Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ Ethiopian Press Agency is a public media enterprise operating in Ethiopia.
(255)

የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በ2019 በጀት ዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ጭነት ለማጓጓዝ አቅዷል++++++++++++++++  - የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በተያዘው የ2019 በጀ...
01/09/2026

የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በ2019 በጀት ዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ጭነት ለማጓጓዝ አቅዷል
++++++++++++++++

- የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በተያዘው የ2019 በጀት ዓመት 9 ቢሊዮን ቶን ጭነት ለማጓጓዝ ማቀዱንና ተቋሙን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የተቋሙ የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዋና ክፍል ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ኃይለማርያም እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት 7 ቢሊዮን ቶን ጭነት አጓጉዟል። በጀት ዓመቱ 157 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል። ከ500 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

በዚህ በጀት ዓመት ደግሞ ከባለፈው ዓመት በ2 ቢሊዮን ቶን ብልጫ ያለው 9 ቢሊዮን ቶን ጭነት በማጓጓዝ የሕዝብ አገልጋይነቱንና ትርፋማነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የ2019 በጀት ዓመት በ50 ቢሊዮን ብር የካፒታል ኢንቨስትመንት አይሲቲን (ICT) ጨምሮ የተቋሙን አሠራር ለማቀላጠፍና የጭነት ሂደቱን ከመነሻ እስከ መዳረሻ በቴክኖሎጂ ለመቆጣጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 850 ሚሊዮን ብር ማዳን የቻለ ሲሆን፣ ከደረቅ ወደቦች፣ ከፋይናንስና ቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሥራት የደንበኞችን የጊዜና የገንዘብ ብክነት ለመቀነስ ማቀዱንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በመካከለኛው ምሥራቅ በተከሰተው የፖለቲካ ውጥረት ምክንያት ጊቤ የተባለችው መርከብ በሆርሙዝ ሰርጥ ለ116 ቀናት ለመቆም መገደዷ፣ የዱቤ ተጠቃሚዎች ክፍያ አለመፈጸም፤ በጂቡቲ ወደብ ብቻ መወሰን በሥራው ላይ ጫና ፈጥረው እንደነበር አቶ ስንታየሁገልጸዋል።

በክፍለዮሐንስ አንበርብር

#ኢትዮጵያ

ለመጪው አዲስ ዓመት የፍጆታ ዕቃዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓል-  የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ+++++++++++++++++   - በአዲስ አበባ ለዘመን መለወጫ በዓል የፍጆታ ...
01/09/2026

ለመጪው አዲስ ዓመት የፍጆታ ዕቃዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓል
- የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ
+++++++++++++++++

- በአዲስ አበባ ለዘመን መለወጫ በዓል የፍጆታ ዕቃዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ። ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ምርቶችም ወደ ከተማዋ ገብተዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን 2019 ዓም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በተደረገው ዝግጅት ላይ በሰጡት መግለጫ፤ በከተማዋ ለአዲስ ዓመት የገበያ አቅርቦትና ቁጥጥር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የአቅርቦትና የሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መሠራቱንም ያነሱት ቢሮ ኃላፊዋ፤ በአዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሚገኙ ሰባት የንግድ ማዕከላት፣ በ264 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በአምስቱ የቁም እንስሳት ገበያዎች በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ንግድ ሥራዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የበዓል ባዛር መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

ከምርት አቅርቦት በተጨማሪ በመጋዘን ውስጥ ምርት የመሸሸግና የክምችት ድርጊት እንዳይኖር ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል ያሉት ወይዘሮ ሀቢባ፤ ሕገ-ወጥ ደላሎች፣ ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች ወደ ገበያ በሚያስገቡና ያለአግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ

#ኢትዮጵያ

የኃይማኖት ተቋማት የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ጽናት በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲገነባ ከፍተኛ ሚና አላቸው - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ+++++++++++++++++   - የኃይማኖት ተቋማት፣ የእም...
01/09/2026

የኃይማኖት ተቋማት የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ጽናት በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲገነባ ከፍተኛ ሚና አላቸው
- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
+++++++++++++++++

- የኃይማኖት ተቋማት፣ የእምነት መሪዎችና አገልጋዮች የሕዝባችን የሞራልና የሥነምግባር ዋና ጠባቂዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ እንደገለጹት፤ የእምነት መሪዎች፣ ተቋማትና አገልጋዮች የሕዝባችን የሞራልና የሥነ-ምግባር ዋና ጠባቂዎች ናቸው።

ኢትዮጵያ ተከታታይ ትውልዶች በሐሳባቸው፣ በጉልበታቸው፣ በደማቸውና በጸሎታቸው የገነቧት ታላቅ ሀገር መሆኗን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ የሃይማኖት ተቋማት የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ጽናት በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲገነባ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ገልጸዋል።

