Construction Management Institute

Construction Management Institute CMI is a newly established government body with vision to see a sustainable construction industry

በፕሮጀክቶች የሚታዩ የአፈጻጸም ስብራቶችን በመቅረፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ ኢንዱስትሪ መገንባት ዓላማችን ነው ተባለነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. / አዲስ አበባበበፕሮጀክቶች የሚታዩ የአፈጻጸም ...
23/08/2026

በፕሮጀክቶች የሚታዩ የአፈጻጸም ስብራቶችን በመቅረፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ ኢንዱስትሪ መገንባት ዓላማችን ነው ተባለ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. / አዲስ አበባበ

በፕሮጀክቶች የሚታዩ የአፈጻጸም ስብራቶችን በመቅረፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ የግንባታ ኢንዱስትሪ መገንባት ዓላማችን ነው ሲሉ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታማራት ሙሉ ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ ይህን የገለጹት የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር ለተከታታይ 6 ቀናት በፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል (Project Management Professional) ላይ ያተኮረ ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት ነው።

ኢንጂነር ታምራት በንግግራቸው፣ ውስብስብ የሆኑ የሀገራችን ፕሮጀክቶች በብቃት፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲጠናቀቁ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች አሁን በውጭ ተቋራጮች ተይዘው የሚገኙ ሥራዎችን በብቃት ለመረከብ የሚያስችላቸውን አቅም ማሳደግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።በተጨማሪም በግንባታ ዘርፉ የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ስብራቶችን በመቅረፍ በሌሎች የዓለም አገራት እየታየ ያለውን ውጤታማና ተወዳዳሪ የፕሮጀክት አፈጻጸም በሀገራችን ማስመዝገብ የኢንስቲትዩቱ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስለሆነም ሰልጣኞች በዚህ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ የግንባታ ኢንዱስትሪ ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት በእውቀትና በተግባር ማገዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በሌላ በኩል፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በመወከል በስነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአቅም ግንባታና አሠራር ሥርዓት ዳይሬክተር ወ/ሮ ማናለብሽ ዳኘው ናቸው።ወ/ሮ ማናለብሽ ባደረጉት ንግግር፣ የተቋሙን አመራሮችና ባለሙያዎች በዘመናዊ የፕሮጀክት አመራር ብቁ ለማድረግ ታስቦ ስልጠናውን ላዘጋጀው ኢንስቲትዩት ምስጋና አቅርበዋል።

የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ የሚመሩትን ፕሮጀክቶች ዘመናዊ የፕሮጀክት አመራር መርሆችን በመከተል ውጤታማ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም እያንዳንዱ ሰልጣኝ ራሱን በማዘጋጀት በሥራ ላይ ውጤታማ ተግባር መፈጸም እንዳለበት አሳስበዋል።
“ይህን በማድረግ ከዘመኑ ጋር መራመድ ይቻላል” በማለትም ገልጸዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ሰልጣኞችም የተሰጣቸው ስልጠና ጥሩ ግንዛቤ ያስጨበጠና ለሥራቸው ጠቃሚ የሆነ እውቀት ያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም የስልጠናው ጊዜ አጭር መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት የዕለቱ መርሐ ግብር ፍጻሜውን አግኝቷል።

በተቋም ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ችግኝ ተተከለነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. / ሰንዳፋየኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል...
21/08/2026

በተቋም ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ችግኝ ተተከለ

ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. / ሰንዳፋ

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ሰንዳፋ ቤከ እያስገነባ በሚገኘው የኢንጅነሪንግና ምሕንድስና ልዕቀት ማዕከል ግቢ ችግኝ ተከሉ።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የተቋሙ ሠራተኞች እንደገለጹት፣ ይህ በ2018 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሲሆን፣ ይህን ልዩ የሚያደርገው ግን በተቋሙ የራሱ ግቢ ውስጥ መካሄዱ ነው።

በተጨማሪም የተተከሉት ችግኞች ከተተከሉበት ዕለት ጀምሮ በተቋሙ ሠራተኞች እንክብካቤ እንደሚደረግላቸውና ጸድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እስኪደርሱ ድረስ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራው እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ የተተከሉት ችግኞች ወደ 1,000 የሚጠጉ ሲሆኑ፣ በአብዛኛው ለምግብነትና ለጥላነት የሚውሉ የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶች መሆናቸው ታውቋል።

