Addis Ababa city Auditor General

Addis Ababa city Auditor General we audit all addis ababa city government organization.
(1)

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለኦዲተርሮች እና ለአስተዳደር ሰራተኞች ሙያዊ ስልጠና መስጠት ጀመረ። ***********************************************...
24/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለኦዲተርሮች እና ለአስተዳደር ሰራተኞች ሙያዊ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

*************************************************
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የሚከናወኑ የኦዲት ሥራዎችን ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ታማኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ዘመናዊ አሰራርን የተከተለ ሙያዊ ስልጠና ለኦዲተሮች እና ለአስተዳደር ሰራተኞች መስጠት ጀመረ።

ይህ ስልጠና የተዘጋጀው የከተማው ተቋማት የፋይናንስ አስተዳደር፣ የንብረት ቁጥጥር እና የኦዲት አሰራር ሂደት ለማዘመን እና የሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ ጠቅሰው ተቋሙ አሰራሩን በማዘመን ውስን የሆነውን የህዝብ ሃብት በአግባቡ መያዙን የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ ለማድረግ ይህ ስልጠና የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ዋና ኦዲተር አመንቴ መቻሉ አክለው ኦዲተር መስሪያ ቤቱ ተቋማዊ አቅሙን በመገንባት የከተማዋን የፋይናንስ ደህንነት እና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሰል ስልጠናዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው በስልጠና የተሳተፉ ሰራተኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ህግንና ስርዓትን የተከተለ ጥራት ያለው የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚያስችል አቅም ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
**********************************************
የኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት
ነሐሴ 18/2018

23/08/2026
22/08/2026
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀጣናዊ የጤና ጉባኤ በዘርፉ ያስመዘገበችውን ሁለንተናዊ ድል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ታጋራለች - ዶ/ር መቅደስ ዳባ********************ኢትዮጵያ በ76ኛው የዓለ...
21/08/2026

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀጣናዊ የጤና ጉባኤ በዘርፉ ያስመዘገበችውን ሁለንተናዊ ድል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ታጋራለች - ዶ/ር መቅደስ ዳባ
********************

ኢትዮጵያ በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጉባኤ ላይ የጤና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ስኬታማ ተግባራት ተሞክሮ አድርጋ እንደምታጋራ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለፁ፡፡

76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ (RC76) ከነሐሴ 18 - 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በጉባኤው ኢትዮጵያ የጤና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሰራች ያለውን ስራ በተሞክሮነት የምታጋራበት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ካንትሪ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሀመድ ጃናቢ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን አህጉራዊ ጉባኤ ለ4ኛ ጊዜ የምታዘጋጅ ሲሆን፣ በጉባኤው ከ47 የአፍሪካ አባል ሀገራት የተወጣጡ የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እና የልማት አጋሮችን ጨምሮ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች በመገኘት በ1.5 ቢሊዮን ህዝብ የጤና ሁኔታ ላይ የሚያተኩሩ የጋራ መፍትሔዎችን ይመክራሉ።

በመድረኩ ኢትዮጵያ ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ስርዓት መገንባት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎትን ማጠናከር፣ የዲጂታል ጤና ስርዓትና በሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅምን ማሳደግ ላይ የነበራትን ስኬታማ ተሞክሮዎች የምታጋራ ይሆናል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ካንትሪ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሀመድ ጃናቢ ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን በፈጣን ሁኔታ የተቆጣጠረችበትን መንገድ በማደነቅ፣ ይህ ጉባኤ አፍሪካን ከተጋላጭነት ወደ አይበገሬነት እንዲሁም ከተረጅነት ወደ ራስን መቻል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ መፍትሔ የሚያስቀምጥ ታሪካዊ መድረክ መሆኑን አብራርተዋል።

አዲስ አበባ፥ ከአፍሪካ ከተሞች ምርጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባለቤት መሆኗን “ግሎባል ስታስቲክስ ዋየር” ገለፀ! ግሎባል ስታትስቲክስ በኤክስ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፥ በአፍሪካ የተ...
20/08/2026

አዲስ አበባ፥ ከአፍሪካ ከተሞች ምርጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባለቤት መሆኗን “ግሎባል ስታስቲክስ ዋየር” ገለፀ!

ግሎባል ስታትስቲክስ በኤክስ ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፥ በአፍሪካ የተሻለ እና ጥራት ያለው የከተማ መንገድ መሠረተ ልማት ያላቸው ከተሞች መዲናችን አዲስ አበባ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧል።

መዲናችን አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራት ያለው የመንገድ መሠረተ-ልማት እና ሰፊ የከተማ ትራምስፎርሜሽን ውጤት፣ ከተማዋ ዓለማቀፍ የስህበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል።

18/08/2026
18/08/2026

ለሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የቀረበ የከተማችን ስጦታ!

