Lideta Woreda 04 Communication Office

Lideta  Woreda 04 Communication Office በቂና የተሟላ መረጃ ያለው፣ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ያጐ�

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የትምህርት ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

በክፍለ ከተማው የቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ለሸማች ማህበረሰቡ በተጠናከረ መልኩ እየቀረበ ይገኛል፡፡በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 14 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕ...
29/08/2026

በክፍለ ከተማው የቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ለሸማች ማህበረሰቡ በተጠናከረ መልኩ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 14 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕከላት ጥራታቸውን የጠበቁ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የማቅረብ ስራ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በነዚህ የገቢያ ማእከላት ነጋዴዎች፣አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ ፣የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን በቀጥታ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ በመደረጉ የኑሮ ውድነቱን ለማቀለልና ገበያውን ለማረጋጋት ያስቻለ ሲሆን ነዋሪዎችም በአቅራቢያቸው በመሸመት የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ብክነት እንዲቀንሱ አግዟል።

የክፍለ ከተማው አስተዳደር በነዚህ የቅዳሜና የእሁድ ገቢያዎች ህብረተሰቡን ካልተገቢ የዋጋ ጭማሪ ለመጠበቅ እንዲሁም የአቅርቦት ስርዓቱን ይበልጥ በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ማዕከላት የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ፣ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ ከአቅራቢያው በማገናኘት፣የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በሚያስችል መልኩ ስራዎች በቅንጅት እየሰሩ ነው።

በልደታ /ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የጽዳት ዘመቻ ተካሄደየወረዳ 04 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኢንጂነር  #ሺበሺ ታምሩ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት የወረዳውን ምድረ ግቢ በየሳምንቱ አ...
28/08/2026

በልደታ /ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

የወረዳ 04 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኢንጂነር #ሺበሺ ታምሩ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት የወረዳውን ምድረ ግቢ በየሳምንቱ አረብ አርብ በማጽዳት ውብ ፅዱና አረንጓዴ የስራ አካባቢን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

በፅዳት ንቅናቄው ላይም የወረዳው አመራሮችን እና ሰራተኞች ተሳትፏል።

ነሐሴ_22_2018

28/08/2026
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 “ከስክሪን ቀንሰን መጽሐፍትን እንግለጥ!” በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት  መርሃ ግብር ተካሄደ።የንባብ ፌስቲቫሉ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የን...
27/08/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 “ከስክሪን ቀንሰን መጽሐፍትን እንግለጥ!” በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት መርሃ ግብር ተካሄደ።

የንባብ ፌስቲቫሉ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የንባብ ባህልን በማሳደግ በተለይም ወጣቶች ከስክሪንና ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ በመቀነስ ለመጽሐፍ ንባብ ትኩረት እንዲሰጡ ለማበረታታት ያለመ መርሀ ግብር ነው።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በክረምት መርሃ ግብር ከሚያካሂዳቸው የስፖርት ውድድሮች አንዱ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር አስጀምሯል።በውድድሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያ...
26/08/2026

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በክረምት መርሃ ግብር ከሚያካሂዳቸው የስፖርት ውድድሮች አንዱ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር አስጀምሯል።

በውድድሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እንዳሉት ስፖርትን ማገዝ አገርን በስፖርቱ ዘርፍ ከፍ እንድትል ስለሚያግዝ ሁላችንም በአንድነት ሆነን ስንሰራ የምንፈልገውን ማሳካት እንችላለን በማለት የስፖርትን አስፈላጊነትና ለወጣቶች ያለውን ጠቀሜታ አስገንዝበዋል።

የእግር ኳስ ውድድሩ ወጣቶች ክረምታቸውን በጤናማና በአስደሳች መንገድ እንዲያሳልፉ፣ የስፖርት ፍላጎታቸውን እንዲያዳብሩ እና በመጪው ጊዜ የሚጠቅማቸውን የቡድን ሥራ፣ ትዕግሥትና ተግባቦት ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በውድድሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ በዛብህ፣ ውድድሩ በክረምት በጎ ተግባር መርሃ ግብር ውስጥ ወጣቶችን በማሰባሰብ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር፣ እንዲሁም ወጣቶች ጤናማና አስደሳች ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

