አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac

አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን 🇪🇹

Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation 🇪🇹

Bulchiinsa Magaalaa Addis Ababa Korporeeshinii Bulchiinsa Iddoowwan Bashannanaa Uummataa 🇪🇹

🌐 Website
AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC


👉Titkok
Tiktok.com/AACAPRAC
👉YouTube
youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC

ለ5ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ  በመምጣት ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia  (የኸርት አታክ  ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና  የበጎ ...
18/07/2026

ለ5ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia (የኸርት አታክ ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑን በጽ/ቤታችን ተቀብለናቸዋል።

የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ በፍቅር የምትሰጡት እጅግ የላቀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከልብ የሚደነቅ ነው ።
በቀጣይም የህክምና ተራ እየጠበቁ ላሉ የልብ ህሙማን ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ በጋራ ተቀናጅተን የብዙዎችን ሕይወት ለመታደግ አብረን ለመስራት ተስማምተናል።

እንደዚህ ትልቅ የህክምና ቡድን አቀናጅታችሁ ለወገኖቻችሁ ትልቅ ህይወትን የማዳን ስራ ለመተግበር የተጋችሁ መስራቾቹን እና የበጎ ፍቃድ የህክምና ቡድኑን አባላት በራሴ እና በታካሚዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣  ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር  ክብርት ማርያም ሳሊም ጋር የአዲስ አበባን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሻሻል  በጋራ መስራት ላይ ፍሬያማ  ውይይት ...
18/07/2026

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ክብርት ማርያም ሳሊም ጋር የአዲስ አበባን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሻሻል በጋራ መስራት ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

በከተማ አስተዳደራችን የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በተለይ E- mobility (የጭስ አልባ ትራንስፖርት) ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየሰራን ያለነውን ስራ ለማጠናከር እና በዘርፉ የተሰማሩ የግል ሴክተሮችንም ለመደገፍ ከዓለም ባንክ ጋር በአጋርነት እና በትብብር ለመስራት ከክብርት ከማርያም ሳሊም ጋር ተግባብተናል ።

ክብርት ማርያም ሳሊምን እና የቴክኒካል ቡድናቸውን በራሴና በከተማው ህዝብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

18/07/2026
17/07/2026
የአየር ንብረት ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ለሀገራዊ እድገት አዲስ አቅም እየፈጠረ ያለው አረንጓዴ ዐሻራAMN- ሐምሌ 10/2018 ዓ.ምኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚል የጀመ...
17/07/2026

የአየር ንብረት ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ለሀገራዊ እድገት አዲስ አቅም እየፈጠረ ያለው አረንጓዴ ዐሻራ

AMN- ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚል የጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የሀገሪቱን ምጣኔ- ሀብታዊ መዋቅር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

መርሐ ግብሩ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የኢኮ-ቱሪዝም ዘርፍን በማነቃቃት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ትልቅ የኢኮኖሚ ምሰሶ እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል።

እንዲሁም የአፈር መሸርሸርን መከላከል እና የከርሰ-ምድር ውሃን ማበልጸግ ከአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ትሩፋት ውስጥ ተጠቃሽ ሲሆኑ ለግብርናው ዘርፍ መነቃቃትም ትልቅ አቅም ፈጥሯል፡፡

በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኩረት የተሰጠው የፍራፍሬ እና ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸው የአርሶ አደሩን የገቢ ምንጭ ከማሳደጉም በላይ የሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማሟላት አስችሏል።

የአቮካዶ፣ የማንጎ፣ የፓፓያ እና የቡና ምርቶች በስፋት መመረታቸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ሲሆን ይህም ግብርናው ከተለመደው አሠራር ወጥቶ ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸው ምርቶች እንዲመረቱ በር ከፍቷል።

በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን በማዘጋጀት፣ በመትከል እና በመንከባከብ ሂደት ውስጥ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች እና ሴቶች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

ከችግኝ ጣቢያዎች ዝግጅት ጀምሮ እስከ ደን ልማት ጥበቃ ድረስ ያለው ሰንሰለት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም በከተሞች የተገነቡት ዘመናዊ መናፈሻዎች እንዲሁም ፓርኮች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች መዳረሻ በመሆን የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛል፡፡

ይሄም የከተማ ውበትን ከመፍጠር ባለፈ በቱሪዝምና መስተንግዶ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር እና የሀገር ገጽታ እንዲገነባም አድርጓል።

አረንጓዴ ልማት ለአሁኑ ትውልድ የምግብ ዋስትና ከመሆን ባለፈ ወደፊት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የካርቦን ሽያጭ ገበያ ላይ እንድትሳተፍ እና ከዓለም አቀፍ አረንጓዴ ፈንድ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያስችል ትልቅ መዋዕለ-ነዋይ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳደግ መቻሏ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኘውን አረንጓዴ ፋይናንስ እና የካርቦን ሽያጭ ገበያን ለመቀላቀል ሰፊ ዕድል ከፍቶላታል።

በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የሚድነውን የሀገር ሀብት ሳይጨምር የተፈጠረው ለምለም አካባቢ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ዋስትናን የሚያረጋግጥ ነው።

የአረንጓዴ ዐሻራ ትሩፋቶች ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድም አስተማማኝ ምጣኔ-ሀብታዊ መሰረት የሚጥሉ ነው፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል። ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ያ...
17/07/2026

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ያስቀመጥናቸውን ግቦች፣ እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዳችን ማጠቃለያ ዓመትም በመሆኑ ከባለፉት 5 ዓመታት አፈፃፀም ጋር አያይዘን የምንገመግም ይሆናል።

እንደሚታወቀው ባለፉት 5 ዓመታት ያቀድናቸውን ስትራቴጂክ ግቦች በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር በታማኝነት፣ በቅንነት፥ ያለ እረፍት 24/7 ሰርተን በርካታ ውጤቶችን አስመዝግበናል።

