MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

MFAEthiopia Amharic  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ነው።

This page is aimed at informing the public both in Ethiopia and the rest of the world about Ethiopia's foreign relations by focusing on the activities of the Federal Democratic Republic of Ethiopia's Ministry of Foreign Affairs.

07/09/2026
ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?ለበለጠ መረጃ:➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et➜ ፋይዳ: id.gov.et➜ መሶብ: https://mesob...
06/09/2026

ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?

ለበለጠ መረጃ:

➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et

➜ ፋይዳ: id.gov.et

➜ መሶብ: https://mesobcenter.et/

➜ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት: aii.et

Office of the Prime Minister-Ethiopia

06/09/2026
05/09/2026
ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የአሜሪካን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ተቀብለው አነጋገሩ__________________________________________(ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ...
04/09/2026

ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የአሜሪካን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ተቀብለው አነጋገሩ
__________________________________________
(ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሽያ ጋር ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በተለይም የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የኤኮኖሚ ትስስርን በማስፋፋት ዙሪያ መክረዋል።

በተጨማሪም በጋራ ፍላጎቶች እንዲሁም በቀጣናዊ ሰላምና ደኀንነት ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ባካሄዱት የተቀናጀ የሁለትዮሽ ውይይት በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም፦ በኢኮኖሚ ብልጽግና፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፤ በመከላከያና ደኀንነት ትብብር፤ እንዲሁም በቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት ደኀንነት ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።

04/09/2026

ሳምንቱ በምስል/ ነሐሴ 29 ቀን 2018

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ በኢኮኖሚና በሁለትዮሽ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ ________________________________________________________...
03/09/2026

ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ በኢኮኖሚና በሁለትዮሽ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ
________________________________________________________
(ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከኔዘርላንድ የዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ፓስካሌ ግሮተንሁስ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የተሳካ ፍፃሜ ያገኘው 4ኛው የኢትዮጵያ–ኔዘርላንድ የፖለቲካ የምክክር መድረክ ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በልማት ትብብር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም የኔዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ባሏቸው የኢንስትመንት ዕድሎች ላይ ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።

ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርቶች ወደ አውሮፓ ገበያ ሰፊ ዕድል የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲሁም የቀጣናው ሰላምና ደኀንነት እና የባለብዙ ወገን ትብብር አስፈላጊነት ላይ ከምክትል ሚኒስትሯ ጋር መክረዋል።

ከ130 በላይ የኔዘርላንድ ኩባንያዎች ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ካፒታል በአበባና አትክልት፣ በወተትና ምግብ ማቀናበር፣ እንስሳት መኖ፣ ሎጂስቲክስ እና ማምረቻው ዘርፎች ላይ ማፍሰሳቸው ተጠቅሷል።

ሁለቱ ወገኖች ይህን ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግና ተጨማሪ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

"በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖ...
03/09/2026

"በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።"
ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያየኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡  የምዝገባ ቦታ፡- በወጭ ...
02/09/2026

ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡- በወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን፤

https://forms.gle/R7PmwCNeqEE3EQBN6

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

"የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝትየአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (...
01/09/2026

"የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር። ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሮጀክቶች ጉብኝት እና ምረቃ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል። አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችን እና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል።

‎ማኅበራዊ ጉዳይ፦
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።" Office of the Prime Minister-Ethiopia

Address

Menelik II Avenue, P. O. Box Addis Ababa
Addis Ababa
393

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115158928

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር:

Shortcuts

Share