Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን

Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን ህዝብና መንግስትን ማገናኘት፣ተጨባጭ ፣ታማኝ ወቅታዊ ፣ ቀላጣፋና ጠቃሚ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስ ነው ። (በቅንነት follow )አድርጉና እናመሰግናለን 🙏https://linktr.ee/yekaworedafourcomm
(3)

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡***ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪ...
17/08/2026

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡
***
ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አካባቢ ጓደኛቸውን ሲደበድቧት የሚያሳይ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ህብረተሰቡ አስተያየት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከመሰራጨቱ ከወራት በፊት ወንጀሉን የፈፀሙትን ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማጣራቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሦስት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ልጅቷ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዩ መለቀቁ በልጅቷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ቪዲዮውን የለቀቀውን አካል ለማረጋገጥ ፖሊስ ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ ድርጊቱን በማውገዝ ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳየውን መቆርቆር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አድንቋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የተጀመረው የሰንበት ገበያ የነዋሪውን ኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ  በማገዝ ተጠናክሮ ቀጥሏል !አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 10/2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ...
16/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የተጀመረው የሰንበት ገበያ የነዋሪውን ኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማገዝ ተጠናክሮ ቀጥሏል !

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 10/2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ****************************

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር፣ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ (ኮሪያ ሰፈር) ያቋቋመው የሰንበት ገበያ በተጠናከረ መልኩ ለሸማቹ ማህበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነቱን በማቀላጠፍ እንደቀጠለ ነው ።

የሰንበት ገበያው በዋናነት ከአምራች ወደ ሸማች የግብይት ሥርዓትን በመዘርጋት፣ የዕለት ተዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው በማቅረብ ላይ ይገኛል። ገበያው እንደ ዘይት፣ ዱቄት፣ ጥራጥሬዎች እንዲሁም የጓሮ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን በቀጥታ ከገበሬው እና ከህብረት ስራ ማህበራት በማቅረብ ረገድ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የግብይቱ ተጠቃሚዎች ይገልጻሉ።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ የሰንበት ገበያው በተለይም አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ እፎይታን የፈጠረ ነው። በየሳምንቱ የሚከናወነው ይህ ገበያ፣ አቅርቦትን በማሳደግ እና የዋጋ መለዋወጥን በመግታት የነዋሪውን እርካታ እየጨመረ መምጣቱን አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች ተናግረዋል።

የወረዳው ንግድና ኢንዱስትሪ ከህብረት ሥራ ጋር በጋራ በመሆንም፣ የሰንበት ገበያው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን በማቀላጠፍ ለቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ይህም የከተማዋን ነዋሪ የኑሮ ውድነት ተግዳሮቶች ለመቋቋም ከሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች አንዱ አካል መሆኑ ታምኖበታል።

ገበያው በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ በኮሪያ ሰፈር የሚከናወን ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች ሙሉ እምነት ጥለውበት ግብይት እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ የሰንበት ገበያ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ እንዲሆን የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በቁርጠኝነት እየሰራበት ይገኛል።

16/08/2026
ኢትዮጵያ የዘመናት ስብራቶቿን ለመጠገን እየመከረች ነዉ!የአንዲት ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በህዝቦች የጋራ መግባባትና በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ላይ...
16/08/2026

ኢትዮጵያ የዘመናት ስብራቶቿን ለመጠገን እየመከረች ነዉ!

የአንዲት ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በህዝቦች የጋራ መግባባትና በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ላይ ሲገነባ ብቻ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በገለልተኛ ተቋም የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር የቆዩና የተወሳሰቡ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ፈትተን፣ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የተከፈተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነዉ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልተኛ ሆነ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። አሁን ላይ ሂደቱ እጅግ ተስፋ ሰጪና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ኮሚሽኑ በመላው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መዋቅሩን ዘርግቶ፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግብዓቶችንና አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራን በስኬት አጠናቋል።

አሁን ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ከ4,000 በላይ ተወያዮቹ ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ከትጥቅ ትግል ወደ ሳላም አማራጭ የተመለሱ ሃይሎች ፣ የዲያስፖራ አባለት፣ ምሁራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገናኝተው ታሪካዊ ምክክሩን እያሳለጡ ነዉ።

ሀገራዊ ምክክር የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ የወደፊት እጣ-ፈንታ የሚወሰንበት ብሄራዊ መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክርን በአግባቡ በመጠቀም ከተወሳሰበ ቀውስና ከእርስ በርስ ጦርነት ወጥተው ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻገሩ በርካታ ሀገራትን ማንሳት ይቻላል።

ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት ካደረሰባት ጥልቅ ማህበራዊ ቁስልና የርስ በርስ ጦርነት ስጋት የወጣችው በሀገራዊ ምክክር (CODESA) አማካኝነት ነው። የፖለቲካ ሃይሎች በጥላቻ ፈንታ ይቅርታንና እርቅን በማስቀደማቸው ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ጠንካራ ዲሞክራሲ መገንባት ችላለች።

