Ministry of Agriculture - Ethiopia

Ministry of Agriculture - Ethiopia Ministry of Agriculture
(5)

Create a modern and a highly productive agricultural system that uses a more advanced technology which enables the society to get rid of poverty

23/08/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

የሩዝ ክላስተር ልማት በጅማ ዞን አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በጅማ ዞን የሩዝ ልማትን በክላስተር አሰራር ለማስፋፋት ሰፊ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዞኑ በአጠቃላይ ...
23/08/2026

የሩዝ ክላስተር ልማት በጅማ ዞን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በጅማ ዞን የሩዝ ልማትን በክላስተር አሰራር ለማስፋፋት ሰፊ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዞኑ በአጠቃላይ 393,602 ሄክታር መሬት ላይ ሩዝ እየለማ ነው።

ከጠቅላላው የሩዝ ልማት መሬት ውስጥ 325,550 ሄክታር በ15,202 ክላስተሮች ተደራጅቶ በ350,277 አርሶ አደሮች እየለማ ይገኛል።

‎የክላስተር አሰራሩ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን፣ የተሻሻሉ የእርሻ ዘዴዎችንና የግብርና ግብዓቶችን በተቀናጀ መልኩ ለመጠቀም በማስቻል ምርታማነትንና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ እያገዘ ነው።

‎በተለይም በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ጫራቂ ቀበሌ
‎ በ200 ሄክታር መሬት ላይ የሩዝ ክላስተር ልማት እየተካሄደ ሲሆን፣ 18 አርሶ አደሮችና በማህበር የተደራጁ 12 ወጣቶች ተሳትፈዋል።

‎በሊሙ ኮሳ ወረዳ በአጠቃላይ 38 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሩዝ እየለማ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 17 ሺህ ሄክታር በክላስተር አሰራር እየተመረተ ነው።

‎የሩዝ ክላስተር ልማቱ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሻሻል፣ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማጠናከርና የጅማ ዞንን የሩዝ ምርት አቅም ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል።

ፎቶ፦ ተክለመድህን አቻምየለህ

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

ከውጭ የሚገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ!አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በግብርና ሚኒስቴር እና በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ...
22/08/2026

ከውጭ የሚገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ!

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በግብርና ሚኒስቴር እና በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) ትብብር የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ላም ተኮር የምክር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አዚዝ አያሌው መንግስት ያስቀመጠውን ግብ መሰረት በማድረግ ከውጭ የሚገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ የወተት ምርት ለመተካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመድረኩም ዋና ዓላማ በ”SNV” የብሪጅ ፕላስ ፕሮጀክት የወተት ልማትን ለማሳደግ በቴክኖሎጂ፣ በገበያ ትስስር እና በአቅም ግንባታ ያስመዘገባቸውን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለወተት ላም አርቢዎች ተደራሽ በማድረግ ከውጭ የሚገባውን የወተት ምርት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ ለማዘጋጀት ያለመ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡

ፍኖተ-ካርታውን በጋራ የሚያዘጋጁት ግብርና ሚኒስቴር፣ የሳይንስ አካዳሚ እና በ”SNV” የብሪጅ ፕላስ ፕሮጀክት ናቸው፡፡

በ”SNV” የብሪጅ ፕላስ ፕሮጀክት ም/ሥራ አሰኪያጅ የኔነው በዛብሀ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አርሶ/አርብቶ አደሩ ትርፍ ወተት አምርተው ለገበያ በማቅረብ ገቢ እንዲያገኝ ትኩረት አድርጎ በመስራቱ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው፣ የውይይት መድረኩም የተገኙ ተሞክሮዎችን ላማስፋት የግዛል ብለዋል፡፡

ግብርና ሚኒስቴር የወተት ምርትና ምረታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እያከናወና ያለውን ስራ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በቀጣይም በፋይናንስም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ምክትል ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ላም-ተኮር የምክር አገልግሎት ምንነት፣ የተቋማዊ ላም-ተኮር የምክር አገልግሎት እና በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎች ላይ ያተኮሩ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ እንደ ተገለፀው፣ በአምስት አመት የፕሮጀክቱ ዘመን ላም-ተኮር የምክር አገልግሎትን በ350 ሺህ አርሶ/አርብቶ አደሮች ዘንድ ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡

