Ethiopian Health Insurance Service

Ethiopian Health Insurance Service to promote Health Insurance in Ethiopia Ethiopian Health Insurance Service

ከህመም ስጋት ወደ ሙሉ ተስፋ፡ የ70 ዓመቷ ወይዘሮ አብረሀት ገብረ የህይወት ምስክርነት22/12/2018 ዓም ኢጤመአእድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሰውነት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ የተለያዩ ህመሞች ...
28/08/2026

ከህመም ስጋት ወደ ሙሉ ተስፋ፡ የ70 ዓመቷ ወይዘሮ አብረሀት ገብረ የህይወት ምስክርነት
22/12/2018 ዓም ኢጤመአ
እድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሰውነት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ የተለያዩ ህመሞች የመከሰታቸው አጋጣሚ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይም በቋሚ ገቢ ላይ ላልተመሰረቱና ዝቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም ላላቸው አዛውንቶች ድንገት የሚከሰት የጤና መታወክ ህይወትን ለከባድ አደጋ ከማጋለጡ ባሻገር፣ የቤተሰብን ምጣኔ ሀብት ምስቅልቅሉን ያወጣዋል፡፡ ሆኖም ይህንን የህክምና ወጪ ስጋት በዘላቂነት በመቅረፍ ረገድ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ለአያሌ ዜጎች ትልቅ የህይወት አለኝታ እየሆነ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑት የ70 ዓመቷ አዛውንት ወይዘሮ አብረሀት ገብረ፣ የዚሁ ተስፋ ሰጪ ስርዓት እውነተኛ ተጠቃሚ ምስክር ናቸው፡፡
ወይዘሮ አብረሀት ከእድሜ መገፋት ጋር ተያይዞ ከቆዩባቸው የወገብ ህመም፣ የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል ችግሮች ጋር ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ህመሞች ደግሞ ተከታታይነት ያለው የህክምና ክትትልና የመድኃኒት አቅርቦት የሚሹ በመሆናቸው፣ በየጊዜው የሚጠየቀውን የህክምና ወጪ መሸፈን ለእሳቸው እጅግ አታካችና ከአቅም በላይ የሆነ ፈተና ነበር፡፡ "እድሜ ሲገፋ የመስራት አቅም ይቀንሳል፤ የመስራት አቅም ሲቀንስ ደግሞ ገቢ አብሮ ያንሳል" የሚሉት ወይዘሮ አብረሀት፣ በራሳቸው የኢኮኖሚ አቅም ብቻ ተደጋጋሚ የህክምና ወጪዎች መሸፈን እንደማይችሉ በቁጭት ያስታውሳሉ፡፡
ሆኖም የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ያጋጠማቸው የፋይናንስ ስጋት ሙሉ በሙሉ ሊቀረፍ ችሏል፡፡ አሁን ላይ በቅርባቸው በሚገኘው በአብነት የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና መስጫ ማዕከል በመገኘት አስፈላጊውን የህክምና ክትትልና መድኃኒት በሙሉ ጥራትና ያለ ምንም የገንዘብ ስጋት በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
አዛውንቷ ወይዘሮ አብረሀት ስለ ጤና መድኅን ጠቅሜታ ሲናገሩ «ጤና መድኅን ለእኔ ነፍሴ ነው!» በማለት በከፍተኛ ስሜትና ምስጋና ይገልጻሉ። የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል በመሆናቸውና በመደገፋቸው ምክንያት፣ ህይወታቸው ሊረዝምና በሙሉ ጤንነት እንዲኖሩ እንደረዳቸው በደስታ ያስረዳሉ፡፡
ህመም አቅዶና አውጥቶ እንደማይመጣና መቼ እንደሚከሰት የማይታወቅ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ነገን ሳይጠብቅና ጊዜ ሳይሰጥ የአባልነት ምዝገባውን ማጠናቀቅ እንዳለበት ይመክራሉ፡፡
በአጠቃላይ የሦስትዮሽ ትስስር ያለው የማህበረሰብ መደጋገፍ፣ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት እና የዜጎችን ህይወት የመታደግና የማራዘም አቅሙ የጎላ መሆኑን የወይዘሮ አብረሀት ገብረ የህይወት ታሪክ ግልጽ ማረጋገጫ ነው፡፡
"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

