Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ

Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማችንን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት !!
(1)

ይህ የፌስቡክ ገጽ ትክክለኛው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

This is the official page of Kolfe Keranio Communication.

በክፍለ ከተማው የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት  መጪውን በአላት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶችን በስፋት ማቅረባቸውን ገለፁ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30/2018 ዓ.ምመጪውን  በአላት ም...
05/09/2026

በክፍለ ከተማው የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት መጪውን በአላት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶችን በስፋት ማቅረባቸውን ገለፁ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

መጪውን በአላት ምክንያት በማድረግ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በክፍለ ከተማው የሚገኙ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ዝግጅት ማድረጋቸው ገልፀዋል።

በክፍለ ከተማው የሚገኙ የወይራ ቤተል፣ራዕይና ጀሞ የህብረት ስራ ማህበራት ለበአሉ የኢንዱስትሪና የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን በቂ ምርትም እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ለበአሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ጤፍ፤ የጥራጥሬ እህሎች፤ዘይት፤ ሽንኩርት፤ እንቁላል ፤ ቅቤና ፣ ዱቄት የመሳሰሉ ምርቶችን ማቅረባቸዉንም ጠቁመዋል።

የክፍለ ከተማው የህብረት ስራ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀረግ አብርሀ እንዳሉት በክፍለ ከተማዉ በሚገኙ 13 የሸማች ህብረት ሰራ ማህበራት እና 1 ዩንየን መጪውን በአል ታሳቢ ያደረጉ የግብርናና የኢንዱስትሪ እና ለበአሉ የሚያስፈልጉ ምርቶችን በበቂ መጠን መኖሩን ገልፀዋል።

ማህበራቱ አስፈላጊዉን ዝግጅት ማድረጋቸዉን የጠቀሱት ሀላፊዋ ለበአሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ጤፍ፤ የጥራጥሬ እህሎች፤ዘይት፤ ሽንኩርት፤ እንቁላል ፤ ቅቤና ዱቄት የመሳሰሉ ምርቶችን በማቅረብ ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

በአላቱን ታሳቢ ያደረጉ መሰረታዊ የፎጆታ ምርቶች በማህበራቱ ሱቆችና መጋዘኖች በቂ መጠን መኖሩንና በቀጣይ ቀናቶችም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የገለፁት ወ/ሮ ሀረግ አንድ ኪሎ ስጋም በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ስጋ ቤቶች በ1200 ብር እንደቀረበም አንስተዋል።

ሲገበያዩ ያገኘናቸው ሸማቾች እንደገለፁት በአቅራቢያቸው በሚገኙ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እየተሻሻለ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ባለድርሻ አካላት ተናገሩ። ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30 /2018 ዓ.ም የኮልፌ ቀራኒ...
05/09/2026

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እየተሻሻለ መምጣቱን ያነጋገርናቸው ባለድርሻ አካላት ተናገሩ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30 /2018 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎች በማከናወን በአዕምሮ የበለፀገ ትውልድን ለማፍራት ዘርፈብዙ ተግባራት ማከናወኑን ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት ገልፀዋል።

ከኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ጋር ቆይታ ያደረጉ የትምህርት ባለደርሻ አካላት እንደገለፁት በክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት በ2018 በጀት አመት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ከመፍጠር በተጨማሪ የትምህርት መሰረተ ልማቶች፣ የትምህርት ለትውልድ ስራዎች፣ ማህበራዊ ፍትህ ለማስፈን የተማሪዎች ምገባ ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውን ተናግረዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ በበኩላቸው ትምህርት የነገው ሀገር ተርካቢ ትውልድ ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር በማሻሻል፣ ሰፋፊ የትምህርት ቤት ማስፋፍያዎች በመገንባት፣ የተምህርት ግብአቶች በሟማላት፣ እንዲሁም ሰለማዊ የመማር ማስተማር በመፍጠር በፈጠራ የተካነ ትውልድ በመገንባት ረገድ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም በክፍለ ከተማውም የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነት ለማስፋት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ380 ሚሊየን ብር በላይ ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ የትምህርት ቤት ደረጃ የማሻሻል፣ ት/ቤቶች ከፈረቃ ትምህርት ለማስቀረት የሚያስችሉ አዳዲስና የማስፋፊያ የትምህርት ቤቶች ግንባታዎች ስራ መሰራቱንም ጨምረው ተናግረዋል።

በክፍለ ከተማው ያለፈው አመት የትምህርት ጉባኤ አፈፃፀምና 33ኛው የትምህርት ጉባኤ የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ የትምህርት አመራሮች፣ በዘርፉ ያሉ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂደዋል ፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ   አስተዳደር «የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም» በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሔደ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30/2018 ዓ.ምበመድረኩ ከ11 ...
05/09/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር «የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም» በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሔደ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

