አዲስ-ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት Addis Ketema Subcity Health Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አዲስ-ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት Addis Ketema Subcity Health Office

አዲስ-ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት Addis Ketema Subcity Health Office Addis Ketema subcity health office officially page

28/07/2026
በዛሬው እለት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በክፍለ ከተማው ስር ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ጋር በጋራ እቅድን ካስኬድ አደረገ።
28/07/2026

በዛሬው እለት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በክፍለ ከተማው ስር ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ጋር በጋራ እቅድን ካስኬድ አደረገ።

16/07/2026

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በህዝብ በተነሳ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መሰረት በወረዳ 4 አካባቢ እየተሰራ ያለ የጤና ጣቢያ ግንባታ 4ኛ ወለል ላይ መድረሱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ዘውድነሽ ሽፈራው አስታውቃዋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በህዝብ በተነሳ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መሰረት በወረዳ 4 አካባቢ እየተሰራ ያለ የጤና ጣቢያ ግንባታ 4ኛ ወለል ላይ መድረሱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ...
16/07/2026

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በህዝብ በተነሳ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መሰረት በወረዳ 4 አካባቢ እየተሰራ ያለ የጤና ጣቢያ ግንባታ 4ኛ ወለል ላይ መድረሱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ዘውድነሽ ሽፈራው አስታውቃዋል።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በበጎ ፈቃድ ነፃ ህክምናና የደም ልገሳ ተግባር በስኬት መከናወኑ ተገለፀ።******************************ሐምሌ 2 -2018ዓ/ምበአዲስ ከተማ ክፍለ ከተ...
09/07/2026

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በበጎ ፈቃድ ነፃ ህክምናና የደም ልገሳ ተግባር በስኬት መከናወኑ ተገለፀ።
******************************
ሐምሌ 2 -2018ዓ/ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትና ጤና ጽ/ቤት እንዲሁም ምግብና መድኃኒት ክብካቤ ጽ/ቤት በመተባበር በባለድርሻ አካላትና በህብረተሰቡ ሰፊ ትብብር የበጎ ፈቃድ ነፃ ህክምናና የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሐብታሟ ቡልቻ በበኩላቸው በጎ ፈቃድ ከእርዳታ ባለፈ የህብረተሰብ መተሳሰብና አብሮነትን የሚያጠናክር እሴት መሆኑን ጠቁመው፣ የነፃ ህክምናና የደም ልገሳ ተግባራት በተከታታይ በማካሄድ ለተጋላጭ ዜጎች ተደራሽ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታላሚ በማድረግ ጠንክሮ መሥራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘውድነሽ ሽፈራው በበኩላቸው የነፃ ህክምና ደም ልገሳ ለህብረተሰቡ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ፣ ምክርና ህክምና አገልግሎት በማቅረብ በሽታዎችን አስቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል ጠቃሚ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ የደም ልገሳ አንድ ሰው በመለገስ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ሊታደግ የሚችል ሰብዓዊ ተግባር መሆኑን በማስገንዘብ ህብረተሰቡ በቀጣይም በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የክፍለ ከተማው ምግብና መድኃኒት ክብካቤ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሰላም ነሪ በበኩላቸው ለህብረተሰቡ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ጥራትና ደህንነት እንዲጠበቅ የመድኃኒትና የምግብ ቁጥጥር እና ክትትል በተጠናከረ መልኩ እንደሚከናወን ገልጸው፣ የጤና አገልግሎት ከጥራት የተላበሰና ለህብረተሰቡ አስተማማኝ እንዲሆን ተቋማቸው ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።
በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ ነዋሪዎችም የተሰጣቸው ነፃ ህክምናና የጤና ምክር እንዲሁም የደም ልገሳ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ጠቃሚ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም መሰል የበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል።

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018/19 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ምክፈቻ ተካሄደ።  *****************************የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና  ...
09/07/2026

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018/19 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ምክፈቻ ተካሄደ።
*****************************
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ሠራተኞች እንዲሁም የጤና ጣቢያ ሃላፊዎች እና በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘውድነሸ ሽፈራው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከችግኝ ተከላ በላይ ለትውልድ የሚተላለፍ የአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም እና አረንጓዴ ከተማን ስትራቴጂክ የመገንባት ሀገራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ዘውድነሸ አክለው አረንጓዴ አሻራ የዛሬን ተስፋ እና የነገን ሕይወት የምንገነባበት ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ለትውልድ የምናስቀምጠው ተስፋ መሆኑ ጠቅሰው፤ ሁሉም ዜጎች በችግኝ ተከላ ብቻ ሳይወሰኑ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብና በመጠበቅ ለመርሃ ግብሩ ዘላቂ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል።
ባለሙያዎችም በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት መሻሻል፣ ለአፈር ጥበቃ እና ለከተማው ውበት የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ በመገንዘብ፣ በቀጣይም በመሰል መርሃ ግብሮች በንቃት እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251948337446

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ-ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት Addis Ketema Subcity Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share