28/08/2026
ከካንሰር የተመለሰው ህይወት እና የጤና መድኅን ዋስትና፡ የወይዘሮ አዳነች ረጂብ ተስፋ ሰጪ ጉዞ21/12/2018 ዓም ኢጤመአየጤና ህመም ድንገት ተከስቶ በርን ሲያንኳካ የቤተሰብን ሰላም ከመን...
27/08/2026

ከካንሰር የተመለሰው ህይወት እና የጤና መድኅን ዋስትና፡
የወይዘሮ አዳነች ረጂብ ተስፋ ሰጪ ጉዞ
21/12/2018 ዓም ኢጤመአ
የጤና ህመም ድንገት ተከስቶ በርን ሲያንኳካ የቤተሰብን ሰላም ከመንሳቱ ባሻገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ይዞ ይመጣል። በተለይም በያዝነው ወቅት የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በጣለበት ሁኔታ፣ የታመመን ወገን ማከም ይቅርና ቀላል የሕክምና ወጪዎችን እንኳ መሸፈን ለብዙዎች ፈታኝ ሆኗል። ነገር ግን የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ለእነዚህ ተፈጥሯዊና ድንገተኛ የጤና ተደራሽነት አጥር ለሆኑት ፈተናዎች ትልቅ መፍትሔ እና አስተማማኝ ከለላ እየሆነ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑት የ50 ዓመቷ ጎልማሳ ወይዘሮ አዳነች ረጂብ የዚሁ ህይወት አደጋች መርሃ-ግብር እውነተኛ ማረጋገጫ ምስክር ናቸው።
ወይዘሮ አዳነች የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል ከሆኑበት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እሳቸውን እና የልጅ ልጃቸውን ጨምሮ የሁለት አባላት ያሉት ቤተሰባቸው የአገልግሎቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
ከአሁን በፊት ወይዘሮ አዳነች እጅግ አደገኛ ከሚባሉት የህመም አይነቶች አንዱ በሆነው የማህጸን ካንሰር ህመም ተይዘው በከፍተኛ ስቃይ እና ጭንቀት ውስጥ አልፈዋል። በዚያ ፈታኝ ወቅት የጤና መድኅን መርሃ-ግብሩ በሰጠው የሕክምና እገዛ፣ ሽፋን እና ወጪ የማካካስ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ታክመው ከህመማቸው መዳን ችለዋል። ዛሬ ላይ ቆመው ያንን አስቸጋሪ ጊዜ ሲያስታውሱ፣ የጤና መድኅኑ ባያጋጥማቸው ኖሮ የሕክምና ወጪውን መሸፈን እና ህይወታቸውን ማትርፍ ያን ያህል ቀላል እንዳልነበር በእንባ በተቀላቀለ ደስታ ይናገራሉ።
በአሁኑ ወቅት ወይዘሮ አዳነች የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል ህመም ስለሚገኝባቸው አዘውትረው መድኃኒት መውሰድ ይኖርባቸዋል። አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ የመድኃኒት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ቢመጣም፣ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል በመሆናቸው ምክንያት ያለ ምንም የገንዘብ ስጋት ተገቢውን መድኃኒትና ሕክምና ሳያቋርጡ እያገኙ ይገኛሉ።
ለተደረገላቸው አገልግሎት እና ድጋፍ በሙሉ ከፍተኛ ደስታቸውን የገለጹት ወይዘሮ አዳነች፣ መርሃ-ግብሩ የድሆችና የአነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ እየታደገ እንደሚገኝ መስክረዋል።

