House of Federation of Ethiopia

House of Federation of Ethiopia unity in diversity for development

05/09/2026

ጳጉሜ 1፡ ‹‹የእመርታ ቀን››

ያለፈውን በመመዘን፣ ዛሬን በማሻሻል፣ ነገን በመገንባት—ጳጉሜ ልዩ ጊዜ ናት።
የዓመቱ መጨረሻ ብቻ ሳትሆን፣ ያለፈውን ዓመት የምንመለከትበት፣ የተጓዝነውን መንገድ የምንገመግምበትና ለሚመጣው ዓመት አዲስ አቅጣጫ የምንወስንበት የሽግግር ጊዜ ናት።

በዚህ ልዩ ጊዜ የመጀመሪያዋ ቀን “የእመርታ ቀን” ተብላ መሰየሟም ጥልቅ መልእክት ይዟል። እመርታ ማለት ከትናንት ወደ ዛሬ፣ ከዛሬ ወደ ነገ የሚደረግ ቀጣይ ጉዞ ነው። ሁልጊዜ በአንድ ትልቅ ውጤት ወይም በአንድ ታላቅ ስኬት ብቻ አይለካም። አንድ ትንሽ መሻሻል፣ አንድ የተሻለ ውሳኔ፣ አንድ የተሻሻለ አሠራር ወይም አንድ የተጠናከረ ግንኙነት እንኳን የእመርታ ምልክት ነው። ዋናው ነገር፣ ዛሬ ከትናንት በተሻለ ደረጃ መቆማችን ነው።
እመርታ የሚጀምረው ከራሳችን ነው
የግለሰብ እመርታ የሚጀምረው ራስን ከመገምገም ነው። ባለፈው ዓመት ምን አሳካሁ? የት ተሻሻልኩ? የት ደከምኩ? ምን መማር እንዳለብኝ ተገነዘብኩ? የሚሉ ጥያቄዎችን በቅንነት መጠየቅ ለእመርታ መነሻ ነው።
እመርታ ራስን ከሌሎች ጋር በማወዳደር ማሸነፍ ሳይሆን፣ ከትናንት ራሳችን የተሻለ ለመሆን መጣር ነው። የግል እመርታ ግን በግለሰብ ደረጃ ብቻ አይቆምም፤ በቤተሰብ፣ በሥራ ቦታ፣ በማኅበረሰብና በሀገር ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል።
እመርታ በቤተሰብ ውስጥ
ጠንካራ ቤተሰብ የጠንካራ ማኅበረሰብ መሠረት ነው። በቤተሰብ ውስጥ መከባበር፣ መተማመን፣ ኃላፊነትን መጋራትና ችግሮችን በውይይት መፍታት ሲጠናከር የቤተሰብ እመርታ ይገለጣል። ስለዚህ ጳጉሜ 1ን የእመርታ ቀን ስናስብ፣ “ቤተሰቤ ከባለፈው ዓመት የተሻለ የሆነው በምን መስክ ነው?” የሚለውን ጥያቄ ለራሳችን ማቅረብ ይገባል።
እመርታ በተቋም ውስጥ
የአንድ ተቋም እመርታ በተገኘው ውጤት ብቻ አይለካም። ተቋሙ ለሕዝብ የሚሰጠው አገልግሎት፣ የሥራ ባህሉ፣ ተጠያቂነቱ፣ ግልጽነቱ፣ የሰው ኃይሉ ብቃትና ለለውጥ ያለው ዝግጁነት የእመርታው ዋና መለኪያዎች ናቸው።

ተቋም የሚያድገው በሕንፃና በመሣሪያ ብቻ አይደለም፤ በሥነምግባር፣ በተጠያቂነት፣ በትብብርና በሕዝብ አገልግሎት ጥራት ጭምር ነው። ስለዚህ የእመርታ ቀን ተቋማት ያላቸውን አሠራር በጥልቀት እንዲገመግሙና የቀጣዩን የሥራ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ የሚጋብዝ ቀን ነው።
እመርታ እንደ ሀገር
የሀገር እመርታ በአንድ መስክ በተገኘ ውጤት ብቻ አይለካም። ሰላምና መረጋጋት፣ የዜጎች ተሳትፎ፣ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ የማኅበራዊ ትስስር ጥንካሬ፣ የተቋማት አቅምና የዜጎች የነገ ተስፋ በጋራ የሚያመለክቱት የሀገር እመርታን ነው።
በ2018 ዓ.ም. በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች የሀገር እመርታን ለመመልከት ከሚያስችሉ አመላካቾች መካከል ናቸው። እነዚህ ውጤቶች ግን የጉዞው መጨረሻ ሳይሆኑ፣ ለቀጣዩ የልማት ጉዞ መነሻ መሆን ይገባቸዋል።
እመርታን ወደ ዘላቂ ስኬት

