Amhara popular force APF

Amhara popular force APF Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara popular force APF, Armed forces, Addis Ababa.

21/05/2023
ወለጋና ማዲንጎ 📌 ትላንት ማዲንጎን አጣነው። መንደሩ በደቂቃዎች ውስጥ ከበዐል ድባብ ወጣ። የበዐል ምግቦች የደመራው ችቦዎችና በባህል ልብስ ያጌጡ የወዳጆቻችን ምስሎች አየሩን ለቀው የማዲንጎ...
28/09/2022

ወለጋና ማዲንጎ

📌 ትላንት ማዲንጎን አጣነው። መንደሩ በደቂቃዎች ውስጥ ከበዐል ድባብ ወጣ። የበዐል ምግቦች የደመራው ችቦዎችና በባህል ልብስ ያጌጡ የወዳጆቻችን ምስሎች አየሩን ለቀው የማዲንጎ ምስሎችና የሃዘን መግለጫዎች ሰፈር አለሙን ተቆጣጠሩት። ተራው ዜጋ ፣ ባለስልጣኑ ፣ ታዋቂውም ፣ አላዋቂውም በሃዘን መግለጫ ተረባረቡ። በአጠቃላይ በዚህ መንደር መኖራቸውን የረሳናቸው ሰዎች ሳይቀር ስለማዲንጎ ፃፉ።

📌 ትላንት 200 ሰው አጣን። መንደሩ የሃሳብ ዝብርቅርቁን አልተወም። ከጥቂት እርጉማኖች በቀር ሁሉም ሰው ሊያዝንላቸው ቢችልም ሁሉም ሰው #ድምፅ ሊሆናቸው አልቻለም። ለወለጋ ሟቾች የምናሰማው ለቅሶና ድምፅ ከቀደመው የማዲንጎ ድንገተኛ ህልፈት የላቀ ከሰማይና ከምድርም የራቀ ለቅሶ ብቻ ያልሆነ ሰፊ ጥቅም ነበረው። ወራት እየዘለለ ሺዎችና መቶዎች ሃገር አማን ብለው ተኝተው በአረመኔዎች ይቀጠፋሉ። ከመቀጠፋቸው በዘለለ የነፍሳቸውን የሰውነታቸውን ዋጋ የሚመጥን ለቅሶ አይለቀስላቸውም። ሞት በቃን የሚል የቆራጦች ጩኸት የለም። በአሁኑ የወለጋ የግፍ ግድያና የማዲንጎ ህልፈት መሃል የተሰማው የድምፅ ልዩነት አጀብ አጀብ የሚያሰኝ ነው።

በአንዳንድ ጉምቱዎቻችን( ታዋቂዎችና ተሰሚዎች) ላይ የገባኝ ነገር ለማዘን እና ለሞቱት ድምፅ ለመሆን እንኳን የመንግስትና የገዢዎች ፊት እንደሚታይ ነው። የዛሬ ገዢዎችን ፊት የሚያጠቁር ሃዘንና ጩኸትን በአደባባይ ማውጣት ያስፈራቸዋል። ወገን ለአንድ ሺህ አንደኛ ጊዜ እየረገፈ "ወቅቱ በጥንቃቄ የምናልፈው የፈተና ወቅት ነው" የሚል ህዝብን የሚያሞኝ የብልጣብልጦች ማባበያ ይሰጣል።

የወለጋን ሞት ከማዲንጎ ሳነፅር ሞትና ሃዘኑ በቁጥር ባይሰፈር እንኳን ለሁለቱም አሳዛኝ ሁነቶች የተሰሙት ድምፆችና የተሰጣቸው ትኩረት በሰውኛ አይን ሌላ የሃዘን በር ይከፍታሉ!

ስለ ወለጋ በመጮህ የምንገልፀው በክስተቱ የተሰማንን ሃዘን ብቻ አይደለም። በወገን ላይ የተቆመሩ ሌሎች የሞት ድግሶችን ለማቆም በአንድ ላይ የመጮህና ጫና የማሳረፍ ሌላ ሞትና ሃዘንን የማስቀረት አቅም ስላለው ነው!

