Federal First Instance Court Of Ethiopia

Federal First Instance Court Of Ethiopia Justice Organization

የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ስልጠና ለአመራሮች ተሰጠ።********* በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት  ትግበራ በፌደራል የመጀመሪያ...
03/09/2026

የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ስልጠና ለአመራሮች ተሰጠ።
*********
በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ትግበራ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስጀመር ለፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት፣ የየምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች እና የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች ነሐሴ 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።

የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን የኢ-ፍሊት ማኔጅመንትን (e-Fleet Management) በተለያዩ ተቋማት በሙከራ ትግበራ በማረጋገጥ በሁሉም የፌደራል ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ በተወሰነው መሰረት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱም ተግባራዊ ለማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን አቶ ተስፋዬ ከበደ የፍርድ ቤቱ የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ በስልጠናው መክፈቻ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለስልጣን ባለሙያዎች አቶ ኢሳያስ መንግስቱ ሲኒየር አፕሊኬሽን ዲቨሎፐር እና አቶ አለምሸት ክንፈ የኢጂፒ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ ሲሆኑ ሲስተሙ ፍርድ ቤቱን ወደ ዘመናዊ፣ ዲጂታል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ ከመርዳቱ በተጨማሪ ኢ-ፍሊት ማኔጂመንት ሲስተምን መጠቀም ግልፅ እና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ለማግኘት፣ የወረቀት ስራዎችን ለማስቀረት፣ ከሰዎች ንኪኪ ነፃ የሆነ አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት፣ የተጠቃሚዎች ጊዜን ለመቆጠብ እንዲሁም የነዳጅ ዘይት እና ቅባት ወጪን ለመቆጣጣር እና ለተሸከርካሪ የሚወጣዉን ወጪ ለማወቅ የሚያስችል አሰራር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ እንደ አሰልጣኞቹ ገለፃ ኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ክንውኖችን በጥራት፣ በብቃት፣ በሰዓት እና በበጀት መጥኖ መፈፀም የሚያስችል ዘመናዊ የአሰራር ስርአት እንደሆነ በተለይም የተሽከርካሪ ንብረት አጠቃቀም፣ አያያዝ፣ የግዥ ሂደት እና አወጋገድን በተመለከተ የላቀ ጠቀሜታ ያለው የአሰራር እና ቁጥጥር ስርአት መሆኑ ተገልጿል።
መንግስት የግዥ ስርአቱን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ ዲጂታላይዜሽን ስርአት በማስገባት ኢጂፒ (e-GP) ተግባራዊ እንደተደረገ ሁሉ በተመሳሳይ በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የለማ የኢ-ፍሊት ማኔጅመት ሲስተም መተግበሪያን ተግባራዊ በማድረግ የተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀምን ከማሻሻል ባለፈ የሃብት ብክነትን ለማስቀረት እየተጋ መሆኑ ተነግሯል።
ኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም ከተሽከርካሪ ጥገና እና ነዳጅ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን በመግለፅ ለግልጽ አሰራር እና የሃብት ክትትል መተግበሪያውን በአግባቡ በመጠቀም ለአሰራሩ ውጤታማነትም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እና ትብብር በስልጠናው የተገኙ ኃላፊዎች በማድረግ በተገቢው ወደ ስራ እንዲገባ በስልጠናው ተገልፆል።
ስልጠናው ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ለሹፌሮች፣ ለዳይሬክተሮች ፀሃፊዎች እና በትራንስፖርት ስምሪት ቡድን መሪ ስር ላሉ ሁሉም ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

መልካም የመውሊድ በዓል ! *****የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ በማለት...
24/08/2026

መልካም የመውሊድ በዓል !
*****
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅድ  ላይ ውይይት  ተደረገ።                                                ...
21/08/2026

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።
********
የፌደራል ፍ/ቤቶች 3ኛው ስትራቴጂያዊ እቅድ ማብቂያው በ2018 መሆኑን መነሻ በማድረግ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት ሲዘጋጅ የቆየው 4ኛው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የማኔጅመንት አባላት፣ የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች፣ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እና የስራ ክፍሎች ዳይሬክተሮች በተገኙበት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች 4ኛው (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅዱ ለተሳታፊዎች አስቀድም በመላክ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን ለማቅረብ እንዲመቻቸው ተዘጋጅተው እንዲመጡ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም በአቶ ተስፋዬ ደጀኔ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ለውጥ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዕቅዱን ከ3ኛው ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር በማነፃፀር በተለይም በአዲስ በተካተቱ ፍሬ ነገሮች ላይ በመመስረት ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ክቡር ዳኛ አቶ የምስራች ከተማ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር እና ሰው ሃብት ስራ አመራር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የአብይ ኮሚቴው አባል በሰነዱ ላይ ለውይይት መነሻ የሆኑ ሃሳቦችን አቅርበዋል።
ክቡር አቶ ፋዓድ ኪያር የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት መድረኩ ጠቃሚ እና ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ፍሬ ሃሳቦችን ለመሰብሰብ መዘጋጀቱን በመግለፅ ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችሉ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች እንዲቀርቡ ለተወያዮች እድል የሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎች አስቀድመዉ በፅሁፍ እንዲሁም በመድረኩ ላይ ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ግብአቶች እና የማብራሪያ ጥያቄዎች አቅርበዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ በፕሬዝዳንቱ የማጠቃለያ ሃሳቦች እና ማብራሪያዎች የሰጡ ሲሆን ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተጠቃለው ለአዘጋጅ ኮሚቴው እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጦ ውይይቱ ተጠናቋል።

የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን አስመልክቶ ዳኞች እና ጠበቆች ምን ይላሉ ? የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን አስመልክቶ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  ያሰራነውን ልዩ ፕሮግ...
19/08/2026

የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን አስመልክቶ ዳኞች እና ጠበቆች ምን ይላሉ ?
የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን አስመልክቶ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያሰራነውን ልዩ ፕሮግራም ሙሉ ይዘት ይከታተሉ ።

በዚህ የፍትህ ለሀገሬ ፕሮግራም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ2017 ዓ.ም. የድህረ ውሳኔ ምርመራ...

የፌደራል ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።*********    የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስ...
19/08/2026

የፌደራል ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።
*********
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ በተመለከተ የተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት እና እቅድ ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት፡፡
የስልጠና እቅዱን ለበላይ አመራሮች ያቀረቡት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሮን ደጐል ሲሆኑ በጥናት ሠነዱ የ2018 የስልጠና እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣የነበሩ ጠንካራ ጐኖች፣ክፍተቶች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የተካሄደበትን አግባብ እና የፍላጎት ዳሰሳ መሰረት በማድረግ የተለዩ 21 የስልጠና ርዕሶች እና ሰልጣኞች እቅድ አቅርበዋል፡፡
የዳሰሳ ጥናቱ ከቀረበ በኃላ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራሮች በርከታ አስተያየት እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶል፡፡
በመጨረሻም በሰነዱ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች እና ግብአቶች እንዲካተቱ እና ሰነዱ በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ከዳበረ በኋላ በቀጣይ በጋራ በድጋሚ እንደሚታይ በመግባባት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !********    አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እ...
18/08/2026

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !
********
አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 1410/18 መፅደቁን ተከትሎ በርካታ አዳዲስ አሠራሮች በአዋጁ የተካተቱ ከመሆኑም በላይ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎች ወደ ፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መውረዳቸዉ እና የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ መካተቱ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ አዲሡ አዋጅ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሚኖረውን / ሊያስከትል የሚችለውን የአደረጃጀት እና አተገባበር ለውጥ በተመለከተ ጥናት አጥንቶ የሚያቀርብ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በማዋቀር ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በዚህ መሠረት የተዋቀረው ኮሚቴ የጥናት ሠነዱን የመጀመሪያ ረቂቅ ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራር (ማኔጅመንት) አቅርቧል፡፡
ጥናት ሰነዱ ያቀረብት የኮሚቴው ሰብሳቢ እና አባላት ሲሆኑ የጥናት ሠነዱ ከቀረበ ቡሃላ በርካታ አስተያየቶች ተነስተው ሊጨመር፣ሊቀነስ፣እና ሊሻሻል ይገባሉ በተባሉት ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ሠነዱ በተሰጡት አስተያየቶች እንዲዳብር እና የመጨረሻ ይዘቱን ከያዘ ቡሃላ ለትግበራ ስራ ለበላይ አመራሮች የሚቀርብ ይሆናል፡፡

17/08/2026

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የድህረ ውሳኔ ምርመራ/ኦዲት ሪፖርትን ለፍ/ቤቱ ሁሉም ዳኞች ያቀረበበት መድረክን አስመልክቶ የተሰራነው ልዩ ፕሮግራም ረቡዕ ምሽት 2:00 ሰዓት በዓባይ ቲቪ እና በፍትሕ ለሃገሬ ዩቱዩብ ገፅ ላይ ስለሚቀርብ እንድትከታተሉት በአክብሮት ተጋብዣችኋል ።

የሀዘን  መግለጫ !*******የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ ክቡር ዳኛ ተመሰገን ወንድምአገኝ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።‎የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክቡር ዳ...
15/08/2026

የሀዘን መግለጫ !
*******
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ ክቡር ዳኛ ተመሰገን ወንድምአገኝ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
‎የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክቡር ዳኛ ተመስገን ወንድምአገኝ ህልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።********የፌደራል  የመጀመሪያ  ደረጃ  ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ  መድን ሰጪዎች ማህበር ጋር...
08/08/2026

በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
********
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት (ነሐሴ 2 እና 3 ) የሚቆይ በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ የታኮረ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየሰጠ ይገኛል ።
በስልጠናዉ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ሁሉም ዳኞች እና የምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞቸ የተገኙ ሲሆን ስልጠናዉ በዋናነት ከኢንሹራንስ ጋር የተያያዙ ህጎች እና አከራካሪ ጉዳዮች ላይ እየተሰጠ ነዉ ። በተለይም
-Insurance contract formation and related issues, Issue with Insurer's limit of liability under Insurance contract, Denial of liabllity (Defence raised by Insurers), Subrogation Suits and defense raised, Issue related with COMESA Treaty and Insurance related cassation decision ላይ በማተኮር እየተካሄደ ነው።
በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ እመቤት አለማየሁ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በሃገሪቱ የኢንሹራንስ ተቋማት እና አገልግሎት እየተስፋፋ መሆኑን በመግለፅ ስለ ኢንሹራንስ ስራው ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር ከዚህ በፊት ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ጋር የዚሁ አይነት የስልጠና መድረክ ተዘጋጅቶ ከተገኘው ግብአት እና ውጤታማነት በመነሳት እንዲሁም በፍርድ ቤቱ በኩልም በነበረ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ክቡር አቶ ፋዓድ ኪያር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በበኩላቸዉ የስልጠናውን አስፈላጊነት በዝርዝር በመግለፅ ዳኞች ከጠቅላላ የህግ እዉቀት በተጨማሪ ልዩ እዉቀት (specialized Knowledge ) በሚፈልጉ ጉዳዩች ላይ ተከታታይ ግንዛቤ ሊያገኙ እንደሚገባ ገልፀዋል ። በዚህም መርሃ-ግብሩን ላዘጋጁት የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር እና ስልጠናው እንዲዘጋጅ ላስተባበሩት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክብርት ዳኛ ወይዘሮ ሮዛ አበበ ምስጋና አቅርበው ስልጠናውን ከፍተዋል። ስልጠናው በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው አቶ ፈቃዱ ያሚ እና አቶ ጌቱ መልኬ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል።

በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት በተረኛ ችሎት የሚሰሩ ጉዳዬችን ይመለከታል*********የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ከመደበኛ የፍርድ ቤት የ...
04/08/2026

በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት በተረኛ ችሎት የሚሰሩ ጉዳዬችን ይመለከታል
*********
የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ከመደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜ ውጭ አስቸኳይ ጉዳዬች እንደሚስተናገዱ በተደነገገው መሰረት እንዲሁም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑበት ወቅት ለዳኞች ተራ ወጥቶ በሚደርሳቸዉ ተራ መሰረት መደበኛ የፍርድ ቤቱ የስራ ጊዜ የማይጠብቁ አስቸኳይ ጉዳዬች በፍርድ ቤቶች እየታዩ እልባት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ሲሰራ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት መሰረታዊ የመብት ጥሰት የሚያስከትሉ በባህሪያቸው ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱ የስራ ጊዜ እስኪጀመር አፋጣኝነታቸው ታይቶ ዉሳኔ ካልተሰጠባቸው የመብት መጣስን ሊያስከትል የሚችሉ እና ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን አይቶ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑባቸው ጊዜ ማለትም ከነሃሴ 01 ቀን እስከ መስከረም 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በተረኛ ችሎት በወንጀል እና በፍታብሄር ጉዳዮች መደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜን የማይጠብቁ ጉዳዮች አስቸኳይ ጉዳዮች ሲቀርቡ የሚታዩ ይሆናል በዚሁ መሰረት፡- በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎቶች

በፍታብሄር ከሚቀርቡ ጉዳዮች ፡-

➢ አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች
➢ የልጅ ቀለብ
➢ አካል ነጻ ለማውጣት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች
➢ እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች
➢ ሰራተኞች በአሰሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቡት የደመወዝ ክፍያ የሚመለከቱ አፈጻጸም ጉዳዮች
➢ ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ አስቸኳይ የማህተም አገልግሎት ጥያቄዎች (ለእግድ, መጥሪያ ለማድረስ..)
➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የፍታብሄር ጉዳዮች

በወንጀል ከሚቀርቡ ጉዳዮች፡-

➢ ዋስትና
➢ አመክሮ
➢ አርቲዲ (እስረኛ ያለባቸው የሚቀርቡ የወንጀል መዛግብት )
➢ በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች
➢ ጊዜ ቀጠሮ(አራዳ ምድብ ችሎት)
➢ ለመሰየም የሚቀርብ አቤቱታ
➢ እስረኛ ያለባቸው መዝገቦች
➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች

ባጠቃላይ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆንባቸው ጊዜያት መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ የማይጠብቁ ጊዜ የማይሰጡ እና አጣዳፊ የሆኑ የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳዮች በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ መሆኑን በማወቅ ሁሉም የፍርድ ቤቱ ማህበረሰብ እንዲሁም ተገልጋዩ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲወጣ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

Address

Addis Ababa
LIDETASUBCITY

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal First Instance Court Of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Federal First Instance Court Of Ethiopia:

Shortcuts

Share