Ethiopian Wildlife Conservation Authority

Ethiopian Wildlife Conservation Authority We are the Guardians of the Wild and Natives!
(1)

The Ethiopian Wildlife Conservation Authority is established under proclamation number 575/2008 having the responsibility to undertake appropriate conservation and development of wildlife for its sustainable use, under the mission “To develop and conserve scientifically Ethiopia’s Wildlife resources and protected areas through active participation of community and other stakeholders, to bring ecol

ogical, economic and social benefits for Ethiopians as well as the global community and pass them to the next generation as a heritage.”

14/06/2026
ብሔራዊ ፓርኮችን ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የአጋር ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ። ጎንደር፣ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢዱጥባ) – ብሔራዊ ፓርኮችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎ...
13/06/2026

ብሔራዊ ፓርኮችን ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የአጋር ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ።

ጎንደር፣ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢዱጥባ) – ብሔራዊ ፓርኮችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ምቹ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማድረግ መንግሥት እያከናወነ ካለው የመሠረተ ልማት ሥራ ጎን ለጎን ማህበረሰቡን በጥበቃ ሂደት ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የአጋር ተቋማት ድጋፍ የማይተካ ሚና እንደነበረው አቶ ስለሺ ግርማ የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ገልፀዋል።

ሚንስትር ድኤታው ይህ የተገለፁት በጀርመን ልማት ባንክ KfW የገንዘብ ምንጭነት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን (EWCA) የረጅም ዓመት አጋር በመሆን በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በርካታ የጥበቃ ሥራዎችን በአጋርነት ሲተገብር በቆየው የአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን (AWF) ፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነው።

መንግሥት የቱሪዝም ዘርፉን የኢኮኖሚ ዕድገት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም በሰፊው አንስተዋል።

እንደ አቶ ስለሺ ገለጻ፣ ብሔራዊ ፓርኮች የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ቅርሶችና የቱሪዝም ሀብቶች በመሆናቸው ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ ይሆኑ ዘንድ በርካታ የመሠረተ ልማት ሥራዎች አየተከናወኑ ይገኛሉ ። ሆኖም የጥበቃ ሥራው ዘላቂ እንዲሆን ማህበረሰቡ የጥበቃ ሂደቱ ባለቤት እና ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ በዚህ ረገድ የአጋር ድርጅቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አስረድተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በተለይም አፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የጥበቃ ሥርዓትን ለማዘመን፣ የፓርኩን የተቋም አቅም ለማጠናከር፣ በፋይናንስና በሎጂስቲክስ ድጋፍ የጥበቃ ሥራዎችን ለማሳደግ እንዲሁም ማህበረሰብ ተኮር የልማት ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት ያደረገውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል። በዚህም የፕሮጀክቱን አመራሮችና ሠራተኞች ለበርካታ ዓመታት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በበኩላቸው በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተመዘገቡ ውጤቶች የመንግሥት፣ የማህበረሰብና የአጋር ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት መሆናቸውን ገልጸዋል።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ AWF በፓርኩ ዙሪያ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በመተግበር የማህበረሰቡን የባለቤትነት ስሜት ከማጠናከሩም በላይ በፓርኩ ላይ ይደርሱ የነበሩ ሰው ሠራሽ ጫናዎችን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

ፕሮግራሙ የትምህርት ተሳትፎን ከማሳደግ ባለፈ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዙሪያ የማህበረሰቡን ግንዛቤ እንዲጠናከር አድርጓል ብለዋል።
አቶ ኩመራ በተጨማሪም በፕሮጀክቱ ቆይታ ውስጥ የተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና የማህበረሰብ ልማት ሥራዎችን በዝርዝር አንስተዋል።
ልቅ ግጦሽን መቀነስ፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን ማጠናከር፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማሻሻል፣ አማራጭ የኑሮ ዘይቤን ማበረታታት እና የፓርኩን የጥበቃ ሥርዓት ማጠናከር ተጠቃሽ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

“የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እና በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ዘላቂ የጥበቃ ሥርዓት ለማጠናከር የተከናወኑ ሥራዎች ለሌሎች አጋር ድርጅቶች አርአያ የሚሆኑ ናቸው” ሲሉም ገልጸዋል።

የKfW እና የAWF የተቀናጀ ድጋፍ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ በጥበቃ ሥራው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ሚዛናዊ ይሆን ዘንድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደነበረው በመርሃ ግብሩ ላይ ተጠቅሷል።
በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የፕሮጀክቱ አመራሮች በተገኙ ውጤቶች ላይ በመመስረት የተጀመሩ የጥበቃና የማህበረሰብ ተሳትፎን ማሳደግ ሥራዎች በተሻለ መልኩ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶችም መሠል ተሞክሮን ሊቀስሙ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ሁለተኛው አገር አቀፍ የዱር እንስሳት ጥናት ሴሚናር ማካሔድ ጀመረ።ሰኔ 5/2018 ዓ.ምአዲስ አበባየዱር እንስሳትና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃን በሳይን...
12/06/2026

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ሁለተኛው አገር አቀፍ የዱር እንስሳት ጥናት ሴሚናር ማካሔድ ጀመረ።

