Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency

Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency C R R S A - Civil Registration and Residency Service Agency - የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ

የልደትና የሞት ዲጂታል ማሳወቂያ ሥርዓት ሲስተም በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን ሆስፒታሎች ላይ ምልከታ ተደረገ CRRSA፡ነሐሴ16/2018ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀን...
22/08/2026

የልደትና የሞት ዲጂታል ማሳወቂያ ሥርዓት ሲስተም በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን ሆስፒታሎች ላይ ምልከታ ተደረገ

CRRSA፡ነሐሴ16/2018ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ዓመት የተሟላ የኩነት ምዝገባ ለማድረግ በተመረጡ አራት ሆስፒታሎች ላይ ያስጀመረው የልደት እና ሞት ዲጂታል የማሳወቂያ ስርዓት ሲስተም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር፣ከእስታስቲክስ አገልግሎት፣ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ከዩኒሴፍ ፣ ከቫይታል ስትራቴጂ፣ከብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት(ፋይዳ) እንዲሁም ከኤጀንሲው የተውጣጡ እና በተመረጡ ሆስፒታሎች እየተተገበረ የሚገኘውን የልደት እና ሞት ዲጂታል የማሳወቂያ ስርዓት ሲስተም የተመለከቱት የቴክኒካዊ ቡድን አባላት ሲሆኑ አበረታች ውጤት መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ቴክኒካዊ ቡድኑ ባደረገው የሱፐር ቪዥን ምልከታ የተደረገባቸው የሚኒሊክ፣ዘውዲቱ እና ጋንዲ መታሰቢያ የሆስፒታል ኃላፊዎች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡በሆስፒታሎቹ የሚከሰቱ ሁሉም ኩነቶች እንደሚመዘገቡ የተናገሩት የጤና ተቋማቱ ኃላፊዎች በቀጣይ ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ የተናገሩ ሲሆን የሚመለከታቸው የጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ፈጠራ እና ቴክኒካዊ ስልጠናዎችን ወስደው ወደ ስራ መገባቱንም አክለዋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ፣ በበጀት ዓመቱ በጤና ተቋማት የሚከሰቱ የልደትና የሞት ኩነቶችን በሙሉ በዲጂታል ሥርዓት በመመዝገብ ትክክለኛና አስተማማኝ የሕዝብ መረጃ ምንጭ ለመፍጠር ኤጀንሲው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ይህም ሥርዓት ለሀገራዊ ፖሊሲና ዕቅድ ዝግጅት፣ ለስታቲስቲካዊ መረጃ አያያዝ እና ለተለያዩ የልማት ውሳኔዎች የሚያገለግል ታማኝ የመረጃ መሠረት ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም አቶ ጥጋቡ አመልክተዋል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፈጣን፣ቀልጣፋ እና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት የኦን ላይ አገልግሎት መስጫ ፖርታል እና የተቀናጀ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ሲስተም አስመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

የነዋሪነት መታወቂያ ህትመት በወረዳዎች መጀመሩ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አስችሏልCRRSA:ነሐሴ14/2018ዓ.ም‎በአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ...
20/08/2026

የነዋሪነት መታወቂያ ህትመት በወረዳዎች መጀመሩ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል

CRRSA:ነሐሴ14/2018ዓ.ም

‎በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪነት መታወቂያ ህትመት በወረዳ ደረጃ መጀመሩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ፈጣንና እና ተደራሽ በማድረግ አገልግሎቱን የበለጠ ወደ ህብረተሰቡ በመቅረብ እንዲሰጥ ማስቻሉን አስታወቀ፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ እና በአራዳ ክፍለ ከተሞች የመታወቂያ ህትመት በተጀመረባቸው ወረዳዎች ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች እንደገለፁት የመታወቂያ ህትመት በወረዳ መጀመሩ እና በጠየቁበት ዕለት አገልግሎት ማግኘታቸው ከእንግልት እና ተደጋጋሚ ምልልስ ብሎም በመታወቂያ መዘግየት ሲስተጓጎሉ የነበሩ ሌሎች አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በከተማዋ ከፍተኛ የተገልጋይ ቁጥር ባላቸው እና በተመረጡ 22 ወረዳዎች የመታወቂያ ህትመት በመጀመር ተገልጋዮች በመጡበት ቅፅበት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማስቻሉ ይታወቃል፡፡

ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተለያዩ አማራጮች ወደ ህብረተሰቡ በማቅረብ ምቹ፣ ተደራሽ እና ተመራጭ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

የተሟላ የኩነት ምዝገባ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ CRRSA: ነሐሴ 13/2018 ዓ.ምአዲስ አበባየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ11ም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የኩ...
19/08/2026

የተሟላ የኩነት ምዝገባ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

CRRSA: ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ11ም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የኩነት ቡድን መሪ እና ከጤና ተቋማት የተወጣቱ ተወካዮች በተመረጡ ጤና ተቋማት ላይ በተደረገ ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በጤና ተቋሟቱ የሚከሰቱ ሁሉንም ኩነቶች በወቅቱ በመመዝገብና የተሟላ የኩነት ምዝገባ ወቅታዊ የምዝገባ በማድረግ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን ለፖሊሲ አውጭዎች እና ለአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ትክክለኛ የመረጃ አመንጭ መሆን እንደሚገባ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ገልፀዋል፡፡

በጤና ተቋማት የሚከናወነውን ምዝገባ የተሳለጠ እና ምቹ ለማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በተመረጡ ተቋማት አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በበጀት አመቱ ጤና ተቋማት ከተከሰቱ 147ሺ ወቅታዊ ኩነቶች መካከል 117ሺ መመዝገብ መቻሉን የገለፁት ምክትል ዳይሬክተሩ የምዝገባ ሽፋን በቅንጅት የመስራት ውጤት መሆኑን አክለዋል፡፡

በመድረኩ ኤጀንሲው በጤና ተቋማት በኩል ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ሽፋን በጥራት እንዲሰጥ ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተገቢው መወጣት እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን በምልከታው የተለዩ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግና ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ሽፋን ውጤታማ ማድረግ ወደ ተሟላ ምዝገባ መሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpres

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram)

ሀሰተኛ መረጃን በመከላከል ግልጽ፣ ተደራሽና ተዓማኒ አገልግሎትን ማረጋገጥCRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ምየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋሙ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የብልሹ...
18/08/2026

ሀሰተኛ መረጃን በመከላከል ግልጽ፣ ተደራሽና ተዓማኒ አገልግሎትን ማረጋገጥ

CRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተቋሙ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የብልሹ አሰራር ምክንያቶችንና የአደጋ ምንጮችን በመለየት፣ተገቢ የመከላከያ ሥርዓቶችን በመዘርጋት እና የሥራ አፈጻጸምን በቋሚነት በመከታተል ብልሹ አሰራርን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችል አቅጣጫ በማስቀመጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም ሠራተኞች በሕግና በሥነ-ምግባር መርሆች መሠረት በታማኝነት፣ በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በፍትሐዊነት እንዲሠሩ ማበረታታት፣ የተገልጋዮችን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና ለብልሹ አሰራር የማይመች የሥራ አካባቢ በመፍጠር ለከተማዋ ነዋሪዎች ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በዲጂታል ዘመን መረጃ በፍጥነትና በስፋት የሚሰራጭ በመሆኑ፣ ትክክለኛ መረጃን ከሀሰተኛና ከተዛባ መረጃ መለየት እየተፈታተነ መጥቷል። ሀሰተኛ መረጃ በተለይም ከመንግሥታዊ ተቋማት፣ ከሕዝብ አገልግሎቶችና ከማኅበረሰብ ከሚመለከቱ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሲሰራጭ የሕዝብን ግንዛቤ ሊያዛባ፣ አላስፈላጊ ጥርጣሬን ሊፈጥር እና በተቋማት ላይ ያለውን እምነት ሊያሳንስ ይችላል።