የጤና ቡድን የእግር ኳስ ውድድሩ አብሮነትን፣ አንድነትንና የቡድን መንፈስን በማጠናከር የስፖርት ፍቅርን ለማሳደግና ወጣቶችን በጤናማ መንገድ ለማሳተፍ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው ዓለሙ እንደገለጹት፣ የእግር ኳስ ውድድሩ ወጣቶችን በስፖርት በማሳተፍ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን በሥነ ምግባር እንዲታነፁ፣ ጤናማና ብቁ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ በክረምት መርሃ ግብሩ ወጣቶች በተለያዩ የስፖርትና የማህበራዊ ተሳትፎ መርሃ ግብሮች እንዲሳተፉ በማድረግ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትንና የቡድን መንፈስን ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ ውድድሩ ወጣቶችን በስፖርት ከማሳተፍ ባለፈ ጤናማ፣ ብቁና ሥነ ምግባራዊ ትውልድ ለመገንባት የሚያበረክት መሆኑ ውድድሩን የክፍለ ከተማው እና የወረዳው ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት በጋራ እንደሚያስተባብሩት ተገልጿል::

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት   ለልደታ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የብሎክ ካውንስል መልሶ ማደራጀት ንቅናቄ አካሂዷል። የብሎክ ካውንስል ህብረተሰቡ በየ...
24/08/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት ለልደታ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የብሎክ ካውንስል መልሶ ማደራጀት ንቅናቄ አካሂዷል።

የብሎክ ካውንስል ህብረተሰቡ በየአካባቢው ያሉ የመልካም አስተዳደር፣ የጸጥታ፣ የጽዳትና የልማት ስራዎች ላይ በቀጥታና በባለቤትነት እንዲሳተፍ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

የብሎክ ካውንስል አደረጃጀት በብሎክ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን በማስተባበር፣ የአካባቢ ችግሮችን በጋራ የመፍትሔ ባለቤት ለማድረግና የአገልግሎት አሰጣጥን እስከ ታችኛው የህብረተሰብ እርከን ድረስ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።
ነሃሴ 18_2018

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጽዳትና ውበት አስተዳደር   #የመውሊድ አን-ነቢ በዓልን ምክንያት በማድረግ  በአባድር መስጊድ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።በጽዳት ዘመቻው የተገኙት የወረዳው ዋና ...
24/08/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጽዳትና ውበት አስተዳደር #የመውሊድ አን-ነቢ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአባድር መስጊድ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

በጽዳት ዘመቻው የተገኙት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ጀሚላ ረዲ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው አካባቢያችንና ተቋማትን ዘወትር በማጽዳት የከተማዋን ውበት መጠበቅ ያስፈልጋል::

ለረዳን ፈጣሪ አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሁንለት!አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ምእራፍ፣ በአዲስ የመከባበር፣ የመመካከርና የመደማመጥ የመግባባት ታሪክ የተደረገ ሽግግር!!"ከአሸናፊ-ተሸናፊ” ትርክ...
22/08/2026

ለረዳን ፈጣሪ አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሁንለት!

አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ምእራፍ፣ በአዲስ የመከባበር፣ የመመካከርና የመደማመጥ የመግባባት ታሪክ የተደረገ ሽግግር!!

