FDA Kirkos Branch Claster Three Office

FDA Kirkos Branch Claster Three Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FDA Kirkos Branch Claster Three Office, Government Organization, Addis Ababa.

‎በአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ክላስተር 3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከባ...
30/01/2026

‎በአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ክላስተር 3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
***‎ጥር 07/2018 ዓ.ም***
‎በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር አፈጻጸም እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከጤና ፎረም፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከነዋሪው ጋር ዉይይት ተካሄደ።

‎የቂርቆስ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር አለምሽ አባይ ባለፉት ስድስት ወራት በጽ/ቤቱ የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ለማስጠበቅ በመደበኛ ቁጥጥር እንዲሁም በዘመቻ በርካታ ስራዎች መከናወናቸዉን ጠቅሰዉ በእቅድ ከተያዙት ስራዎች በተጨማሪ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከመከላከል አንጻር፣ተቋማዊ ውጤታማነት በማሻሻል የሰራተኛና ተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር፣ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና አገልግሎትን ከማሻሻል አንጻር እንዲሁም የህዝብ፣ሲቪል ማኅበራትና የግል ሴክተር ተሳትፎ ስርዓትን ከማሳደግ አንፃር በ6 ወራት ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

‎በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸምና በአዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ዙሪያ የወይይት ሰነድ በማድረግ የቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 ጽ/ቤት ስራ አስካጅ አቶ ዳኛቸው ግዛው ለባለድርሻ አካላት በዛሬው ዕለት ግንዛቤ ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠል ከአዋጅና ደንብ መመሪያ ጋር የብቃት ማረጋገጥ ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ ጋሻው ከትምባሆ እና አደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ከመመሪያና አዋጅ ጋር በማመሳከር በቀረበው ሰነድ ተወያይተዋል።

‎ጽ/ቤቱም በ2018 ግማሽ አመትየህብረተሰብን ጤና ደህንነቱን የጠበቀ አገልግሎት ለሚሰጡ 349 ተቋማት ብቃት መረገገጫ መስጠቱን አስታውቆል።

‎በመጨረሻም ባለድርሻ አካላቱ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቤቱም ለቀረቡ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የክላስተር 3 የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ግዛው ምላሽ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አንዳንድ ቀሪ ስራዎች ያሉ መሆናቸውን በመግለጽ የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፎና ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጥቆማ ነጻ 8864 ላይ ጥቆማ በመስጠት እንደሚቻል በመግለጽ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል::

የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ምግብና ጤና ነክ ምርቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር ላይ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ፡፡‎‎==========================...
08/10/2025

የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ምግብና ጤና ነክ ምርቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር ላይ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

‎============================
‎መስከረም 28/2018ዓ.ም
‎የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙንና የ2018 ዕቅዱን እንዲሁም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላትና ከህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አድርጓል ።

‎በመድረኩ የነጋዴ ፎረም፣የብሎክ አደረጃጀት፣ከሴት ማህበር፣ከወጣት ማህበር እና ከሚመለከታቸው ጽህፈት ቤቶች የተዉጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ መሆን እንዲችሉ ተደርጓል።

‎በተያዘው በጀት አመት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙንና የ2018 ዕቅዱን እንዲሁም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸሙን ቤቱ ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ ጋሸው አማካኝነት ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

‎የቀረበውን ሠነድ መነሻ በማድረግና ከጽህፈት ቤቱ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ጥያቄና አስተያየት ከባለድርሻ አካላቱ ተነስቶ ዉይይት ተደርጓል።

‎ከመድረኩ የሚሰነዘሩ ሀሳብና አስተያየቶች ለቀጣይ እንደ ግብዓት ይሆናል ያሉት የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍክላስተር 3 ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸውግዛው ፤ከባለድርሻ አካላት በተነሡቱ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ በመስጠት የመድረኩ አላማ ይህ ጽህፈት ቤት የሠራቸዉን ተግባራት ለህብረተሰቡ ግልጽ ከማድረግ ባለፈ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት አርጎ ለመስራት እንዲሁም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል የሚረዳ በመሆኑ ነዉ ተብሏል።
‎የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር አለምነሽ አባይ ማጠቃለያ እና መዝጊያ ያደረጉ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሪፎርም ተግባራትን በማከናወን በርካታ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በማስቀጠል ለማህበረሰቡ ጎጂ እና አደገኛ የሆኑ ማናቸዉም አይነት ድርጊቶችን በጋራ ለመከላከል የህብረተሰቡን ጤና በዘላቂነት መጠበቅ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱን ገልጸዋል፡፡ በከተማችን ህብረተሰቡ ጤናን ለማስጠበቅ ግብዓቶች ጥራታቸውን ፣ ብቃታቸውን፣ መጠናቸውን እና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እንዲቀርቡ የክትትልና ድጋፍ ገልፀው በከተማ ያሉ የምግብና መጠጥ አቅራቢ ድርጅቶችም ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ሙያዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገርም ህግን ተላልፈው በሚገኙ ተቋማት ላይ የእርምት እርጃ መውሰዳቸውንም አክለው ገልፀዋል።

17/12/2024
14/11/2024
የአዲስአበባ ከተማ ምግብ መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 በቀን 30/11/2016 በአቃቂ ኢንዱስትሪ መንደር በመገኘት የችግኝ ተከላ ተከናውኗል ። በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ...
07/08/2024

የአዲስአበባ ከተማ ምግብ መድሀኒት ባለስልጣን ቂርቆስ ቅርንጫፍ ክላስተር 3 በቀን 30/11/2016 በአቃቂ ኢንዱስትሪ መንደር በመገኘት የችግኝ ተከላ ተከናውኗል ። በችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ላይ የፅ.ቤቱ ሰራተኞች ና የክላስተር አመራር በቦታው በመገኘት ችግኝ ተተክሏል ።

18/06/2024
18/06/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FDA Kirkos Branch Claster Three Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share