ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia This is the page of Ministry of Culture and Sport of Ethiopia!
(2)

10/08/2026
የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ሳቦም አበራ ሚልኬሳን በፕሬዚዳንትነት መረጠ ።     ነሐሴ 03፣ 2018 ዓ/ም               አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ቴኳ...
09/08/2026

የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ሳቦም አበራ ሚልኬሳን በፕሬዚዳንትነት መረጠ ።

ነሐሴ 03፣ 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። ጉባኤው የኦዲትና የስራ ሪፖርቶችን መርምሮ በማጽደቅ፣ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያቶ በማፅደቅ እና አዳዲስ የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሳቦም አበራ ሚልኬሳ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ፌዴሬሸኑ ባላፉት ዓመታት የቴኳንዶ ስፖርትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ በማድረግ በዘረጋው የውድድር መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮናዎችን፣ የግል እና የቡድን ውድድሮችን በዕድሜና ክብደት ደረጃ በማካሄድ ዉጤታማ ስራዎችን እንደሰራ አውሰተዋል።

በማከልም ሳቦም አበራ የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ለአሰልጣኞች፣ ለዳኞች እና ለስፖርተኞች የሙያ ማሻሻያ እና የቴክኒክ ስልጠናዎችን በመስጠት አንድ ወጥ የአሰራር ደረጃ በመፍጠር በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሀገራቸውን የሚወክሉ ብሔራዊ የቴኳንዶ ቡድኖችን መምረጥና ማዘጋጀት እንደቻለ ገልፀዋል።

በጉባኤው የተሳተፉ አካላት በበኩላቸው ፌዴሬሸኑ በሚቀጥሉት ዓመታት ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር የቴኳንዶ ስፖርት በሀገራችን በተዘረጋው የታዳጊ ወጣቶች የምዘናና የውድድር መርሀ ግብር ተካቶ ተተኪ ስፖርተኞች እንዲፈሩበት በትኩረት እንዲሰራ፣ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን በማብዛት ዓለም አቀፍ የውድድር ተሳትፎን እንዲያሳድግ እና ፌዴሬሸኑን ገቢ የሚያሰስገኙ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

ጉባኤው ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸንን የሚመሩ ስራ አሰፈፃሚዎችን ለመምረጥ የፌዴሬሸኑን ህግና ደንብ መሰረት በማድረግ በሰጠው ድምፅ ለሁለተኛ ዙር ሳቦም አበራ ሚልኬሳን በፕሬዚዳንትነት በሙሉ ድምፅ ሲመርጥ በስራ አስፈፃሚነት አቶ ከድር አህመድ፣ አቶ ተገኑ በቀለ፣ አቶ መኪ ገመቹ ፣ ወ/ሮ አስቴር ደርበው፣ ወ/ሮ ማዓዛ ጋሻው እና ወ/ሮ በዓል ግርማቸውን መርጧል።

ተመራጮቹም ጉባዔው እምነት ጥሎ ለሰጣቸው ድምፅ በመታመን ለስፖርቱ እድገት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ከበደ እጅጉ 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሸን እንደ ሃገር የሚያከናውናቸው ማሕበራዊ አበርክቶዎች የሚደነቅ መሆኑን በመግለፅ በዛሬው እለት ያካሄደው ጉባኤም በጉባዔተኞች የነቃ ተሳትፎ የደመቀ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ የተደረገበት መሆኑን ተናግረው ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የሚያከናውናቸው ተግባራት በስትራቴጅክ እቅድ ተደግፈው ጉባኤተኛው ያነሳቸው ሀሳቦች በግበዓትነት ተይዘው የሚተገበሩ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

በሴቶች 3000 ሜትር ኢትዮጵያ ወርቅና ብር ሜዳሊያ አገኘች!እንኳን ደስ አለን !በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3000 ሜትር ውድድ...
09/08/2026

በሴቶች 3000 ሜትር ኢትዮጵያ ወርቅና ብር ሜዳሊያ አገኘች!

እንኳን ደስ አለን !