የእምነት መሪዎች በጨለማ ውስጥ ብርሃንን የሚፈነጥቁ መብራቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለዘመናት የተገነባውን መተሳሰብ ለመሸርሸር የሚጣጣሩ አካላትን መከላከል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

መንግሥት የእምነት ተቋማት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ዕድገት የሚያደርጉትን የላቀ አስተዋጽኦ ድጋፍ ያደርጋል።

የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው፣ የሃይማኖት ተቋማት ሀገራዊ አንድነትን፣ አጋርነትንና ወዳጅነትን ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ዓመታት በሰላምና በአብሮነት በርካታ ችግሮችን በጋራ ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን በትብብርና በአንድነት በመቆም የበለፀገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል የሃይማኖት ተቋማትን በማስተባበር፣ በሀገራችን አብሮነትን ለመገንባትና ሰላምን ለማፅናት አበራች ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በማርቆስ በላይ

#ኢትዮጵያ

በሁለት በሬ ዋጋ ሦስት የግብርና ሥራዎችን የሚያከናውነው ትራክተር++++++++++++  - አንድ አርሶ አደር ማረስ ሲፈልግ በሬ፣ ማጨድ ሲደርስ የሰው ጉልበት፣ ለመስኖ የውኃ ፓምፕ ያስፈልገዋ...
01/09/2026

በሁለት በሬ ዋጋ ሦስት የግብርና ሥራዎችን የሚያከናውነው ትራክተር
++++++++++++

- አንድ አርሶ አደር ማረስ ሲፈልግ በሬ፣ ማጨድ ሲደርስ የሰው ጉልበት፣ ለመስኖ የውኃ ፓምፕ ያስፈልገዋል። እነዚህ ሁሉ አንድ ላይ ሲደመሩ የግብርና ሥራ ወጪንና ጉልበትን ይጨምራሉ።

በተለይ የአጨዳ ወቅት ሲደርስ በቂ የሰው ጉልበት ካልተገኘ አርሶ አደሩ በወራት የደከመበትን ምርት በሜዳ ላይ ለብክነት ሊዳርግ ይችላል። ይህ ሁኔታ አብዛኛውን አርሶ አደር በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያመርት ከሚገድቡት ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።

ይህንን ችግር ከራሱ አካባቢ በመመልከት መፍትሔ ለመፍጠር የተነሳው ወጣት ሰለሞን ቡታ የተለየ አማራጭ ይዞ ቀርቧል። በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ተቋም ሥር በመሆን ማረስ፣ ማጨድና የመስኖ ውኃ መጥለፍ የሚችል ባለብዙ ጥቅም ትራክተር ሠርቷል።

ፈጠራውን ልዩ የሚያደርገው ሦስት የግብርና ሥራዎችን በአንድ ማሽን ማከናወኑ ብቻ ሳይሆን፤ አርሶ አደሩ በሚችለው ዋጋ እንዲገዛው ታስቦ መሠራቱ ነው። የትራክተሩ ዋጋ ከሁለት በሬዎች ዋጋ ጋር ተቀራራቢ መሆኑን ወጣት ሰለሞን ያስረዳል።

ትራክተሩ በማጨድ ሥራ አንድ ሄክታር መሬትን በአራት ሰዓታት ውስጥ ማጨድ ይችላል። በማረስ ሥራ በአራት ሰዓታት ግማሽ ሄክታር መሬት ማረስ የሚችል ሲሆን፤ የመስኖ ውኃን ከወንዝ በፓምፕ በማንሳት በአራት ሰዓታት አንድ ሄክታር መሬት ማጠጣት ይችላል።

እንደ ወጣቱ ገለጻ፣ ቀደም ሲል አንድ ሄክታር ምርት ለመሰብሰብ ከ30 እስከ 50 ሰዎች እና እስከ 30 ሺህ ብር የሚደርስ ወጪ ይጠይቅ ነበር። ትራክተሩ ግን ይህንን ሥራ በአራት ሰዓታት ውስጥ ማከናወን ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ የማሽኑ የማጨጃ ሥርዓት በከፍተኛ ፍጥነት (RPM) የሚቆርጥ በመሆኑ በአጨዳ ሂደት የሚከሰተውን የእህል ብክነት ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ዝቅ ያደርገዋል።

ማሽኑ ከውጭ ከሚመጡ ትራክተሮች የሚለየው የጊር ቦክስ አካሉ እዚሁ ሀገር ውስጥ የተሠራ በመሆኑና እንደ አስፈላጊነቱ ሞተሩን በመቀየር በናፍጣ፣ በጋዝና በኤሌክትሪክ ኃይል መሥራት የሚችል በመሆኑ ነው። በጋዝና በኤሌክትሪክ መሥራቱ ደግሞ የአየር ብክለትን ለመቀነስ አማራጭ ይሰጣል።