ስልጠናው ስንቅ ሆኖልናል አሉ ሰልጣኞችነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ“ስልጠናው ለሥራችን የሚያግዘን እውቀትና ልምድ የሰጠን ስንቅ ሆኖልናል” ሲሉ ሰልጣኞች ገለጹ።ይህን የገለጹ...
20/08/2026

ስልጠናው ስንቅ ሆኖልናል አሉ ሰልጣኞች
ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ

“ስልጠናው ለሥራችን የሚያግዘን እውቀትና ልምድ የሰጠን ስንቅ ሆኖልናል” ሲሉ ሰልጣኞች ገለጹ።

ይህን የገለጹት የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከየኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር በመተባበር ለ8 ተከታታይ ቀናት በOrganizational Project Management, Leadership እና Communication & Stakeholder Management ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ላይ ነው።

ሰልጣኞቹ በሰጡት አስተያየት፣ የስልጠናው ርዕሰ ጉዳዮች ከሥራቸው ጋር ተያያዥ መሆናቸው፣ ስልጠናው በወሳኝ ወቅት መሰጠቱ እና በልምድ በበለጸጉ አሰልጣኞች መሰጠቱ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ እንዲያገኙ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። በተለይም በሳይት ላይ ለሚሰሩ አመራሮችና ሙያተኞች ተግባርንና ንድፈ ሐሳብን ባጣመረ መልኩ መሰጠቱ ለሥራቸው ወሳኝ ተሞክሮ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱና የመንገዶች አስተዳደር አመራሮችም በሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ፣ ማብራሪያ እንዲሁም የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሁሉንአየሁ ወጂ እንደገለጹት፣ የመንገዶች አስተዳደር የበለጸገ ዕውቀትና ልምድ ያለው ተቋም ቢሆንም፣ በየወቅቱ በሚለዋወጠው ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪና ውጤታማ አመራር ለመሆን ቀጣይነት ያላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይም የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM) በመንገድ ዘርፍ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሜ ዝግጅቶች እየተደረጉ በመሆኑ፣ ለዚህ የሚያስፈልግ አቅም ለመፍጠር ከዚሁ አመራር ጋር በመተባበር የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ውጤት ለማምጣት ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ሰልጣኞቹም ለዚህ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የመንገዶች አስተዳደር የመንገድ ሀብት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አየለ፣ ስልጠናው አስፈላጊና ዘመናዊ እውቀትን የሚያላብስ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በቀጣይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።

የኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ቅድስት ማሞ በበኩላቸው፣ ተወዳዳሪና ውጤታማ ለመሆን ተግባርን መሠረት ያደረጉ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የተሰጠው ስልጠና ሰልጣኞቹ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤት እንዲያመጡ እንደሚያግዝ ተስፋቸውን ገልጸዋል። በስልጠና አሰጣጥ ሂደት ላይ የተነሱ ጉዳዮችም በቀጣይ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስገንዝበዋል።

የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት ደግሞ የመንገዶች አስተዳደር የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ብርሃኑ ተስፋዬ ናቸው። እንደገለጹት፣ በተለያዩ ፕሮጀክቶች በተደረገ ዳሰሳ መሠረት በአመራር፣ በተቋማዊ ፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በደንበኞች አያያዝና በተግባቦት ላይ ክፍተቶች መኖራቸው በመገንዘቡ ስልጠናው በተለያዩ ዙሮች እንዲሰጥ መወሰኑን ጠቁመዋል።
“ከስልጠናው ብዙ እውቀት እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ” ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ፣ በቀጣይም በሥራ ቦታ ያሉ ፈጻሚዎችን በማብቃትና በመካከላቸው ተመሳሳይ አረዳድ በመፍጠር ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ለተከታተሉ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት የዕለቱ መርሐ-ግብር ተጠናቋል።

ኢንስቲትዩቱ በሙያ ደረጃዎች፣ የብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀመረነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከኮንሶል ኃ/የ...
19/08/2026

ኢንስቲትዩቱ በሙያ ደረጃዎች፣ የብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀመረ

ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ

ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከኮንሶል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በመተባበር Occupational Standards, Competence Assessment & Certification ላይ ያተኮረ የሁለት ቀናት ስልጠና ለኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች መስጠት ጀመረ።

ስልጠናው ዓላማው ተሳታፊዎች በሙያ ደረጃዎች፣ በሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ሥርዓት ላይ ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኙና ሥርዓቱን በኢንዱስትሪው ውስጥ ተግባር ላይ እንድውል የሚያስችላቸውን አቅም እንዲያዳብሩ ለማስቻል ነው።

