Amanuel mental specialized hospital

Amanuel mental specialized hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amanuel mental specialized hospital, Addis Ababa ethiopia Addis ketema subcity at the vicinity of Mesalemeya, Addis Ababa.

Emmanuel mental specialized hospital is apionner one which provides mental health care and treatment for about people who are from all corners of the nation and mental health rehabilitation services since it has been established in 1938

ለዜጎች ሁለንተናዊ ፈውስ ዛሬን እንትከል!​አዲስ አበባ፦ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምዕራብ ሸዋ ዞን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር...
06/08/2026

ለዜጎች ሁለንተናዊ ፈውስ ዛሬን እንትከል!
​አዲስ አበባ፦ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)
አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምዕራብ ሸዋ ዞን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።
​"ጤናማ አእምሮ በለም አካባቢ ይለመልማል" በሚል መሪ ቃል አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ከተማ በ1.3 ሄክታር መሬት ላይ 5,000 ችግኞችን በመትከል አሻራውን አሳርፏል።
​በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የበጎ ፈቃድ ስራ ወጣቶች፣ የኤጀሬ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኤጀሬ ከተማ ከንቲባ በቦታው በመገኘት ችግኞችን በጋራ በመትከል የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ ሆነዋል።
​የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የተተከሉት ችግኞች ከሚሰጡት አጠቃላይ ሃገራዊ ጠቀሜታ ባለፈ ከፍተኛ ማህበረሰባዊ ቁርኝትና ትስስር የፈጠረ ነው ብለዋል።
​ሆስፒታሉ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በኤጀሬ ከተማ በቋሚነት የተለያዩ ሃገር በቀል ችግኞችን ሲተከል የቆየ ሲሆን አካባቢውን አረንጓዴ በማልበስ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ተፅዕኖዎች በመከላከል ላይ ይገኛል። "ጤናማ አእምሮ በለም አካባቢ" እንደሚለመልመው ሁሉ ለምለምና የተፈጥሮ ጸጋ የተሞላበት አካባቢ ለዜጎች ሁለንተናዊ የአእምሮና የአካል ጤና ፈውስ በመፍጠር እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ለምግብነት እና ለመድሃኒትነት አገልግሎት የሚውሉ የዛፍ ችግኞች መካተታቸው ደግሞ ጠቀሜታውን ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
​የሰው ልጅ ከዕለት ወደ ዕለት ከሚያጋጥሙት ፈተናዎች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ፣ የሀብት መመናመን እና የስነ-ምህዳር መዛባት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ኢትዮጵያ ይህንን ዓለም አቀፍ ችግር በግንባር ቀደምነት ለመቋቋም ከቀረፀቻቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች መካከል «የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር» ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ይህ መርሃ ግብር የነገውን ትውልድ ደህንነት ለመጠበቅ ዛሬ የሚቀመጥ ቋሚ ማዕዘን ነው።
​በመሆኑም ጤናማ ማህበረሰብን ለመገንባት የሕክምና አገልግሎት ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የተገነዘበው አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከህክምና አገልግሎቱ ጎን ለጎን እንዲህ ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡ ሆስፒታሉ ጤናማ ማህበረሰብ እንዲኖር ጤናማ አካባቢ አስፈላጊ ነው ብሎም ያምናል።
​በዚህም መሰረት ሆስፒታሉ በመጀመሪያው ምዕራፍ (ከ2015 ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ዓመታት)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት በ50,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ 20,000 ለምግብነትና ለመድሃኒትነት የሚውሉ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን በማልማትና በመትከል የአየር ንብረት ፅናትን በማስጠበቁ ሂደት የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል።
በአሁኑ ምዕራፍ (በ2018 ክረምት) ደግሞ እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብን ለማሳካት በተያዘው ኢኒሼቲቭ ሆስፒታሉ በአራተኛው ዙሩ 5,000 ሀገር በቀል ለምግብነትና ለመድሃኒትነት አገልግሎት የሚሰጡ ችግኞችን በኤጀሬ ከተማ በ1.3 ሄክታር መሬት ላይ በመትከል ለትውልድ ተሻጋሪ የሆነ አሻራውን አሳርፏል።
​ይህ ተግባር ሆስፒታሉ የማህበረሰብን አዕምሯዊ ጤና ከመጠበቅ ባሻገር የስነ-ምህዳር ሚዛንን በመጠበቅ በኩል ያለውን ከፍተኛ ኃላፊነት በግንባር ቀደምትነት ያሳየበት እና ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ሉዓላዊት ሃገር የመሆን ራዕይዋ እንዲሳካ የበኩሉን አሻራ ያሳረፈበት ድንቅ ምዕራፍ ነው።
​የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የነገዋን ኢትዮጵያ ገጽታ የሚወስን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው። በመሆኑም እንደ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሉ ተቋማት ከዕለት የዕለት የስራ አፈፃፀማቸው ባለፈ ለአካባቢና ስነምህዳር ደህንነት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የጋራ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ቁልፍ ሚና ያለው ሲሆን የዛሬው ትብብርና ትጋት ለነገው ትውልድ የሚተላለፍ የህይወት ውርስ ነው።

የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 30 ሺህ ችግኞችን ተከሉ።​አዲስ አበባ - ሐምሌ 27/ 2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)​"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ...
03/08/2026

የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 30 ሺህ ችግኞችን ተከሉ።
​አዲስ አበባ - ሐምሌ 27/ 2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)
​"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ አጠቃላይ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስመልክቶ በተከናወነው በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ኘሮግራም ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴራል ሆስፒታሎች፣ ተጠሪ ተቋማት፥ ኤጀንሲዎች የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በጋራ በመሆን በሸገር አስተዳደር በገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ በገፈርሳ ሀይቅ አካባቢ ችግኞችን ተከሉ።
​በጤናው ዘርፍ በ2018 ክረምት ወራት 250 ሺህ ችግኞችን ለመትከል በዕቅድ ተይዞ እየተሠራ የሚገኝ ሲሆን በዕለቱም በተከናወነው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ 30 ሺህ ችግኞችን መትከል ተችሏል።
​በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ "እጃችን ሥራ ሰርቶ ለትውልድ አሻራ የምናስቀምጥበት ዕለት እንኳን አደረሳችሁ" ብለዋል። አያይዘውም ሀገራችን በነፃነት ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ እንደቆየችው ሁሉ በአረንጓዴ አሻራም የሁልጊዜም ሉዓላዊት ሀገር እንድትሆን እንሰራለን ሲሉ በአጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ደጉማ በበኩላቸው "ጤናና ችግኝ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው" ያሉ ሲሆን ችግኝን መትከል የምንተነፍሰውን አየር፣ የምንመገበውን ምግብ እንዲሁም የሕክምና መሰረት የሆነውን መድሃኒታችንን ማምረት መቻል ነው ብለዋል።
በዚህ ታላቅ የህዝብ ተሳትፎ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚ/ር ከፍተኛ ባለስልጣናት ፥ የማኔጅመንት አባላት እና የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት አረንጓዴ ልማቱ የነገን ትውልድ ደህንነት እና የስነምህዳር ጽኑ መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸው በቀጣይም የተተከሉትን በመንከባከብ የነቃ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የጤና ተቋማት ለአየር ንብረት ጽናትአዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/ 2018 ዓ.ም  የጤና ሚኒስቴር ።፥የተጠሪ ተቋማት ፥ ፌዴራል ሆስፒታሎች እና የኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በ...
31/07/2026