"ከአሸናፊ-ተሸናፊ” ትርክት በመላቀቅ፣ በሀሳብ ልዕልና ወደ በጋራ የማሸነፍ፣ ለጋራ ተጠቃሚነት ሲባል የጋራ መፍትሄ ለማምጣት በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ወደ መግባባት የተሸጋገርንበት ታላቅ የታሪክ እጥፋት ነው፡፡ በዚህ የምክክር ሂደት የተለየ አሸናፊና ተሸናፊ ፈጽሞ አልተፈጠረም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

እንዲመከሩባቸው ከቀረቡት 400 ከሚጠጉ አበይት ጉዳዮች (ምክረ ሀሳቦች) ኢትዮጵያውያን ተደማምጠውና አንዱ የሌላውን ህመም ተረድተው ወደ አንድ በመሰብሰብ በ99 % ላይ ሙሉ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል። አንድ አይነት ድምዳሜ ላይ ባልተደረሰባቸው በአራት 4 (1%) ጉዳዮች ላይ ብቻ በአማራጭ መፍትሄዎች እንዲታለፉ በሙሉ መግባባት ላይ ተደርሷል። ይህም ሂደቱን እስካሁን በዓለም ላይ ከሰማናቸው የምክክር ሂደቶች እጅጉን በምሳሌነት የሚጠቀስና አስደናቂ አድርጎታል።

ያለፉት ትውልዶች በጽኑ ተመኝተውት ያላዩትን ይህንን የሰለጠነ አብሮነት የሰፈነበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ በዓይናችን እንድናይ ስለፈቀደልን ቸሩ አምላካችንን ከልብ እናመሰግናለን። የእኛም ትውልድ ይህን ስላሳካን በእውነትም እጅግ የታደልን ትውልዶች ነን።

ለዚህ ሀገራዊ ድል መሳካት ከየአካባቢው የመጡ ውድ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት አስደናቂ በሳልነት እና ጥልቅ አስተዋይነት እጅግ የሚመሰገን ነው።

ሀገር የምትገነባውና ኢትዮጵያ የምትጸናው በትክክልም በዚህ የሰለጠነ መንገድ ነው! በመተሳሰብ፣ በአብሮነት፣ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ለማዳመጥና ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን፣ እንዲሁም በመከባበር የምንገነባት ኢትዮጵያ የሁላችንም ኩራት ናት። ይህ አስደናቂ የመደማመጥ አዲስ ባህል እና የጋራ ታሪካችን በመሆኑ ላሳኩት ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።

በርግጥ ዛሬ ተመካክረን በእነዚህ ጉዳዮች ተግባብተናል ማለት ነገ ምንም አይነት ልዩነቶች አያጋጥሙንም ማለት አይደለም። ነገር ግን ልዩነትን በመመካከርና በሰለጠነ መንገድ መፍታት ተጀምሯል፤ በሩም ተከፍቷል፤ ከእንግዲህ ወደ ኋላ አንመለስም። ከእንግዲህ ልጆቻችን ልዩነቶቻቸውን በጠመንጃ ለመፍታት በመሞከር እና እርስ በእርስ በመገዳደል አይቀጥሉም። ይህ የጦርነት እዳ ወደ እነሱ እንደማይተላለፍ እምነት አለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

በክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ለሸማች ማህበረሰቡ በተጠናከረ መልኩ እየቀረበ ይገኛል፡፡የቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕከላት ጥራታቸ...
22/08/2026

በክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የቅዳሜና እሁድ ገበያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ለሸማች ማህበረሰቡ በተጠናከረ መልኩ እየቀረበ ይገኛል፡፡

የቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕከላት ጥራታቸውን የጠበቁ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የማቅረብ ስራ በዛሬው እለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በነዚህ የገቢያ ማእከላት ነጋዴዎች፣አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን በቀጥታ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ በመደረጉ የኑሮ ውድነቱን ለማቀለልና ገበያውን ለማረጋጋት ያስቻለ ሲሆን ነዋሪዎችም በአቅራቢያቸው በመሸመት የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ብክነት እንዲቀንሱ አግዟል።

የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ማዕከላት የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ፣ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ ከአቅራቢያው በማገናኘት፣የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በሚያስችል መልኩ ስራዎች በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።

Address

Sarbet , Infront Of Vatican Embassy
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta Woreda 04 Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share