ቱኒዚያ እ.ኤ.አ በ2011 ከነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ፣ የሀገር መፍረስ ስጋትና አለመረጋጋት ህዝቧን የታደገችው በሲቪል ማህበራት መሪነት በተደረገ ብሄራዊ ምክክር ነው። ይህ ምክክር ሀገሪቱን አዲስና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ለማርቀቅ አብቅቷታል።

የእነዚህ ሀገራት ተሞክሮዎች የሚያሳየን በቅንነትና በቁርጠኝነት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተቀመጥን የማይፈታ የትኛውም ውስብስብ የፖለቲካ ቀውስ እንደሌለ ነዉ።

ስለዚህ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግና ከልቡ የሚሻ ሁሉ ዜጋ ሀገራዊ ምክክሩ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ የሚወስን ስለሆነ በሃሳብ፣ በዕውቀት፣ በንቁ ተሳትፎና በጸሎት መደገፍ የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው።

prosperity

ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባየመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት ተዋህደው አዲስ አበባን ምቹ የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርገዋታል...
15/08/2026

ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ

የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት ተዋህደው አዲስ አበባን ምቹ የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርገዋታል፡፡

የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ፣ በ2018 ዓ.ም በርካታ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችንና ስብሰባዎችን በደመቀ ሁኔታ አስተናግዳለች።

ከተማዋ ከተለያዩ የዓለም ማዕዘናት የመጡ መሪዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቢዝነስ ሰዎችንና ባለሙያዎችን በክብር ተቀብላ፣ በብቃት በማስተናገድ በሰላም ሸኝታለች።

ይህ ስኬት ከተማዋ ያላትን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ከማሳየቱም በላይ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበቻቸውን ፈጣን የእድገትና የመዘመን ጉዞ ለዓለም ያበሰረ አጋጣሚ ሆኗል።

አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ለነበሩት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች አዲስ ፊትና ድምቀት ይዛ እንድትቀርብ ካደረጓት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል በከተማዋ የተተገበረው መጠነ-ሰፊ የኮሪደር ልማት ግንባታ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ሰፋፊና ንፁህ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መስመሮች፣ ዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና ውብ የአረንጓዴ ስፍራዎች የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።

ይህ የመሰረተ ልማት መዘመን በኮንፈረንሱ ወቅት የመጡ እንግዶች በከተማዋ ውስጥ ያለምንም እንግልትና በከፍተኛ ደህንነት እንዲንቀሳቀሱ ከመርዳቱም በላይ፣ ለአዲስ አበባ ዘመናዊና ማራኪ ውበትን አላብሷታል።

የትራፊክ ፍሰቱን በማቃለልና የእይታ ውበትን በመጨመር ረገድ የኮሪደር ልማቱ ለኮንፈረንስ ቱሪዝሙ ትልቅ አጋዥ ሆኗል።

ከተማዋ በቅርብ ጊዜያት የገነባቻቸው ድንቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችና ዘመናዊ ፓርኮች ለስብሰባ የመጡ እንግዶች የትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ተመራጭ ስፍራዎች ሆነዋል።

እንደ አንድነት ፓርክ፣ እንጦጦ ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ እና ሌሎች አዳዲስ የወንዝ ዳርቻ መዝናኛዎች እንግዶችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

እነዚህ ስፍራዎች ከተማዋ ከመደበኛ የስብሰባ አዳራሾች ባለፈ፣ እንግዶች የሚዝናኑባቸው፣ ተፈጥሮን የሚያደንቁባቸውና የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በአንድ ቦታ የሚያዩባቸው የቱሪዝም ማዕከላት ሆነው አገልግለዋል።

ይህም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከባህላዊና ከተፈጥሮ ቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር የከተማዋን የቱሪዝም ገቢና ዝና ከፍ አድርጎታል።

ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ታዋቂ የሆቴል ብራንዶች በአዲስ አበባ መበራከታቸው ከተማዋ በ2018 ዓ.ም ላስመዘገበችው ስኬት ሌላኛው ምሰሶ ነው።

ሆቴሎቹ እንግዶችን በከፍተኛ የደህንነት፣ የፅዳትና የቅልጥፍና ደረጃ ከማስተናገዳቸውም በላይ፣ የኢትዮጵያውያንን ባህላዊ የእንግዳ ተቀባይነት ጨዋነት ከዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር አዋህደው አቅርበዋል።

የስብሰባ አዳራሾች ዝግጁነት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችና የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖር ሆቴሎቹ ለኮንፈረንሶቹ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አስችሏቸዋል።

ከተማዋ በአንድ ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ እንግዶችን በምቾት የማሳደርና የማስተናገድ ሙሉ ብቃት እንዳላት በተግባር የታየበት ሆኗል።

በአጠቃላይ አዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ያስተናገደቻቸው በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ከተማዋ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያላትን የማይተካ ሚና ዳግም ያረጋገጡ ነበሩ። ከተማዋ እንግዶቿን ተቀብላ፣ በከፍተኛ ፍቅር አስተናግዳ፣ በሰላም በመሸኘት ያሳየችው ብቃት የሚደነቅ ነው።

