28/08/2026
#ማስታወቂያ
በክፍለ ከተማው ለምትገኙ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ!
የካ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሥራ ቦታዎች ላይ ተደራጅተው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች የ2019 በጀት ዓመት የውል ማደሻ ጊዜ ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሆኑን በመግለጽ ውላቸውን ያላደሱ አካላት በአስቸኳይ ቀርበው እንዲያድሱ ጥሪ እናቀርባለን።
ጽ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የውል ማደስ ሂደቱ የሚመለከተው የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ያልሞላቸውን ኢንተርፕራይዞች እንደሆነ ያሳወቀ ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውላቸውን በማያድሱት ላይ መመሪያውን ተከተሎ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል።
-ውል ለማደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦
-የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የነዋሪነት መታወቂያ
-ነባር የኪራይ ውል እና የታደሰ የደረጃ ዕድገት ማስረጃ
-የኪራይ ክፍያ ደረሰኝ
-የግቢ ኮሚቴ ግዴታዎችን በአግባቡ መወጣታቸውን የሚያረጋግጥ የኮሚቴ ማረጋገጫ
ኢንተርፕራይዞች እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማደስ ኃላፊነታችንን እንወጣ!!!