዎችን ይዞ መጥቷል። ተቋማቱም ይሄንን ፍላጎት ለማስተናገድ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን አቅም እንዲፈጥሩ አግዟቸዋል ብለዋል አቶ ኢብራሂም።
ሆኖም የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፣ በአሁኑ ወቅት የወረፋ መረዘም ዋነኛ ቅሬታ ሆኖ መነሳቱን የገለጹት ተወካዩ፤ ችግሩን ለመፍታት ሆስፒታሉ ልዩ ልዩ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዱን ጠቁመዋል።
ሌላኛው የሕክምና አገልግሎት ጥራትን ሊቀንስ የሚችለው ማነቆ የመድኃኒት አቅርቦት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ኢብራሂም፣ የሚቀርበው የመድኃኒት መጠን ከተገልጋዩ ቁጥር ጋር አለመመጣጠኑን ገልጸው፤ ከሆስፒታሉ በኩል ግን ችግሩን ለመቅረፍ መደረግ ያለበት ሁሉ እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ቀደም ሲል በነበረ የመረጃ አያያዝ ጉድለት ምክንያት ሆስፒታሉ ሕክምና ከሰጠ በኋላ ማግኘት የሚገባውን የመልሶ ክፍያ ያጣ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን መረጃዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግና ለሠራተኞች ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ በተሠራው ሥራ ውድቅ ይሆኑ የነበሩ የመልሶ ክፍያዎችን በተገቢው መንገድ ማስመለስ መቻሉን ገልጸዋል።
"በገባነው ውል መሠረት አገልግሎት ማቅረብ ስላለብን፣ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን እያደረግንና መረጃዎችን በተለያዩ ዘዴዎች እየሰበሰብን ነው" ያሉት አቶ ኢብራሂም፤ ተገልጋዮች ያሉባቸውን ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ባሉበት ሆነው የሚገልጹበት አጭር የስልክ መስመር ቁጥር ተዘጋጅቶ በሙከራ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም አቶ ኢብራሂም፣ ኤጀንሲው ከተቋማት ጋር በቅርበትና በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም ተጠቃሚዎች የሚያገኙትን ሕክምና በቅርበት በመከታተል፣ ለጤና ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ በመስጠትና የጤና ተቋማትን አቅም በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

Address

Https://maps. App. Goo. Gl/vyAHoZB7d4Kg9MnEA
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል / Kidus Petros Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል / Kidus Petros Hospital:

Shortcuts

Share