Federal Ethics and Anti-Corruption Commission

Federal Ethics and Anti-Corruption Commission Federal Ethics and Anti-Corruption Commission
(1)

የጥቆማመስመር ስልክ =0115533852 ወይም 0935947533
Youtube:https://www.youtube.com/channel/UCO_WiCAiDIkMMwqsZGK47nw/?guided_help_flow=5/
Twitter: https://twitter.com/EthiopiaFeacc
Facebook: https://www.facebook.com/feaccOfficial/
Telegram: https://t.me/feacc
Asset registration and Declaration: https://feaccdars.gov.et

ሙስናን ለመታገል የተጀመሩ እርምጃዎች ዘላቂነት ባለው መልኩ ሊጠናከሩ ይገባል ***************(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀገሪቱ የጀመረችውን አጋዥ እና...
05/09/2026

ሙስናን ለመታገል የተጀመሩ እርምጃዎች ዘላቂነት ባለው መልኩ ሊጠናከሩ ይገባል

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) ሀገሪቱ የጀመረችውን አጋዥ እና ተስፋ ሰጪ የልማት ጉዞ ለማስቀጠል ብሎም የህዝብ ሀብት እንዳይባክን ለመከላከል የሚደረገው የሙስና እና የብልሹ አሰራር ትግል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የህግ ባለሙያና አማካሪው ግርማ መኮንን(ዶ/ር) ገለጹ።

ግርማ(ዶ/ር) ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ሙስና ዓለም አቀፍ በሽታ መሆኑን ጠቅሰው፡ ሀገራት የራሳቸውን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የመከላከል ስልቶችን እንደሚከተሉ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያም በቅርቡ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን የጠቆሙት የህግ ባለሙያው፣ የተጀመሩት በጎ ስራዎች የበለጠ ዘላቂነት እና ተከታታይነት ሊኖራቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ባለሙያው ሙስና ማለት ገንዘብ መቀበል ወይም መስጠት ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው፤ አገልግሎት ፈላጊን ማንገላታት፣ ውሳኔ ሳያገኙ ማመላለስ እንዲሁም ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት አለመስጠት ትልቁ የሙስና መገለጫ መሆኑን አስረድተዋል።

መንግስት አሰራሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ እና ግልጽነት ያለው አሰራር ለመዘርጋት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት ግርማ(ዶ/ር)፤ በተለይም በቅርቡ የተዘረጉት የዲጂታል እና የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ብልሹ አሰራርን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ በመሆናቸው ተስፋፍተው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሙስና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያዛባና የሀገርን ሰላም የሚያናጋ በመሆኑ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለማስቀረት ከቤተሰብ እና ከትምህርት ቤት ጀምሮ በትውልዱ ላይ የሥነምግባር እና የሀገር ፍቅር ግንዛቤን ማጎልበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በዘርፎች የ2018 የእቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሄደ***************(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም) የፌዴራል የሥነምግባር እና...
05/09/2026

በዘርፎች የ2018 የእቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት ተካሄደ

***************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 30/2018 ዓ.ም) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ እሸቴ አስፋው፣ ሙስናን ለመከላከል እያንዳንዱን አገልግሎት አሰጣጥ ከሰው እጅ ንክኪ ነፃ በማድረግ አሠራሮችን ወደ ዲጂታል ማሸጋገር እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሙስና መከላከል ሥራን ውጤታማ ለማድረግም ከፍትሕ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ጠቁመው፣ በተለይም ከፍትሕ ሚኒስቴርና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር የጀመረውን የቅንጅት አሠራር እንደሚጠናከር ተናግረዋል።

