05/08/2026
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በመጎብኘት የተለያዩ የጤና ልማት ፕሮጀክቶችን ስራ አስጀምረዋል
__________
ለጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ቢሮዎች የጋራ መድረክ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህር ዳር ከተማ የገቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በመጎብኘት የተለያዩ የጤና ልማት ፕሮጀክቶችን ስራ አስጀምሯል።
የሆስፒታሉን የተለያዩ የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋዉረዉ የጎበኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ በ 200 ሚልዮን ብር ወጪ የተገነባ የኦክስጂን ማምረቻ ማእከልን መርቀዉ ስራ አስጀምሯል።
በተመሳሳይ የሆሲፒታሉ የቀዶ ጥገና እና የጨቅላ ህጻናት ህክምና ማዕከል እድሳት እንድደረግለት በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን የዲጅታል ቋት ማእከልና ማህበረሰቡን ከመድሃኒቶች እና አገልግሎቶች ጋር ማገናኘት ዓላማ ያደረገውን የጤንነቴ መተግበሪያ መርቀው ስራ አስጀምሯል።
በጤንነቴ መተግበሪያ አገልግሎት ከ 560 በላይ የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች መረጃ ተጭነዉ ወደ ስራ መገባቱ የተገለጸ ሲሆን ከመድሃኒት አገልግሎትና ተያያዝ መረጃዎች ጋር ተያይዞ ያለዉን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀርፍ የጤንነቴ መተግበሪያ አገልግሎት በሁሉም ክልሎች በፍጥነት እንዲተገበርና የህብረተሰባችን ተጠቃሚነት እንዲረጋጥ ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ አሳስበዋል።
የመርሃ ግብሩ ታዳሚዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ችግኝ ተከለዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V