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3000 ሜትር ውድድር አትሌቶቻችን ተከታትሎ በመግባት ተጨማሪ ሜዳልያዎች ለኢትዮጵያ አስገኝቷል

አትሌት ዮርዳኖስ ፅጋብ በ8:43.65 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ በአንደኝነት አሸንፋለች ።

አትሌት ሽቶ ጉሚ በ8:45.06 በመግባት የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ይህም በ3000 ሜትር ውድድር ወርቅና ብር በኢትዮጵያ እጅ እንዲገባ ያደረገ አስደናቂ የስኬት ጊዜ ሆኗል።

አትሌት ሽቶ ጉሚ በዚህ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ማስገኘቷም ይታወሳል።

በሌሎች ውድድሮች በሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሀብታም ገበየሁ በ2:03.99 አራተኛ ስትወጣ፣ አትሌት ደራርቱ ሽብሩ በ2:04.81 ሰባተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በወንዶች 5000 ሜትር እርምጃ ፍፃሜ የተሳተፈው አትሌት ነገሮ አዱኛ በ20:22.82 የግል ምርጥ ሰዓቱን በማስመዝገብ 19ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል።

ሻምፒዮናው ዛሬ ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች*******************በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ...
08/08/2026

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበች
*******************

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የወርቅና ብርና ሜዳሊያ አግኝታለች።

አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ርቀቱን በ9:15.81 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

አትሌት ወሰኔ አሰፋ ደግሞ 9:30.50 በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

ኢትዮጵያ እስካሁን በውድድሩ አንድ የወርቅ ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።
Sport

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

የባህልና ስፖርት ሴክተር ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንና የጥበብ ማዕከላትን ጎበኙ።ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የባህል...
08/08/2026

የባህልና ስፖርት ሴክተር ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንና የጥበብ ማዕከላትን ጎበኙ።

ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የባህልና ስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሞያዎች፣ የስፖርትና የጥበባት ማህበራት ፕሬዚዳንቶች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሞያዎች፣ የጉባኤው ተሳታፊዎች በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡ የስፖርት፣ የባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።

ማዕከላቱ ዘመናዊና ወቅቱ በደረሰበት ቴክኖሎጂ የተደራጁ መሆናቸው ለኪነ-ጥበብና ስፖርት ዕድገት እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

ባህል፣ ጥበባትና ስፖርት 2.5% በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ሀገራዊ ምርት (GDP) እንደሚሸፍኑ ተገለፀ፤***************************************ነሐሴ 01፣ 2018ዓ.ም አዲስ...
07/08/2026

ባህል፣ ጥበባትና ስፖርት 2.5% በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ሀገራዊ ምርት (GDP) እንደሚሸፍኑ ተገለፀ፤
***************************************

ነሐሴ 01፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ያስጠናው የባህል፣ ጥበባትና ስፖርት ጉዳዮች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦን የሚዳስስ ጥናታዊ ፅሁፍ ይፋ ተደርጓል።

''የባህል፣ ጥበባት እና ስፖርት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበረሰባዊ አበርክቶ በኢትዮጵያ'' በሚል የተዘጋጀው ጥናታዊ ፅሁፍ፤ ስፖርት በሀገር ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁሟል።

ባህል፣ ጥበባት እና ስፖርት ከኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት ውስጥ 2.5% በመቶ ድርሻ እንዳላቸውም የጥናቱ ግኝት አመላክቷል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በ2019 በጀት ዓመት በተዋረድ የሚያከናውናቸውን ተግባራት መሰረት በማድረግ ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር የዕቅድ ውል ስምምነት ፈፀመ።ሐምሌ 30፣ 2018...
07/08/2026

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በ2019 በጀት ዓመት በተዋረድ የሚያከናውናቸውን ተግባራት መሰረት በማድረግ ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር የዕቅድ ውል ስምምነት ፈፀመ።

ሐምሌ 30፣ 2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየው የሴክተር የባህል፣ ጥበባትና ስፖርት ጥናትና ምርምር ጉባኤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት በተዋረድ የሚያከናውናቸውን ተግባራት መሰረት በማድረግ ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር በውጤት አመላካች መለኪያዎች የታቀዱ የእቅድ ውል ስምምነቶችን ፈፅሟል ።