ወይዘሮ አዳነች “በሽታ ወይም አደጋ በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ ሊከሰት ስለሚችል አስቀድሞ ዝግጁ መሆን ወሳኝ በመሆኑ አባል መሆን እኛ ባንታመም እንኳ አቅም የሌለውን ሌላውን የታመመ የህብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ የሚያስችል የወንድማማችነት መንገድ ነው፤ በተጨማሪም ብንታመም ደግሞ እንደ ህመማችን አይነት እና ደረጃ ያለ አንዳች የፋይናንስ ስጋት የመታከም መብታችንን ያረጋግጣል።” ብለዋል፡፡
ስለሆነም እያንዳንዱ ዜጋ ሳይዘናጋ እና ጊዜ ሳይሰጥ በአቅራቢያው በሚገኝ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ጽሕፈት ቤት በመቅረብ በፍጥነት እንዲመዘገብና የአገልግሎቱ አባል በመሆን የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት እንዲታደግ ወይዘሮ አዳነች ረጂብ አጥብቀው ይመክራሉ።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከቅርንጫፍና ክላስተር ጽሕፈት ቤቶች ጋር የዕቅድ ማናበብ መድረክ አካሄደ21/12/2018 ዓም ኢጤመአየኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከክላስተርና ከቅር...
27/08/2026

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከቅርንጫፍና ክላስተር ጽሕፈት ቤቶች ጋር የዕቅድ ማናበብ መድረክ አካሄደ
21/12/2018 ዓም ኢጤመአ
የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከክላስተርና ከቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች፣ ከዕቅድ ዝግጅትና ከክትትል ባለሙያዎች ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ሲያካሂድ የቆየውን የዕቅድ ማናበብና የማጣጣም መድረክ አጠናቋል።
የመድረኩን አስፈላጊነት አስመልከተው ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ከፍያለው ሞቲ እንደገለጹት፤ ዕቅድ ዝግጅት አንድ ተቋም ወደየት መድረስ ይፈልጋል? እንዴትስ ይደርሳል? ለሚሉት መሠረታዊ ጥያቄዎች አስቀድሞ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ይገኛል።
አክለውም አቶ ከፍያለው፤ «ውጤታማ ተቋማዊ ዕቅድ የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች መሠረት ያደረገ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን (ጥንካሬ፣ ድክመት፣ መልካም አጋጣሚና ሥጋቶችን) በአግባቡ ያገናዘበና በቁጥር ሊለኩ የሚችሉ (SMART) ስትራቴጂካዊ ግቦችን ያካተተ መሆን አለበት» ብለዋል። በተጨማሪም የበጀትና የሀብት ድልድልን፣ የኃላፊነት ስርጭትን፣ የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን እንዲሁም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሥጋቶችን የመፍትሔ አቅጣጫዎች አስቀድሞ በማስቀመጥ ከሁሉም ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር ማናበብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፈንድና ኢንቨስትመነት ስራ አስፈጻሚ አቶ አዳሙ ወንድምተካሁ በበኩላቸው በጀትና ዕቅድ መጧጣም እንዳለባቸው ጠቁመው ስራውን በቅንጅት፣ በጀቱን ውጤት ማምጣት በሚያስችል ደረጃ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የዕቅድ፣ በጀት፣ ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ለሜሳ በቀለ በእቅድ ዝግጅት ወቅት ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ዋና ዋና ተቋማዊ ጉዳዮችና በቅርንጫፍ/ክላስተር ደረጃ በተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ የማስተካከያ ግብረ-መልስ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አማካሪ አቶ ገነቱ አንተነህ በእቅድ ዝግጅት ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችን በሚሞሉ መሠረታዊ መርሆዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በየደረጃው የሚዘጋጁ ሪፖርቶች በትክክለኛና በተጨባጭ መረጃዎች ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በቀረቡት ገለጻዎችና ሰነዶች ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ተጨማሪ ማብራሪያዎች የተሰጡ ሲሆን፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችና የጋራ መግባባቶች ላይ በመድረስ መድረኩ ፍጻሜ አግኝቷል፡፡"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

አገልግሎቱ የ5 ዓመት የ3ኛ ደረጃ ሆስፒታሎች የማአጤመ ክፍያ ወጪ ትንተና ጥናት ይፋ አደረገ20/12/2018 ዓ.ም ኢጤመአየኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደ...
26/08/2026