የጤና ተቋማት ለአየር ንብረት ጽናት
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/ 2018 ዓ.ም የጤና ሚኒስቴር ።፥የተጠሪ ተቋማት ፥ ፌዴራል ሆስፒታሎች እና የኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በጋራ በመሆን «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ ከተማ ብሎክ 5 አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።
​ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነትን መሠረት በማድረግ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን በመተግበር ላይ ትገኛለች። መርሃ ግብሩ የአየር ንብረት መዛባትን ከሚያስከትሉ የካርቦን እና ሌሎች የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት መጠንን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ ነው። በተለይም እንደ አፍሪካ ላሉ ታዳጊ ሀገራት በድርቅ፣ በጎርፍ እና በሌሎች የአየር ንብረት ቀውሶች ሳቢያ ለሚደርስባቸው ጉዳት የመቋቋም አቅም ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
​ሀገራችን በ2018 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሃ ግብር እውን ለማድረግ ባስቀመጠችው ግብ እና በኮፐንሃገን በ2032 የተያዘውን የአየር ንብረት ለውጥ ኢኒሼቲቭ በግንባር ቀደምትነት ለማሳካት በሚደረገው አጠቃላይ ሐገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የጤና ተቋማት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
​በዕለቱ በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሁለገብ ጠቀሜታ ያላቸው ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች እና ለመድኃኒትነት አገልግሎት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው የዕፅዋት ዝርያዎች መትከል ተችሏል።
​ይህ በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተካሄደው መርሃ ግብር ኢትዮጵያ በሥነ-ምህዳር ግንባታ እና በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ሥራዎች ላደረገችው ጽኑ ቁርጠኝነት ድጋፍ ከመስጠቱም በላይ የጤና ተቋማት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ መሆናቸውን ያሳዩበት እንደሆነ ተገልጿል።

29/07/2026

ነፃ የጤና ምርመራ፣ ህክምና እና የባለሙያ ምክር አገልግሎት በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሠጠቱን የቀጠለ መሆኑን አውቃችሁ በመሣለሚያ በአውቶቡስ ተራና በሆስፒታሉ ግቢ በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን!

27/07/2026

ይምጡ! ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ነፃ የጤና ምርመራ፥ ህክምናና የምክር አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ

24/07/2026
ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በሙሉ፣ ጤናዎን በነፃ እንዲመረመሩ እና አስፈላጊውን የሕክምና እና ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ15/11/2018 ዓ.ም ...
22/07/2026

ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በሙሉ፣
ጤናዎን በነፃ እንዲመረመሩ እና አስፈላጊውን የሕክምና እና ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ15/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎቱን ይዞላችሁ ቀርቧል ።
​ይህንን እድል በመጠቀም ራስዎን ፥ ቤተሰብዎን እና ጓደኞችዎን ይዘው በመምጣት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነፃ አገልግሎቶች ያግኙ!
​የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ​የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ምርመራ
• የኤች አይ ቪ ምርመራና ምክር አገልግሎት
• ​የውስጥ ደዌ ህክምና
• ​ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጥ የጤና ምክር አገልግሎት
• ከሱስ ጋር በተያያዘ የካውንስሊንግ አገልግሎት
• ​ቅድመ መከላከያ እና የንጽህና ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ሌሎችንም አገልግሎቶች ያገኛሉ

• ​ቦታ፡ በሆስፒታሉ ውስጥ እና በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይሰጣል።
ጤናማ ሕይወት ለተሻለ ነገ! ዛሬውኑ በመምጣት የጤናዎ ባለቤት ይሁኑ።

አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ​አዲስ አበባ:ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)​“በጎነት ለጤና...
22/07/2026

አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ
​አዲስ አበባ:ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)
​“በጎነት ለጤና፤ ፈውስ ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ።
​በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የሆስፒታሉ ቦርድ አባል ክቡር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የክፍለ ከተማው ጤና ፅ/ቤት ሃላፊ ክቡር ወ/ሮ ዘውድነሽ ሽፈራው፥ የወረዳ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
​የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢዳኦ ፈጆ በመክፈቻ ንግግራቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጊዜን፣ እውቀትንና ጉልበትን ለሌሎች ማካፈል ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለወገን ያለንን ኃላፊነት በተግባር የምንገልጽበት የላቀ የዜግነት መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። ዘንድሮ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ከሆስፒታሉ ዕቅዶችና ዓላማዎች ጋር ተቀናጅተው ህብረተሰቡ ተጠቃሚ በሚሆንባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከእነዚህም መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ20 ሚሊዮን ዜጎች አገልግሎት ለመስጠት የታቀደ ሲሆን ሆስፒታሉ ለ67 ሺህ ዜጎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አያይዘውም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 10 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እንዲሁም 3 የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ቤቶች እድሳት ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀስ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የጤና ምርመራና የህክምና ምክር አገልግሎት በሽታን ቀድሞ ከመለየትና ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማጎልበት እና በአእምሮ ጤና ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም ትልቅ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።
​ክቡር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው በአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስተባባሪነት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ከሌሎች አጋር የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር የሚከናወነው ነፃ የጤና ምርመራ፥ ህክምናና ምክር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ምክንያቶች ወደ ጤና ተቋማት መድረስ የማይችሉ ወገኖችን በመድረስ የጤና እኩልነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
​በመጨረሻም የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች መሠረታዊ የጤና ምርመራ ያደረጉ ሲሆን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የአንድነት፥ የመተሳሰብና የሰብአዊነት እሴቶች መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በጋራ በመስራት ለወገኖቻችን ጥራት ያለው፥ ተደራሽና ርህራሄን የተላበሰ የጤና አገልግሎት በመስጠት የፈውስ እጅ እንዘርጋ፥ የአንድነታችንን ውጤትም በተግባር እናሳይ በማለት ጥሪ ቀርቧል።

The 2018.E.C. Summer Volunteer Health Service is formally launched by Emmanuel Mental Specialized Hospital.
Addis Ababa: July 15, 2018 E.C. (EMSH)
Emmanuel Mental Specialized Hospital began its 2018 E.C. Summer Volunteer Health Service with the theme "Goodness for Health: Healing for All!"
Honorable Ato Tarekegn Workneh, the Chief Executive Officer of Addis Ketema Sub-City Administration and a member of the hospital board; Honorable Ms. Zewdnesh Shiferaw, the Head of the Sub-City Health Office; woreda leaders; medical professionals; and invited guests attended the program.
Ato Edao Fejo, chief executive director of Emmanuel Mental Specialized Hospital, stated in his introductory remarks that volunteering is not only about imparting knowledge, skills, and energy to others but also about exhibiting our duty to the nation and its citizens. He added that this year's volunteer activities are in line with the hospital's plans and objectives and concentrate on important issues that will benefit the community. Among these, the hospital intends to offer comprehensive medical care to 20 million people across the country, and it is striving to make the services available to 67,000 people at the hospital level. Additionally, he said that it plans to renovate three homes for the elderly and disabled and plant 10,000 seedlings by aligning the national green program. Health screening and medical counseling services have been demonstrated to play a significant role in promoting a healthy lifestyle, correcting misconceptions about mental health, and early detection and prevention of disease.
The CEO of Addis Ketema Sub-City Administration, Honorable Ato Tarekegn Workneh, stated that the free health screening, treatment, and counseling voluntary service program, which is being carried out under the direction of Emmanuel Mental Specialized Hospital in cooperation with Addis Ketema Sub-City and other partner health institutions, has significantly contributed to ensuring health equity by reaching out to those who are unable to access health institutions due to social and economic reasons.
Lastly, a basic health screening was performed on the program participants. All citizens are urged to collaborate in order to provide our people with high-quality, easily accessible, and compassionate health services and to show the practical outcomes of our unity since volunteer work is an expression of human values, compassion, and unity.

የጤና እንክብካቤ መሰረታዊ መብትዎ ነው! የነፃ የጤና ምርመራ እና ህክምና በማድረግ ጤንነትዎን ያረጋግጡ። ቀድሞ መመርመር ከብዙ የጤና ችግሮች ይታደጋል። ዛሬውኑ ይመርመሩ!"
20/07/2026

የጤና እንክብካቤ መሰረታዊ መብትዎ ነው! የነፃ የጤና ምርመራ እና ህክምና በማድረግ ጤንነትዎን ያረጋግጡ። ቀድሞ መመርመር ከብዙ የጤና ችግሮች ይታደጋል።
ዛሬውኑ ይመርመሩ!"

Address

Addis Ababa Ethiopia Addis Ketema Subcity At The Vicinity Of Mesalemeya
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel mental specialized hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share