በዚያው መድረክ በ2018 በጀት ዓመት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በውጤት አመላካች መለኪያዎች ያቀዳቸውን እቅዶች 99.5% ሲያሳካ በየደረጃው አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት ሁሉ የምስጋና የምስክር ወረቀት ሲበረከት የጤና ማህበራዊ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሰቢ ለሆኑት ክብርት ወርቀሰሙ ማሞና ለምክትል ሰብሳቢው ዶ/ር ታደሰ ቡራቃ ባለፉት ዓመታት ለሴክተሩ ለነበራቸው ድጋፍና ክትትል እውቅና ሰጥቷል።

በተያያዘ በባህልና ስፖርት መዋቅር ክልሎችን፣ ከተማ
አስተዳደሮችን እና ተጠሪ ተቋማትን በመመዘን ሲሸልም በባህልና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ አማራ ክልል 1ኛ፤ ኦሮሚያ ክልል 2ኛ እና አዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የተዘጋጀላቸውን ሸልማት ተረክበዋል።

በተመሳሳይ በስፖርት ዘርፉ በተደረገ ምዘና ኦሮሚያ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ 1ኛ፤ የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ 2ኛ እንዲሁም ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3ኛ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ሸልማት ወስደዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማን ከተልዕኳቸው አንፃር በመመዘን የምስጋና ሰርትፍኬት ሲያበረክት የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ በነበረው የላቀ አፈፃፀም ልዩ ተሻለሚ መሆን ችሏል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚመሩ ዘርፎች ለብልፅግና ጉዞ  አይነተኛ አበርክቶ እንዲኖራቸው በጥናት እየተደገፉ ነው፦ ክብርት ሸዊት ሻንካ ሐምሌ 30፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ  በጉባዔው ሁለ...
06/08/2026

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚመሩ ዘርፎች ለብልፅግና ጉዞ አይነተኛ አበርክቶ እንዲኖራቸው በጥናት እየተደገፉ ነው፦ ክብርት ሸዊት ሻንካ

ሐምሌ 30፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

በጉባዔው ሁለተኛ ቀን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በሴክተሩ ልማት ዙሪያ እያስጠና የሚገኘው የጥናት ሰነድ ገለፃ የሚደረግበት መርሀ ግብርን ማስተናገድ ሲጀምር መርሀ ግብሩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት ክብርት ሸዊት ሻንካ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚመሩ ዘርፎች ለብልፅግና ጉዞ አይነተኛ አበርክቶ እንዲኖራቸው በጥናት በተደገፈ ስትራቴጅክ አቅም እየተመሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በማከልም ሚኒስትሯ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚመሩ የባህል፣ የጥበብና የስፖርት ሴክተሮች ያላቸውን አቅም አሟጦ ለሀገር ጥቅም ለማዋል የሚያስችል ስትራቴጅክ አመራር ለመሰጠት በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ በርካታ ምሁራን የተሳተፉበትን ጥናት አስጠንቶ ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን አሳውቀው በመድረኩ የሚቀርቡ የጥናት ሰነዶች ላይ ጉባዔተኞች ግብአት የሚሆን ሀሳብ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በሴክተሩ ልማት ዙሪያ እያስጠና የሚገኘው ጥናት ለሀገር ኢኮኖሚ፣ ለማሕበራዊ ትስስር፣ ለአገር ገፅታ ግንባታ ከፍተኛ አበርክቶ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘም በጥናቱ ውጤት መሠረት፣ ዘርፎቹ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ያላቸው አበርክቶ ሲተነተን ጥቅል ድርሻቸው 2.52 መሆኑ ተገልፆል። በጥናቱ ከተካተቱት ንዑስ ዘርፎች በተናጠል ሲታይ የባህል ዘርፍ 38.44 በመቶውን ድርሻ በመያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ሲይዝ፣ ስፖርት በ31.65 በመቶ እንዲሁም የጥበብ ዘርፍ በ29.91 በመቶ በመያዝ በተከታታይ ተቀምጠዋል።

