Gullele woreda 9 communication

Gullele woreda 9 communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gullele woreda 9 communication, Government Organization, Addis Ababa.

“ወርቃማው ሰኞ” ለሀገር ማንሰራራት(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን 2/13/18)በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር በተካሄደው የ“ወርቃማው ሰኞ” የመንግሥት ሰራተኞች ውይይት መድረክ ላይ የ...
07/09/2026

“ወርቃማው ሰኞ” ለሀገር ማንሰራራት

(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን 2/13/18)

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር በተካሄደው የ“ወርቃማው ሰኞ” የመንግሥት ሰራተኞች ውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች፣ መድረኩ ለሃገር ማንሰራራትና ለተቋማዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገለጹ።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ሰራተኞች እንደተናገሩት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ የሚካሄደው ይህ የውይይት መድረክ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የአስተሳሰብ አንድነት ለመፍጠርና የስራ ተነሳሽነትን ለማሳደግ የሚረዳ ነው::

በተጨማሪም ሰራተኛው በቁርጠኝነትና በተነሳሽነት ህዝብን ለማገልገል የሚያስችለውን አቅም እንደሚፈጥርለት ጠቁመዋል።

የውይይቱ ዋነኛ ዓላማውም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውጤታማ አሰራርን በመገንባትና የአገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ ለአገራዊ ማንሰራራት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ማስቻል መሆኑ ተመልክቷል።

 በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።የጳጉሜ ቀናት በክፍለ ከተማው በተለያዩ ስያሜዎችና ዝግጅቶች ...
07/09/2026



በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

የጳጉሜ ቀናት በክፍለ ከተማው በተለያዩ ስያሜዎችና ዝግጅቶች እየተከበረ የዛሬው ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ የታክሲ ባለንብረቶች ፣ የነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጥተዋል፣

ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞዋን የጀመረችበት የብልጽግናዋን መሠረት የጠላችበት ነው ፤ ትላልቅ ለውጦች የተመዘገበበት ይህንን የምንዘክርበት ሲሆን በክፍለ ከተማችንም የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት ለህብረተሰቡ እየተሰጠ ይገኛል።

የማንሰራራት ቀንን ስናከብር የኢትዮጵያን መጻኢ ዘመንን የብልጽግና መሆኑን በማሰብ ለመጪው አዲስ አመት ብሩህ ተስፋን መሰነቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ተሰጠ።(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን:2/13/18)
07/09/2026

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ተሰጠ።

(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን:2/13/18)

የፕሬስ መግለጫእንኳን ለጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!ኢትዮጵያ የብልጽግና ትልሞቿን በፅኑ መሠረት እየገነባች ነው፡፡ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ፖሊሲዎች እና ዕቅዶች እ...
07/09/2026

የፕሬስ መግለጫ

እንኳን ለጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ኢትዮጵያ የብልጽግና ትልሞቿን በፅኑ መሠረት እየገነባች ነው፡፡ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት ፖሊሲዎች እና ዕቅዶች እየተመራች ለኹለንተናዊ ብልጽግና እየተጋች ትገኛለች፡፡ በየዘመን አንጓዉ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በተደመረ ዐቅም እየተሻገረች፤ ከችግሮች እና ፈተናዎች ዕድሎችን መንጭቃ እያወጣች፤ ነገዋን በጠንካራ መሠረት ላይ እያጸናች ነው፡፡

ለዘመናት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከዓድማስ እስከ ዓድማስ የሚያውለበልበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነገዉን ታሳቢ አድርጎ እንደ ቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባሉ መሠረተ ልማቶች እና ኹለንተናዊ ለውጦች ውስጥ እያለፈ ነው፡፡ ፡፡ ነባር እና ዐዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች እየለሙ እና ተደራሽነታቸዉ እያደገ ነው፡፡ ግብርናችን ከዝናብ ጥገኝነት እየተላቀቀ እና የገጠሩም የከተሜዉም የሥራ ዕድል እየኾነ ነው፡፡ የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችን ከውኃ፣ ከነፋስ፣ ከፀሐይ፣ ከጂኦተርማል እና ከኑክሊየር ኃይል እንዲኾኑ የመደመር መንግሥት ሌት ተቀን እየሠራ ነው፡፡

ከተሞቿ ጎስቋላ ገጽታቸዉ እየተቀየረ እና ነገን እየዋጁ፤ መሠረተ ልማቶቿ እየተስፋፉ እና እየተቀናጁ፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዐቅሟ እየተጠናከረ፤ የቀጣናዉ የታዳሽ ኃይል ማእከልነቷ እያደገ፤ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ እያዋለች ለመጪዉ ትውልድ ኹለንተናዊ ብለጽግና እየሠራች ነው፡፡

የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያበስሩ፤ እመርታዊ ዕድገቷን የሚያፋጥኑ ፅኑ መሠረቶች ላይ እየተገነቡ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያንም ሥርዐቱን ለማጽናት እና መሻታቸዉን እውን ለማድረግ ያላቸዉን ቁርጠኝነት በመንግሥት ጥሪዎች በሚያሳዩዋቸው ተሳትፎዎች እየገለጹ ነው፡፡

በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ከሌሊት እስከ ሌሊት ፈተናዎችን ተቋቁመዉ ድምፅ መስጠታቸዉ እና ውጤቱን በደስታ መቀበላቸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ በየዓመቱ እያደገ የመጣ ተሳትፎ እና ስኬት ማስመዝገባቸው፤ የልዩነት ሐሳቦችን በሰላማዊ መንገድ ለመግራት ሀገራዊ ምክክርን መምረጣቸው ኢትዮጵያውያን በመደመር መንግሥት ትልሞች ላይ የያዙትን የጋራ ተስፋ እና ለስኬቱም እያደረጉ ያለዉን ርብርብ የሚያሳይ ነው፡፡

የዴሞክራሲ ሥርዐትን በማንበር፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመከተል፤ የከተሞችን ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ወደ ገጠር በማላመድ፤ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን በመሻሻል፤ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቱን በማዘመንና በማስፋፋት ለኢትዮጵያ ኹለንተናዊ ብልጸግና ፅኑ መሠረት እየተቀመጠ ነው፡፡ ለዚህም ነው ጳጒሜን 2ን “የማንሰራራት ቀን” በሚል ስያሜ እያከበርን የምንገኘው፡፡

ጳጒሜን 2 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ

የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን:2/13/18)በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የጽዳትና ውበት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት “የማንሠራራት ቀ...
07/09/2026

የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።

(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን:2/13/18)

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የጽዳትና ውበት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት “የማንሠራራት ቀን”ን ምክንያት በማድረግ የማህበረሰብ አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል እና በቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እና በአካባቢው በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በዚሁ የጽዳት ዘመቻ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳትና ውበት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማርታ አበበ፣ የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ ክብረት፣ የወረዳው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ምንዳዬ፣ የወረዳው አመራሮች፣ አባቶች ካህናት ፣ የወረዳው ነዋሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም የጽዳት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

07/09/2026
የማንሰራራት ቀንን ምክኒያት በማድረግ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው።የአዲስ አመት መቀበያ  የሆነችው ጳጉሜን ቀናት በተለያየ ስያሜዎች እየተከበሩ ሲሆን የዛሬው ጳጉሜን 2 ደግሞ...
07/09/2026

የማንሰራራት ቀንን ምክኒያት በማድረግ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

የአዲስ አመት መቀበያ የሆነችው ጳጉሜን ቀናት በተለያየ ስያሜዎች እየተከበሩ ሲሆን የዛሬው ጳጉሜን 2 ደግሞ በማንሰራራት ተሰይሟል።

የአዲስ አበባ የማንሰራራት ማሳያ የሆነው የትራንስፖርት ዘርፍም ለከተማዋ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ቀኑን እያከበረ ነው።

ለግማሽ ቀን በሚቆየው ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የከተማ አውቶብስና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ለደንበኞቻቸው መልካም የአዲስ አመት በመመኘት ጭምር እየተሳተፉ ነው።

በቦሌ ሚሊኒየም አካባቢ የተሰጠውን ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በነጻ ትራንስፖርቱ 1.1 ሚሊየን የመዲናዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ የማንሰራራት ማሳያ ከሆኑ ልማቶች መካከልም የትራንስፖርት ዘርፉ ዋነኛው ነው ያሉት አቶ ዳኛቸው የአዲስ አበባን ዝማኔ የሚመጥኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስፋፋት ዘርፉን ማንሰራራት ተችሏል ብለዋል።

ምቹ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋትና የዘመነ አገልግሎትም በዘርፉ መሻሻል ማሳየቱ ነው ምክትል ቢሮ ኃላፊው የገለጹት።


"የማንሠራራት ቀን ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስ...
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።"

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


06/09/2026


(ጉለሌ ወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን:1/13/18)

 #ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን!በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 1  " የእመርታ ቀን "  ምክንያት በማድረግ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን የሚያፋጥኑ የዶሮ እና የኬጅ ስርጭት ተከናወነ። በዕ...
06/09/2026

#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 1 " የእመርታ ቀን " ምክንያት በማድረግ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን የሚያፋጥኑ የዶሮ እና የኬጅ ስርጭት ተከናወነ።

በዕለቱ የመንግስትን የሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብር ተስፋ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የገለጹት ነዋሪዎች የተደረገላቸው ድጋፍ በቤተሰብ ደረጃ አምራች ለመሆን እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደገለጹት "የእመርታ ቀን" በርካታ ለውጦች የተመዘገቡባቸውና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውንና ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደ ማንሰራራት የምታደርገውን ጉዞ የሚያሳይ እንደሆነ ተናግረው፤ በሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን በተግባር በማረጋገጥና በማስፋፋት የስራ እድል በመፍጠር የሀገርን ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው "የእምርታ ቀን" ሲከበር ህብረተሰባችንን ከተረጂነት አስተሳሰብ እና ተግባር በማውጣት በሁሉም መስኮች አምራች እና ራስን ወደ መቻል ማሸጋገርን አላማ ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፤ በኢኮኖሚ ራስን ከመቻል ባለፈ በገበታ ላይ የሚቀርበውን ምግብ በራስ አቅም ማምረት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ የከፍታና የማንሰራራት ምዕራፍ እንደተሸጋገረች ገልፀው የዛሬውን የጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን" የምናከብረው በክፍለ ከተማችን በሥራ ዕድል ፈጠራና በከተማ ግብርና የተመዘገቡ ስኬቶችን መሠረት በማድረግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በ10ሩም ወረዳ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት የከተማ ግብርና ምርቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን፣ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የዶሮ እና የኬጅ ተደርጎ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gullele woreda 9 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gullele woreda 9 communication:

Shortcuts

Share