አገልግሎቱ የ5 ዓመት የ3ኛ ደረጃ ሆስፒታሎች የማአጤመ ክፍያ ወጪ ትንተና ጥናት ይፋ አደረገ
20/12/2018 ዓ.ም ኢጤመአ
የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 24 የ3ኛ ደረጃ (ከፍተኛ) ሆስፒታሎች ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም የተከናወነውን የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን (CBHI) የተጠቃሚዎች የክፍያ ወጪ ትንተና ጥናት ይፋ አደረገ።
በጥናቱ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ላይ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታል ስራ አስኪያጆች፣ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የክላስተርና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፤ ከ3 ዓመት በፊት 53 ሚሊዮን የነበሩት የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ተጠቃሚዎች በአሁኑ ወቅት ወደ 70 ሚሊዮን አድገዋል። የተጠቃሚው ቁጥር መጨመር ለአገልግሎት ሰጪ የጤና ተቋማት የሚከፈለው ክፍያም በዚያው ልክ እንዲያድግ ማድረጉን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የጥናቱ ውይይት ክፍተቶችን በማሳየት ወደ ተግባር ለመግባት አቅጣጫ በማስያዝ የተጠናከረ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ አመላክተዋል።
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ያምሮት አንዱዓለም ፣ የውይይቱ ዋና ዓላማ በ3ኛ ደረጃ ሆስፒታሎች ለተጠቃሚዎች ለሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች የወጣውን የአምስት ዓመት የህክምና ወጪ አዝማሚያና የወደፊት ትንበያ ለባለድርሻ አካላት ማሰራጨት እንደሆነ ገልጸዋል። ጥናቱ የወጪዎችን መጨመር፣ መንስኤዎቻቸውን፣ በሆስፒታሎች መካከል ያለውን ልዩነት እና የፕሮግራሙን የፋይናንስ ዘላቂነት ፈተናዎች በግልጽ እንደሚያሳይ አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጣዓመ ኣረዶም በበኩላቸው፤ ጥናቱ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል። አያይዘውም ጥናቱ በ3ኛ ደረጃ (ቴርሸሪ) ሆስፒታሎች የሚጠየቀው ክፍያ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ማሳየቱን ገልጸው፣ ይህም ከዳታ አያያዝ ጀምሮ ያሉ አሰራሮችን ለማስተካከልና ለፖሊሲ ውሳኔዎች እንደ መልካም ግብዓት ለማገልገል ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት የፈንድ፣ ሥጋትና ኢንቨስትመንት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አዳሙ ወንድምተካሁን የጥናቱን ዓላማና የመረጃ አሰባሰብ ሂደት ያቀረቡ ሲሆን፤ መረጃው ሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ባካተተ መልኩ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
በመድረኩ የጥናቱን ውጤት ያቀረቡት በኢትዮጵያ ጤና መድኅን የክሌም ማኔጅመንት ባለሙያ ዶ/ር ሱራፌል ጌታቸው እንደጠቆሙት፤ ለከፍተኛ ደረጃ ሆስፒታሎች የሚደረገው የCBHI ወጪ በፍጥነት ያደገ ሲሆን ወደፊትም እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃል። የጤና መድኅኑ መስፋፋት የኅብረተሰቡን የፋይናንስ ጥበቃና የሕክምና ተደራሽነት ያሳደገ ቢሆንም፣ አብሮ ያደገው የወጪ መጠን የፕሮግራሙን ዘላቂነት የሚፈታተን ሆኗል።
ስለሆነም ፖሊሲ አውጪዎች ከመንግሥት ድጎማ ወይም አባላት ከሚያደርጉት መዋጮ ጋር የተጣጣመ የፈንድ ዘላቂነት ማረጋገጥ እንዳለባቸው ዶ/ር ሱራፌል አሳስበዋል። በተጨማሪም የመረጃ ጥራትን ማሻሻልና የሪፈራል ሥርዓቱን በአግባቡ መምራት፣ እያደገ የመጣውን የጤና መድኅን ሥርዓትና ፍትሐዊ የአገልግሎት ተደራሽነት ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