በስልጠናው መድረክ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ቅድስት ማሞ እንደገለጹት፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ፣ ውጤታማና ከኢንዱስትሪው የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ በተገቢው ሁኔታ እንዲያበረክት የዘርፉ የሙያ ብቃት በምዘና ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

ይህንንም ለማሳካት ኢንስቲትዩቱ በኮንሶል ኃ/የተ/የግ/ማህበር አማካሪነት የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘና እና ሰርተፊኬሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ላይ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ለሥርዓቱ ተግባራዊነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ስልጠናው መዘጋጀቱንም አስረድተዋል።

ስልጠናው በኮንሶል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ሲሆን፣ በዋናነት የሚከተሉትን ጉዳዮች ዳስሷል፦

Overview of Bodies of Knowledge
Overview of Professions/Disciplines National Occupational Standards
Professionals’ Competence Assessment & Certification System Implementation Manual
Education Accreditation, Competence Assessment and Registration

በስልጠናው ላይ ወደ 25 የሚጠጉ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ከመርሐ-ግብሩ መረዳት ተችሏል።

በፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል (PMP) ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ተጀመረነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባየኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት  ግ...
17/08/2026

በፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል (PMP) ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ተጀመረ
ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል (Project Management Professional—PMP) ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

የስልጠናው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሚድሮክ ኢትዮጵያ አመራሮች ዶ/ር ልዑል አስራቴ፣ የሚድሮክ ኮንሰልት አርክቴክቸር & ኢንጅነርስ ጀነራል ማኔጀር፣ እና ኢ/ር ወልደ በርሄ፣ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ. ፥ ፥፥፥
ጀነራል ማኔጀር፣ በመልዕክታቸውም የፕሮጀክት አመራር ዘይቤ ከቀድሞው በእጅጉ የተለወጠ በመሆኑ፣ በቀድሞ አሠራር መቀጠል ተወዳዳሪ፣ ውጤታማና ደንበኛን ማርካት የቻለ ፕሮጀክት ለማስፈጸም እንደማያስችል ገልጸዋል።

በመሆኑም ዘመናዊ የፕሮጀክት አመራር ዘዴዎችን መከተል አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የግድ እንደሆነ አመራሮቹ አስገንዝበዋል። ይህንንም ለማሳካት በፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል ስልጠና መውሰድና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ይህንን በመገንዘብ ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ በመከታተል፣ እውቀትና ክህሎታቸውን በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያውቁበትን የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አመራሮቹ አበክረው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ ኢንስቲትዩቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሻሻል በዘርፉ ለተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ያደረጉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሆኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ገልጿልኢ/ር ቤዛዊት ጌታቸው ( በኢንስቲትዩቱ የስልጠናና ብቃት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈጻሚ) ተናግሯል። ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ስልጠናዎች መካከልም የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል (PMP) አንዱ መሆኑን ጠቅሷል።

ስልጠናውም የዘርፉ ፕሮጀክቶች በተቀላጠፈ፣ በውጤታማና በተወዳዳሪ ሁኔታ እንዲመሩና እንዲፈጸሙ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው አያይዘው ገልጿል።

በስልጠናው መድረክ ላይም ከሚድሮክ ኢትዮጵያ የተውጣጡ 25 አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ስልጠናውም ለ6 ተከታታይ ቀናት በተለያዩ አሰልጣኞች የሚሰጥ መሆኑን ከወጣው መርሐ ግብር ማወቅ ተችሏል።

ኢንስቲትዩቱ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን ማጠቃለያ ሪፖርት ለገምጋሚ ኮሚቴ አቀረበአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኮማኢ) — የኮንስትራ...
13/08/2026

ኢንስቲትዩቱ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን ማጠቃለያ ሪፖርት ለገምጋሚ ኮሚቴ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኮማኢ) — የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በዌቭ ሁለት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን ለመተግበር ባለፈው አንድ ዓመት ሲያከናውናቸው የቆዩ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን የሚያጠቃልል ሪፖርት ለገምጋሚ ኮሚቴ አቀረበ።

ማጠቃለያ ሪፖርቱ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሚመራውና ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ የገምጋሚ ኮሚቴ አባላት ፊት የቀረበ ሲሆን፣ ኢንስቲትዩቱ ሪፎርሙን በተቋሙ በተገቢው ሁኔታ ለመተግበር በዝግጅት ምዕራፉ ያከናወናቸውን ተግባራትና ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በሰነዶች በማስደገፍ አቅርቧል።