በጥናቱ በሶስቱም ዘርፎች ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች ተለይተው የተጠቀሱ ሲሆን ለአብነትም በቂ የግል ኢንቨስትመንት አለመኖር እና በመንግስት በጀት ላይ ያላቸው ጥገኝነት፣ ደካማ የፈጠራ ውጤቶች ባለቤትነት መብት ጥበቃ እና የዘርፉን መረጃዎች በሥርዓት ለመመዝገብ የሚያስችል የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት አለመኖር ተጠቃሸ ሆነዋል።

ጥናቱ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታትም አያሌ የፖሊሲ ምክረ-ሃሳቦችን አቅርቧል ለአብነትም ለዘርፉ የተለየ ብሔራዊ የሳተላይት አካውንት ማቋቋም፣ በዘርፉ ለሚሰማሩ አካላት የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን መስጠት፣ የሙያ ክህሎትን የሚያሳድጉ የልማት ስራዎችን እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በሴክተሩ ልማት ዙሪያ ባስጠናው አገራዊ ጥናት 3 ሺህ 904 ድርጅቶች እና 576 ተቋማት መሠረት የተደረጉበት መሆኑ ተገልጿል።

በጥናቱ ላይ በጥልቀት የተወያየው ጉባኤተኛ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጥናቱ ያገኘውን ትልቅ የእውቀት ሀብት በተግባር የሚተረጎምበት መደላድል በመፍጠር ወደ ስራ እንዲያሰገባ ጠይቋል።

በመጨረሻም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ የመደመር መንግስት ይህን ዘርፉ የህብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ መልክ መሳያ አቅም መሆኑን በማመን በከፍተኛ ትኩረት የሚደግፈው መሆኑን በመግለፅ ለተጠናው ጥናት ተግባራዊነት በሶስቱም ዘርፍ የሚገኙ አመራሮች፣ የሞያ ማህበራት እና ባለሞያዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።ሐምሌ 30፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባየባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለም...
06/08/2026

ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።

ሐምሌ 30፣ 2018ዓ.ም አዲስ አበባ

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለምትወክለው ሞዴል ሩት ይርጋለም የእንኳን ደስ አለሽና የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ።

ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሞዴሏ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ በድል እንድትመለስ ተመኝተዋል።

​ክብርት ሸዊት በንግግራቸው ሞዴሏ የባህል አምባሳደር ሆና ከተሾመች በኋላ የሀገሪቱን ብዝሃ ባህላዊ ዕሴቶች በቅርበት ለመረዳት በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ማድረጓን አንስተዋል።

በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ በመገኘት የህዝቡን ባህል፣ በአማራ ክልል ጎንደር በመሄድ የክልሉን ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ በመገኘት የገዳ ስርዓትንና ድቅ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን በበቂ ሁኔታ ጎብኝታለች ብለዋል።

​ይህ በክልሎች ያደረገችው ቆይታ የሀገሪቱን ባህልና ጥበብ ጠልቃ እንድታውቅ የረዳት ሲሆን፣ ከ130 በላይ የዓለም ሀገራት ሞዴሎች በሚሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያን በብቃት ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዛት ገልፀዋል።

​የገጠማትን ማንኛውንም ፈተና ተቋቁማ የሀገሯን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ አደባባይ ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ጠንካራ ወጣት በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እንደሚገባትም ክብርት ሸዊት ሻንካ አክለዋል።

ክብርት ሸዊት ​ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው መልዕክት በመጪው ውድድር ላይ በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ (Link) አማካኝነት ሁሉም ድጋፉን እንዲሰጥና ለሞዴሏ ስኬት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ሞዴል ሩት ይርጋለም በበኩሏ ለተደረገላት የሸኝትና መልካም ምኞት መርሀ ግብር ምስጋና አቅርባለች።

ሞዴሏ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ቆርጣ እንደተነሳች በመግለፅ የገጠማት ችግር ወደሗላ እንደማይመልሳት አንስታለች።

ከዓለም አቀፉ ውድድር በሗላም በሀገሯ ያሉ ባህላዊና ጥበባዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ እደምሰራ ገልፃለች።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ሴክተር አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና የሞዴሏ ቤተሰቦች ተገኝተው ለሞዴሏ የሀገር አደራ ተሰጥቷል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