የሕይወት ተስፋ የሆነው ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን፡ የወይዘሮ ብርቄ ለሚ እውነተኛ ምስክርነት20/12/2018 ዓም ኢጤመአበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (...
26/08/2026

የሕይወት ተስፋ የሆነው ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን፡ የወይዘሮ ብርቄ ለሚ እውነተኛ ምስክርነት
20/12/2018 ዓም ኢጤመአ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (ማአጤመ) ፕሮግራም ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በርካታ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና ሽፋን አግኝተው የተስፋ ብርሃን ፈንጥቆላቸዋል። በተለይም በጉልበት ሰርተው መኖር በማይችሉበት የዕድሜ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና ለጽኑ ሕመምተኞች የፕሮግራሙ አስፈላጊነት ወደር የለውም። ከእነዚህ ተጠቃሚዎች መካከል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ብርቄ ለሚ አንዷ ናቸው።
የ67 ዓመቷ አረጋዊት ወይዘሮ ብርቄ ለሚ የ5 ልጆች እናት ሲሆኑ፣ ባለቤታቸውን ከ20 ዓመት በፊት በሞት ካጡ በኋላ ልጆቻቸውን በብዙ ውጣ ውረድ ብቻቸውን አሳድገዋል። በአሁኑ ወቅትም የደም ግፊት፣ የኮሌስትሮል እና የወገብ ሕመም አለባቸው።
ወይዘሮ ብርቄ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በአዲስ አበባ ሲጀመር አባል መሆን የቻሉ ሲሆን፣ የአባልነት መዋጮ መክፈል ስለማይችሉ ወጪያቸው በሙሉ በመንግስት ድጋፍ ይሸፈንላቸዋል። የደም ግፊት፣ የኮሌስትሮል እና የወገብ ሕመም ስላለባቸው በአብነት ጤና ጣቢያ እና በራስ ደስታ ሆስፒታል በተከታታይ ህክምናቸውን ይከታተላሉ፤ በጤና ጣቢያው የተገኙትም መደበኛ የህክምና ክትትል ጊዜያቸው እንደሆነ ይናገራሉ።
በአብነት ጤና ጣቢያ ያጡት የህክምና አገልግሎት እንደሌለ የሚገልፁት ወይዘሮ ብርቄ፣ በተለይም ክትትል የሚያደርጉላቸው ሐኪሞች የሚያሳዩዋቸው እንክብካቤ በጣም የሚያስደስት መሆኑን ያመላክታሉ። በራሳቸው አቅም ከፍለው የጤና መድህን አባል መሆን ስለማይችሉ፣ ከፍለው መታከም ለእሳቸው ጨርሶ የማይታሰብ እንደነበርና ይህ የጤና መድህን ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ሕይወት ታዳጊ መሆኑን ይመሰክራሉ።
ወይዘሮ ብርቄ በግላቸው የጤና መድህን ይዞላቸው የመጣውን ጥቅም መግለጽ እስከሚያቅታቸው ድረስ እንደሚረዱት ይናገራሉ። በዚህ ወቅት የፓራሲታሞል ዋጋ እንኳ ከአቅም በላይ በሆነበት እና እሳቸው ደግሞ እንደበፊቱ ሰርተው ማደር በማይችሉበት ሁኔታ ላይ በሚገኙበት ወቅት፣ የሚሰጣቸውን ህክምና በራሳቸው ወጪ ከፍለው ቢሆን ኖሮ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጨርሶ እንደማያውቁት በቁጭት ያስረዳሉ።
የወይዘሮ ብርቄ ምስክርነት የሚያሳየው ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተራ የህክምና ሽፋን ብቻ ሳይሆን፣ የበርካታ አረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ሕይወት ቀጣይነትና አሁናዊ ዋስትና መሆኑን ነው።"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu

X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X

Address

Nifase Silke Lafto Around Gotera Pepsi , GUAVA Building
Addis Ababa
21254/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health Insurance Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share