በዚህም ኢንስቲትዩቱ የሪፎርሙን ተግባራት በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም የተለያዩ ኮሚቴዎችና ንዑስ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ያከናወናቸውን ሥራዎች፣ የተዘጋጁ ሰነዶችን እና የተወሰዱ ርምጃዎችን በዝርዝር አቅርቧል።

የገምጋሚ ኮሚቴው አባላትም የቀረበውን ሪፖርትና ማስረጃዎች በጥሞና በመገምገም፣ የተጠቃለለ ግብረመልስ በቀጣይ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። በእስካሁኑ የሪፎርም አፈጻጸም ሂደት የተከናወኑ ሥራዎች ጥሩና ተምሳሌታዊ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የኢንስቲትዩቱ አመራሮች በበኩላቸው፣ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጡና የተቋማትን አፈጻጸም እንዲያሻሽሉ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
በተለይም በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሻለ ሁኔታ እንዲወጣ ለማስቻል ሪፎርሙ የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑን በመጠቆም፣ የሪፎርም ሥራዎች በቁርጠኝነት እየተተገበሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

አመራሩ አክሎም፣ ከገምጋሚ ኮሚቴው የሚሰጠውን ግብረመልስ መነሻ በማድረግ ያሉትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን በመሙላትና ተገቢውን ማሻሻያ በማድረግ የተሳካ የሪፎርም ሂደት ለማስፈጸም ኢንስቲትዩቱ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በጤናና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ የሥልጠና መርሐ ግብር ተጠናቀቀነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባኢንስቲትዩቱ ከአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ባለሥልጣን...
11/08/2026

በጤናና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ የሥልጠና መርሐ ግብር ተጠናቀቀ

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ

ኢንስቲትዩቱ ከአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ጋር በመተባበር፣ በከተማ አስተዳደሩ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በጤናና ደህንነት (Health and Safety) አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና አጠናቋል።

በማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሁሉንአየሁ ወጂ፣ ተቋሙ ተግባርን መሠረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለዘርፉ ተዋናዮች ሲሰጥ መቆየቱን ተናግሯል። በኮንስትራክሽን ጤናና ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍም ከተለያዩ የዘርፉ ተቋማት ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ሥልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ የኢንስቲትዩቱ ግብ ሥልጠና መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ በሥልጠናው የተገኘው ዕውቀት በፕሮጀክቶች ላይ በተግባር እንዲውል ማድረግ ነው ብለዋል። በዚህም በጤናና ደህንነት ጉድለት ምክንያት በዘርፉ ተዋናዮችና በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ የሚደርሱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መቀነስ እንደሚቻልም ገልጸዋል።

በመሆኑም የሥልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙትን ዕውቀት ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በተግባር እንዲያውሉ፣ እንዲሁም በቀጣይ የዚህ ፕሮግራም አምባሳደሮች በመሆን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር የመጡት የማኅበሩ ቦርድ ዋና ፀሐፊ ኢ/ር ሰለሞን አለማየሁ በበኩላቸው፣ የሥልጠናው የመጨረሻ ዓላማ ሥልጠናውን መጨረስ ሳይሆን፣ በሚገነቡ ፕሮጀክቶች ላይ በጤናና ደህንነት አጠባበቅ ጉድለት ምክንያት የሚከሰቱ የአካል ጉዳትና የሕይወት መጥፋት አደጋዎች ሳይከሰቱ፣ ፕሮጀክቶቹ ለማኅበረሰቡ አገልግሎት ሲሰጡ ማየት መሆኑን ገልጸዋል። “የመጨረሻ እርካታችንም ይህ መሆን ይኖርበታል” በማለት ተናግሯል።