ይህ ስኬት ከተማዋ የገነባቻቸው ዘመናዊ የኮሪደር መሰረተ ልማቶች፣ ማራኪ የወንዝ ዳርቻዎችና የቱሪዝም ፓርኮች እንዲሁም የላቀ የሆቴሎች ዝግጁነት ጥምር ውጤት ነው።

አዲስ አበባ አሁን ላይ ስብሰባዎች የሚካሄዱባት ከተማ ብቻ ሳትሆን፣ የመሰረተ ልማት መዘመንና የተፈጥሮ ውበት የተዋሃዱባት፣ አስተማማኝና ምቹ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል መሆኗን ለዓለም አስመስክራለች።

ይህ ተሞክሮ ወደፊትም ከተማዋ ይበልጥ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እንድትስብና እንድታስተናግድ በር የሚከፍት ነው።

በየካ ሰማይ ስር የአዲስ አበባ ከተማን ከፍታ ያረጋገጡ የኮሪደርና የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች!ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን
15/08/2026

በየካ ሰማይ ስር የአዲስ አበባ ከተማን ከፍታ ያረጋገጡ የኮሪደርና የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች!
ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የተጀመረው የሰንበት ገበያ የነዋሪውን ኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ  በማገዝ ተጠናክሮ ቀጥሏል !አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽ...
15/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የተጀመረው የሰንበት ገበያ የነዋሪውን ኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማገዝ ተጠናክሮ ቀጥሏል !

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የካ ወረዳ 04 ኮሙኒኬሽን ****************************

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር፣ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ (ኮሪያ ሰፈር) ያቋቋመው የሰንበት ገበያ በተጠናከረ መልኩ ለሸማቹ ማህበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነቱን በማቀላጠፍ እንደቀጠለ ነው ።

የሰንበት ገበያው በዋናነት ከአምራች ወደ ሸማች የግብይት ሥርዓትን በመዘርጋት፣ የዕለት ተዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው በማቅረብ ላይ ይገኛል። ገበያው እንደ ዘይት፣ ዱቄት፣ ጥራጥሬዎች እንዲሁም የጓሮ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን በቀጥታ ከገበሬው እና ከህብረት ስራ ማህበራት በማቅረብ ረገድ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የግብይቱ ተጠቃሚዎች ይገልጻሉ።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ የሰንበት ገበያው በተለይም አቅመ ደካማ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ እፎይታን የፈጠረ ነው። በየሳምንቱ የሚከናወነው ይህ ገበያ፣ አቅርቦትን በማሳደግ እና የዋጋ መለዋወጥን በመግታት የነዋሪውን እርካታ እየጨመረ መምጣቱን አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች ተናግረዋል።

የወረዳው ንግድና ኢንዱስትሪ ከህብረት ሥራ ጋር በጋራ በመሆንም፣ የሰንበት ገበያው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር እና የአቅርቦት ሰንሰለቱን በማቀላጠፍ ለቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ይህም የከተማዋን ነዋሪ የኑሮ ውድነት ተግዳሮቶች ለመቋቋም ከሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች አንዱ አካል መሆኑ ታምኖበታል።

ገበያው በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ በኮሪያ ሰፈር የሚከናወን ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች ሙሉ እምነት ጥለውበት ግብይት እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ የሰንበት ገበያ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች አካባቢዎችም ተሞክሮ እንዲሆን የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በቁርጠኝነት እየሰራበት ይገኛል።

14/08/2026
የየካ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት የታደሰውን የአቅመ ደካማ እናት ቤት አስረከበ !የካ ክፍለ ከተማ (ወረዳ 04) መንግስት ኮሙኒኬሽን ነሃሴ 8/2018 ዓ/ም...
14/08/2026

የየካ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት የታደሰውን የአቅመ ደካማ እናት ቤት አስረከበ !

የካ ክፍለ ከተማ (ወረዳ 04) መንግስት ኮሙኒኬሽን
ነሃሴ 8/2018 ዓ/ም ************************

የካ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር በወረዳ 04 ያስገነባውን/ያደሰውን የአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት አጠናቆ በዛሬው ዕለት ለባለቤቷ አስረክቧል።

የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎትን ማጠናከርና የአቅመ ደካሞችን ህይወት ማሻሻልን ዓላማ ያደረገው ይህ የበጎ አድራጎት ስራ፣ በዛሬው ዕለት ፍጻሜ አግኝቶ ቤቱ ለእናቲቱ መሰረከቡ ተገልጿል።

ህብረተሰቡንና በጎ ፈቃደኞችን አስተባብሮ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረግ የማህበራዊ ትስስርን ከመፍጠሩ ባሻገር የወገን አለኝታነትን በተግባር የሚያሳይ ነው።

ቤቱ የታደሰላቸው እናት በበኩላቸው በችግራቸው ወቅት አጠገባቸው በመቆም ቤታቸውን አድሶ ላስረከቡ አካላት በሙሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታና ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይነትም በተለያዩ የልማትና የማህበራዊ ድጋፍ ዘርፎች ላይ የበጎ ፈቃደኞችን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፅህፈት ቤቱ አረጋግጠዋል።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00
Sunday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka Wereda 4 Communication የካ ወረዳ 4 ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share