Transport Bureau

Transport Bureau Bureau

15/05/2026
15/05/2026
በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የመሶብ (MESOB) የአገልግሎት ማዕከል ስለሚሰጡ አገልግሎቶችየመሶብ (MESOB) የአንድ ማዕከል የአገልግሎት ስርዓት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር...
14/05/2026

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የመሶብ (MESOB) የአገልግሎት ማዕከል ስለሚሰጡ አገልግሎቶች

የመሶብ (MESOB) የአንድ ማዕከል የአገልግሎት ስርዓት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ዘመናዊ እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ የተዘረጋ የአገልግሎት ማዕከል ነው።

ማዕከሉ ተገልጋዮች በተለያዩ ቢሮዎች መዘዋወር ሳያስፈልጋቸው በአንድ ቦታ ፈጣንና የተቀናጀ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል የጊዜና የወጪ ቁጠባ እንዲኖር አድርጓል።

የመሶብ (MESOB) የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

1. የንግድ የመንገድ የህዝብ ትራንስፖርት ኦፕሬተርነት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት

ይህ አገልግሎት በህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ ለመስራት ለሚፈልጉ ኦፕሬተሮች የሚሰጥ ሲሆን፣ ድርጅቱ ወይም ግለሰቡ በህግ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልቶ መገኘቱን ያረጋግጣል።

2. የንግድ የመንገድ የህዝብ ትራንስፖርት ኦፕሬተርነት ፈቃድ እድሳት

የተሰጠ ፈቃድ የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ ተገልጋዮች ፈቃዳቸውን በወቅቱ እንዲያድሱ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

3. የንግድ የመንገድ ጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀትና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት

በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ኦፕሬተሮች በህጋዊ እና በቴክኒክ መስፈርቶች መሰረት ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፈቃድ ነው።

4. የንግድ የመንገድ ጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር ፈቃድ እድሳት

ነባር የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች የፈቃዳቸውን ትክክለኛነት በመጠበቅ በህጋዊ ሁኔታ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።


5. የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት መግቢያ ፈቃድ መስጠት

በዓለም አቀፍ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ትራንስፖርት ስራ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች የሚሰጥ ፈቃድ ነው።

6. የድንበር ተሻጋሪ መግቢያ ፈቃድ እድሳት

የተሰጠው የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ በጊዜው እንዲታደስ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

የመሶብ (MESOB) አገልግሎት ጠቀሜታዎች

1. ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት
ቀደም ሲል ቀናት ወይም ሳምንታት ይወስዱ የነበሩ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል በፍጥነት እንዲጠናቀቁ በማድረግ የጊዜ ፣ወጪ እና ጉልበት መቆጠብ አስችሏል፡፡

2. ግልጽነትና ተጠያቂነት
ተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት የሚያስፈልጉ ሰነዶች፣ የአገልግሎት ሂደቶች እና ክፍያዎችን አስቀድመው እንዲያውቁ በመደረጉ ግልጽ የአሰራር ስርዓት ተፈጥሯል።

3. የዲጂታል አሰራር መዘርጋት
የወረቀት ስራዎችን በመቀነስ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋቱ የመረጃ አያያዝ ቀላልና ዘመናዊ ሆኗል።

4. የደንበኞች እርካታ ማሳደግ
የደንበኞች አቀባበል ስርዓት እና የእንግዳ ማረፊያ ቦታዎች እንዲሻሻሉ በመደረጉ ተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

5. የኦንላይን አገልግሎት ተደራሽነት
በቴክኖሎጂ የታገዘ ስርዓት በመሆኑ ተገልጋዮች በአካል ሳይገኙ መረጃ ማግኘት፣ ቀጠሮ መያዝ እና አንዳንድ አገልግሎቶችን በኦንላይን ማከናወን ይችላሉ።

የመሶብ (MESOB) አላማ
የሞስብ አገልግሎት ዋና አላማ በትራንስፖርት ዘርፍ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተጠያቂ የአገልግሎት ባህል በመፍጠር ለተገልጋዮች ቀላልና ፈጣን አገልግሎት ማቅረብ ነው።

https://www.facebook.com/100068876633464/posts/1303704535268755/?app=fbl

Address

Megenagna Beside Tamegaz @ 3M City Mall Building
Addis Ababa
2395

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Transport Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Transport Bureau:

Share