በመሆኑም ሀሰተኛ መረጃ በሚሰራጭበት ጊዜ በተረጋገጠ ማስረጃ ላይ በመመስረት በፍጥነት፣ በግልጽነትና በሙያዊ አግባብ ማስተባበል አስፈላጊ ነው። ይህም ሕዝብ ትክክለኛውን መረጃ ከተዛባ መረጃ እንዲለይ ከማገዝ ባሻገር የተቋሙን ተዓማኒነትና የሕዝብ እምነት ለማጠናከር ያስችላል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሚሰጠው አገልግሎት ዙሪያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ፣ የተዛቡ ወይም ከእውነታው የራቁ መረጃዎችን በመለየት፣ በተረጋገጠ መረጃ በመደገፍ እና ተገቢውን የማስተባበያ መልዕክት በወቅቱ ለሕዝብ በማድረስ የተሳሳተ ግንዛቤን ለመቅረፍ የሚያስችል አቅጣጫ ለመዘርጋት አስፈላጊ ነው።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ለማረጋገጥ ግልጽነት፣ተጠያቂነትና ተዓማኒነት በማጠናከር ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል፡፡

ኤጀንሲው ፈጣን፣ተደራሽ እና ከብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ እነዚህንም በዝርዝር ስንመለከታቸው

1ኛ.የነዋሪዎችን መረጃ ማደራጀት (DMS):-የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የነዋሪዎችን መረጃ ከሰው ሰራሽ እና ከተፈጥሮ አደጋ በመከላከል እንዲሁም ከሰው ንክኪ የፀዳ ለማድረግ የነዋሪዎችን መረጃ ወደ ሶፍት ኮፒ የመቀየር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ይህ አገልግሎት መረጃዎችን ከአዳጋ ከመጠበቁም ባሻገር ነዋሪዎች በየትኛውም ቦታ በቀላሉ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል፤በተጨማሪም ያለባለቤት ፈቃድ ማንኛውም ሰው ወይም ባለሙያ ያለባለቤቱ ፈቃድ ተጨማሪ መረጃ መስጠት እንዳይቻል በማድረግ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለመከላል ያስችላል፡፡

2ኛ.የኦንላይን አገልግሎት መጀመር፡-ይህ አገልግሎት ነዋሪዎች በየትኛውም ቦታ ሆነው እጃቸው ላይ በሚገኝ የቴክኖሎጂ አማራጭን በሞባይል ስልክ ወይም ኮምፒውተር በመጠቀም አገልግሎት መጠየቅ የሚችሉበት የዲጂታል አሰራር ስርዓት ሲሆን የፊት ለፊት አገልግሎትን በማስቀረት ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ያለው የአገልግሎት አማራጭ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

3ኛ.የኦዲት ስርዓት መዘርጋቱ፡-የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ በኤጀንሲው የሚሰራጩ የህትመት ውጤቶችን ትክክለኛ አገልግሎት መስጠታቸውን እና ለታለመለት ዓላማ ስለመዋላቸው በየጊዜው የኦዲት ስርዓት በመዘርጋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

4ኛ.የተጠያቂነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱ፡ ኤጀንሲው ብልሹ አሰራርን እና ሌብነትን በቁርጠኝነት እየተከላከለ ሲሆን ተፈፅሞ ሲገኝም አስቸኳይ እርምጃ ወስዷል፣እየወሰደም ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በበጀት ዓመቱ ከማዕከል እስከ ወረዳ በሚገኙ ተጠያቂ የተደረጉ ባለሙያዎች፣አመራሮች እና ተገልጋይ ደንበኞች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ማሳያ ይሆናሉ፡፡

5ኛ.የብልሹ አሰራር የጥቆማ ስርዓት የዘረጋ መሆኑ፡-ኤጀንሲው ብልሹ አሰራርን በመከላከል ፈጣን ተደራሽ እና የህብረተሰቡን እርካታ ያረጋገጥ አገልግሎት ለመስጠት የነፃ ጥሪ መቀበያ መስመር በ7533 ጥቆማዎችን እና ቅሬታዎችን በመቀበል እና በመከታተል አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በእውነታና በሚታመኑ ምንጮች ላይ የተመሠረተ መረጃን ከሚያሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን በመከታተል፣ ሕዝብን ከሚያሳስቱ እና ትክክለኛ ካልሆኑ የመረጃ ምንጮች ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምንም አይነት የሚዲያ ፈቃድ በሌላቸው እና ህብረተሰቡን ለማሳሳት ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ አካላት ራሱን እንዲጠብ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ከኤጀንሲው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመከታተል፣በነፃ የስልክ መስመር 7533 ላይ በመደወል እንዲሁም ከትክክለኛ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች መረጃ እንዲወስድ ኤጀንሲው ጥሪ ያቀርባል፡፡

በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpres

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram)

ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ስለማሳወቅCRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ምዋዜማ ሬዲዮ ሃገር ዉስጥ ምንም የዘገባ ፍቃድ ሳይኖረዉ በቀን 12/12/2018  ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር የሰራዉ ዘገባ ሚዛኑን ያ...
18/08/2026

ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ስለማሳወቅ

CRRSA:ነሐሴ12/2018ዓ.ም

ዋዜማ ሬዲዮ ሃገር ዉስጥ ምንም የዘገባ ፍቃድ ሳይኖረዉ በቀን 12/12/2018 ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር የሰራዉ ዘገባ ሚዛኑን ያልጠበቀና አግባብነት የሌለዉ አሉባልታ መሆኑን እያሳወቅን፤

ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ጉዳዮች ተጠያቂ የሆነ ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ተቋሙ ምን እየሰራ እንዳለ ሳያረጋግጥ የተሳሳተ ዘገባ በመስራት ተቋሙ እየሰራ ያለዉን ሪፎርም ለማጠልሸት የተሰራ ዜና መሆኑን በማወቅ ኤጀንሲዉ አሁን ላይ በዉስጡ ያሉ ህገ ወጥ አሰራሮችን በአግባቡ እየታገለና ተጠቂነትን እያሰፈነ ሪፎርም ያደረገ ሲሆን ተገልጋዩ ከቤቱ ሳይወጣና ባለሙያ ጋር መገናኘት ሳያስፈልገዉ የኦንላይን አገልግሎት ጭምር በመስጠት ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለዉ ደረጃ ላይ እየደረሰ ያለ ሲሆን፤ችግሮች ካሉም ኤጀንሲዉ በዘረጋዉ ነፃ የስልክ መስመር 7533 በመቀበል ተጠያቂነትን እያሰፋነ መሆኑን እያሳወቅን፤

የተሰራዉ ዘገባ አገር ውስጥ በሌለው ሪፖርተር በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ ሄዶ ይህን ዘገባ ሊሰራ ቻለ? በኤጀንሲው በአካል ተገኝቶ ለምን መረጃ መውሰድ አቃተው? አዲስ አበባ ውስጥ ሳይገኙ ስለኤጀንሲው ትክክለኛ መረጃ በምን የዜና መስፈርትና የሙያ ስነምግባር ማሰራጨት ቻለ? ስለሆነም የሰራውን ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ ፈጥኖ በማስተካከል ሚዛናዊ አድርጎ እንዲያቀርብና ከገፁ ላይ አንስቶ ይቅርታ እንዲጠይቅ እያሳሰብን በህግ አግባብ ጉዳዩን የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

“ኤጀንሲው አገልግሎቱን  ወደ ልህቀት ደረጃ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ ነው” አቶ ጥጋቡ ሹመይ  CRRSA:ነሐሴ10/2018ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎቱን ወ...
16/08/2026

“ኤጀንሲው አገልግሎቱን ወደ ልህቀት ደረጃ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ ነው” አቶ ጥጋቡ ሹመይ

