Bole Subcity Information Technology Team

Bole Subcity Information Technology Team Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bole Subcity Information Technology Team, Public & Government Service, Addis Ababa.

01/09/2023
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቡድኖችና ወረዳዎች ዕውቅና ሰጠ።በዕውቅና ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጽ/ቤት ኃላፊ...
01/09/2023

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቡድኖችና ወረዳዎች ዕውቅና ሰጠ።

በዕውቅና ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሸምሲያ ነጋሽ እንደገለጹት በክፍለ ከተማው ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሰፊ ሥራዎች የተከናወነ ሲሆን፣ በተከናወነው ሥራም አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን፣ የካይዘን ሥርዓትን ተግባራዊ የድርጊት አንዲሁም ሌሎች መስኮች አበረታች ውጤቶች እንደተገኙባቸው ተናግረዋል። በ2016 በጀት ዓመት በተቋሙ የሚከናወኑ ሥራዎች በተሻለ አካሄድ እንዲመሩ ዘርፉ "የቴክኒክ ሙያና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት" እንዲሁም "የኢኖቬሽን ልማት ጽ/ቤት" በሚል በሁለት ጽ/ቤቶች መዋቀሩን ያስታወቁት ኃላፊዋ፣ በ2015 ከዚህ ቀደም ወረዳዎችና ተቋማትን በእኩል ለማዘመን የተደረገውን ጥረትና የተገኘውን ውጤት በቀጣዩም በጀት ዓመት የበለጠ ለማሳደግ በከፍተኛ መነሳሳት መሥራት እንደሚያስፈልግ አክለው አስገንዝበዋል።

ነሐሴ 25/2015

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት  በአሥራ አንዱም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ባለደርሻ አካላት የ 12015  በጀት ...
27/07/2023

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በአሥራ አንዱም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ባለደርሻ አካላት የ 12015 በጀት አመት የ አስራ ሁለት ወር ስራ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡
30/05/2015

ዒድ ሙባረክ !ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ  በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም፣የመተሳሰብ እና የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።መልካም በዓል !
21/04/2023

ዒድ ሙባረክ !
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም፣የመተሳሰብ እና የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?✴️በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።✴️ይሁን እንጂ የሰዎ...
21/04/2023

ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

✴️በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

✴️ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

✴️ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

✴️እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

🔰ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

✴️የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል
ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
♻️ለምሳሌ፦♻️
✴️1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

✴️2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን
ከኢንተርኔት
የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

✴️ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

✴️ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

✴️በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

✴️የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

✴️የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

“በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር፣ ለውጤታማ የሥራ አፈጻጸምና ለመልካም አስተዳደር መስፈን!”በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን ለማስፋፋትና የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ተግባራትን በማከና...
21/04/2023

“በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር፣
ለውጤታማ የሥራ አፈጻጸምና ለመልካም አስተዳደር መስፈን!”
በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን ለማስፋፋትና የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ እንደተገለጸው የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች በአንድ ጽ/ቤት ሥር እንዲዋቀሩ ከተደረገ ወዲህ የአሠራር ሥርዓትን በማዘመንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ እንዲሁም የካይዘን ፍልስፍናን ለክፍለ ከተማና ለወረዳ ፈጻሚና አመራሮች በማስተዋወቅ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፣ የመንግሥትን ንብረት ከብክነት ለማዳን የጥገናና የካይዘን ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ በበጀት ዓመቱ 905,800 ዋጋ ያለውን የመንግሥት ንብረት ለማዳን መቻሉ ተመልክቷል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ በውይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት ተቋሙ የቴክኖሎጂ ተቋም እንደመሆኑ ከሁሉም ሴክተሮች ጋር ተቀናጅቶ የሚሠራ ሲሆን፣ ከተቋቋመበት ዓላማና ከሥራው ስፋት አንፃር ባለሙያዎች በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበትና የሰው ኃይል እጥረት በሚታይበት ሁኔታ ውስጥ ውጤታማ ሥራ በማከናወናቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ በቀጣይም በሁሉም ሴክተር ጽ/ቤቶችና በወረዳዎች የካይዘን ፍልስፍናን የማስረጽ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት ኃላፊው፣ “በቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን በካይዘንም መበልጸግ አለብን” በሚል እሳቤ ውጤታማና ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓትን ለማስፈን ጽ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መጋቢት 27/2015

✝️ "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።"   ዮሐንስ 15፥13 እንኳን ለጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክትስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ...
16/04/2023

✝️ "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።"
ዮሐንስ 15፥13
እንኳን ለጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክትስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!🌿

ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች✅ መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።✅ የሳይበር ጥ...
14/04/2023

ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

✅ መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።

✅ የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።

✅ የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡

✅ የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡

✅ የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።

✅ የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡

✅ የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው::

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ሥልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሶፍትዌር ማኔጅመንት ቡድን  በክፍለ ከተማ ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና  ለባለ ድርሻ አካላ...
14/04/2023

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ሥልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሶፍትዌር ማኔጅመንት ቡድን በክፍለ ከተማ ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ለባለ ድርሻ አካላቶች ለሚገኙ ባለሙያዎች የፋይል ማኔጅመንት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ፡፡
የካቲት 8 /2015 ዓ.ም
*****************************************************
የሥልጠናው ዓላማ በክፍለ ከተማው እና በወረዳዎች የሚገኙ በወረቀት የነበረውን ፋይል አያያዝ እንዲሁም የሪፓርት አላላክ ስርአትን በዘመናዊ መንገድ የታገዘ እንዲሆን ላማድረግ ነው፡፡

ኮምፒውተራችሁ እየተንቀራፈፈ ተቸግራችኋል?እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን ልይገራችሁ።📌1. Power option- Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣ...
18/02/2023

ኮምፒውተራችሁ እየተንቀራፈፈ ተቸግራችኋል?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን ልይገራችሁ።

📌1. Power option
- Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

📌2.Disable unwanted start up programs
- ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

- Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

- እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

📌3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
- Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

📌4.Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

- እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

📌5. Clean up Memory
- This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

📌6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

📌7. Registry tweaks
- Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

📌8. visual effects
- Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት  በአሥራ አንዱም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ባለደርሻ አካላት የ ስድስት ወር ስራ ...
07/02/2023

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በአሥራ አንዱም ወረዳዎች ለሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና ባለደርሻ አካላት የ ስድስት ወር ስራ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡
30/05/2015

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Subcity Information Technology Team posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share