እመርታ አንድ ጊዜ ተመዝግቦ የሚቆም ነገር አይደለም። ዛሬ የተገኘው ውጤት ነገ ካልተጠበቀ፣ ካልተሻሻለና ካልተጠናከረ ወደኋላ ሊመለስ ይችላል። ስለዚህ እመርታ ከጽናት፣ ከተጠያቂነት፣ ከሥነምግባርና ከቀጣይ መሻሻል ጋር መቆራኘት አለበት።
ጳጉሜ 1ን “የእመርታ ቀን” ብለን ስናከብር፣ ያለፈውን ስኬት ለማድነቅ ብቻ ሳይሆን፣ የተሻለ ዛሬን ለመፍጠርና የተሻለ ነገን ለመገንባት ቃል የምንገባበት ቀን ሊሆን ይገባል።
እመርታ የሚጀምረው በትልቅ እርምጃ ሳይሆን፣ በተሻለ አስተሳሰብ፣ በትክክለኛ ውሳኔና በተግባር ነው።

ስለዚህ በዚህ የእመርታ ቀን ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለተቋማችንና ለሀገራችን አንድ ጥያቄ እናቅርብ፦ “ከትናንት የተሻለ ዛሬን ለመፍጠር የእኔ ድርሻ ምንድን ነው?” የዚህ ጥያቄ መልስ በቃላት ብቻ ሳይሆን፣ በየዕለቱ በምናደርገው ተግባር ይገለጥ።
የእመርታ ቀን የተገኘውን ለማክበር ብቻ ሳይሆን፣ የተሻለውን ለመፍጠር የምንነሳበት ቀን ይሁን!
እንኳን ለ2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ አደረሳችሁ!
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የስኬትና የብልጽግና ዓመት ይሁንላችሁ!

“የሥራ ባለቤትነት የውጤት ባለቤትነትን ያመጣል” ክቡር አቶ ትግሉ መለሰ ******************************(ዜና ፌዴሬሽን)፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም.፣አዲስ አበባ፣ የሠራ...
04/09/2026

“የሥራ ባለቤትነት የውጤት ባለቤትነትን ያመጣል” ክቡር አቶ ትግሉ መለሰ
******************************
(ዜና ፌዴሬሽን)፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም.፣አዲስ አበባ፣

የሠራተኛው የሥራ ባለቤትነት ሲረጋገጥ ውጤታማ የተቋም አፈጻጸም እንደሚመዘገብ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ትግሉ መለሰ ገለጹ።

ኃላፊው ይህን ያሉት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

የጽሕፈት ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከየሥራ ክፍሎቹ መንጭቶ በየደረጃው የጋራ ውይይት ሲደረግበት መቆየቱን ጠቁመው፣ በመጨረሻም በአስተባባሪ ኮሚቴው ጸድቆ ለተግባራዊነቱ ወደ ሠራተኛው መውረዱን አስረድተዋል።

አንድ ተቋም የሚጠነክረው ዕቅድን በጋራ በማቀድ፣ በጋራ በመፈጸምና በጋራ በመገምገም እንደሆነ የጠቀሱት ኃላፊው፤ ከምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት መልካም ተሞክሮዎች አንዱ እቅድ በአመራሩ ብቻ ታቅዶ ሠራተኛው እንዲፈጽመው የሚደረግ ሳይሆን፣ ሠራተኛው ራሱ የዕቅዱ ባለቤት ሆኖ የሚያከናውነው መሆኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም ዕቅዱ የተቋሙን ፍላጎትና የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው እንደሚከለስ የጠቆሙት አቶ ትግሉ፤ ሁሉም ሠራተኛ ለዕቅዱ ስኬታማነት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ዕቅድና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑር አብዲ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia

የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለስትራቴጂክ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።*************************************************(ዜና ፌዴሬሽን) – ነ...
02/09/2026

የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለስትራቴጂክ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።
*************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) – ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ለስትራቴጂክ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት የተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

የምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የታቀዱ ዋና ዋና ሥራዎች በፌዴሬሽኑ አስተባባሪ ኮሚቴና በምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ተወያይተውባቸዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ በ2019 በጀት ዓመት ለህዝቦች አንድነትና ትስስር ጠንካራ መሠረት የሚጥሉ ተግባራት በልዩ ትኩረት እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።

አፈ-ጉባኤው አክለውም፣ የህዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ አንድነትንና ትስስርን የሚያጠናክሩ ተግባራት በዕቅዱ ውስጥ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው መካተታቸውን ገልጸዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ዕቅድና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑር አብዲ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አቅርበዋል።

በዕቅዱ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና ግብዓቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብዓቶችን በማካተት ዕቅዱ ጸርቋዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ድረ-ገጽ፦ www.hofethiopia.gov.et
ፌስቡክ፦ House of Federation of Ethiopia
ዩትዩብ፦ House of Federation of Ethiopia
ትዊተር/X፦
ፍሊከር፦ House of the Federation of Ethiopia

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዝኀነት የደመቀች በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ    ****(ዜና ፌዴሬሽን) ነሐሴ 26 ቀን...
01/09/2026

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዝኀነት የደመቀች በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ
****
(ዜና ፌዴሬሽን) ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በዛሬው እለት ባካሄደው ውይይት 21ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዝኅነት የደመቀች በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መሪ ዕቅድ መቅረቡን ተከትሎ ከተሳታፊዎች በተሰጡ አስተያየቶች ባለፉት 5 ዓመታት የተከበሩ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የአስተናጋጅ ክልሎችን እምቅ አቅም በሰፋት የተዋወቀበት፣ በዓሉ በይዘት፣ በቅርጽና በሚካሄዱ የሁነት አይነቶች እያደገ የመጣበት፣ ሕዝቡ በጉጉት የሚጠብቀው ተናፋቂ በዓል እየሆነ የመጣበት፣ በማህበራዊ ትስስርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች መሠረት የተጣለበት፣ ከአስተናጋጅ ክልሉ ባሻገር በሌሎችም ክልሎች የሚካሄዱ የማጠቃለያ ምዕራፎች ሕብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር አገራዊ በዓሉን በሚመጥን ውጤታማ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በዚህም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በዛሬው እለት ያካሄደውን ውይይት የመሩት የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በሰጡት ማጠቃለያ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች ለማስከበር፣ ብዝሃነት እንዲጠናከር፣ አብሮነትና ወንድማማችነት ሥር እንዲሰድና በአጠቃላይ ጤናማ የፌዴራል ሥርዓት እንዲጎለብት የሚያግዙ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል ያሉ ሲሆን 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዝኅነት የደመቀች በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ሲከበርም ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በቅርቡ በተደረገው ሀገራዊ ምክክር የተገኙ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የዜጎችን ሕብረብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መንገድ መሠራት አለበት ብለዋል፡፡

ያለፉት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ዜጎች ባህላቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል የፈጠረላቸው ከመሆኑ ባላፈ ህብረብሔራዊነት በተጨባጭ የተረጋገጠበት መድረክ ስለሆነ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ለሰለም፣ ለፍትህ፣ ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መከበር በጋራ እንዲቆሙ በሚያስችል መልኩ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ አፈ ጉባኤው አሳስበዋል::

አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴውም የቀረቡለትን እቅዶች ከመረመረና ከተሳታፊዎች የተሰጡ ሀሳብ፣ አስተያየቶች በግብዓትነት ከአካተተባቸው በኋላ እቅዶችን በማጽደቅ 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “በብዛኀነት የደመቀች በምክክር የፀናች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከሕዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር እና የማጠቃለያ በዓሉም በኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማ ከሕዳር 25 እስከ 29 ቀን 2019 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚደረጉ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበር በማመላክት ውይይቱን አጠናቋል::

ለተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia
See less
See translation

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ዝግጅት በኦሮሚያ ክልል መጀመሩ ተገለጸ*************************************************(ዜና ፌዴሬሽ...
01/09/2026

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ዝግጅት በኦሮሚያ ክልል መጀመሩ ተገለጸ
*************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) – ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የተሳካ እንዲሆን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመሩን የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማን ገለጹ።

የተከበሩ አፈጉባኤዋ ይህንን ያሳወቁት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የ21ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አዘጋጅ አቢይ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው።

ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማን ባደረጉት ንግግር፣ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በዝግጅት ምዕራፉ በርካታ አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው በቀሪው ጊዜ የሚከናወኑ ቀሪ ሥራዎችን በትኩረት በመሥራት በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ክልሉ በሙሉ ቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዓሉ የሕዝቦችን የርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክር፣ ወንድማማችነትንና አንድነትን የሚያጎለብት እንዲሆን የተቀናጀ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ አብራርተዋል።

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ከተማ እንደሚከበር ይታወቃል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ድረ-ገጽ፦ www.hofethiopia.gov.et
ፌስቡክ፦ House of Federation of Ethiopia
ዩትዩብ፦ House of Federation of Ethiopia
ትዊተር/X፦
ፍሊከር፦ House of the Federation of Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር የሚያገለግል ብሔራዊ መድረክ ሆኖ እ...
01/09/2026

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር የሚያገለግል ብሔራዊ መድረክ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ ገለጹ ።

***************************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) ነሐሴ 26 ቀን 2018፣ አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር የሚያገለግል ብሔራዊ መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲዊ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ ገልጸዋል ።
የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ ሀገር አቀፍ የበዓሉን መነሻ እቅድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት በዓላት የተካሄዱ የአስተምህሮ መድረኮች፣ ሥልጠናዎች፣ የሕዝብ ውይይቶች እና የሚዲያ ስርጭቶች የሕገ መንግሥቱን ዓላማና የፌዴራል ሥርዓቱን መሠረታዊ እሴቶች ወደ ሕዝቡ በሰፊው እንዲደርሱ ከማስቻላቸው በተጨማሪ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ ሲቪል ሰርቫንቶችን፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰቦችን እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ያማከለ የአስተምህሮ ሥራ በመካሄዱ ከ29 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተደራሽ መሆናቸው በሕገ መንግሥት እውቀት ማስፋፋት ዘርፍ የተመዘገበ ታላቅ ስኬት እንደነበረ አመላክተዋል።
21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልም በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ሲከበር የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች፣ ትስስርና አንድነት የሚያጠናክሩ እንዲሁም የብሄሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህሎቻቸው፣ እሴቶቻቸው የሚያቀርቡበት አንዱ ከሌላው የሚማማሩበት መድረክ እንዲፈጠር በማድረግና ዉጤታማ የሕዝብ ግንኑነት ሥራዎችን በመሥራት የሀገር ገጽታን መገንባት ላይ በትኩረት እንደሚሰራና በድምቀት እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ታረቀኝ አድማሱ በበኩላቸው አስተናጋጁ ክልል በዓሉን አስመልክቶ እየሰራቸው ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችና የቀጣይ ዕቅዶቻቸውን በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ከተማ በድምቀት መከበሩ ይታወሳል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia
See less
See translation

በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ጉልህ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸው ውጤቶች እንዲመዘገቡ ከወዲሁ በትኩረት ይሠራል- የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክ...
01/09/2026

በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ጉልህ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸው ውጤቶች እንዲመዘገቡ ከወዲሁ በትኩረት ይሠራል- የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር

***************************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) ነሐሴ 26 ቀን 2018፣ አዲስ አበባ፣
በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸው ውጤቶች እንዲመዘገቡ ከወዲሁ በትኩረት እንደሚሠራ የበአሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