የሚካሄዱ ጥናቶችና የሚሰጡ ሥልጠናዎች ችግር ፈቺ መሆን እንዳለባቸውም አቶ እሸቴ ጠቁመው፣ በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በ2019 በጀት ዓመትም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው፣ ሙስና የአመለካከትና የአስተሳሰብ ችግር መሆኑን በመገንዘብ፣ መልካም ሥነምግባርን በመላበስና ለሕግ ተገዥ በመሆን ሙስናን መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን የተቋማት አመራሮች የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን ማገዝ አለባቸው ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የሥነምግባር ሥራ አስፈፃሚዎችም የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው ገልጸው፣ የአንድ ዕቅድ፣ የአንድ ሪፖርት መርህን በመከተል መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም፣ የዓመቱ የሱፐርቪዥን ሥራና የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በተጨማሪም የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማነት የሚያግዝ በሥራ ቦታ ሥነምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በግምገማው የተሳተፉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች፣ የሕዝባዊ ድርጅቶችና ተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች ሀሳብ፣ ጥያቄና አስተያየቶችን አቅርበዋል። በተነሱት ጉዳዮችም ላይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ሌብነት ክፉ ሥር ነው፤ እየሰረቁ ሀገር ማልማት አይቻልም፤ ሌቦች ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ብር ታከማቻላችሁ እንጂ አትበሉትም!**************************ትውልድን በሥነምግባር...
05/09/2026

ሌብነት ክፉ ሥር ነው፤ እየሰረቁ ሀገር ማልማት አይቻልም፤ ሌቦች ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ብር ታከማቻላችሁ እንጂ አትበሉትም!

**************************

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት እየተካሄደ ነው ******************(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም)...
04/09/2026

በዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

******************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ግምገማዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የግምገማዊ ውይይቱ ዓላማ በ2018 በጀት ዓመት በዘርፎች የተከናወኑ የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴዎችን፣ የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ሥራ ውጤቶችንና የእቅድ አፈፃፀሙን መገምገም እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት እቅድን በመወያየት የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።

በመድረኩ የዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም፣ የዓመቱ የሱፐርቪዥን ሥራ እና የፀረ-ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

በግምገማዊ ውይይቱ የ2018 በጀት ዓመት የታዩ ጠካራ ጎኖችና ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ ሊሰጥ የሚገባው የትኩረት አቅጣጫ በመለየት ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ በሥራ ቦታ ሥነምግባር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እንደሚሰጥ በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

በግምገማዊ ውይይቱ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነሮችና የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች፣ የሕዝባዊ ድርጅቶችና ተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ሌብነት ጠቃሚ አይደለም፤ ማስረጃ ማግኘት በህግም በአስተዳደርም ርምጃ ለመውሰድ ያግዛል፤ ሌብነት ክፉ መሆኑን አምነን መጀመሪያ ራስን መታገል አልፎ ሲሄድ ደግሞ በህግ የሚያስጠይቅ ማስረጃ መያ...
03/09/2026

ሌብነት ጠቃሚ አይደለም፤ ማስረጃ ማግኘት በህግም በአስተዳደርም ርምጃ ለመውሰድ ያግዛል፤ ሌብነት ክፉ መሆኑን አምነን መጀመሪያ ራስን መታገል አልፎ ሲሄድ ደግሞ በህግ የሚያስጠይቅ ማስረጃ መያዝ ጠቃሚ ይሆናል!

**********************

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...።

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በስህተት ወደ አካውንቱ የገባውን 300 መቶ ሺህ ብር በታማኝነት ለባለቤቱ የመለሰው ወጣት ምስጋና ተቸረው***************************(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ...
01/09/2026

በስህተት ወደ አካውንቱ የገባውን 300 መቶ ሺህ ብር በታማኝነት ለባለቤቱ የመለሰው ወጣት ምስጋና ተቸረው

***************************

(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሙዱላ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ስጦታ ወ/የሱስ በስህተት ወደ ንግድ ባንክ አካውንቱ የገባውን 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር በታማኝነት ለባለቤቱ ተመላሽ በማድረጉ ምስጋና ተቸረው።

