Industry Development Bureau - አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Industry Development Bureau - አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Industry Development Bureau - አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ልማት ለከተማችን ብልጽግና

የስራ ስምሪት አገልግሎትን በማስፋፋት፤ ሰላማዊ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን በማስፈን ለስራ ፈላጊው ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር፣የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመተግበር ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን ኑሮ ማሻሻል እንዲሁም የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የካፒታል ሊዝ፣ የገበያ፣ ቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ምክር ድጋፍ በማድረግ ኢንተርፕራይዝና አምራች ኢንዱስትሪ በምርትና ምርታማነት ብቁና ተወደዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ለቢሮዉ የተሰጠዉ ተልዕኮ ነው::

አምራችና ሸማቹ በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲስ አመት ባዛሮች በ11 ከፍለ ከተሞች ለህዝብ ክፍት ሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበዓላት ወቅት የሚከሰተውን የምርት እጥረትና የዋጋ ን...
03/09/2026

አምራችና ሸማቹ በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲስ አመት ባዛሮች በ11 ከፍለ ከተሞች ለህዝብ ክፍት ሆኑ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበዓላት ወቅት የሚከሰተውን የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት ለመከላከል አምራቾች ከሸማች ጋር በቀጥታ የሚገናኝባቸው ልዩ የአዲስ አመት ባዘሮችን በ11 ከፍለ ከተሞች በዛሬው ዕለት ለህዝብ ከፍት አድርጓል፡፡

አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከእሁድ ገበያዎች በተጨማሪ በ11 ክፍለ ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ያስጀመረ ሲሆን ሸማቾች ከትራንስፖርት እንግልት ነፃ በሆነ መልኩ በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የሸማቾች ሱቆችና የባዛር ማዕከላት መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን ጨምሮ እንደ ሽንኩርት፣ ቅቤ፣ እንቁላል፣ ዱቄት፣ ዘይት እና የባልትና ውጤቶች እንዲሁም የሀገር ባህልና ዘመናዊ አልባሳትና የተለያዩ ጌጣጌጦች፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች እና ልዩ ልዩ የፅዳት ዕቃዎች በስፋት ቀርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የክፍለ ከተሞቹ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የ በዛሬው ዕለት የተከፈቱትን ባዛሮች በስፍራው በመገኙት በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፤ ዛሬ ከተከፈተው ልዩ የአዲስ ዓመት ባዛሮች በተጨማሪ በከተማዋ በሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው በቀጥታ እየቀረበ ይገኛል፡፡

እነዚህ የዘመን መለወጫ በዓል ልዩ ባዛሮች ከዛሬ ነሀሴ 28 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ በድምቀት የሚቆይ ሲሆን ነዋሪዎች ወደ ባዛሩ እና ወደ በገቢያ ማእከላት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ገቢያ በመምጣት የቀረቡትን ሰፊ የገበያ አማራጮች በመጠቀም ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው ግብዓት መሸመት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ነሐሴ 28/2018 (ኢ.ል.ቢሮ)

መጪውን  የአዲስ አመት በዓል  አስመልክቶ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  ኢግዚብሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡በክፍለ ከተማው መጪው አዲስ አመት  በዓልን አስመልክቶ በአየር ጤና አደባባይ ኤግዚ...
03/09/2026

መጪውን የአዲስ አመት በዓል አስመልክቶ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢግዚብሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡

በክፍለ ከተማው መጪው አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ በአየር ጤና አደባባይ ኤግዚቢሽንና ባዛር በይፋ ተከፍቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ምክትል ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ የኤግዚቢሽንና ባዛር መከፈቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ11 ዱም ክፍለ ከተማዎችና እና በሁሉም ወረዳዎች በዛሬው እለት ኤግዚብሽንና ባዛሮች መከፈቱን አንስተዋል።

የተዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛሮች በዋናነት ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነና የክፍለ ከተማው ነዋሪ በአቅራቢያው በተዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛሮች ላይ በመገኘት ግብይት እንዲፈፅምም ጥሪ አቅርበዋል።

እስከ በአሉ ድረስም ምርቶች በስፋት እንደሚቀርቡ የገለፁት አቶ መሐመድ ለኤግዚብሽኑና ባዛሩ አስፈላጊ ዝግጅት ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አከበረኝ ወጋገን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ በበኩላቸው አዲስ አመትን በማስመልከት የክፍለ ከተማው አስተዳደር በባዛሮች፣ በገበያ ማእከላትና በ22 የቅዳሜና እሁድ ገቢያዎች ምርቶችን በስፋትና በጥራት ማቅረቡን ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለው ህብረተሰቡ በአልን በደስታ እንዲያሳልፍ እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ባዛሩ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው በዓሉን ምክንያት በማድረግ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ መቅረቡን አስታውቀዋል።