ዋና ዓላማ ሦስቱን የግብርና ሥራዎች በአንድ ማሽን ከማከናወን ባለፈ፣ ዝናብን በመጠበቅ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያመርተው አርሶ አደር የመስኖ አቅምን በመጠቀም በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ እንዲያመርት ማስቻል ነው።

በኦሮሚያ ክልል ፊቼ ሰላሌ ተወልዶ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ስቲም (STEM) ሴንተር ያደገው ወጣት ሰለሞን፤ ከ12ኛ ክፍል በኋላ ፌደራል ቴክኒክና ሙያን በመቀላቀል የተለያዩ ትምህርቶችን ተምሯል። ይህን ማሽን ከዲዛይን ጀምሮ ለመገንባት ሦስት ወራት የፈጀበት ሲሆን፤ ቀን በሀገራዊ ምክክር ፕሮግራም የበጎ ፈቃድ ሥራ ሲያከናውን ማታ ደግሞ ማሽኑን ይሠራ እንደነበር ያስታውሳል።

በአሁኑ ወቅት አንድ ማሽን ወደ ክፍለ ሀገር ተልኮ ለአራት ወራት ያህል ያለችግር እየሠራ ይገኛል። ተሠርተው የተዘጋጁ ማሽኖች ያሉ ሲሆን፤ በትዕዛዝ መሠረት የማሽኑን ስፋት እስከ 3 ሜትር በማስፋት የአራት ሰዓቱን ሥራ ወደ ሁለት ሰዓት ዝቅ ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል።

ለዚህ ስኬት የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ተቋም ያደረገለት የቁሳቁስ፣ የስልጠናና የእውቀት ድጋፍ፣ እንዲሁም የቤተሰቦቹና የጓደኞቹ ማበረታቻ ከፍተኛ እንደነበር ገልጾ፤ በቀጣይም የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍ በቴክኖሎጂ የመለወጥ ትልቅ ምኞት እንዳለው ተናግሯል።

በሄለን ወንድምነው

# #ግብርና ቴክኖሎጂ #ፈጠራ #ትራክተር #ኢትዮጵያ

የማዕድን ቦታዎችን መልሶ ለማልማት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከፍ ሊደረግ ነው++++++++++++++  - በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የማዕድን ቦታዎችን መልሶ ለማልማት ሲባል የማዕድን አውጭዎች ...
01/09/2026

የማዕድን ቦታዎችን መልሶ ለማልማት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከፍ ሊደረግ ነው
++++++++++++++

- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የማዕድን ቦታዎችን መልሶ ለማልማት ሲባል የማዕድን አውጭዎች የሚያስይዙት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የሚያደርግ አዲስ መመሪያ ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በባለሥልጣኑ የሥርዓተ ምኅዳርና ብዝኃ ሕይወት አያያዝ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ይታገሱ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የማዕድን ሥራ ከተከናወነ በኋላ ቦታውን መልሶ በማልማት የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር ለመጠበቅና ለአደጋ የሚያጋልጡ ጉድጓዶችን ለመድፈን እየተሠራ ይገኛል።

የመልሶ ማልማት ሥራው የመጀመሪያው በአካላዊ መንገድ አፈር በመመለስና በማስተካከል ቦታው የሚዘጋጅበት ሲሆን ሁለተኛው ሥነ-ሕይወታዊ ልማት በሆነ መንገድ በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት የማዕድን ቦታዎቹን ሥነምኅዳር በሚመልስ መልኩ የሚተገበር ነው ብለዋል።

በቀድሞው መመሪያ መሠረት ለዚህ መልሶ ልማት ሥራ አራት ሺህ ሄክታር መሬት የቆፈረ ማዕድን አልሚ ከ200 እስከ 300 ሺህ ብር ብቻ የሚያስይዝበት ነባራዊ ሁኔታ ነበር። ይህም አልሚዎች የመልሶ ማልማት ግዴታቸውን ሳይወጡ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ ዕድል ፈጥሮ እንደነበር ጠቅሰው አልሚው አካባቢውን ጥሎ ቢሄድ እንኳ ተቋሙ በተያዘው ገንዘብ የመልሶ ማልማት ሥራውን ለማከናወን የሚያስችለው በቂ በጀት አልነበረም።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለማዕድን ቦታዎች መልሶ ልማት የማዕድን አውጭዎች የሚያስይዙት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የሚያደርግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ያስረዱት ዳይሬክተሩ፤ አዲሱ መመሪያ አልሚዎች አካባቢውን ጥለው ቢሄዱ ተቋሙ በተሰበሰበው በቂ ማስያዣ ገንዘብ መልሶ ማልማቱን ለማከናወን የሚያስችለውና ወቅቱን የዋጀ አሠራርን ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

