ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation ይህ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የፌስቡክ ገፅ ነው።
This is the page of the Addis Ababa Housing Development Corporation.
(1)

"የማንሠራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ።በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጳጉሜን 2 የሚከበረውን "የማንሠራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ የፎቶ ግራፍ አው...
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጳጉሜን 2 የሚከበረውን "የማንሠራራት ቀን" ምክንያት በማድረግ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ:: በአውደ ርዕዩ ላይ ኮርፖሬሽኑ በቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ውስጥ ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አየለ ከፋለ አውደ ርዕዩን በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰችበት ከፍታ በታላቅ ጥረት የተገኘ መሆኑን አስታውሰው ከሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱ በሆነው የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት የተሰማራው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ተቋሙ ባከናወናቸው ተግባራት ተስፋ ሰጪ ስኬት ማስመዝገብ እንደተቻለ ጠቁመዋል:: በቀጣዩ በ2019 በጀት ዓመትም እየተመዘገበ ያለውን አበረታች ውጤት ይበልጥ በማዳበር የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ ግንባታው ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከኮርፖሬሽኑ ጎን በመቆም እያሳዩት ያለውን የሥራ ተነሳሽነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበው ኮርፖሬሽኑም አስፈላጊውን ድጋፍ ናክትትል በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር መኮንን ሚጀና በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን በመገንባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን አመልክተው በቀጣይም የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በመከተል ግንባታውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ ላይ ኮርፖሬሽኑ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በተጨማሪ በቸግኝ ተከላ መርሀ ግብር አረንጓዴ አሻራ በማኖር እንዲሁም በማዕድ ማጋራትና በሌሎችም ሰው ተኮርተግባራት ያከናወናቸውን አበይት ሁነቶች የሚያመለክቱ ምስሎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡

"የኢትዮጵያ ማንሠራራት" የሚለውን መሪ ቃል ተከትሎ የተከፈተው የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ እሰከ መጪው ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በዛሬውየመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራሮች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ:-
https://linktr.ee/aahdc

ዻጉሜን 2 ቀን 2018 ዓ/ም

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

"የማንሠራራት ቀን ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስ...
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።"

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።ለቤተሰቦቿ ፣...
06/09/2026

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።

አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።
ለቤተሰቦቿ ፣ለወዳጅ ዘመዶቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሷን በአፀደ ገነት ያኑር

Lubbuun darbuu Artistii fi Qabsooftuu Bilisummaa Ilfinash Qannoo kanan dhagahe gadda guddaa keessatti.

Artist Ilfinash weellistuu qofa osoo hin taane qabsooftuu mirga namummaa fi wal-qixummaa turte.
Maatii ishee, firoottan ishee fi dinqisiifattoota isheef jajjabinan hawwa.
Waaqni Lubbuu ishee Jeennata haa jiraachisu

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

06/09/2026
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

06/09/2026
06/09/2026

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ከቦሌ - መገናኛ የቪአይፒ ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኝ የመንገድ መሿለኪያ ውስጥ የተፈጠረውን የውሃ ማቆር ችግር አስመልክቶ የሰጣችሁትን ጥቆማ በአክብሮት ተቀብለናል።

በእርግጥም የሰጣችሁት ጥቆማ ትክክል እና ተገቢነት ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ ለከተማችን ልማት ያላችሁን ተቆርቋሪነት እና የኔነት ስሜት ያሳየ በመሆኑ ከልብ እያመሰገንን።

ይህ ያልተጠናቀቀው የምድር ውስጥ መሿለኪያ ቦታ የውሃ ማቆር ችግር ያጋጠመው፤ ቀደም ሲል ስራውን ይዞት ከነበረው ኮንትራክተር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የውል መቋረጥ በማጋጠሙ እና የግንባታ መጓተት በመከሰቱ ሲሆን ፤ ይህንን ያልተጠበቀ ችግር በመረዳት ተቋማችን አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ሲሰራ ቆይቷል።

በመሆኑም ያልተጠናቀቀውን የመሿለኪያ የምድር ውስጥ ስራ ዳግም ለማስጀመር በፍጥነት የአዲስ ኮንትራት ግዢ ጨረታ በማውጣት ሂደቱ ተጠናቋል።

በመጨረሻም ሀሳባችሁን ለሰጣችሁ እና በኔነት ስሜት ተቆርቋሪነታችሁን ለገለፃችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ይህንን የተጓተተ ስራ በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱን መልሰን ለእናንተው የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ።

የከተማችንን ልማት ከነዋሪዎቿ ጋር በመሆን እናፋጥናለን!

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነውከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡...
06/09/2026

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

ከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የጸደይ መዳረሻን ለማብሰር ከሚከናወኑ ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “የጎቤ” እና “ሺኖዬ” ጨዋታ ተጠቃሽ ነው።
AMN

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

Address

Bole Olompia, SubCity Kirkos, Wereda 01
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን Addis Ababa Housing Development Corporation:

Shortcuts

Share