በአየር ጤና አደባባይ በተከፈተው ኤግዚብሽን እና ባዛር በክፍለ ከተማው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ኢንተርፕራይዞች ፣ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ አርሶ አደሮች እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የሚሰሩ ነጋዴዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በኤግዝብሽኑ የባህል አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማርና የማር ውጤቶች፣ የኢንደስትሪ ምርቶች ፣ የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ለበአል የሚውሉ የተለያዩ ምርቶች የቀረቡ ሲሆን እስከ ጳጉሜ 05/2018 ድረስም የሚቆይ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ምክትል ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ ፣የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን፣ክብርት ወ/ሮ ቦጋለች ተድላ የክፍለ ከተማዉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ፣አቶ ኢብራሒም መሐመድ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማ ፣ የወረዳ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።

ነሐሴ 28/2018 (ኢ.ል.ቢሮ)

መጪውን የ2019 አዲስ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ ሸማቹንና አምራቹን ያገናኘ ሁሉን አቀፍ ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ፡፡በቦሌ ክፍለ ከተማ የሕብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል እና ...
03/09/2026

መጪውን የ2019 አዲስ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ ሸማቹንና አምራቹን ያገናኘ ሁሉን አቀፍ ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሕብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል እና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ያለመው የ2019 አዲስ ዓመት በዓል የንግድ ባዛርና ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት በይፋ ተከፍቷል።

ባዛሩ ''መሰረታዊ የኢንዱስትሪ እና የግብርና
ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ በማቅረብ፤ ገበያን እናረጋጋለን!" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በርካታ አምራቾች፣ የአርሶ አደር ማህበራት እና የኅብረት ሥራ ማህበራት ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለነዋሪው በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ባዛሩን በይፋ የከፈቱት የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ-አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አንችነሽ ተስፋዬ፤ የባዛሩ ዋነኛ ዓላማ መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ በሕብረተሰቡ ላይ የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት ማቃለል መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ባዛሩ የደላሎችን አላስፈላጊ የሆነ ጣልቃገብነት በማስወገድ አምራቾች እና ሸማቾች በቀጥታ የሚገናኙበት ሰፊ አማራጭ እንደሚፈጥር ገልጸው፤ ሕብረተሰቡም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ የበዓል ገበያ ማረጋጋት በክፍለ ከተማው ሥራና ክህሎት፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና፣ ንግድ እንዲሁም የኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ ነው።

ነዋሪዎች በዓሉን ያለ ስጋት እንዲያከብሩ የሚያስችለው ይህ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እስከ በዓሉ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በመክፈቻው ተመላክቷል።

ነሐሴ 28/2018 (ኢ.ል.ቢሮ)

‎የ2019 አዲስ ዓመት ኢግዚቢሽን እና ባዛር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በድምቀት ተከፈተ‎‎የ2019 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ታላቅ የኢግዚቢሽን እና ባዛር መርሃ...
03/09/2026

‎የ2019 አዲስ ዓመት ኢግዚቢሽን እና ባዛር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በድምቀት ተከፈተ

‎የ2019 ዓመተ ምሕረት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ታላቅ የኢግዚቢሽን እና ባዛር መርሃ ግብር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በደመቀ ሥነ ሥርዓት መካሄድ ጀምሯል። በአዲስ አበባ ደረጃ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን፣ አጠቃላይ የማህበረሰቡን የአዲስ ዓመት የሸመታ ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀ ትልቅ መርሐግብር ነው።

‎በተለይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተመረቱ የሃገር ውስጥ ምርቶች በስፋትና በዓይነት ተዘጋጅተው ለህብረተሰቡ የቀረቡበት በመሆኑ፣ ለሸማቹ ማህበረሰብ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።

‎የተዘጋጁት የኢንዱስትሪ ውጤቶች በብዛትና በጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ በመሆናቸው፣ ህብረተሰቡ የዘመነ መለወጫ በዓልን ሲያከብር የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የምግብ፣ የአልባሳት፣ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

‎አምራቾች ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለሸማቹ ህብረተሰብ እንዲያቀርቡ ከማድረጉም በላይ፣ ህገ ወጥ ንግዶችን በማስቀረት የዋጋ ንረትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

