Addis Ketema Woreda 8 Building Permit and Control

Addis Ketema Woreda 8 Building Permit and Control This is official page of Addis Ketema Woreda 12 Building Permit and Control Office!

17/10/2025
09/08/2025
ጽ/ቤቱ የ90 ቀናት ሥራዎችን ከወረዳ አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አደረገየአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የ90 ቀናት (ከሰኔ እስከ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም) የከተማ...
17/06/2025

ጽ/ቤቱ የ90 ቀናት ሥራዎችን ከወረዳ አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አደረገ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የ90 ቀናት (ከሰኔ እስከ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም) የከተማ ስታንዳርድ የማስጠበቅ ሥራዎችን ከወረዳ አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አደረገ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት

እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር  በዓል በሰላም፣በጤና አደረሳቹህ...
30/03/2025

እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም፣በጤና አደረሳቹህ እያልኩ በዓሉን የሀይማኖቱን ድንጋጌ መሰረት ባደረገ መልኩ በአንድነት ፣በህብረት እና የተቸገሩ ወገኖቻችንን ጋር በመሆን በጋራ በፍቅር ማሳለፍ እንደሚገባ እየገለፅኩ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ደማቅ የሰላምና የደስታ በአል እንዲሆን ከወዲሁ እመኛለሁ።
ኢንጅነር ሰአዳ ሰኢድ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት ሃላፊ

30/03/2025
የዉሸት ዜና / Fake News ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ስለማሳወቅበሕንጻ ግንባታ ወቅት የአደጋ ጊዜ መውጫ አሳንሰር እና ሌሎች የግንባታ መስፈርቶችን በማያሟሉ ገንቢዎች ላይ የሚጣል የገንዘብ ቅ...
16/03/2025

የዉሸት ዜና / Fake News ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ስለማሳወቅ

በሕንጻ ግንባታ ወቅት የአደጋ ጊዜ መውጫ አሳንሰር እና ሌሎች የግንባታ መስፈርቶችን በማያሟሉ ገንቢዎች ላይ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተላለፈው ሀሰተኛ መረጃ ፍፁም ውሸት መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ በሕንጻ ግንባታ ወቅት የአደጋ ጊዜ መውጫ አሳንሰር እና ሌሎች የግንባታ መስፈርቶችን በማያሟሉ ገንቢዎች ላይ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ተብሎ የሚዘዋወረዉ ዜና ፍፁም ዉሸትና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤቱን የማይገልፅ መሆኑን እንዲሁም ሆነ ተብሎ ህዝብን ለማደናገር የተሰራጨ ዜና መሆኑን የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን መ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት ሁንዴሳ በማህበራዊ ድረ ገጽ የገለፁ ሲሆን ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳውቀዋል።

አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡**************************መጋቢት ...
11/03/2025

አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
**************************
መጋቢት 2-2017ዓም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት "አንድ ማህደር የተቀናጀ ሲስተም" የተሰኘ አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ከዘርፉ አመራሮችና ቡድን መሪዎች ጋር የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል፡፡

አሰራሩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑን የገለፁት የክፍለ ከተማው ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሰዓዳ ሰኢድ አንድ ተገልጋይ ከፕላን ስምምነት ጀምሮ ሁሉንም አገልግሎቶች ለማግኘት አንድ ፋይል ብቻ እንዲኖረው የሚያደርግ ዘመኑን የዋጀ አሰራር በመሆኑ የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራም ትውውቅ ስነስርዓቱ የተገኙ አመራሮችና ሰራተኞች በበኩላቸው አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ከዘመኑ ጋር አብሮ መዘመን በመሆኑ ተቋሙ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መሰመሩ የሚያስደንቀው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"አንድ ማህደር የተቀናጀ ሲስተም" የተሰኘው አሰራር ወደ ተግባር ሲገባ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡
👉 ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡
👉 ግልፅና ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመዘርጋት ያስችላል፡፡
👉 የሰራተኞችንና የተገልጋዮችን ጊዜና ወጭ ይቀንሳል፡፡
👉 ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት መጠየቅ ያግዛቸዋል፡፡
👉የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ያዘምናል፡፡
👉የተገልጋዮችን እርካታ ያሳድጋል እንዲሁም
👉ፈጣን የደንበኞች ቅሬታ አፈታት ስርዓትን እውን የሚያደርግ ይሆናል የሚሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

የተሻለ ከተማ ገፅታ ለመገንባት የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ጉልህ ሚና አለዉ!ዛሬ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት በወረዳዉ የሚገኙ አክስዮኖች፣ የግል ማህበራትና ...
07/03/2025

የተሻለ ከተማ ገፅታ ለመገንባት የስታንዳርዳይዜሽን ስራ ጉልህ ሚና አለዉ!