በከተማችን የገነባነው ውቡ የአራዳ ፓርክ ለሁሉም ማህበረሰቦች በእኩልነትና አካታች በሆነ መንገድ በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ስፍራ ነው፡፡ ይህ ፓርክ ለወጣቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት ፣ለስፖርተኞች፣ ለነጋዴውና ፣ ለአርቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ለተማሪዎች በጠቅላላ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ነው፡፡

ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል ከመፍጠርም በላይ ቱሪዝምን በማሳደግም ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ኑ ጊዜያችሁን ከቤተሰባችሁ ጋር በዚህ ውቧ አራዳ ፓርክ አሳልፉ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

ከዲጂታል አሠራር እስከ ዲጂታል ኢኮኖሚ፦ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የስኬት ጉዞ **********************  በዳታ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በፈጣን የቴክኖሎጂ ግስጋሴ በታጀበ...
18/08/2026

ከዲጂታል አሠራር እስከ ዲጂታል ኢኮኖሚ፦ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የስኬት ጉዞ
**********************

በዳታ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በፈጣን የቴክኖሎጂ ግስጋሴ በታጀበው የ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ ኢትዮጵያ ከተመልካችነት ወደ ዋና ተዋናይነት የተሸጋገረችበት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

ሀገራችን የያዘችውን “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ረጅም ርቀት ዓላሚ ስትራቴጂያዊ ራዕይ መሠረት በማድረግ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ እንቅስቃሴዎቿን በዘመናዊ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች ላይ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ ጉዞ የቴክኖሎጂ ሽግግር ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ዕለታዊ ሕይወት የሚያቀልል፣ አሠራርን የሚያፋጥን እና የኢኮኖሚ ምሰሶዎችን በጽኑ መሠረት ላይ የሚተክል ታላቅ የትራንስፎርሜሽን ማዕበል ነው።

ለዚህ ዘመናዊ እና ፈጣን የዲጂታል ምጥቀት በዋና መሠረትነት እየተጠቀሱ ካሉ የለውጥ አበጋዞች መካከል የዜጎችን ሁለንተናዊ ማንነት በዲጂታል መንገድ ማረጋገጥ ያስቻለው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ፋይዳ ግልጽነት ያለው እና ደኅንነቱ የተጠበቀ አሠራርን በመፍጠር፣ የመንግሥት እና የግል ተቋማት አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ እና ያለ እንግልት ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ አድርጓል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፋይናንስ ዘርፉ የታየው እና የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች እመርታ፣ ያለ ጥሬ ገንዘብ የሚፈጸሙ የገንዘብ ዝውውሮችን በማስፋፋት ዘመናዊ እና የተቀናጀ የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት ጥሏል።

የወደፊቷን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ግንባር ቀደም ለማድረግ ደግሞ የሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተበሰረው የ“5 ሚሊዮን ኮደሮች” ኢኒሼቲቭ፣ ወጣቶችን በሶፍትዌር ልማት፣ በዳታ ሳይንስ እና በዲጂታል ክህሎቶች በማነጽ ለነገው የቴክኖሎጂ ዓለም ብቁ እና ተወዳዳሪ የፈጠራ ባለቤቶች እያደረገ ይገኛል።

እንደ “መሶብ” ያሉ የተቀናጁ የኦንላይን መንግሥታዊ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርሞች መዘርጋታቸው ደግሞ፣ ዜጎች ከየትኛውም ቦታ ሆነው በኢንተርኔት አማካይነት አገልግሎቶችን በፍጥነት እና በቅልጥፍና እንዲያገኙ በማድረግ አስተዳደራዊ እንግልትን በአመዛኙ አስቀርተዋል።

የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ከማስፋፋት ጀምሮ እስከ ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና የክህሎት ግንባታዎች ተቀናጅተው እየተከናወኑበት ያለው ይህ ሁለንተናዊ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ ኢትዮጵያን በ2030 የአፍሪካ የቴክኖሎጂ፣ የኢኖቬሽን እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባር ቀደም ማዕከል ለማድረግ የተያዘው ትልቅ ሀገራዊ ሕልም እውን እንዲሆን እያስቻለ ይገኛል።

16/08/2026

ለነዋሪዎቻችን ተጠቃሚነት በተከታታይነት ያልተቋረጠና አዳዲስ ብስራት ማብሰር ያስቻለን ፈጠሪ አምላክ የተመሰገ ይሁን !!

የንፁህ መጠጥ ዉሃ እና የዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ምርቃት ላይ በመገኘት ያስተላለፍኩት መልዕክት

እንኳን ደስ አለን!!ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ  ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት  እና በቀን 20 ሺህ  ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክ...
16/08/2026

እንኳን ደስ አለን!!

ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን አልምተን በከተማችን ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ አድርሰናል፡፡

በተመሳሳይ ለረጅም ዘመን በከተማችን የሚገኙ ወንዞች በፍሳሽም፤ በደረቅ ቆሻሻም ሲበከሉ ቆይተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የፍሳሽ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት በ2009 ዓ .ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ችለናል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎቻችንን ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞቻችንን ብክለት የሚቀንሱ፣ የአካባቢ ጥበቃችንን የሚያጠናክሩ ናቸው። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ውብ፣ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ ዘመናዊና ለትውልድ የምትመች ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ላደረጋችሁ፤ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠን ያለውን የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ከሁሉ በላይ ዘላቂ ኑሯቸውን ሲመሩበት የነበረውን መሬት ለዚህ ታላቅ ልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች እና ለፕሮጀክቱ ስኬት ሌት ተቀን ያለእረፍት የተጉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa city Auditor General posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share