Bole Communication- ቦሌ

Bole Communication- ቦሌ ይህ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ሲሆን፣ በክፍለ ከተማው የሚከናወኑ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁነቶች መረጃ የሚሰጥበት ነው።

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመ...
01/09/2026

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ለዚህም በቂ የበዓል ፍጆታ ምርቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም ከ28/12/18 ዓ ም ጀምሮ በዓሉን በማስመልከት በ11ዱም ክ/ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ገልፀው የእሁድ ገበያዎችም ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በባዛሮቹ ከበዓል ፍጆታዎች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ለትምህርት የሚሆኑ ግብዓቶች እና የተለያዩ አልባሳቶች የሚቀርቡ መሆናቸውን ወ/ሮ ሀቢባ አሳውቀዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመግለጫቸው የበዓል ፍጆታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው፣ ህገ-ወጥ የሆነ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥም የከተማችን ነዋሪ በ8588 ነፃ የስልክ ጥሪ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝትየአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (C...
01/09/2026

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር። ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሮጀክቶች ጉብኝት እና ምረቃ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል። አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችን እና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል።

‎ማኅበራዊ ጉዳይ፦
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።


የሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራት ለአዲሱ ዓመት በቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለኅብረተሰቡ እያቀረቡ ነው።በቦሌ ክፍለ ከተማ በአሥራ አንዱም ወረዳዎች የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ስራ ማ...
01/09/2026

የሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራት ለአዲሱ ዓመት በቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለኅብረተሰቡ እያቀረቡ ነው።

በቦሌ ክፍለ ከተማ በአሥራ አንዱም ወረዳዎች የሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ስራ ማኅበራት መጪውን የ2019 አዲስ ዓመት አስመልክቶ የኅብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቅለልና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ሰፊ ዝግጅት በማድረግ መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ጀምረዋል።

ማኅበራቱ በተለይም ለአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ የምግብ እህሎችን፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ሽንኩርት፣ እንቁላል እና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶችን በአነስተኛ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች እያቀረቡ ይገኛሉ።

ማኅበራቱ ከምርት አቅራቢዎችና ከገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየኖች ጋር በቀጥታ በመስራት ያለምንም የደላሎች ጣልቃገብነት ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርሱ በማድረግ ላይ ናቸው። ይህም አሰራር በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሚፈጠር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በኅብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና እየቀነሰው ስለመሆኑም ተገልጿል።

የክፍለ ከተማው ኅብረት ስራ ማኅበራት ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፣ በሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የመሸጫ ማዕከላት በበቂ ምርት የተደራጁ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ያለ ምንም እንግልትና ሰልፍ ፍላጎቱን እንዲያሟላ የተጠናከረ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ነዋሪዎችም ማኅበራቱ እያቀረቡት ያለው ምርት የገበያ ዋጋን በማረጋጋት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቁመው፣ አቅርቦቱ ከበዓላት ባሻገር በተጠናከረ መልኩ ተገቢው ቁጥጥር እየተደረገበት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ነሐሴ 26/2018
ቦሌ ኮሙኒኬሽን

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
01/09/2026

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።  በውይይታችንም  እቅዶ...
31/08/2026

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።

በውይይታችንም እቅዶቹን ይበልጥ ተጨባጭ በማድረግ በቀጣይ አምስት ዓመታትም አልቀን በመፈፀም፣ የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት ሳንሸራርፍ ለመፈፀም፣ የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እጅግ ጠቃሚ እና ገንቢ ተግባቦት እና ዝግጁነት ፈጥረናል።

ከሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂያችን በመነሳት ህዝባችንም በድጋሚ ሲመርጠን “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር” ብለን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንደ አዲስ አበባ “አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት” ለማድረግ የጀመርነውን ጉዞ ዋና ርዕያችን አድርገናል።

ለእቅዳችን ስኬት መሰረቶች የሆኑት ባለፋት አምስት ዓመታት አቅደን አልቀን ያስመዘገብነው ውጤት፣ የህዝብና መንግሥት ከደህነት የመውጣት ፍላጎት፣ በከተማችን የተፈጠረው የስራ ትጋት፣ በታማኝነት ማገልገል፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በፍጥነትና በጥራት የመፈፀም ልምድ፣ በጀትን በመቆጠብ መጠቀም ትልቅ ስንቅ ናቸው።

በቀጣይ ትኩረታችንም ተቋማዊ ብቃትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ የዘመነ ቴክኖሎጂ በሚጠቀም የላቀ አገልግሎት መስጠት፣ የተቀናጀ ጥራት ያለው ሰፊ መሰረት ልማት በፍጥነት መገንባት፣ አዲስ መሰረተ ልማት መገንባት ብቻ ሳይሆን ነባሮቹን በሚገባ ማስተዳደር፣ የንፁህ መጠጥ ውኃና የቤት አቅርቦት ማሳደግ፣ የማህበራዊ ዘርፍ (ጤና፣ ትምህርት …) ተደራሽነትና ጥራት እንዲሁም ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ አልቀን መፈፀም፣ ዓለማቀፍ ስታንዳርድ ያሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት፣ የጤና ቱሪዝም ማዕከል መሆን፣ የከተማችንን የቱሪዝም መዳረሻ ከተማነት ማረጋገጥ፣ አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ ማድረግ፣ ለወጣቶች ተጠቃሚነት፣ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲሁም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ባህል በማድረግ ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማትን ማጠናከር፣ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ አምራችነትን ማሳደግ፣ ተረጂነትን መቀነስ፣ የስራ እድልን በሰፊው መፍጠር፣ የከተማ ግብርና፣ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን፣ ፅዳትና የቆሻሻ አወጋገድን ባህል ማድረግ … ወዘተ፤ በአጠቃላይ ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና ለሁሉም የምትመች ከተማ ማድረግ የእቅዳችን ትኩረቶች ናቸው።

የእቅዳችን ቅኝትም ስትራቴጂክ እይታ ያለው፤ ራዕያችንን ለማሳካት አቅዶ መተግበር፤ የተለጠጠ፣ አካታች፣ ፍትሃዊ እንዲሁም አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ይህ የእቅድ ውይይት አመራራችን በዋናነት እቅዱን በተሟላ ሁኔታ የተረዳ፣ ስትራቴጂክ አመራር የሚሰጥ፣ በአስተሳሰብ አንድነት የሚቆም፣ ከተለያየ የጥቅም ትስስር ነፃ የሆነ፣ የይቻላል መንፈስን የተላበሰ፣ በአፈፃፀም ተቀራራቢ የሆነ፣ ትጋት እና የአመራር ዲሲፒሊን ያለው፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት እያሰፈንን ህዝቡ የከተማችንን ራዕይና ግብ የተጋራ እንዲሆን በተለየ መንገድ የሄድንበት የውይይት መድረክ ነው።

ልማትን በመንግስት ብቻ ማሳካት እይቻልም። በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪዎች፣ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ የግሉን ዘርፍ ማበረታታት፣ በጊዜ የለንም መንፈስ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ አሳድገን በከተማችን ለማሳካት የተወጠነውን ትልቅ ራዕይ ለመፈፀም በላቀ እንተጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

31/08/2026

ቦሌ በዚህ ሳምንት።

30/08/2026

Address

Megenagna Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Communication- ቦሌ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share