ባለሥልጣኑ የቁጥጥር ሥርዓት ከማዘጋጀት ባለፈ በክረምት መርሐ-ግብሮች ከማዕድን አልሚዎች ጋር በመተባበር በቦታዎቹ ላይ ከ24 ሺህ 350 በላይ ችግኞችን መተከሉን ጠቅሰው፤ የችግኝ ተከላው የመልሶ ማልማቱ አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከ180 በላይ የማዕድን አልሚዎች እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ቴዎድሮስ፤ ባለሥልጣኑ ከቅጣት እርምጃ በፊት በቅድሚያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት መግባባት ለመፍጠርና የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲሱ መመሪያ፣ አዋጆች እንዲሁም የፌደራል ደንብ አስገዳጅነት እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግና ሕጋዊ አሠራርን ሳይከተሉ በሚሠሩ አልሚዎች ላይ እንደ ጥፋት ደረጃቸው እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት፣ የንብረት መወረስ፣ የፈቃድ ስረዛ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በፍትሐ ብሔር ሕግ የመጠየቅ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስረድተዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን

#ማዕድን #አካባቢጥበቃ #ኢፕድ #ኢትዮጵያ

የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረጽ ኢትዮጵያን በጋራ ገንብተዋል— ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ++++++++++++++++++   - በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋ...
01/09/2026

የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረጽ ኢትዮጵያን በጋራ ገንብተዋል
— ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ
++++++++++++++++++

- በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረጽ ኢትዮጵያን በጋራ መገንባታቸውን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

የጉባኤው ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት የሰላም መልእክት በማስተላለፍ፣ ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረጽ ኢትዮጵያን በጋራ ገንብተዋል።

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ደማቅ ታሪክ ያላት፣ የብዙ ሕዝቦች፣ ባህሎችና ቋንቋዎች የጋራ ቤት መሆኗን የጠቀሱት ቀሲስ ታጋይ፤ የአንድነታችንና የመከባበራችን እሴት በዓለም ፊት ደምቀን እንድንታይ ያደረገን የወል ሀብታችን ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያዊነትና ሃይማኖት እንደ ውብ የጥበብ ልብስ የተሳሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ጸሐፊው፤ «ሃይማኖታችን የግላችን፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የጋራ ቤታችን ናት» ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት የሰላም መሠረት በመሆናቸው አለመግባባቶች በውይይትና በመንፈሳዊ አስተምህሮዎች ብቻ እንዲፈቱ አብክረው ማስተማር እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በማርቆስ በላይ

#ኢትዮጵያ

01/09/2026

"የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በራስ አቅም የተቀናጀ ተቋማዊ የለውጥ እርምጃም ተትቶ የቆየውን የሥራ ቦታ ወደ ማራኪ የሥራ ከባቢነት ለመቀየር አስችሎታል" -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

"በአረንጓዴ ዐሻራ አትርፈናል፤ በቡና አትርፈናል፣ በፍራፍሬ አትርፈናል፤ በሻይ ልናተርፍ ነው፤ የድህነትና የችግር ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ያ መልኳና ስሟ እየተቀየረ ነው። ያ የሚቀየረው ግ...
01/09/2026

"በአረንጓዴ ዐሻራ አትርፈናል፤ በቡና አትርፈናል፣ በፍራፍሬ አትርፈናል፤ በሻይ ልናተርፍ ነው፤ የድህነትና የችግር ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ያ መልኳና ስሟ እየተቀየረ ነው። ያ የሚቀየረው ግን ደክመን ነው፣ ጭቃ ነክተን ሰርተን ነው፤ ማንም ሊሰራልን አይችልም"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከመስከረም እስከ መስከረም መጽሐፍ፣ 8ኛ ቅጽ፣ገጽ 243

በወርሀ ሐምሌና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቁልፍ ተግባራት ቅኝት++++++++++++++++++✍️ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐግብር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስም...
01/09/2026

በወርሀ ሐምሌና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
++++++++++++++++++

✍️ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐግብር

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገርአቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል።

ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር። ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

✍️ ፕሮጀክቶች ጉብኝትና ምረቃ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችንና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል።

✍️ ማኅበራዊ ጉዳይ

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ : አዲሲቷ የተስፋ አድማስ

Address

Arat Killo/Arada Sub City
Addis Ababa
30145

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/:

Shortcuts

Share