በመድረኩ ከ11 ዱም ወረዳዎች የተወጣጡ ወጣቶችና የተሳተፉ ሲሆን የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም» በሚል ሰንድ ቀርቦ ውይይትም ተካሔዶበታል ።
የክፍለ ከተማው የወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሳሙኤል አበበ እንዳሉት ውይይቱ ወጣቶች ዘላቂ ሰላም በማፅናት ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ከፊታችን የሚከበሩ የዘመን መለወጫ ፣መስቀልና ኢሬቻ በአላት ሰላማዊና ትውፊታቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ ወጣቶች ሚናቸውን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ሀይሉ በበኩላቸው ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማውን ብሎም የአኪባቢያቸውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ተሳትፎዋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

አቶ ደሳለኝ አክለው ወጣቶች ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲጠናቀቁ በትኩረት እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ከኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጋር ቆይታ ያደረጉ ወጣቶች እንደተናገሩት ወጣቶች በከተማዋ በሚከናወን የሰላም እና የፀጥታ ስራዎች ላይ ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በክፍለ ከተማ አስተዳደር "የምልክት ቋንቋን አካታችነት በማሳደግ አገልግሎትን ለመስጠት   እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 30 /2018የ...
05/09/2026

በክፍለ ከተማ አስተዳደር "የምልክት ቋንቋን አካታችነት በማሳደግ አገልግሎትን ለመስጠት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 30 /2018

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን አካታች ለማድረግ የምልክት ቋንቋን ተደራሽነት በማስፋት በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች በምልክት ቋንቋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑንና በቀጣይም በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተመላክቷል።

"የምልክት ቋንቋ አካታችነት ለማህበረሰብ ግንባታ" በሚል ሀሳብ የክፍለ ከተማው ባህል ኪነጥበብ ጽህፈት ቤት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በምልክት ቋንቋ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ባለሙያዎች ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የምልክት ቋንቋ ለአካታች ማህበረሰብ የሚለው አካታች ፓሊሲ ትግበራ አስፈላጊ እንደሆነም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑሩ በርጌቾ እንዳሉት አካታች ማህበረሰብ እንዲሁም አካታች አገልግሎት ለመስጠት የምልክት ቋንቋን ተደራሽነት ማስፋት ይገባል ብለዋል።

ኃላፊው አክለው መስማት የተሳናቸው ነዋሪዎች አገልግሎት ፈልገው ወደ ክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በሚመጡበት ወቅት ተገቢውን እገዛና አገልግሎት ለመስጠት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ቋንቋውን መማርና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ከአስተዳደሩና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

"ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ ለጎርፍ አደጋ ስጋት ሊሆን አይገባም!" በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  አስተዳደር  የክረምት የፅዳት ንቅናቄ መርሃግብር በዛሬው እለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በ...
05/09/2026

"ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ ለጎርፍ አደጋ ስጋት ሊሆን አይገባም!"

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የክረምት የፅዳት ንቅናቄ መርሃግብር በዛሬው እለትም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬው እለት በክፍለ ከተማ ደረጃ በማእከልነት በወረዳ 10 አባጃሌ አካባቢ በተካሔደው የፅዳት ንቅናቄ ላይም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የፀጥታ አካላት ፣የፅዳት ማህበራት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን እንደገለፁት የክረምት የፅዳት ንቅናቄው ክፍለ ከተማውን ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ ለማድረግ ሚና ያለው ሲሆን
በክረምት ወቅት የተጀመሩ የፅዳት ንቅናቄ ተግባራትም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቶፊቅ በድሩ በበኩላቸው ጽዳት የዘመናዊነት መገለጫ እንደሆነ ገልፀው ከቡሎክ ጀምሮ ተከታታይነት ያላቸውን የፅዳት ተግባራትን በማከናወን በወረዳው የተጀመሩ ተግባርን ተጠናክረው መቀጠላቸውን አንስተዋል።

መርሐ ግብሩም "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ አደጋ ሊሆን አይገባም" በሚል መሪ ቃል የተካሔደ ሲሆን ንቅናቄው የጎርፍ ስጋትን አደጋን ለመከላከል ሚና አለው።

በዛሬው እለት በተከናወነው የፅዳት ንቅናቄም ክፍት ቦታዎችንና የውሃ መውረጃ ትቦዎች የማፅዳት ስራም ተከናዉኗል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን፣የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቦጋለች፣የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኢብራሒም መሐመድ እና ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 30 /2018 ዓ.ም

የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ ጥምር አባላት ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ዝግጁነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን  ነሐሴ 29/2018 ዓ.ምበኮ...
04/09/2026