በተለይም አዲስ አበባን ከማይጠቅሙ አጀንዳዎች አውጥተን የልማት እና የሰላም ማዕከል እንድትሆን አድርገናታል። እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ፅዱ፥ አረንጓዴ፣ ውብ እየሆነች በመምጣቷ የዓለም ትኩረትን ስባለች።

በእርግጥ ከስኬቶቻችን ባሻገር ዛሬም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች አሉብን። በተለይ የአመራራችን የውጤታማነት ልዩነቶች፣ በከተማችን የሚታዩ የኑሮ ውድነት እና ፍልሰት ችግሮችን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል።

በርካታ ስኬቶችን ብናስመዘግብም ከህዝቡ የመልማት ፍላጎት እና ከብልፅግና ግባችን አንፃር ብዙ ስለሚቀረን ስኬቶቻችንን ማስፋት፤ ተግዳሮቶች ደግሞ ለይተን መፍታት በቀጣይ በጀት ዓመት የላቀ ስኬት ማስመዝገብ የግምገማችን ማዕከል ይሆናል። በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም ላይ እንወያያለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር የጋራ ስራዎችን በትብብር በምንሰራበት ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።በቆይታችንም፤ በቀዳማይ ልጅነት...
17/07/2026

በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር የጋራ ስራዎችን በትብብር በምንሰራበት ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

በቆይታችንም፤ በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው-ተኮር ስራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ እየተለዋወጥን፣ ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

እንኳን በሰላም ተገላገልሽ!"ምንም እንኳን የመውለጃዬ ቀን ቢቃረብም “ሀገሬ ጠርታኝ አልቀርም” በማለት ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመጣችው ወጣት ክርኑዶ ኡጁሉ፣...
17/07/2026

እንኳን በሰላም ተገላገልሽ!

"ምንም እንኳን የመውለጃዬ ቀን ቢቃረብም “ሀገሬ ጠርታኝ አልቀርም” በማለት ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመጣችው ወጣት ክርኑዶ ኡጁሉ፣ በጉባኤው ሂደት ላይ እያለች በዘውዲቱ ሆስፒታል ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

የሀገር ፍቅር እና የእኔነት ስሜት ሲኖር የማይቻል ነገር አለመኖሩን ማሳያ የሆነችውን ይህችን ጀግና እናት፤ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር በመሆን ባረፈችበት ቤት በመገኘት እንኳን ደስ አለሽ ብለናታል።
ይህችው ጀግና እናት፤ የተለመደውን ስም የማውጣት ባህል በመተው፣ የልጇን ስም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እንዲያወጣላት በጠየቀችው መሰረት የህፃኑን ስም "ምክክር" ብላዋለች።

ዛሬም በሄድንበት ወቅት፣ ወጣቷ የመጣችበትን ታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ወደ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በልበ ሙሉነት እንደምትመለስ አረጋግጣልናለች። እኛም ጉባኤውን አጠናቃ ወደ መጣችበት እስክትመለስ ድረስ ለእሷና ለልጇ የሚያስፈልገውን ድጋፍ እናደርግላታለን።

እህታችን ወንድ ልጇን በሰላም ተገላግላ በደስታ እንደተሞላች ሁሉ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችንም ከገጠማት አንዳንድ ችግሮች በምክክር እና በንግግር ተገላግላ፣ ትልቅ እና ወሳኝ የሽግግር ምዕራፍ እንደሚሆንላት ፅኑ እምነታችን ነው።

ህፃን ምክክርም፤ እደግ ተመንደግልን! አንተ እና መሰል የኢትዮጵያ ህፃናት ሁሉ ቦርቃችሁ እና ተደስታችሁ የምታድጉባት፣ እንዲሁም የምትረከባት ሀገር ሰላሟ ሙሉ የሆነች፣ የህዝቦች ፍቅር ያበበበት እና የበለፀገች ኢትዮጵያ እንድትሆን ከልብ እንመኛለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

Baga nagaan deesse!

"Yeroon dahumsa koo dhiyaatullee, biyyi koo na waamtee hin hafu” jechuun naannoo Gaambeellaa irraa gara Finfinneetti yaa'ii Marii Biyyoolessaatiif kan dhufte dargaggeettiin Kirnuudoo Ujuluu, adeemsa marii kanarra osoo jirtuu Hospitaala Zawudituutti mucaa dhiiraa nagaan deessee jirti.

Jaalala biyyaa fi miirri kiyya jedhu yoo jiraate wanti hin danda'amne akka hin jirre argarsiistuu kan taate haati gootni kun, Pirezidaantii Naannoo Gaambeellaa Kabajamtuu Aadde Alamituu Umad waliin ta'uun mana isheen boqottee jirtutti argamuun baga gammadde jenneerraan.

Haati gootni kun, aadaa maqaa baasuu barame dhiisuun, maqaa mucaashee Koreen Marii Biyyaalessaa akka baasuuf gaafatte irratti hunda'uun maqaa daa'imichaa "Mikikkir" jettee moggaasteetti.

Har'as yeroo dhaqne, dargaggeettiin kun kaayyoo guddaa biyyaalessaa dhufteef galmaan gahuuf, boqonnaa guyyoota muraasaa booda gara yaa'ii Marii Biyyaalessaatti onnee guutuun akka deebitu nuuf mirkaneessiteetti. Nutis marii kana xumurtee gara iddoo dhufteetti hanga deebitutti

በተፈጥሮ ውበት እና በተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎቶች የታጀበው የቀበና የወንዝ ዳር ልማት
16/07/2026

በተፈጥሮ ውበት እና በተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎቶች የታጀበው የቀበና የወንዝ ዳር ልማት


Address

Bole , Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share