The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት

The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት It is the Supreme Court of the federal state of Ethiopia. It is the highest court of all the regional and federal state courts.
(2)

‎ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ501ኛው የነብዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል አደረሳችሁ። ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ‎መልካም የመውሊድ በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል...
25/08/2026

‎ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ501ኛው የነብዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል አደረሳችሁ።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ‎መልካም የመውሊድ በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ‎‎ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረ...
24/08/2026

‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

‎ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመደገፍ፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

‎በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ክቡራን ዳኞች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል አሻራቸውን አኑረዋል።

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ክቡር ዳኛ ተመሰገን ወንድምአገኝ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 09/2018 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋ...
15/08/2026

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ክቡር ዳኛ ተመሰገን ወንድምአገኝ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 09/2018 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

‎በዳኛ ተመስገን ወንድምአገኝ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የዲጂታል ዳኝነት አገልግሎት መስጠት ጀመረ‎‎ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)‎‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳ...
11/08/2026

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የዲጂታል ዳኝነት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

‎ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

‎በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ አዲሱ አሰራር በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ስራ ወደ ክልል ማዕከላት የማስፋት አካል ነው።

‎ማዕከሉ በአካል መገኘት ሳይያስፈልግ ክስ ለመመልከት የሚያስችል የርቀት ችሎት፣ የምስክሮችን እና የተከራካሪዎችን ቃል በቀጥታና በፍጥነት ለመመዝገብ የሚያስችል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ድምፅን ወደ ጽሑፍ የመቀየር ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም የክስ መዝገቦችን በኢንተርኔት አማካይነት በዲጂታል መንገድ ለማስገባትና ለማስተዳደር የሚያስችል አገልግሎቶችን ይሰጣል።

‎እነዚህ አሰራሮች ህብረተሰቡ ለአገልግሎት የሚያወጣውን እንግልት እና አላስፈላጊ ወጪ በመቀነስ፣ የዳኝነት ሂደቱን ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተዳራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

‎የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ ‎‎ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)‎‎በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎ...
09/08/2026

‎የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ

‎ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

‎በአርባምንጭ ከተማ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመራሮች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ተሳትፈዋል።

የ‎ልዑካን ቡድኑ ከችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተጨማሪ በአርባምንጭ ከተማ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይከታተላሉ፦

‎👉 ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia
‎👉 ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1
‎👉 ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia
‎👉 ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR
‎ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia
‎👉 ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/
‎👉 ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/.supreme.court

‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ‎‎ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)‎‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።‎‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳን...
08/08/2026

‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

‎ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

‎ክቡር ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፤ የዳኝነት አገልግሎቱን ለተገልጋዮች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና የሕዝብን እንግልት እንዲሁም አላስፈላጊ ወጪ ለመቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው፤ ጉባኤው በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠሩ ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል።

‎በመድረኩ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ እና የዳኝነት ግንኙነት መድረክ በአዋጅ የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መነሻ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፤ ተቋማዊ ብቃትን ለማሳደግ ሕጋዊ ውጤትን በግልጽ ማመላከት፣ ውሳኔዎችን ይፋ ማድረግ፣ የክትትል ሥርዓት መዘርጋት፣ የአፈጻጸም መለኪያዎችን ማዘጋጀትና የሥልጣን ወሰንን መለየት እንደሚገባ የሚመክሩ ሀሳቦች ቀርበዋል።

‎የጉባኤው አባላት በቀረበው ሰነድና በተነሱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በዋና ዋና ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ጉባኤው ተጠናቋል።

‎በዚሁ ጉባኤ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ በአዋጁ አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት የተጠቀሱት የጉባኤው አባላት ተገኝተዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይከታተሉ፦

‎👉 ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia
‎👉 ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1
‎👉 ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia
‎👉 ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR
‎ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia
‎👉 ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/
‎👉 ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/.supreme.court

‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ ተጠናቀቀ‎‎ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)‎‎በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድ...
08/08/2026

‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ ተጠናቀቀ

‎ነሐሴ 02/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ ተጠናቋል።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉባኤው ሰብሳቢ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተገልጋዮችን እና የኅብረተሰቡን እርካታ በጋራ ማረጋገጥ የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ በጋራ ሥልጣንና ኃላፊነት መሥራት በአዋጁ የተጣለብን የሁላችንም ኃላፊነት ሲሉ ተናግረዋል።

‎ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከፍትሕ ተዳራሽነት እና ቀልጣፋነት ጋር በተያያዘ በጋራ በመምከር ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ነጻ እና ገለልተኛ ፍርድ ቤት የመፍጠር ኃላፊነት ከመድረኩ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

‎መድረኩ የጋራ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለመመልከት ያስቻለ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፤ እርስ በእርስ የሚያገናኙ ጉዳዮችን በማመቻቸት በተለይም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም በኩል በሁሉም ዘንድ የታየው ለውጥና የተገኘው ውጤት የሚያስደስት መሆኑን ገልጸዋል።

‎በመድረኩ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሚረዱ የተለያዩ ሐሳቦች ተነስተው ጥልቅ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ የድጎማ በጀት አከፋፈል ቀመር መመሪያ፣ የቃለ መሃላ አፈጻጸም ማስፈጸሚያ ማንዋል፣ እንዲሁም የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና ኢ-ፋይሊንግ ማዕከላት አስተዳደር መግባቢያ ስምምነት ሰነዶች ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኃላ ጸድቀዋል።

‎በውሳኔው መሰረት የጸደቁ ሰነዶች የፊርማ ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን መድረኩ የታቀዱለትን ግቦች በማሳካት ተጠናቋል።

‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ‎‎ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)‎‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ...
07/08/2026

‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

‎ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

‎በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረትን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

‎መድረኩ እንደ አገር የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን በሚያሻሽሉ የጋራ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ  በተሰ...
06/08/2026

በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዉክልና ስልጣናቸዉ በቀጥታ ያዩዋቸዉን የፈዴራል ጉዳዮች በይግባኝ የማየት ስልጣን ያላቸዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ በክልሉ እንዲደራጁ የተደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ናቸው ተብሎ ተወስኗል፡፡

የውሳኔውን ሶፍት ኮፒ (PDF) ፋይል ከታች 👇 የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
https://t.me/fscethiopiaPR/4767

ፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዲስ የተሾሙ አመራሮች ...
06/08/2026

ፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ አመራሮች የሥራ ርክክብ አደረጉ

ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዲስ የተሾሙ አመራሮች በዛሬው ዕለት የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

‎የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በፈቃዳቸው መልቀቂያ ባስገቡት የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አመራሮች ምትክ በኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ተመልምለው የቀረቡ እጩዎችን ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ሹመት መስጠቱ ይታወሳል።

‎ክቡር ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሁም ክቡር ሼህ አብዱልመናን መሐመድ አህመዲን የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ በተሾሙት መሰረት በዛሬው ዕለት ከቀድሞ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር ሼህ ሙባራክ ሼህ መሐመድ አወል እና ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሼህ ሸረፈዲን ሚስባህ የስራ ርክክብ አድርገዋል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በስራ ርክክቡ ወቅት፤ የፌዴራል ሼሪዓ ፍርድ ቤቱን እስከ ዛሬ ድረስ በፕሬዝዳንትነት እና በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ አመራሮችን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው፤ በዛሬው ዕለት ኃላፊነት ለተረከቡት አዲስ አመራሮች የበለጠ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው በማሳሰብ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።

‎የስራ ርክክቡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
👉ዌብ ሳይት ↠ https://www.fsc.gov.et/
👉ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia
👉ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1
👉ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia
👉ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR
👉ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia
👉ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/
👉ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/.supreme.court

Address

Sidist Kilo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251111553400

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to The Federal Supreme Court of Ethiopia -የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት:

Shortcuts

Share