05/08/2026
ሐምሌ 28፣ 2018 ዓ.ም — የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018/19 ምርት ዘመን በግብርና ኤክስቴንሽን ምርምር ክፍል ከወረዳዎች ጋር በመተባበር እየሰራባቸው የሚገኙትን የቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ የምርምር ስራዎች የመስክ ምልከታ አካሄደ።
የመስክ ምልከታው በመተከል ዞን ስር በሚገኙት በዳንጉር እና ፓዌ ወረዳዎች ላይ የተከናወነ ሲሆን፣ የማዕከል ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበበ እና ሌሎች የምርምር ማናጅመንት አካላት በመገኘት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በምልከታው ወቅት የተመለከቱዋቸው ዋና ዋና ስራዎች፡
• የኩታ ገጠም ስራዎች (ክላስተር):- የአኩሪ አተር፣ ሩዝ እና ሰሊጥ ክላስተር ስራዎች።
• የቅድመ ሰርቶ ማሳያ ስራዎች:- የበቆሎ፣ የሩዝ፣ የመኖ እና የለውዝ ቅድመ ሰርቶ ማሳያ የምርምር ስራዎች።
ማናጅመንቱ በቦታው ተገኝቶ ባደረገው ምልከታ፣ እየተሰሩ ያሉት የቅድመ ሰርቶ ማሳያ እና ሰፋፊ የኩታ ገጠም ስራዎች በአግባቡ መሬት ላይ ማረፋቸውንና ውጤታማ በሆነ መልኩ መሰራታቸውን አረጋግጧል። እነዚህ የምርምር ስራዎች ለአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግርን በአግባቡ የሚያሳልጡ መሆናቸው በመስክ ምልከታው ተገልጿል።
የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል — ለምርታማነትና ለዕውቀት ሽግግር!!
#መተከል #ዳንጉር #ፓዌ #ኢትዮጵያ