እስከ አሁን በፕሮጀክቱ በተሰራው ስራ በቀን የአንድ ላም ወተት በአማካይ 3.8 ሊትር መጨመር ችሏል፡፡

ዘጋቢ፡- ሸምሱዲን ዩሱፍ
ፎቶ፡- ጌታቸው ምትኩ

#ከማምረትበላይ

------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
**
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
**
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
**
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
**
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
**
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
**
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

የክላስተር እርሻ፦ የመደመር እሳቤ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ በተግባር ሲገለጥ! አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በመደመር እሳቤ ውስጥ የሜካናይዜሽን ግብርና የለውጥ መሠረት...
21/08/2026

የክላስተር እርሻ፦ የመደመር እሳቤ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ በተግባር ሲገለጥ!

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በመደመር እሳቤ ውስጥ የሜካናይዜሽን ግብርና የለውጥ መሠረትና ቅድሚያ የሚሰጠው ዘርፍ ነው ሲሉ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ።

‎የግብርና ልማትን ዘመናዊ ለማድረግ፣ ምርታማነትንና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ የሰው ኃይል፣ መሬት፣ ግብዓት፣ ዕውቀት፣ ቴክኖሎጂና ገበያን በተቀናጀ መልኩ መጠቀም ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አብራርተዋል።

‎በዚህ ረገድ የኩታ-ገጠም (ክላስተር) እርሻ የመደመር እሳቤን በተግባር ለማስረጽ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ሲሆን፣ አርሶ አደሮች በጋራ ተደራጅተው የግብርና ማሽነሪዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን በጋራ በመጠቀም ምርትን በፍጥነትና በጥራት እንዲያመርቱ ያግዛልም ብለዋል።

‎የግብርና ማሽነሪዎችን በስፋት መጠቀም ጊዜንና የሰው ኃይልን ይቆጥባል። በዚህም ጥቂት ሰዎች በማሽነሪ ድጋፍ ብዙ ሥራ በአጭር ጊዜ ማከናወን ይችላሉ፤ ይህም ምርታማነትንና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ያግዛል።

‎የክላስተር እርሻ ከሜካናይዜሽን አጠቃቀም ጋር ተጣምሮ ሲተገበር፣ የእርሻ ሥራን ከባህላዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ፣ ተቀናጅቶና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ሥርዓት ለመለወጥ ያስችላል።

‎ስለሆነም የመደመር እሳቤው በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ በተግባር ሲገለጥ፣ ለከፍተኛ ምርታማነት፣ ለተሻለ ገቢና ለዘመናዊ ግብርና መሠረት ይጥላል ሲሉ በመልዕክታቸው አስፍረዋል።

‎በዚህም በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በኩታ-ገጠም (ክላስተር) የለማው የበቆሎ ማሳ የመደመር እሳቤን በተግባር ገልጦ ያሳየ ነው።

ፎቶ፦ ተክለመድህን አቻምየለህ

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

የቆስጣ ምንነት እና አመራረት!**************የከተማ ግብርና ልማት ሥራ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ገቢ በማሻሻልና ድህነትን በመቅረፍ እንዲሁም ለሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥ...
21/08/2026

የቆስጣ ምንነት እና አመራረት!

**************

የከተማ ግብርና ልማት ሥራ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ገቢ በማሻሻልና ድህነትን በመቅረፍ እንዲሁም ለሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡ “ምግቤን ከጓሮዬ“ ተብሎ የተጀመረው የከተማ ግብርና ዛሬ በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ታግዞ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ በዚህ ፅሑፍ የቆስጣ ምንነት፣ ፋይዳው እና በአነስተኛ ቦታ እንዴት እንደሚመረት እናያለን፡፡

ቆስጣ በስነ-ተፈጥሯዊ ባህሪ የቀይስር እና የስፒናች ቤተሰብ ሲሆን፣ የስር ክፍል የሌለውና ለቅጠል ምርት ብቻ የሚመረት ተክል ነው።