የሰላም ሰራዊትና የጸጥታ ጥምር አባላት ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ዝግጁነታቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 04፣ 06፣ 07 እና 08 የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላትና የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እንዲሁም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጋቸና ሲርና በተገኙበት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት በተደራጀ መልኩ ተሰጥቷል።

በስምሪቱ ወቅት የተገኙት የአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዋና አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ እንደገለፁት የጳጉሜ ቀናትን ጨምሮ መጪው አዲስ ዓመት ህዝባዊና የአደባባይ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ በዓላቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የሰላም ሰራዊትና መላው የፀጥታ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ የጀመሩትን ስራ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታሁን አክለው የህዝብን ተሳትፎ በማሳደግ ማህበረሰቡን በፀጥታ ስራ ላይ ባለቤት ማድረግ ስራዎች መጠናከር እንደሚገባም ገልፀዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን በበኩላቸው በሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተግባር በግንባር ቀደምትነት እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል።

ከፊታችን የሚከበሩ በዓላት ሰላማዊ እንዲሆኑም የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የክፍለ ከተማው ወረዳ 07 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ቱሉ በአንድ ማዕከል የሚሰጡ የተቀናጁ የፀጥታ ስምሪቶች ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል።

በዚህ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት መርሃ-ግብር ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የሰላም ሰራዊት፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ ጋቸና ሲርና እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

04/09/2026

#አገልግሎት አሰጣጥ ቅኝት

''አገልግሎት አሰጣጥ ከተገልጋይ አንደበት በኮልፌ''

#ኮልፌ ዜና

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፦
https://linkmix.co/48811202

በክፍለ ከተማው አስተዳደር አዲስ አመት በዓልን  አስመልክቶ  የተዘጋጀው ባዛር ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ።ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ ...
04/09/2026

በክፍለ ከተማው አስተዳደር አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው ባዛር ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ተገለፀ።

ኮልፌ ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 29 /2018 ዓ.ም

በክፍለ ከተማው አስተዳደር መጪው አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ በትላንትናው እለት በአየር ጤና አደባባይ የተከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ በባዛሩ ላይ የተለያዩ ምርቶችን ያቀረቡ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በአየር ጤና አደባባይ በተከፈተው ኤግዚብሽን እና ባዛር በክፍለ ከተማው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ኢንተርፕራይዞች ፣ ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት፣ አርሶ አደሮች እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የሚሰሩ ነጋዴዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የባዛሩ ተሳታፊዎች እንዳሉት አዲስ አመትን አስመልክቶ ጥራትና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ ምርቶችን ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

በኤግዝብሽኑ የባህል አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ማርና የማር ውጤቶች፣ የኢንደስትሪ ምርቶች ፣ የግብርና ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ለበአል የሚውሉ የተለያዩ ምርቶችን መቅረቡንም አብራርተዋል።

04/09/2026

በክፍለ ከተማው አስተዳደር አዲስ አመት በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው ኤግዚብሽንና ባዛር

ለአዲስ ዓመት በቂ  የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ!የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶ...
04/09/2026

ለአዲስ ዓመት በቂ የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ!

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማዋ ነዋሪዎች መቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኮሚሽኑ የገበያ ጥናትን መሠረት በማድረግ በበዓላት ወቅት በገበያ ላይ የሚፈጠረውን ፍላጎት በመለየት በቂ የፍጆታ ምርቶች እንዲቀርቡ በስፋት መስራቱን ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሽታዬ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ ከአምራቾች፣ ከአስመጪዎች፣ ከዩኒየኖችና ከተለያዩ የኀብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመተባበር የምርት ትስስር በመፍጠር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች እንዲሁም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች በበቂ መጠን መቅረቡን አስረድተዋል።

እነዚህ ምርቶች በከተማው በሚገኙ በዘመኑ 700 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ በአዲስ ዓመት ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በ154 የኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በስፋት ለሸማቹ እየቀረቡ መሆናቸውን ኮሚሽነሯ ገልጸዋል።

ከነፃ ገበያው ጋር ሲነፃፀር በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡት እነዚህ ምርቶች የከተማዋን ነዋሪዎች የበዓል ፍላጎት በማሟላት የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና ገበያውን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በበዓሉ ወቅት 27/4 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሉካንዳ ሥጋ ቤቶች ሥጋን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ዝግጅት መደረጉን ወ/ሮ ሽታዬ ገልጸው፤ ይህም በበዓሉ ወቅት የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

ዋና ኮሚሽነሯ በመጨረሻ ህብረተሰቡ ምርቶቹን ከኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች፣ ከኤግዚቢሽንና ባዛር ማዕከላት እንዲሁም ከቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በመግዛት ከተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኮሚሽኑም በበዓላት ወቅት የምርት አቅርቦትና የገበያ መረጋጋት ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ መከታተሉን አረጋግጠዋል።

Address

Kolfe
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share