ዛሬ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት በወረዳዉ የሚገኙ አክስዮኖች፣ የግል ማህበራትና የህንፃ ባለቤቶች ጋር በስታንዳርዳይዜሽን ስራ ዙሪያ ውይይት አድርጓል ። የተሻላች ዉበቷ የተጠበቀ ከተማና ጥሩ ገፅታ የተላበሰች ከተማ ለመገንባት በወጣው 01/2015 መመሪያ መሰረት Smart አዲስ አበባን ለመገንባት በግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስተባባሪነት እየተሰራ ይገኛል ። በዚህ መሰረታ በአዲስ አበባ ባሉ ክ/ከተማና ወረዳ ፅ/ቤቶች የስታንዳርዳይዜሽን ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ።

ይሄን መነሻ በማድረግ በወረዳችን ስኬታማ ስራ ለመስራት ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አድርጓል ። በውይይቱም
👉በህንፃ ቀለም መቀባት
👉ህገወጥ ማስታወቂያ ማንሳት
👉የህንፃ ላይ ማብራት መስቀልን በተመለከተ ከመመሪያ፣ ከSize(ቁመት) እና ከስታንዳርድ ጋር በተያየዘ ያሉ ነገሮችን በሰፊዉ በመነጋገር ተወያይተው ስራዉም በዉጤት እንድጠናቀቅ በጋራ በመስራት ላይ ተግባብተው ዉይይቱን አጠናቋል ።

በጎ ፍቃድ ስራ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ አብሮነትን ያጠናክራል !በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት  ለአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ ስራ ጀመረ። ...
24/02/2025

በጎ ፍቃድ ስራ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ አብሮነትን ያጠናክራል !

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት ለአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ ስራ ጀመረ። ፅ/ቤቱ ከመደበኛ ስራዎቹ ጎን ለጎን በሰዉ ተኮር ተግባር በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችና ግለሰቦችን በማስተባበር ቤታቸዉ የወደቀባቸዉ ቤተሰቦችን በመለየት በነባር ቀበሌ 09 ቀጠና 06 የማደስ ስራ አስጀምሮዋል።

ዕድሳቱን ያስጀመሩት የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ለሊሳ ዴሬሣ እንደተናገሩት በጎ ፍቃድ ስራ የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ አብሮነትን ያጠናክራል፤ እኛም ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት ያስችለናል ብሏል። ኃላፊ አክለዉ ይሄ ተግባር በየጊዜ የሚደረግና የዜጎችን ችግር የሚፈታ ስለሆነ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ቤቶችን በተሻለ ጥራት ሰርተን እናስረክበዋለን ስሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፏል ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄድ *   *   *   *   *   *   *   *   *   *   *...
28/01/2025

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄድ

* * * * * * * * * * *

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሰዓዳ ሰዒድ እንደተናገሩት የመጀመርያ በጀት አመቱ የተሻለ ስራ መስራቱን ገልፅው ለቀጣይ በጀት አመቱ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

Baga Ayyaana Qillee Geessan!Hojjettoota Waajira keenyaa, Hojjettoota mootummaafi Hooggantoota 0akkasumas jiraattootni   ...
06/01/2025

Baga Ayyaana Qillee Geessan!

Hojjettoota Waajira keenyaa, Hojjettoota mootummaafi Hooggantoota 0akkasumas jiraattootni keenyaa hundi keessan baga ayyaana kan bara 2017 ALH nagaan keessan. Ayyaanni kan nagaa, jaalalaafi gammachuu hunda keenyaaf haa tahu !

መላ የፅ/ቤታችን ሠራተኞች፣ የወረዳችን የመንግስት ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም የወረዳችን ነዋሪዎች እንኳን ለ2017ዓ.ም የገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ ። በዓሉ የሠላም፣ ነፍቅርና የደስታ በዓል ይሁንልን !

Ayyaana Gaarii🙏

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda 8 Building Permit and Control posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share