ቆስጣ ከጥቅሞቹ አንፃር በቫይታሚን ኬ፣ ሲ እና ኤ እንዲሁም በማግኒዚየም እና በማንጋኒዝ የበለጸገ ነው። የደም ግፊትን ለመቀነስና ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል።

ስነ-ምህዳርን በተመለከተ በወይና-ደጋ አካባቢ 1600 እስከ 2200 ሜትር ከፍታ፣ ቀዝቃዛ አየር የሚስማማው ሲሆን፣ ለአስተማማኝ እድገት 15 እስከ 18oC (ከ24oC ያልበለጠ) ሙቀት እና አሸዋ ቀመስ አሲዳማ ያልሆነ አፈር ለቆስጣ ልማት ተስማሚ ናቸው፡፡ በሄክታር 380 እስከ 450 ሚሊ ሊትር ውሃ የሚያስፈልገው ሲሆን በየ14 እስከ 21 ቀን ውሃ ማግኘት አለበት፡፡

የአዘራር ዘዴ

• አዘራር፦ በማሳ፣ በሽቅብ እርሻ ባልዲዎችንና ቱቦዎችን በመጠቀም እንዲሁም በአፈር አልባ እርሻ (ሃይድሮፖኒክስ) ማምረት ይቻላል።
• ችግኝ ማዘጋጀት፦ በመደብ (ስፋት 1 ሜትር፣ ርዝመት ከ5 እስከ 10 ሜትር ወይም በመደብ ካልሆነ በትንንሽ እቃዎች/ባልዲ ችግኝ ማፍላት ይቻላል፡፡ በእቃዎቹ አፈሩን ስናደባልቅ የሚደባለቁት የላይኛው አፈር፣ ኮምፖስት እና አሸዋ (2:3:2) ናቸው። የዘር መጠንን በተመለከተ ለ1 ሄክታር ከ12 እስከ 14 ኪሎ ግራም ዘር ያስፈልጋል። ዘር ሲዘጋጅ ዘሩን ከመዝራት በፊት በ20oC የሞቀ ውሃ ለ2 ሰዓታት ማጠብ/መንከር አበቃቀልን ለማፋጠን ይረዳል።

• ተከላ እና ርቀት፦ በመስመር መካከል 45 እስከ 50 ሴንቲ ሜትር፣ በተክል መካከል ከ15 እስከ 20 ሴንቲ ሜትር ማራራቅ ያስፈልጋል።

የሰብል ፈረቃና የማዳበሪያ አጠቃቀም

• ማዳበሪያ፦ እስከ 3 ዓመት ሊያገለግል የተፈጥሮ ማዳበሪያ እስከ 20 ቶን በሄክታር መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህም ለ3 ዓመት ያገለግላል፡፡ NPS 200 ኪሎ ግራም በሄክታር መጠቀም እና የመጀመሪያው ምርት ከተሰበሰበ በኋላ 90 ኪሎ ግራም ዩሪያ በሄክታር መጠቀም ነው።
• የሰብል ፈረቃ፦ ከቀይ-ስር እና እስፒናች ጋር መፈራረቅ የለበትም። ከቲማቲም፣ ፎሶሊያ እና ሽንኩርት ጋር ማፈራረቅ ይገባል።

የበሽታ ቁጥጥር

• ተባዮች፦ ምስጥ፣ አንጥረኛ (Thrips) እና ግንደ-ቆራጭ በማሳ ንፅህና መከላከል።
• በሽታዎች፦ ሴርኮስፖራ (Cercospora leaf spot) እና ኔማቶድ (ሥር ማሳበጥ) በሽታን በሰብል ፈረቃ መከላከል ይቻላል።