የተከበሩ አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ በአሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን፣ ባህላቸውን እንዲለዋወጡ፣ ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ኢኮኖሚ እድገት እንዲሠሩ እና በሕዝቦች መሀከል አንድነትና ትስስር እንዲኖር በማድረግ በኩል የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡
ቀጣዩ በዓል በኦሮሚያ ክልል በምትገኘውና የገዳ ስርዓትን ጨምሮ የበርካታ ታሪካዊና ባህላዊ መስህቦች ባለቤት እንዲሁም ሕዝቦች ተከባብረው እና ተቻችለው በሚኖሩባት የብዝሃነት ማሳያ በሆነችው ጅማ ከተማ የሚከበር ሲሆን የአገራችን ቀጣይ መንገድ የጠረጉና ወደአዲስ ተስፋና ምዕራፍ ያሸጋገሩ አገራዊ ሁነቶች የተከናወኑበት በተለይም 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተጠናቆ አዲስ መንግሥት በተመሰረተበት፣ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት መሰረት በተጣለበት እና ዘርፈ ብዙ ተግባራት በተከናወኑበት ማግስት የሚከበር በዓል እንደመሆኑ የተለየ ትርጉም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ቀጣዩ የኢትዮጵያ ዕጣፈንታ ተስፋ የሚጣልበት ነው ያሉት የተከበሩ አፈጉባኤው የኢትዮጵያ ህዝቦች ኅብረ-ብሄራዊ አንድነታቸዉን ዲሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ይበልጥ የሚያዳብሩበት እና መብቶቻቸዉን በአግባቡ በመጠቀም ለቀጣይ የዲሞክራሲ ባህል መዳበርና ለህብረብሔራዊ አንድነት መጎልበት ጽኑ መሰረት በተጣለበት ወቅት የሚከበር መሆኑ የቀጣይ በዓል ድምቀት ሌላው ገጽታ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ከልማት፣ ከዲሞክራሲ ግንባታ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ባላቸው ታላላቅ አገራዊ ሁነቶች ታጅቦ እንደሚከበር ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲዊ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ የበዓሉን ረቂቅ መሪ እቅድ አቅርበዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia
See less
See translation

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ  ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ***************************************************...
01/09/2026

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ
***************************************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) ነሐሴ 26 ቀን 2018፣ አዲስ አበባ፣

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የሁሉም ክልል አፈጉባኤዎች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በበዓሉ መሪ እቅድ ላይ ውይይት ማካሄዱን ጀምሯል፡፡

በውይይት መድረኩ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲዊ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ የበዓሉን ረቂቅ መሪ እቅድ፣ በተጨማሪም የበዓሉ አስተናጋጅ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አቶ ታረቀኝ አድማሱ የክልሉን የበዐል ረቂቅ እቅድ አቅርበው ውይይት በማድረግ የበዐሉን መሪ ቃል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ በ3ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛው ዓመት የሥራ ጊዜ፣ ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሔደው 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ሕዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሆኖ እንዲከበር መወሰኑ ይታወቃል፡፡


ለተጨማሪ መረጃ
ድረገጽ፦http://www.hofethiopia.gov.et/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
ትዊተር፦ https://twitter.com/hofethiopia
ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/house of the Federation of Ethiopia
See less

የኢፌዲሪ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናወነ****************                                ...
27/08/2026

የኢፌዲሪ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናወነ
****************
ሶያማ፣ ነሀሴ 20/2018 ዓ.ም