CRRSA:ነሐሴ10/2018ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አገልግሎቱን ወደ ልህቀት ደረጃ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ልህቀትን መገንባት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ አመራሮች እና ቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡ የኩነት እና የነዋሪነት አገልግሎቶችን ታሪካዊ አመጣጥ መነሻ በማድረግ አሁን የደረሰበትን ነባራዊ ሁኔታ ያስረዱት አቶ ጥጋቡ በጋራ ጠንክሮ በመስራት እና የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት የነበሩ ውስንነቶችን በማረም የተጀመሩ ሪፎርሞችን በማጠናቀቅ ተቋሙን ወደ ልህቀት ማሸጋር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከተቋማት ጋር በቅንጅት የምንሰራው የኩነት ምዝገባን ለማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ ጥጋቡ የአሰራር ስርዓትን ዕውን ለማድረግ፣ የምዝገባ ጥራትን ለማረጋገጥ፣ከምዝገባ የተገኘ መረጃን ለታለመለት ዓላማ ለማዋል እንዲሁም የኩነት መዝገባ ሽፋንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልፀው ኩነት በሚከሰትባቸው ተቋማት ሙሉ አገለግሎት በመስጠት ሽፋንን ከማሳደግ ወደ ተሟላ ምዝገባ መሸጋገር እንደሚገባ ምክትል ዋና ዳይሬከተሩ አስገንዝገበዋል፡፡

ወደ ስራ የገባው አዲሱ ሲስተም፣ዌብ2 ሪፎርም፣አይዞ 9001 አሰራር፣የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መሻሻል ፣በወረዳዎች የነዋሪነት ዲጅታል መታወቂያ ህትመት መጀመሩ ልህቀት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታች መሆናቸውን አቶ ጥጋቡ አስረድተዋል፡፡

በዕለቱ የቫይታል ምዝገባ ምንነት እና አስፈላጊነት የቀረበ ሲሆን በመድረኩ የተሳተፉ የክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት አመራሮች እና ቡድን መሪዎች፣የኤጀንሲው የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት የተወያዩ ሲሆን የተጀመረውን ሪፎርም ከግብ በማድረስ የተቋሙን ልህቀት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

ኤጀንሲው በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የክፍለ ከተሞች እና የሥራ ክፍሎች  የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደCRRSA፡ ነሐሴ9/2018 ዓ.ምአዲስ አበባየሲቪል ምዝገባ እ...
15/08/2026

ኤጀንሲው በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የክፍለ ከተሞች እና የሥራ ክፍሎች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ

CRRSA፡ ነሐሴ9/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የማዕከል ጠቅላላ ካውንስል አባላት እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የእውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብር አካሂዷል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ኤጀንሲው ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማስቀጠል እና የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ለማጠናከር የሚረዳ እና የሚያበረታታ የተግባራት አፈጻጸም ስራዎቻችን አመላካች ውጤት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ በኤጀንሲው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች፣ቡድኖች እና የክፍለ ከተማየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤቶች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቡድኖች የዕውቅና የሰጠ ሲሆን የግዥ ቡድን፣የነዋሪዎች መታወቂያ አገልግሎት ቡድን እና የነዋሪዎች መረጃ እና ማስረጃ አገልግሎት ቡድን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በማጠቃለያው የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው ውጤት የአመራሩ እና የባለሙያው ጥረትና ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን በመግለጽ ኤጀንሲው ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት መሰረታዊ በመሆኑ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የስራ ሂደቶችም የምስጋና ሰርተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት በማበርከት ማበረታታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ተቋም በመገንባት ረገድ በቀጣይ በጀት ዓመትም አዲሱን ሲስተም ሙሉ ለሙሉ ትግበራዊ ማድረግና አገልግሎት መስጠት፣ አገልግሎት አሰጣጥን በትኩረት ችግር ፈቺ በሆነ መልኩ ማጠናከር፣ዶክመንት ማኔጅመንት ሲስተም (DMS) በጥራት ማደራጀት፣ የምዝገባ ጥራትንና የሽፋን መጠን ማሳደግ እና ዲጂታል ስርዓት ማጠናከር ለተቋማዊ ሪፎርሙ ቀጣይነት ወሳኝ ሚና እንዳለው አሳስበዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/)

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

በበጀት ዓመቱ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ለማድረግ እየተሰራ ነው’’አቶ ዮሴፍ ንጉሴCRRSA ፡ ነሐሴ 8/2018 ዓ.ምየሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ...
14/08/2026

በበጀት ዓመቱ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ለማድረግ እየተሰራ ነው’’አቶ ዮሴፍ ንጉሴ

