Addis Ababa City Government Bureau of Justice

Addis Ababa City Government Bureau of Justice Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa City Government Bureau of Justice, Government Organization, Mexico, Addis Ababa.

የእመርታ ቀን አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

05/09/2026
03/09/2026
በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣተር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012  በመድረክ ለህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተ...
02/09/2026

በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣተር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 በመድረክ ለህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ።
በቀን 27/12/2018 ዓ.ም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ወጣት እና ሴት ማህበር ጋር በመቀናጀት በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገ ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጪ መላክ ወንጀሎች በዜጎች አካል ፣ ህይወት እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እና ለሰብአዊ መብት ጥሰት እያጋለጡ የሚገኙ ወንጀሎች መሆናቸውን የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ፡፡
አዋጁን መሰረት በማድረግ ዜጎች እራሳቸውን ከአታላይ እና ከህገ ወጥ ደላሎች በመጠበቅ ሊደርስባቸው ከሚችል ከአካላዊ ፣ ስነልቦናዊ እና ከምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት እንዲጠብቁ ፤ በዚህ የወንጀል ተግባር ሰለባ የሆኑ ዜጎች በነፃ የስልክ ቁጥር 6073 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጡ ፤ እንዲሁም ፤ወጣቶች እራሳቸውን ከዚህ አስከፊ ወንጀል ሰለባ ከመሆን እራሳቸውን እንዲጠብቁ እና በዚህ የወንጅል ድርጊት ላይ የሚሳተፉ ህገወጥ ደላሎችን እንዲያጋልጡ የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በዚህ ንቃተ ህግ ስልጠና ላይ የየተሳተፉ ወጣቶች ያገኙት የህግ ግንዛቤ በጣም ጥሩ መሆኑን እና ቀጣይነት ነሮት ሁሉም ዜጋ ተደራሽ እንድሆን በመድረኩ አንተዋል፡፡

Address

Mexico
Addis Ababa
15052

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251115159603

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Government Bureau of Justice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa City Government Bureau of Justice:

Shortcuts

Share