Kolfe woreda nine prosperity

Kolfe woreda nine prosperity Building a brighter future for Kolfe through economic growth, social equity, and community development

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09  "መሰረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን" በሚል መሪ ቃል የ201...
05/09/2026

ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 "መሰረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን" በሚል መሪ ቃል የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የበዓል ገበያ በተከፈተ ባዛር ።

የበዓል ገበያው የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል እና የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ያለመ ሲሆን፤ ይህም አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ተግባራት አንዱ እና ተጠናክሮ የቀጠለ ውጤታማ ስራ ነው።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው የበዓል መጠቀሚያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን፤ ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጪ ለማዳን የገበያ ማዕከላት ጭምር የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋትና በጥራት እየቀረቡ ይገኛሉ።




ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
04/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

01/09/2026
 !!በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ እና የገበያ ማረጋጋት ሥራዎችን እውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። በወረዳችን በሚገኙ የቅዳሜና እ...
29/08/2026

!!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ እና የገበያ ማረጋጋት ሥራዎችን እውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። በወረዳችን በሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት የዛሬው ዕለት የምርት አቅርቦት በታላቅ ድምቀት ቀጥሏል።

በገበያ ማዕከሎቹ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች እና የሸማቾች ማህበራት ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለህብረተሰቡ ያቀረቡ ሲሆን፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶች ለተጠቃሚዎች እየቀረቡ ይገኛሉ። ነዋሪዎችም በአካባቢያቸው በሚገኙ ማዕከላት በመሸመታቸው የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ብክነትን ማስቀረት ችለዋል።




27/08/2026
25/08/2026
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ፋይናንስ ተቋማት አስተባባሪነት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆ...
21/08/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ፋይናንስ ተቋማት አስተባባሪነት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የአቅመ ደካሞች እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት እድሳትና ግንባታ ፕሮግራም በከፍተኛ ንቅናቄ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የዚሁ የበጎ አድራጎት ስራ አካል የሆነው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በወረዳ 09 አስተዳደር በተካሄደበት ወቅት የክፍለ ከተማው ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ተሾመ፣ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱራህማን ክብረት፣ የክፍለ ከተማና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም የልማት አጋሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

ይህ በክፍለ ከተማው ፋይናንስ ተቋማት አስተባባሪነት እና በአቻ ሁለገብ ኮንትራክሽን የግል ማህበር አጋርነት የሚከናወነው የቤት ግንባታ፤ የአረጋውያንን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ የሀገር ባለውለታዎችን እና የዝቅተኛውን ማህበረሰብ ክፍል የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ነው:: ክፍለ ከተማው በ2018/2019 የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን በአዲስ መልክ በመገንባትና በመጠገን የዜጎችን እንባ ለማበስና ማህበራዊ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።




!!

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 09 አስተዳደር "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ተግባራት አንዱ የሆነው የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ መርኃ ግብር ተከናወነ፡፡    ...
19/08/2026

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 09 አስተዳደር "በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ተግባራት አንዱ የሆነው የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ መርኃ ግብር ተከናወነ፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱራህማን ክብረት፣ የወረዳው የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሌክሳንደር ዝናቡ፣ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ናፊያድ ከበደ እንዲሁም የወረዳው አመራሮች፣ አባላትና አመራሮች በተሟላ ሁኔታ ተገኝተዋል።

በወረዳው በእቅድ ተይዘው ከሚተገበሩ የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሮች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የቤት ግንባታ አቅመ ደካማ፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችንና ለሃገር በጎ ያበረከቱ ባለውለታዎችን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን መርኃ ግብሩ የአብሮነት፣ የመተሳሰብና ተባብሮ የመኖር እሴትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፡፡




Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe woreda nine prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kolfe woreda nine prosperity:

Shortcuts

Share