War crimes Documentation Center

War crimes Documentation Center The ongoing silent genocide on Ethnic Amhara is undermined and ignored by the whole world.

Fact!
30/09/2025

Fact!

30/09/2025

በሰሜን ወሎ የአገዛዝ ሥርዓቱ በፈጸመው የድሮን ጥቃት በሕክምና ላይ የነበሩ ታካሚዎች ከነ አስታማሚዎቻቸው የተገደሉ ሲሆን ማዋለጃ ክፍል ውስጥ ገና የወለደች እና ሌላኛዋ በምጥ ላይ የነበረች ነፍሰጡርም ተገድለዋል።

ፋሽስት ጣሊያንም በወረራው ዘመን የፈጸመው ከዚህ የተለየ አልነበረም። ያኛው የውጪ ወራሪ መሆኑ ነው። ከተፋላሚዎች የሚደርስን ጥቃት በንጽሐን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ በመፈጸም ለማወራረድና ለመበቀል መሞከር እጅግ የለየለት የግፍ ግፍ፣ ጭካኔና ፋሽስታዊ ባህሪ ብቻ ሳይሆን ከባድ ወንጀልም ነው። ይህን የአገዛዙን ወንጀል ለመሸፋፈን የምትደክሙ ጋዜጠኞች፣ ተከፋይ አክቲቪስቶችና ልሂቃን እያደረጋችሁት ያለው ነገር ለወንጀሉ ተባባሪ ከመሆን አይተናነስም። ከፋኖም የይሁን ከሽኔ ጋር ከተቻለ ሰላም ማውረድ ካልተቻለም ጦርነቱን ከተፋላሚዎቹ ጋር ብቻ ማድረግ ሲገባ እየደጋገሙ ንጹሃንን በድሮን እየጨፈጨፉ ሕግ የማስከበር እርምጃ ወይም ከጦርነት የሚጠበቅ ክስተት ለማስመሰል ብዙ እርቀት የምትሄዱ የብልጽግና ልሂቃን ነገ የማታርሙት፣ ስማችሁ በጥቁር ቀለም ተጽፎ በአደባባይ የምትሸማቀቁበትና ታሪክ በነውረኝነትና በጭካኔ የሚያወሳችሁ መሆኑን ልብ በሉ።

እመጫትና ነፍሰጡር በድሮን እየገደሉ ሕግ ማስከበር የለም። ከወንጀልም የከበደ ወንጀል ነው።
Dr Yared Hailemariam

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ተመራማሪው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው!የታሪክ እውነቶችን በመናገራቸው ወንጀለኛ ተብለው በብልፅግና ዳኞች 6 ዓመት ከ 4 ወር የተፈረደባቸው ጋዜጠኛ እና...
18/12/2024

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ተመራማሪው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው!

የታሪክ እውነቶችን በመናገራቸው ወንጀለኛ ተብለው በብልፅግና ዳኞች 6 ዓመት ከ 4 ወር የተፈረደባቸው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ተመራማሪ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በደረሰባቸው ግፍ ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው::

የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ጌዲዮን አቶ ታዲዮስ በይቅርታ እንዲፈቱ ቢወስንም አቶ ተስፋዬ ዳባ የተባለ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ ደውሎ ሊፈቱ ነው በማለቱ አቶ ሽመልስ በቀጭን ትዕዛዝ ለፍትህ ሚኒስትሩ እንዳይፈቱ ይፈረድባቸው ብሎ በማዘዙ ነው የተፈረደባቸው::

ጋሽ ታዲዮስ ባለፋት ሁለት አመታት በደረሰባቸው ግፍ ታመው በቃሊቲ ማረሚያ ጤና ጣቢያ ጉልኮስ ተደርጎላቸው ተኝተዋል:: በካቲተር ሽንት እየሸኑ የነበረ ቢሆንም አሁን ደም በቱቦው እየፈሰሳቸው ነው:: በተጨማሪም ፕሮስቴት ካንሰር ስለተገኘባቸው የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ በሀኪሞች ቢታዘዝም ብልፀግናው ህክምና ከልክሎ እንደ ፕሮፌሰር አስራት ሊገድላቸው ነው::

እባካችሁ ድምጽ ሁኗቸው
የቃሊቲ እስረኞች ነን!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when War crimes Documentation Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share