የኢፌዲሪ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በሶያማ ከተማ የችግኝ ተከላ፣ የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናወኑ።
የኢፌዲሪ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱ ታዬ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ማዕከሉ ህገ መንግስታዊነትና ፌደራላዊ አስተሳሰብ እንዲዳብር በርካታ የአስተምህሮ፤ስልጠና እና ምርምር ስራዎችን በመስራት የዜጎችን ንቃተ ህገ መንግስት እያሳደገ ነው።
ማዕከሉ በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ስራዎች ባሻገር በክረምት በጎ ፈቃድ የማህበራዊ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጀራ ከተማ እና ደብብ ምህራብ ክልል ሺሽንዳ ከተማ ላይ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ማከናወኑ አንስተዋል።
ነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር ማዕከሉ በሶያማ ከተማ ላይ የሚገነባቸው የአጸደ ህጻናት ትምህርት ቤቶች ትልቅ አበርክቶ ያላቸው መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።
አክለውም ማዕከሉ በከተማው አቅራቢያ የችግኝ ተከላ ማካሄዱን፣ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሩን፤ ለወጣቶች ማነቃቂያ ስልጠና መስጠቱ ና ለ300 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማደረጉን ገልጸው፣ በቀጣይም በአካባቢው መሰል ድጋፎች ማደረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የቡርጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ትንሳኤ ዩሐንስ በመልዕክታቸው የበጎ ፈቃድ ተግባር ለአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመጥቀስ፣ የማዕከሉ አመራሮችና ሰራተኞች ለዞኑ ልማት የሚያደርጉት አስተዋፅኦ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ በዞኑ የክረምት በጎ ፍቃድ ተግባራትን ለማከናወን ቡርጂ ድረስ መምጣቱ አድንቀዋል:፡፡ ይህም ማዕከሉ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በቀላሉ እንዲታወስ እና ተቀባይነት እንዲኖር ያደረጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የሶያማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር አድማሱ ሂርቦ በበኩላቸው፤ የማዕከሉን አመራሮችና ሰራተኞች በከተማዋ የበጎ ፍቃድ ለማከናወን ከተማውን መምረጣቸው በማድነቅ ፤ማዕከሉ ለማህበረሰቡ እያደረጋቸው ላላው አስተዋፅኦም ከልብ እናመሰግናለን ሲሉ ተናግረዋል።
የማዕከሉ የአስተምህሮ እና ስልጠና ዳይክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት አለሚቱ በየነ እና የስልጠና ማስተባባሪያ ዴስክ ሀላፊ አቶ ዘውዴ ደምሴ በፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ እና ፌደራሊዝም ለውጣቶች የሚሰጠው ጠቀሜታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለከተማዋ ወጣቶች የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጥቷል።ስልጠናው ወጣቶች በፌደራሊዝም ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ ወጣቶች በአካባቢያቸው የሚከናወኑ የልማትና የማህበራዊ ተግባራት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያበረታታ መሆኑ ተጠቁሟል።

እስካሁን የተገኙ ድሎች በበዓሉ አማካኝነት ጠንካራ የህዝብ መሠረት እንዲኖራቸው ይሠራል፦ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ****************...
27/08/2026

እስካሁን የተገኙ ድሎች በበዓሉ አማካኝነት ጠንካራ የህዝብ መሠረት እንዲኖራቸው ይሠራል፦ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ
*******************************************
(ዜና ፌዴሬሽን) – ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ ጅማ

በሀገራዊ ምርጫ፣ በሀገራዊ ምክክር፣ በልማት ሥራዎችና በዲፕሎማሲ የተገኙ ውጤቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ጠንካራ የህዝብ መሠረት እንዲኖራቸው በበዓሉ አማካኝነት በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ ገለጹ።

ምክትል አፈ-ጉባኤዋ ይህን የገለጹት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመመልከትና ለመገምገም በጅማ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።

ወ/ሮ ዛህራ እንደገለጹት፣ በሀገሪቱ በምርጫ፣ በሀገራዊ ምክክር፣ በልማት ሥራዎችና በዲፕሎማሲ የተገኙ ውጤቶች ዘላቂ ትርጉም እንዲኖራቸውና ህዝቡ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን በዓሉን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የህዝብ ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል ።

በተለይም በበዓሉ አማካኝነት የህዝቦችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የገበያ ትስስር መፍጠርና የህዝቦችን የኢኮኖሚ እድሎች ማስፋት የበዓሉ አካል ተደርጎ መሠራት እንዳለበት አፈ-ጉባኤዋ አስገንዝበዋል።

በዓሉ የባህልና የእሴት ልውውጥ መድረክ ከመሆን ባሻገር፣ የህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ ትስስርና ተጠቃሚነት በማጠናከር ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን በትኩረት መሠራት እንደሚገባም ወ/ሮ ዛህራ ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ድረ-ገጽ፦ www.hofethiopia.gov.et
ፌስቡክ፦ House of Federation of Ethiopia
ዩትዩብ፦ House of Federation of Ethiopia
ትዊተር/X፦
ፍሊከር፦ House of the Federation of Ethiopia

Address

Addis Ababa
20212/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when House of Federation of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to House of Federation of Ethiopia:

Shortcuts

Share