የምርት አሰባሰብ እና አያያዝ

• ጊዜ፦ ከተዘራ ከ40 እስከ 70 ቀናት (ከ8 ሳምንታት) በኋላ የመጀመሪያ ምርት ይደርሳል።
• አሰባሰብ፦ ከአንድ ተክል እስከ 8 ጊዜ መልቀም (ማምረት) ይቻላል (በየ3/4 ሳምንት)።
• አቆራረጥ፦ ከምድር 5 ሴንቲ ሜትር ከፍ አድርጎ በስለታም ቢላዋ መቁረጥ።
• ማቆየት፦ ቅጠሎቹ እንዳይጠወልጉ ከ5 እስከ 8 ሴንቲ ሜትር ውሃ ባለው ዕቃ/ባልዲ ውስጥ በማቆም ከ12 እስከ 24 ሰዓት፣ የሙቀት መጠኑ ዘሮ ድግሪ (0 oC) ከሆነ እስከ 15 ቀን ማቆየት ይቻላል።

#ከማምረትበላይ

---------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
****
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
****
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
****
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
****
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
****
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
****
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

ኢትዮጵያ የግብርና ምርቷን ለማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ በትኩረት እየሰራች ነውአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ኢትዮጵያ የግብርና ልማትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀ...
21/08/2026

ኢትዮጵያ የግብርና ምርቷን ለማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ በትኩረት እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ኢትዮጵያ የግብርና ልማትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በመስኖ ልማት፣ በተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችና በግብርና ሜካናይዜሽን ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ገለጹ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት አምባሳደሮች ኮሚቴና የኢጋድ ፓርላማ ፎረም በአግሪፉድ ሲስተም ዙሪያ በአዲስ አበባ ያዘጋጁት ከፍተኛ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የግብርና ልማትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በመስኖ ልማት፣ በተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችና በግብርና ሜካናይዜሽን ላይ በትኩረት እየሰራች ነው።

የክላስተር እርሻ ልማት አርሶ አደሮች የግብዓት፣ የቴክኖሎጂ፣ የባለሙያ ምክክር አገልግሎትና የገበያ ትስስሮችን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌማት ትሩፋት ተነሳሽነቶች የአካባቢ ጥበቃን፣ የግብርና ምርታማነትንና የቤተሰብ ምግብና የአመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ተወካይና በድርጅቱ የውጭ አገልግሎት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦማር ጃማ የአግሪፉድ ሲስተም ለውጥ የካምፓላ የግብርና ልማት ቃል ኪዳንን ወደ ተግባር በማሸጋገር፣ በጠንካራ ፖሊሲ፣ የሕግ ማዕቀፍ፣ በጀትና ኢንቨስትመንት በመደገፍ እንደሚሳካ ጠቁመዋል።

ሀገራቱ ለምግብ ዋስትና ችግር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለዝቅተኛ ምርታማነትና ለውስን የገበያ ትስስር የተጋለጡ በመሆኑ፣ የግብርና ለውጥን ለማፋጠን አባል ሀገራት የተቀናጀ ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።

በመድረኩ የአግሪፉድ ሲስተም ልማትን ለማፋጠን የፖሊሲ ቅንጅትን፣ የግብርና ኢንቨስትመንትን፣ የቀጣናዊ ንግድ ትስስርንና የፓርላማ ክትትልን ማጠናከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

21/08/2026

‎በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በኩታ-ገጠም (ክላስተር) እየለማ የሚገኝ የበቆሎ ማሳ አሁናዊ ገፅታ፤

#ከማምረትበላይ

---------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
****
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
****
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
****
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
****
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
****
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
****
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

📸 የሳምንቱ የግብርና ፎቶ #ከማምረትበላይ ---------በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇  📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et****📌ፌስቡክ፦ h...
21/08/2026

📸 የሳምንቱ የግብርና ፎቶ

#ከማምረትበላይ

---------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
****
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
****
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
****
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
****
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
****
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
****
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

የሙዝ ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የሙዝ ምርትን በዓለም አቀፍ ገበያ...
20/08/2026

የሙዝ ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የሙዝ ምርትን በዓለም አቀፍ ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የጥራት ማሻሻያና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር የሙዝ ወጪ ንግድ ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ ጉባዔ አካሂዷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሙዝ ምርት መጠን ቢኖርም ለውጭ ንግድ የሚቀርበው ለጎረቤት ሀገራት ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ያላትን ለግብርና የተመቹ አግሮ-ኢኮሎጂያዊ ሁኔታዎች ወደ ሀብትና ካፒታል በመቀየር ዓለም አቀፍ የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት ይገባል ብለዋል።