CRRSA ፡ ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ዓመት ለህዝብ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለባለ ድርሻ አካላት እና ለመማክርት ጉባኤ አባላት ያወያየ ሲሆን በመድረኩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በተያዘው በጀት ዓመት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በሙሉ ዲጂታላይ በማድረግ የከተማዋ ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበት አሰራርን ማጠናከር እንዲሁም የተሟላ የኩነት ምዝገባ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በኤጀንሲው የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት በቀለ የከተማዋን ነዋሪዎች መረጃ በዲጂታል መንገድ ማደራጀት እና አገልግሎት መስጠት፣ አስተማማኝ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መፈፀም፣ መልካም አስተዳደርን መዘርጋት እንዲሁም ሙስናንና ብልሹ አሰራርን መታገል እና በማክሰም ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዕቅድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ያለውን ቅንጅታ አሰራር በማሳደግ የወቅታዊ ኩነት ምዝገባ ሽፋንን ማሳደግ እንዲሁም ከማመክርት ጉባኤ ጋር በጋራ በመሆን ውጤታማ ስራ ለመፈፀም መታቀዱን የገለፁት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሰፍ ንጉሴ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ የቀረቡት አስተያየቶች ኤጀንሲው ያቀደውን ግብ ለማሳካትና የአገልግሎት ጥራቱን ለማሻሻል ከፍተኛ እሴት እንደሚጨምሩ ገልጸዋል።

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA1935

የአሜሪካ ኢምባሲ ኮንሱላር ፍራዉድ ፕሪቬንሽን (Consular Fraud Prevention) ኤጀንሲው ህገወጥነትን በመከላከል እና በመረጃ ደህነንት አጠባበቅ ላይ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መ...
13/08/2026

የአሜሪካ ኢምባሲ ኮንሱላር ፍራዉድ ፕሪቬንሽን (Consular Fraud Prevention) ኤጀንሲው ህገወጥነትን በመከላከል እና በመረጃ ደህነንት አጠባበቅ ላይ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገለፀ፡፡

CRRSA: ነሐሴ7/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በአሜሪካ ኢምባሲ ኮንሱላር ፍራዉድ ፕሪቬንሽን (Consular Fraud Prevention) የተመራ ልዑካን ቡድን የተጎበኘ ሲሆን ተቋሙ በፎርጀሪ መከላከያ ሥራ ላይ እያሳየ ያለው ለዉጥ አበረታች መሆኑን አባላቱ ተናግረዋል፡፡

ለቡድን አባላቱ በመረጃ ደህንነት ስርዓት፣ የፎርጀሪ መከላከያ መርሀ ግብሮች ዙሪያ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ኤጀንሲው በስራ ላይ ያሳየውን ውጤታማ አፈጻጸም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፎርጅድ መከላከል ዘርፍ በዉስጥ አቅም ተቋሙ የሚጠቀማቸዉ የቴክሎኖጂ ግብዓት እና የሰነድ ማረጋገጥ ሂደትን ለቡድኑ አብራርተዋል፡፡

ኤጀንሲው በመረጃ ደህንነት መጠንከርና ፎርጀሪ መከላከል የሚታዩ ሥራዎች የሀገር ደህንነት ለማስጠበቅ ትልቅ ውጤት ያለው መሆኑን ጭምር በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ ሰብሳቢ የሆኑት ኮንሱላር የውጭ ሀገር ወንጀል መርማሪ መኮንን አሮን ክሊንገር (Overseas criminal investigator) Aaron Clinger እና የቡድን አባላቶች የኤጀንሲውን በቴክኖሎጅ የተደገፉ ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

የኦንላይን መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aacrrsa.gov.et

ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686

ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisvaitalpress

ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/

ቲክቶክ (TikTok): www.tiktok.com/ (

ኢንስታግራም (Instagram) https://www.instagram.com/aacrrsa_head_office/

ትዊተር (Twitter): https://x.com/CRRSA193

13/08/2026

Address

Tunisia Avenue, Gulelle Subcity Woreda 8
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa CRRSA - Civil Registration and Residency Service Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share