‎ይህ በየክፍለ ከተሞቹ የተጀመረው ታላቅ የኢግዚቢሽን እና ባዛር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል። ህብረተሰቡ እስከ በዓሉ ዋዜማ ድረስ በሚቆዩት በእነዚህ የገበያ ስፍራዎች በመገኘት የሚፈልጋቸውን አቅርቦቶች በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንደሚችሉ ተገልጿል።

‎በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የገበያ ማዕከላት ደረጃቸውን ጠብቀው የተዘጋጁ በመሆናቸው፣ ሸማቾች ወደየአካባቢያቸው ባዛሮች በመሄድ እንዲሸምቱ እና የበዓሉን ድምቀት እንዲጋሩ ጥሪ ተላልፏል።

‎በአጠቃላይ ይህ ዝግጅት የአገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ የአምራቾችንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘትና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። መላው የከተማዋ የማህበረሰብ ክፍል እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ በተዘጋጁት የገበያ ቦታዎች በመገኘትና የሃገር ውስጥ ምርቶችን በመግዛት ለበዓሉ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ይበልጥ ይበረታታል።

‎ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኢ.ል.ቢሮ)

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

01/09/2026
ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪቃል አስጀምረናል።ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ፥ ተደራሽነትን ለማስፋት፥...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ፥ ተደራሽነትን ለማስፋት፥ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ ፥ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፥ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ ለመስጠትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የትምህርት ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል ታይቷል። ነገርግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፥ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፥ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፥ ችግር የሚፈቱ፥ በሥነ ምግባር የታነፁ፥ በእውቀት የታጠቁ ተማሪዎች በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንሸስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ ዋና የእዕምሮ እድገት ከጨቅላ ህፃንነት ወቅት የሚጀምር በመሆኑ ከቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፒሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፥ በስነምግባር የታነፁ፥አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፥ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት  መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል። በ6ኛዉ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠን...
30/08/2026

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል።

በ6ኛዉ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት መነሻ ያደረገ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፈን ቃላችንን በተግባር ቆጥረን ፈፅመን የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ከተማችን ደግሞ ተወዳዳሪ እንድትሆን አድርገናል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የከተማችን ነዋሪ እምነት አድሮበት ዳግም መርጦን ሀላፊነት ሰጥቶናል።
የዛሬው ውይይትም የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት መነሻ ያደረገ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ዝርዝር ግቦች ላይ ተወያይተን በማዳበር የባለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀምን በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ ነው።

እነዚህን ዝርዝር ውይይቶች ስናደርግ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ በማሳደግ፣ አመራራችን ከፊት ሆኖ የበለጠ እየሮጠ ህዝባችንንና የልማት አጋሮቻችንን በማስተባበርና ተሞክሮዎችን በማስፋት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሀገራዊ ማንሰራራት ውስጥ የአዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ እንተጋለን።

በተጨማሪም በክረምት የያዝናቸው የ90 ቀን ስራዎች ውስጥ የ60 ቀናት አፈፃፀማችንንም የምንገመግምበት የውይይት መድረክ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የቦሌ ክፍለ ከተማ  ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን አስጀመረ፡፡ጽህፈት ቤቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስተባበር  በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረ...
27/08/2026

የቦሌ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን አስጀመረ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስተባበር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሁለት አቅመ ደካማ አባወራዎች እና እማወራዎች ቤቶች ለማደስ አስጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አምራቾች የሚገጥማቸውን የመሠረተ ልማትና የግብዓት አቅርቦት ማነቆዎችን መፍታት፣ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ በተቀመጠው የ90 ቀን እቅድ መሰረት በትኩረት እንዲሰሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የቦሌ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ስራዉን አስጀምሯል፡፡

ቤቶችንም በፍጥነት እና በጥራት በመገንባት በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎቹ ለማስረከብ በትኩረቶ እንደሚሰራ የቦሌ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር አብዲ ገልጸዋል።

አምራቾች በኢኮኖሚ ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እና የሚገጥማቸውን የመሰረተ ልማት ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የመንገድ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነም አቶ ኡመር ገልጸዋል።

ነሃሴ 21/2018 ዓ.ም (ኢ.ል.ቢሮ)

ለተጨማሪ መረጃ

Face book
https://www.facebook.com/AACIDB
Telegram Address
https://t.me/AACIDB
Website Address
https://www.industrydevelopment.gov.et
YouTube Address https://www.youtube.com/channel/UCfh4g0AVsFaHY2s0CnSRkjQ
Tiktok
https://www.tiktok.com/.industry.devel?_t=8rjntizEz

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Industry Development Bureau - አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Industry Development Bureau - አዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ:

Shortcuts

Share