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ትብብር በሆርቲካልቸር ዘርፍ ስኬቶች እንዲመዘገቡ ማድረጉን በማንሳት፤ በአትክልትና ፍራፍሬ ያለውን ተቋማዊ ልምድ፣ የሎጂስቲክስ እውቀት እና ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ሚኒስቴር ዘርፉን ገበያ ተኮር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገርና ዘላቂ ለማድረግ በርካታ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ማዕቀፎችን ቀርጿል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ሆርቲካልቸር ዘርፍ ለማሳደግ የ10 ዓመት ብሔራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ በመቅረጽ ለዘርፉ እድገት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የሙዝ ምርት ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የጥራት ማሻሻያና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በአበባና በአትክልት ዘርፍ የተገነባው ተቋማዊ ልምድ፣ የሎጂስቲክስ እውቀት እና ዓለም አቀፍ የገበያ ትስስር ለሙዝ ኢንዱስትሪው ስኬት መጠቀም ይገባልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ፤ በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም ከግብርና ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት ከሚመረቱ የፍራፍሬ ዝርያዎች አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ከምግብነት ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የገቢ ምንጭና ሥራ ዕድል ፈጥሯል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

#ከማምረትበላይ

-----------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
******
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
******
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
******
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
******
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
*****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
******
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
******
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

የበለስ ልማትን በማስፋፋት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓልአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ሀገራችን ለበለስ ልማት ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም ምርቱ...
20/08/2026

የበለስ ልማትን በማስፋፋት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ሀገራችን ለበለስ ልማት ያላትን እምቅ አቅም በመጠቀም ምርቱን ለማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን ለመተግበር፣ ምርቱን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረበ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተለይም በትግራይ ክልል የበለስ ልማት በስፋት የሚከናወን ሲሆን ይህንንም ልማት በተለያዩ የሃገራችን አባባቢዎች ለማስፋፋትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ደሳለኝ ተሻለ በለስ ከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥንና ድርቅን መቋቋም የሚችል ድንቅ ሰብል ነው ብለዋል።

ለምግብ ዋስትና፣ ለአለማቀፍ ገበያ፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለኮስሞቲክስ እንዲሁም ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆን ሰፊ አቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ሀገራችን ለበለስ ልማት ያላትን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር በማድረግ በግብርና ኤክስቴንሽን ስራዎች ውስጥ አብራርተዋ።

በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ እስቲቪል በበኩላቸው በሜክሲኮ ባህልና ኢኮኖሚ ውስጥ በለስ የሀገሪቱ ብሔራዊ ምልክት እስከመሆን የደረሰ እጅግ ከፍተኛ ቦታ ያለው ተክል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለበለስ ልማት እጅግ ተስማሚና ከሜክሲኮም የተሻለ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ያላት መሆኑን ያነሱት አምባሳደሩ ሀገራቸው በዘርፉ ያላትን የረጅም ዘመን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ፍቃደኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅት የሜክሲኮ ሀገር የበለስ ልማት ልምድ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተሞክሮዎች የቀረበ ሲሆን ለመነሻነት የቀረቡ ጽሁፎችን መሠረት በማድረግ ኢትዮጵያ በበለስ ልማት ያላትን ምቹ ሥነ-ምህዳር በመጠቀምና የልማት ሥራውን ለማስፋፋት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተነስቷል።

በለስን ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለአምራቾች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማድረግ የሚያስችሉ የፖሊሲና የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በመቀየስ በቅንጅት ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

ዘጋቢ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ዮዲት እንዳለው

#ከማምረትበላይ

---------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
****
📌ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
****
📌ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/-ethiopia
****
📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
****
📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia
****
📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs
****
📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/
****
📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

Address

Addis Ababa
6234

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+25101116460746

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Agriculture - Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Agriculture - Ethiopia:

Shortcuts

Share