በሁሉም የሃገራችን ክፍል ለረገፉ ለሚረግፉ ለተሰደዱና ላዘኑ ሁሉ ሰላምና መፅናናትን ይስጥልን!

 #አጤ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ የቆረቆሯትን ከተማ እና አገር ለወራሪ አሳለፎ የሰጠ ትውልድ የነገስታቱን ስም ጠርቶ ልደት የማክበር ሞራሉን ከየት አገኘው???ነገስታቱን ማክበር ወይም መዘከር...
18/08/2022

#አጤ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ የቆረቆሯትን ከተማ እና አገር ለወራሪ አሳለፎ የሰጠ ትውልድ የነገስታቱን ስም ጠርቶ ልደት የማክበር ሞራሉን ከየት አገኘው???

ነገስታቱን ማክበር ወይም መዘከር ማለት የሰጡንን የታሪክ አደራ ተቀብለን ስናስቀጥል ነው። በደም እና አጥንታቸው የገነቡትን ሀገር፣ከተማ፣ቅርስ፣አሻራ፣እሴት እና ትውፊት ስናስቀጥል ብቻ ነው።የነገስታቱን ልደትማ ማን ይቀማናል?

እኔ በግሌ የዚህ ትውልድ አንድ አካል በመሆኔ ለጊዜው የነገስታቱን ስም ጠርቼ ልደታቸውን ለማክበር ብቃቱም ሞራሉም የለኝም።አፍራለሁ።

#ኢትዮጵያ ድል ስታደርግ እንገናኛለን።

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው

"እንደ አሁኑ ደካማ መንግስት በሚኖርበት ጊዜ ፋኖነት ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው" - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔፋኖ ማለት የአማራ ህዝብ የክብር መጠሪያ ነው። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበት የዘር መጥ...
17/08/2022

"እንደ አሁኑ ደካማ መንግስት በሚኖርበት ጊዜ ፋኖነት ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው" - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

ፋኖ ማለት የአማራ ህዝብ የክብር መጠሪያ ነው። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበት የዘር መጥፋት አደጋ እስኪቀለበስ ድረስ ሁላችንም ፋኖ ነን። በተለይም እንደ አሁኑ ደካማ መንግስት በሚኖርበት ጊዜ፣ ህዝብ መሪ ባጣበት ጊዜ፣ ህዝብ ሰብሳቢ ባጣበት ጊዜ ፋኖነት መሰባሰቢያ መድረክ ነው።

"ልጄ 'የመቶ አመት እድፍ ታጠበ' የሚል የኦሮምኛ መዝሙር እንዲዘምር አልፈልግም" - አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉቋንቋ ችግሬ አይደለም። የትኛውንም ቋንቋ ብማር ደስ ይለኛል። ኦሮምኛም በላቲን ፊደ...
16/08/2022

"ልጄ 'የመቶ አመት እድፍ ታጠበ' የሚል የኦሮምኛ መዝሙር እንዲዘምር አልፈልግም" - አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ

ቋንቋ ችግሬ አይደለም። የትኛውንም ቋንቋ ብማር ደስ ይለኛል። ኦሮምኛም በላቲን ፊደል ሳይሆን፣ በአማርኛ የፊደል ገበታ ከተሰጠ መማር እችላለሁ። ችግር የሆነብን ልጆቻችን ዘምሩ የሚባለው የኦሮምኛ መዝሙር ነፍጠኛን ሰብረነዋል፣ የመቶ አመት እድፍ ታጠበ ... የሚል መሆኑ ነው። የፖለቲከኞቹ አላማ አማርኛ ቋንቋን ለማቀጨጭ፣ የላቲን ፊደል ለማስፋፋት፣ ለእልህ ... መሆኑ ነው ሁላችንንም በተቃራኒው እንድንቆም ያደረገን።

(አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ - ለየኛ ቲቪ የተናገረው)

"በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመውን ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ኖሮ ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር?" - አቶ ዮሐንስ ቧያለውበኢትዮጵያ 3 አይነት ዜጋ አለ። አማራ በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ዜጋ ...
16/08/2022

"በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመውን ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ኖሮ ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር?" - አቶ ዮሐንስ ቧያለው

በኢትዮጵያ 3 አይነት ዜጋ አለ። አማራ በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ደረጃ ዜጋ ነው። በወያኔ ጊዜ 2ኛ ደረጃ ዜጋ ነበር። አንደኛ ደረጃ ዜጋው ጊዜው የእኛ ነው የሚለው አካል ነው። ሁለተኛ ደረጃ ዜጋው ደግሞ ሌላው ብሄር ነው። በሶስተኛ ደረጃ የአማራ ህዝብ ነው። አሁን ላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ የሚኖረው ከሱዳን ስደተኞች፣ ከኤርትራ ስደተኞች፣ ከሶሪያና ከየመን ስደተኞች በታች ነው።

በጦርነት ጊዜ ያልተባለ፣ ከጦርነቱ በሗላም ያልተነሳ ... ድንገት ሰሞኑን ፋኖ ከመከላከያ ላይ ጥቁር ክላሽ ቀማ የሚለው እንዴት መጣ? አትሞኙ፣ ይሄ አዲስ የአማራ ጥላቻ ትርክት እየተፈጠረልን ነው። ነባሩ ትርክት አልበቃቸው ስላለ ነው። የጥቁር ክላሽ ትርክት የመጣው፣ የኦሮሚያ ብልፅግና ተረኛ አመራሮችን ጥቁር ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። በእነዚህ አመራሮች መሪነት አማራ ታርዷል። የ15 ቀን ህፃን ከእነ እናቷ ተገድላለች። ታዳጊ ህፃን ሁለተኛ አማራ አልሆንም ብላለች። ጥቁር ታሪካቸው ተዘርዝሮ አያልቅም።

በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመው ግፍ፣ አማራ ፈፅሞት ቢሆን ምን ይፈጠራል? ኦሮሚያ ውስጥ የታረዱትን ያህል፣ አማራ ውስጥ ሌላ ብሄር ታርዶ ቢሆን ምን ሊፈጠር ይችላል? ብላችሁ አስቡት። በበቀል አፀፋ ኢትዮጵያ የደም ጎርፍ ትሆን ነበር። ሀገር ሙሉ በሙሉ ይፈርስ ነበር። ስንት አኖሌ ሀውልት ይሰራ ነበር።

(አቶ ዮሐንስ ቧያለው - ፋኖነት በሚለው የመፅሐፍ ምርቃት ላይ የተናገረው)

ረ/ፕሮፌሰር ትንግርቱ ዝምታቸውን ሰበሩ❗❗❗"ድረሱልኝ ብለህ አውጀህ ህዝብ ተሰልፎ ከስልጣንህ ከታደገህ በሗላ፣ ህዝብን ተመልሰህ መፈረጅ አደገኛ ክህደት ነው" - ትንግርቱ ገ/ፃዲቅየአማራ ፖለ...
14/08/2022

ረ/ፕሮፌሰር ትንግርቱ ዝምታቸውን ሰበሩ❗❗❗

"ድረሱልኝ ብለህ አውጀህ ህዝብ ተሰልፎ ከስልጣንህ ከታደገህ በሗላ፣ ህዝብን ተመልሰህ መፈረጅ አደገኛ ክህደት ነው" - ትንግርቱ ገ/ፃዲቅ

የአማራ ፖለቲከኞች ሃላፊነታቸውን በሚገባ ባለመወጣታቸው፣ ትግሉ የፖለቲካ ሃላፊነት የሌላቸው ሰዎች ላይ ወድቋል። የአማራን ፖለቲካ መምራት ያለበት በአማራ ፖለቲካ ሂደት ውስጥ የሚሳተፍ ሰው ነበር። ነገር ግን ዛሬ ላይ በተቃራኒው ሸክሙ በእያንዳንዱ የአማራ ተወላጅ ላይ ወድቋል።