ሰኔ 5/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የዱር እንስሳትና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለማጠናከር ያለመው ሁለተኛው አገር አቀፍ የዱር እንስሳት ጥናት ሴሚናር በአዲስ አበባ በመካሔድ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አካል በሆነው በዚህ ሁለተኛ አገር አቀፍ የዱር እንስሳት ጥናት ሴሚናር፣ ተመራማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አጋር እና ባለድርሻ አካላት በዱር እንስሳትና በብዝሃ ሕይወት ዙሪያ የተከናወኑ ጥናቶችን ያቀርባሉ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ሴሚናር የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንደገና አበበ መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ወቅጅራ የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በዘርፉ ላይ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮችን ያከናወኑ ተመራማሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አጋር ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ ሴሚናር በዱር እንስሳትና በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ላይ ያተኮሩ የምርምር ጥናቶች ይቀርባሉ።

ከሴሚናሩ የሚገኙ ግኝቶች የዱር እንስሳትና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ፖሊሲዎችን፣ የአስተዳደር ሥርዓቶችን እና የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችን ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል።

ሴሚናሩ በዱር እንስሳትና በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ዙሪያ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ከፖሊሲ እና ከተግባራዊ ጥበቃ ሥራዎች ጋር በማስተሳሰር የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገሰኔ 04/2018 ዓ.ም ኢዱጥባየኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለመቄዶን...
11/06/2026

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
ኢዱጥባ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከተ።

የባለስልጣኑ መሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ አቶ እዳለ ጣፋ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ተወካይ አስረክበዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዱር ህይወት ጥበቃ ተልዕኮው ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለበጎ አድራጎት ተቋማት ከሚያደርጋቸውን ድጋፎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ለተቋማዊ ውጤታማነት   ሰኔ 04/2018 ዓ.ም ኢዱጥባ  በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ ከኢትዮጵ...
11/06/2026

የስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ለተቋማዊ ውጤታማነት

ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
ኢዱጥባ

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ ከኢትዮጵያ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለባለስልጣኑ አመራሮች የስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ፣ ስነ-ምግባር የሁሉም ተቋማዊ ስኬት መሠረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነትና ተልዕኮ በተገቢው መንገድ ለመፈጸም እንዲሁም በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችንና ሙስናን ለመታገል መሰል ስልጠናዎች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አወቀ አሸናፊ በ“ሙስናን መከላከልና የስነ-ምግባር ግንባታ” በሚል ርዕስ ያቀረቡት ስልጠና፣ በቱሪዝምና ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ያለውን የሙስና ተጋላጭነት፣ በዘርፉ የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራሮች የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲሁም የመከላከያ ስልቶችን በስፋት ዳስሷል።

ስልጠናው በተቋሙ ውስጥ የተጠያቂነት፣ የግልጽነት እና የመልካም አስተዳደር ባህልን ለማጠናከር እንዲሁም ከሙስና እና ከብልሹ አሰራሮች የጸዳ ተቋማዊ አሠራር ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዋና ጽሕፈት ቤትን በዘመናዊ መልክ ለማስገንባት ከCCCC ጋር ውል ተፈራረመአዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ም. (ኢዱ...
09/06/2026

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዋና ጽሕፈት ቤትን በዘመናዊ መልክ ለማስገንባት ከCCCC ጋር ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ም. (ኢዱጥባ) – የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን (EWCA) በቅርቡ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዋና ጽሕፈት ቤት በዘመናዊና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማስገንባት ከቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (China Communications Construction Company – CCCC) ጋር የግንባታ ውል ተፈራርሟል።

የውል ስምምነቱ ዛሬ በባለስልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመ ሲሆን፣ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እና በሌላ በኩል የCCCC ጀነራል ማናጀር ሚስተር ዢን ቢን በውሉ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

በውል ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን እና የአረንጓዴ ልማት አጀንዳዋን ለማጠናከር በርካታ ሥራዎችን እያከናወነች ሲሆን፣ ከቻይና መንግሥት ጋር በተለይም በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ያላት ትብብር ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ባለስልጣኑ ያለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በመጠቀም ለሰራተኞቹ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮችን በማስፋፋት ትብብሩን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ኩመራ እንደገለጹት፣ የCCCC ካምፓኒ ለባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዘመናዊ የጽሕፈት ቤት ግንባታ ያሳየው ፍላጎት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት እየጠነከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። ካምፓኒውም በገባው ውል መሠረት ግንባታውን በተያዘለት ጊዜና ጥራት አጠናቆ እንደሚያስረክብ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በበኩላቸው የCCCC ጀነራል ማናጀር ሚስተር ዢን ቢን፣ ካምፓኒያቸው በኢትዮጵያ የ“ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በርካታ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በተፈለገው ጥራት በማጠናቀቅ ጥሩ ስም ማትረፉን ገልጸዋል። በዚህ ፕሮጀክትም በገባው ውል መሠረት ከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት በማሳየት ሥራውን በወቅቱ አጠናቆ ለባለስልጣኑ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።

በብዝሃ ሕይወት ሀብቱ፣ በልዩ ሥነ-ምህዳሩ እና በዓለም አቀፍ እውቅናው የሚታወቀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚያገኘው ይህ አዲስ የጽሕፈት ቤት ግንባታ የፓርኩን የአስተዳደር አቅም ከማጠናከር ባለፈ ለቱሪዝም እና ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል።

በውሉ መሠረት የግንባታ ሥራው በአምስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለባለስልጣኑ እንደሚተላለፍ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ኢዱጥባ

09/06/2026

Address

Head Office, Mexico Square
Addis Ababa
386

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115504838

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Wildlife Conservation Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share