የሥልጠናው ተሳታፊዎችም ሥልጠናው ከዕለት ተዕለት ሥራቸው ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ከትምህርት ቤት የቀሰሙትን ዕውቀት በተግባር ላይ ለማዋል የሚታዩ ግድየለሽነቶችንና የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ሥልጠናው ጠቃሚ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በቀጣይም ይህንን ሥልጠና ላላገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች በተከታታይ መሰጠቱ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ከጤናና ደህንነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ከመቅረፍ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ የጤናና ደህንነት ጉዳቶች በአጭርና በረጅም ጊዜ ሊያስከትሉ የሚችሉት አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ የተማሩትን የጤናና ደህንነት አጠባበቅ ሥርዓት በተግባር ማዋል እንደሚገባ ከገጠማቸው የሥራ አደጋ በመነሳት አስተያየት ሰጥተዋል።
“ችግሩ በመጀመሪያ የሚጎዳው የዘርፉን ባለሙያ በመሆኑ፣ ለራሳችን ሲባል በሥልጠናው መሠረት የጤናና ደህንነት አጠባበቅ ሥርዓቱን በተግባር በማዋል ግንባር ቀደም በመሆን በቁርጠኝነት መሥራት ይኖርብናል” ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ስልጠና መስጠት ጀመረሰኔ 19 ቀን 2018ዓ.ም. አዳማየኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  ከሁሉም ክልሎች...
26/06/2026

ኢንስቲትዩቱ ስልጠና መስጠት ጀመረ
ሰኔ 19 ቀን 2018ዓ.ም. አዳማ

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ፕሮጀክቱን እየተገበሩ ላሉ የፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ቅድስት ማሞ ናቸው፡፡ በንግግራቸውም ኢንስቲትየቱ ዘርፉ ላየ ሚታዩትን የጥራት፣ ከተያዘለት ወጪ በላይ የመጠየቅና በጊዜ ያለመጠናቀቅ ችግሮችን በመቅረፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡፡

የመንገድ ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራሙ በታቀደው መሠረት በተቀደው ጥራት፣ወጪና ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ለፕሮግራሙ ተዋናዮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተናግሮ ይኼውም ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያየዘውም ፕሮጀክቱ ለሀገራችን ማህበረ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጾኦ የሚያበረክት በተለይም መንገድ አንደ ደም ሥር የሚታይ በመሆኑ ይህንን በተገቢው ሁኔታ በመፈጸም ከግብ እንዲደርስ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም የፕሮጀክቱ አመራሮች በዚህ መድረክ ላይ የተገኙ ስለሆነ ፕሮጀክቱን በየደረጃው ለመፈጸም አዳጋችና የሆኑት ጉደዮችን በማንሳት ምላሽ ማግኘት እንደሚቻልም አሳስበል፡፡

በዚህ ስልጠናም የፕሮግራሙ አፈጻጸም የደረሰበት ደረጃ፣ በጀት ማኔጅመንት ሁኔታው፣ የፋይናንስ ማኔጅመንት እና በመሳሰሉት ላየ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ ሲሆን መሆኑን ከመርሐ-ግብሩ መረዳት ተችሏ፡፡

በፕሮግራሙ ሁሉም ክልሎችና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የታቀፉበት እና ከፈዴራል ተቀማት የተካተቱበት ሲሆን በዚህ ፕሮግራምም ከ10 ሺ ኪሎሜትር በላይ የመንገድ ጥገና፣ 7ሺ አዳዲስ የገጠር መንገድ፣ 375 የተለያዩ ተንጠልጣይ ድልድዮችና 715 calverts በመገንባት የመንገድ ተደራሽነቱንና ትስስሩን በማጠናከር የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ ታስቦ የተቀረጸ ፕሮግራም ነው፡፡

ባለስልጣኑ ስለ BIM  ቴክኖሎጂው አስፈላጊነት በመረዳት በዘርፉ ጥቅም ላይ እንዲውል በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑ ተገለጸሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም አምቦይህም የተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ከኦሮሚያ...
25/06/2026

ባለስልጣኑ ስለ BIM ቴክኖሎጂው አስፈላጊነት በመረዳት በዘርፉ ጥቅም ላይ እንዲውል በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም አምቦ
ይህም የተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና አምቦ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖችና ከተሞች ለተውጣጡ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች ለተከታታይ 16 ቀናት BIM ቴክኖሎጂ ላይ በማተኮር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡

