05/09/2026
በወረዳው አስተዳደር መጪው አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ ኢግዚብሽንና ባዛር ግብይይት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡
ኮልፌ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 30 /2018 ዓ.ም
መጪው አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ በወረዳ 05 አስተዳደር በዘነበወርቅ አደባባይ ኤግዚቢሽንና ባዛር ግብይይት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ።
በባዛሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳኛቸው ሹመት የተዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛሮች በዋናነት ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነና የወረዳው ነዋሪ በአቅራቢያው በተዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛሮች ላይ በመገኘት ግብይት እንዲጠንይከር ጥሪ አቅርበዋል።
እስከ በአሉ ድረስም ምርቶች በስፋት እንደሚቀርቡ የገለፁት አቶ ዳኛቸው ለኤግዚብሽኑና ባዛሩ አስፈላጊ ዝግጅት ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ አሰፋ አዱኛ የወረዳው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ በበኩላቸው አዲስ አመትን በማስመልከት የወረዳ አስተዳደር በባዛሮች፣ በገበያ ማእከላትና በ2 የቅዳሜና እሁድ ገቢያዎች ምርቶችን በስፋትና በጥራት ማቅረቡን ገልፀዋል።
ሀላፊው አክለው ህብረተሰቡ በአልን በደስታ እንዲያሳልፍ እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ባዛሩ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው በዓሉን ምክንያት በማድረግ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ መቅረቡን አስታውቀዋል።
በወረዳው በዘነበወርቅ አደባባይ በተከፈተው ኤግዚብሽን እና ባዛር በወረዳው የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ፣ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ አርሶ አደሮች እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የሚሰሩ ነጋዴዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በሁለቱ የገበያ ማእከላት ኤግዝብሽኑ የባህል አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማርና የማር ውጤቶች፣ የኢንደስትሪ ምርቶች ፣ የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ለበአል የሚውሉ የተለያዩ ምርቶች የቀረቡ ሲሆን እስከ ጳጉሜ 05/2018 ድረስም የሚቆይ ነው።