ወጣት ስጦታ ገንዘቡ ከማያውቀው ሌላ አካውንት ወደ አካውንቱ መግባቱን እንዳረጋገጠ የገንዘቡን ባለቤት ለማፈላለግ በአካባቢው በሚሰራጩ የሚዲያ ተቋማት አማካኝነት ገንዘቡ በትክክለኛው አካውንቱ ሲላክለት ተመላሽ እንደሚያደርግ የሚገልጽ አጭር ቪዲዮ በመስራትና የጽሑፍ መረጃዎችን በማሰራጨት ጥረት አድርጓል።

በተጨማሪም ወጣት ስጦታ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነፃ የስልክ መስመር 951 በመደወል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብሩ ከሀዋሳ ንግድ ባንክ ታቦር ቅርንጫፍ ሙሉነሽ ኦሌቦ ወደተባለች ግለሰብ አካውንት ለመላክ በተደረገ ስህተት ወደ ወጣት ስጦታ አካውንት የገባ መሆኑ በመረጋገጡ ወጣቱ ገንዘቡን ለባለቤቷ ተመላሽ አድርጓል።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዋና እንስፔክተር ኃይሉ ደፋር በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ከሆሳዕና ኤፍ ኤም ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ፥ ወጣት ስጦታ ወ/የሱስ የሰው ገንዘብ እንደማይጠቅም በመገንዘብ በታማኝነት ለባለቤቱ እንደመለሰ በመጠቆም ወጣቱ ላደረገው በጎ ተግባር አመስግነዋል።

ሌሎች ወጣቶችም የወጣት ስጦታ ወ/የሱስን ዓይነት ተሞክሮ በመቀበል የራስ ነገር ያልሆነ ማንኛውም ነገር የማይጠቅም መሆኑን በመረዳት ታማኝ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

በዚህ የገንዘብ ፍቅር በበዛበት ዘመን እንደ ስጦታ ያሉ ታማኝና የመልካም ግብረ ገብነት ባለቤት መሆን የህሊና እረፍትን የሚሰጥ እንደመሆኑ ወጣቱ ትውልድ ይህን መልካም ተሞክሮ ሊቀምር እንደሚገባ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

መልካምነት ሁልጊዜም ለራስ ነውም ብለዋል በመልዕክታቸው።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 #ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን!**************ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇...
01/09/2026

#ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን!

**************

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዜጎችን በፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ለማሳተፍ እና የሙስና ወንጀሎችን ለሕዝብ በግልጽ የማጋለጥ እንዲሁም አግባብነት ያላቸው የተጠያቂነት ሥራዎች በቁ...
31/08/2026

የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዜጎችን በፀረ-ሙስና ትግል ይበልጥ ለማሳተፍ እና የሙስና ወንጀሎችን ለሕዝብ በግልጽ የማጋለጥ እንዲሁም አግባብነት ያላቸው የተጠያቂነት ሥራዎች በቁርጠኝነት እንዲፈጸሙ ዘርፈ-ብዙ እና የተቀናጁ የፀረ-ሙስና ትግል ሥራዎች በ2019 በጀት ዓመት ሥራ ላይ እንዲውሉ ርብርብ ይደረጋል።

በተለይም፣ የተለያዩ የመደበኛ እና ማህበራዊ ሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የሙስና ወንጀሎችን በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ የማጋለጥ እርምጃዎችን ያካትታል። በመሆኑም፣ ዜጎች የሙስና ወንጀል ሥጋትና ተጋላጭነት ያለባቸው የተቋማት አሰራር ሥርዓት (የመንግሥት፣ የልማት ድርጅቶች፣ ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶች) ሲያጋጥማችሁ ለኮሚሽኑ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር በመጠቆም ለሰላ የፀረ-ሙስና ትግል በትብብር እንፈጽም።

ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፣ በህብረት እንታገል!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች

https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

30/08/2026

#ሌብነትን በጋራ መታገል አለብን!

Address

Addis Ababa
KAZANCHES

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal Ethics and Anti-Corruption Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share