በ2018 በጀት ዓመት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተከናወኑ ተግባራት ሀገርን የማሻገር ተልዕኮን የተወጡ እንደነበር ተገለፀ።ሐምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም  አዲስ አበባየባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ20...
06/08/2026

በ2018 በጀት ዓመት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተከናወኑ ተግባራት ሀገርን የማሻገር ተልዕኮን የተወጡ እንደነበር ተገለፀ።

ሐምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሴክተር ጉባኤ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም በቀጣይ ሦስት ዓመታት የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ላይ የሚመክርበት ጉባኤ ትላንት ከስዓት በኋላ ቀጥሎ ሲውል ጉባዔተኞች በቀረቡ የሪፖርት እና እቅድ ሰነዶች ላይ በስፋት በመምከር ሀሳቦችን አንሰተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ሸዊት ሻንካም ከጉባዔተኞች የተሰጡ ሀሳቦች ግብአት መሆናቸውን በመግለፅ በበጀት ዓመቱ በሚኒስቴር መስሪያቤቱና በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለው መዋቅር የተከናወኑ ተግባራት መንግስት ለስፖርት፣ ባህልና ጥበባት ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ተጠቅመን ተጨባጭ ለውጥ ያመጣንባቸው ነበሩ ብለዋል።

በማስከተልም ሚንስትሯ በ2019 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ ስታዲየሞችን በመጨረስ፣ የወጣውን የስፖርት ማህበራት ፖሊሲ በመተግበር፣ የህዝብ ክብረ በዓላትን የህዝብን አንድነት በሚያጎላ መንገድ በማክበር፣ መንግስት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰጠውን ግብ በማሳካት በዘርፉ የሀገራችን ብልፅግና ለማረጋገጥ መረባረብ ይገባናል ብለዋል።

የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር መኪዩ መሀመድ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በስፖርት ዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እንደ ሀገር የስፖርት ዕይታ ለውጥን በማምጣት በስፖርቱ ንቁ ብቁና አሸናፊ ሀገርን ለመገንባት በተከናወኑ ተግባራት በሀገር ውስጥ ያካሄድናቸው የስፖርት ውድድሮች ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት እና ለጋራ እሴት ግንባታ ተጠቅመንባቸዋል ብለዋል።

የኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት በጥበብ ዘርፉ ትልቅ ስኬት እንደ ተመዘገበ በመጥቀስ ለአብነትም በለውጡ መንግስት ጥበብን ወደ ህዝብ በሚል ሀሳብ በተጀመረው ስራ ለሃገራችን የጥበብ ዲፕሎማሲ ከ30 በላይ መድረኮችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በመፍጠር የሀገራችን ገፅታ የገነባንበት ከመላዉ ሀገሪቱ የተወጣጡ የጥበብ ሰዎች የተሳተፉበት የጥበባትና የፈጠራ ኢንድስትሪ ፖሊሲ ሰነድ የተዘጋጀበት ስኬታማ ዓመት መሆኑን በአስረጂ አብነት ለጉባዔተኛው ገልፀዋል።

የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ክብርት ነፊሳ አልማኸዲም በበጀት አመቱ በዘርፉ የምልክትና የግዕዝ ቋንቋን ጨምሮ በሀገራችን የሚገኙ 76 ቋንቋዎች ፕሮፋይል የተዘጋጀበት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የባህል ህክምና ባለሞያዎች ማህበርን በመመሰረት የሀገር በቀል እውቀትን ለህዝብ ጥቅም ለማዋል ውጤታማ ስራ የተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል።

ጉባዔው የዛሬው ውሎውን ሲያጠናቅቅ በ2018 በጀት ዓመት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተከናወኑ ተግባራት ሀገርን የማሻገር ተልዕኮን በብቃት የተወጡ እንደነበሩ መግባባት ላይ ተደርሶበታል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡ https://t.me/MoCSofficial

ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/cultureandsportethiopia?mibext

ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMAV65gyo/

ትዊተር/ኤክስ፡https://x.com/Mocs_20252017?t=tdzYOBsTjbL7y-JBgDKIBQ&s=09

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Culture & Sport-Ethiopia:

Shortcuts

Share