Akaki Kality Woreda 8 Communicatio-አቃቂ ቃሊቲ

Akaki Kality Woreda 8 Communicatio-አቃቂ ቃሊቲ ዓላማችን የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋት የማህበረሰቡን የማወቅ መብት ማሟላት ነው!!

  ምክንያት በማድረግ የብሎክን የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።=========================ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ወረዳ 8 ኮሙኒኬሽን)በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር መኖርያ...
06/09/2026


ምክንያት በማድረግ የብሎክን የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።
=========================
ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ወረዳ 8 ኮሙኒኬሽን)

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር መኖርያ አካባቢን ንጹህና ጤናማ ለማድረግ አላማ ያደረገ የብሎክ የጽዳት ዘመቻ ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ አደጋ ስጋት ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪ ቃል የፅዳት መርሀ ግብር ተካሄደ።

በዚህ የንቅናቄ ላይ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚአቶ ሀዋዝ አስፋው፣የወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዳዊት፣ የብሎክ ነዋሪዎች፣የጽዳትና አስተዳደር ባለሙያዎች የጸጥታ አካላትና የጽዳት አምባሳደሮችበ እና ርካታ የወረዳው ነዋሪዎች በንቃት ተሳትፈዋል።

05/09/2026
የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።==========================ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም(ወረዳ 8 ኮሙኒኬሽን)በአቃቂ ቃ...
05/09/2026

የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
==========================
ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም(ወረዳ 8 ኮሙኒኬሽን)

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈተው የበዓል ባዛር እና በዛሬው ዕለትም ህብረተሰቡ የግብይት ሂደቱን በደመቀ ሁኔታ እያከናወነ ይገኛል።

በዚህ ባዛር ላይ አምራቾች የህብረት ስራ ማህበራት እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ናቸው።

የወረዳው አስተባባሪዎች ግብይቱ ምን ይመስላል ሲል ምልከታ አካሂዷል ።

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ፣በብዙ አማራጭ በባዛር ይሸምቱ!የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲበአቃቂ ...
04/09/2026

ይምጡ በተመጣጣኝ ዋጋ፣በብዙ አማራጭ በባዛር ይሸምቱ!

የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የተከፈተው የበዓል ባዛር በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈተው የበዓል ባዛር እና በዛሬው ዕለትም ህብረተሰቡ የግብይት ሂደቱን በደመቀ ሁኔታ እያከናወነ ይገኛል።

በዚህ ባዛር ላይ አምራቾች የህብረት ስራ ማህበራት እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ናቸው። ይህም ደንበኞች ጥራት ያላቸውን መሰረታዊ የቤት ውስጥና የበዓል ሸቀጦች በግልጽና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበዩ ዕድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም የበዓል ገበያው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና ማህበረሰቡ አዲሱን ዓመት ያለ አላስፈላጊ የኢኮኖሚ ጫና በደስታ እንዲያከብር ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።========================ነሀሴ :28/2018 ዓ.ም (ወረዳ 8 ኮሙዩኒኬሽን)የአዲስ አመት መዳረሻ ባዛ...
03/09/2026

መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።
========================
ነሀሴ :28/2018 ዓ.ም (ወረዳ 8 ኮሙዩኒኬሽን)

የአዲስ አመት መዳረሻ ባዛር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፈተ ።

በዛሩ በአል በአል የሚሸቱ ግብአቶችን በስፋትና በጥራት በማካተት በዛሬው ተከፍቷል ።

ባዛሩን በይፋ መርቀው የከፈቱት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ እና የወረዳ 8 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀዋዝ አስፋው እንዲሁም የወረዳው አስተባባሪዎች ናቸው ።

ባዛሩ ህገወጥ የንግድ አሻጥርን በማክሸፍ በአል ነክ የሆኑ ግብአቶችን እንደ ዘይት ፣ዱቄት፣ እንቁላል እና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን በሰፋት በማቅረብ ነዋሪው እንዲገበያይ ዕድል ከፍቷል ።

በዛሩ አስከ በአል መዳረሻ የሚቆይ መሆኑን አዘጋጆቹ ንግድና ህብረት ስራ ጽ/ቤቶች አስታውቀዋል ።

ይምጡ ይሸምቱ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር !!

የግብይት ቦታ ወረዳ 8 ታክሲ ተርሚናል እንዲሁም ጨፌ ኮንዶሚኒየም

03/09/2026
‎በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ምክር ቤት 2ተኛ ምርጫ ዘመን 14ተኛ አመት የስራ ዘመን  1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ ።‎=============================‎ነሀሴ ...
03/09/2026

‎በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ምክር ቤት 2ተኛ ምርጫ ዘመን 14ተኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ ።
‎=============================
‎ነሀሴ 28/2018ዓ.ም ወረዳ 8 ኮሙንኬሽን

‎በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ምክር ቤት 2ተኛ ምርጫ ዘመን 14ተኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ ።
‎በጉባኤው በአስተዳደሩ የ2018 አፈጻጸም ቀርቦ በምክር ቤት አባላቱ ውይይት ተካሂዶበት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

‎በዛሬው ምክር ቤት ውሎ በአስተዳደሩ የ2019 በጀት ድልድል በወረዳው ፋይናንስ ፅ/ቤት ሀላፊ በአቶ ሂወቴ ተስፋዬ ቀርቦ ለወረዳው አስተዳደር ለደሞዝ እና ለስራ ማስኬጃ ወጪዎች ብር 210,069,612.00 በጀት ሆኖ ፀድቋል።
‎የተለያዩ ሹመቶች ቀርበ ጸድቀዋል
‎1ኛ.አቶ ታደለ በየነ የወረዳ 8 ም/ስራ አስፈፃሚ እና የስራናክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ
‎2ኛ.አቶ ወንድም ተፈራ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት
‎3ኛ .ሰላም አዲስ የወጣቶችናስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ
‎4ኛ.ሰራዊት ቴሮሬ ፐ/ሰ/የሰ/ሃ/ል/ፅ/ቤት ሃላፊ
‎በመሆን ተሹመዋል።

‎በስተመጨረሻም ምክር ቤቱ በ2018 ዓ.ም አፈጻጸም የላቀ አፈጻጸም ለነበራቸው ተቋማት ዕውቅና መርሀ ግብር በመስጠት ጉባዔው ተጠናቋል ።

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki Kality Woreda 8 Communicatio-አቃቂ ቃሊቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share