ይህንንም ያሉት የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ታምራት ሙሉ ናቸው፡፡
በንግግራቸውም ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በዘርፉ የሚታዩትን የጥራት ጉድለት፣ በታቀደለት ጊዜ ያለማጠናቀቅና ከታሰበው ወጪ የመጠየቅ ችግሮች ለመቅረፍ እና የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ቴክኖሎጂው በዘርፉ ጥቅም ላይ እንድውል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ ጥቅም ላይ እንድውል ለተለያዩ ክልሎች፣ ዩንቨርሲቲዎችና የዘርፉ ተቋማት ድጋፎች ቢደረጉም የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ግን ከሌሎች በተሻለና በላቀ መልኩ ቴክኖሎጂው በዘርፉ ጥቅም ላይ እንድውል በስፋት እየሰራበት ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህም አመራሩም ለኢንዱስትሪው ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት እንዲሻሻል ያለውን በጎ አመለካከትን የሚያመላክት ነው በማለት ተናግሯል፡፡ ሁሉም ባለው አቅም በዚህ መልኩ በቅንጅት በመሥራትና ለውጤት መብቃታችን ለማንም ሳይሆን ለጋራ ግባችን የሆነው የሀገራችን ልማት መሆኑን በመረዳት በቀጣይም ከዚህ በበለጠ መሥራት ያስፋልጋል ብለዋል፡፡
የባለሥልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሌንሳ መርጋ በበኩላቸው ሰልጣኙ ስልጠናውን በዚህ መልኩ በትኩረት በመከታተል ማጠናቀቁ ቴክኖሎጂውን ውጤታማ በሆነ መልኩ መሬት ላይ ለማውረድ ያላችሁን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል፡፡ መሰልጠን ግብ አይደለም ያሉት ኃላፊዋ ከዚህ በፊት ለ3 ዙር ስልጠና ወስደው ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ካሉት እንደነ ሻሸማኔ ከተማ ከዚህ እንደተመለሳችሁ ከዞኖቹ አመራሮችና ከከተማ ከንቲባዎች ጋር በመነጋገርና ግብዓት በማሟላት ቴክኖሎጂውን በኢንዱስትሪው ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ ባለስልጣኑና ኢንስቲትዩቱም የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው በመግለጽ፡፡

ስልጠናውን የሰጠው የአምቦ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ባይሳ ለታ በበኩላቸው ዩንቨርሲቱ በዘርፉ ከነነበረው በበለጠ ሚናውን እንድወጣ በማመን ይህን ስልጠና እንድንሰጥ ላደረጋችሁት እናመሰግናለን እንኳንም ወደ ውብቷ አምቦ ከተማ መጣችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በቀጣም ከዚህ በበለጠ ሰልጣኞችን በማፍራት ለኢንዱስትሪው እናበረክታለንም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ለተከታተሉት ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት እንዱም ከሰልጣኙ ለአሰልጣኞቹ የተበረከተውን ስጦታ በመስጠት የመርሐ-ግብሩ ፊጻሜ ሆነዋል፡፡




ኢንስቲትዩቱ በጤናና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረሰኔ 17 ቀን 2018ዓ.ም(ኮማኢ)በዚህ ለ3 ቀናት በሚቆየው ስልጠና ላይ ከተለያዩ ተቋማትና የዘርፉ ማህበራት የተውጣጡ የዘርፉ...
24/06/2026

ኢንስቲትዩቱ በጤናና ደህንነት አጠባበቅ ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ

ሰኔ 17 ቀን 2018ዓ.ም(ኮማኢ)

በዚህ ለ3 ቀናት በሚቆየው ስልጠና ላይ ከተለያዩ ተቋማትና የዘርፉ ማህበራት የተውጣጡ የዘርፉ ተዋናዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢንስቲትዩቱ የስልጠና አስተባባሪ ኢንጅነር ወርቅነ ጅሩ ናቸው፡፡ በንግግራቸውም ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆዬ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የስልጠናው አስፈላጊነትንም ሲጠቅሱ በዘርፉ የጤናና የደህንነት አጠባባቅ ጉዳይ በዘርፉ ባለሙያዎችች፣ በአከባቢው በሚገኙ ማህበረሰቦች ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተሉ የሚገኙ እና በኮንስትራክ ኢንዱስትሪው ላይ ደግሞ በተፈለገው ልክ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የዘርፉ ተዋናዮች ስለጉዳዩ አሳሳቢነት እንድረዱና ግንዛቤ እንድወስዱ በማስቻል በቀጣ በስራ ቦታቸው ችግሮቹን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን እንድቀርፉና ተወዳዳሪና ብቁ ኢንዱስትሪ ከመፍጠር አንጻር የተቀመጠው ግብ እንድሳካ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናውም ከሥራ ተቋራጮች ማህበር እና ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባባር በተከታታይ ዙሮች እየተሰጠ የሚገኘው አካል አንዱ መሆኑን ለማራጋገጥ ተችሏል፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Construction Management Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share