የአማራ ፖለቲከኞች ስህተት፣ የአማራ ፖለቲከኞች Failure መገለጫ በህዝቡ ላይ መከራ እንዲወርድ አድርጎታል። ከማይመስላቸው ጋር ጥምረት መፍጠር አደገኛ ነው። የአማራ ህዝብ የፖለቲከኞቹን ፍዳ መሸከም የለበትም። ፍዳውን ራሳቸው ፖለቲከኞቹ እንዲሸሸከሙት ማድረግ አለብን።

ህዝባዊ ጦርነት ካደረክ በሗላ የሰላም ድርድሩን በተወሰኑ ቡድኖች ብቻ ማድረግ እውነተኛ ሰላም አያመጣም። በመንግስት በኩል ጦርነትን ለሌላ ትውልድ ለማሳደር መፈለግ ይታያል። እውነተኛ ተደራዳሪ ያስፈልጋል።

ድረሱልኝ ብለህ አውጀህ ህዝብ ተሰልፎ ከስልጣንህ ከታደገህ በሗላ፣ ህዝብን ተመልሰህ መፈረጅ አደገኛ ክህደት ነው። የሚያሳፍረው ነገር አሁን ሳይቀር ህዝቡን መታደግ የሚችል መንግስት የለም። መንግስት ህዝቡን መጠበቅ ቢችል በግሌ አንድም የታጠቀ ኢመደበኛ ሀይል እንዲኖር አልፈልግም ነበር። ነገር ግን መንግስት ይሄንን ማድረግ አይችልም። ይሄ በህዝቡ ላይ የሚደረግ ክህደት ነው።

መንግስት ከህወሃት ጋር ድርድር ከመጀመሩ በፊት የአማራን ጥቅም ሊያስከብሩ የሚችሉ የአማራ ብሄርተኛ ፖለቲከኞችን ከመድረኩ ገለል አድርጓቸዋል። ከአብንም፣ ከብአዴን ብልፅግናም የብሄርተኝነት ስሜት ያላቸው ፖለቲከኞች እንዲወገዱ ተደርጓል። ይሄ ደግሞ በድርድሩ ውጤት የአማራ ህዝብ ተጠቃሚ እንዳይሆን አመላካች ነው።

ረዳት ኘሮፌሰር ትንግርቱ ገ/ፃዲቅ - ለ Blue 24 የተናገረው

ፎጣ ለባሽ ነኝ               "አንቲ የእናቱ ልጅ"; የጀግና ልጅ ነኝመትሮ ቆራጭ ልበ ተራራኢትዮጵያዊ ነኝ ነፍጠኛ አማራ። አማራ ስልህ… ሃገር ለጠላትየማያስደፍር… ፈሪን አንግሶህንፃ...
14/05/2022

ፎጣ ለባሽ ነኝ
"አንቲ የእናቱ ልጅ"
;
የጀግና ልጅ ነኝ
መትሮ ቆራጭ ልበ ተራራ
ኢትዮጵያዊ ነኝ ነፍጠኛ አማራ።

አማራ ስልህ…
ሃገር ለጠላት
የማያስደፍር… ፈሪን አንግሶ
ህንፃ ማያቆም… ሃገር አፍርሶ።
ላ`ንበሶች መንጋ… የማይደነግጥ
በኩሬ ማዕበል… የማይናወጥ።
ተኩላን የማይሾም… ለበግ እረኛ
ላመነበት ሟች… ጀግና ነፍጠኛ።

አማራ ስልህ…
ለትርፍ እራፊ… ክብሩን አይሸጥም
እንደ ጅል ተጓሽ… መንገድ አይስትም።
ባዳፈኑት, ልክ… ፍም አዝሎ አዳሪ
ንስር ነው ልኩ… ቅልጥም ሰባሪ።
ተወርዋሪን ጦር… በሽመል መካች
ከጠላ ገዳይ… ከወደደ ሟች።
ሌማተ ሰፊ… እንግዳ አክባሪ
መደቡን ለቆ… መሬት አዳሪ።

አማራ ስልህ…
አርሶ በሌ ነው… ሰላም ቀማሪ
ትርክትን ነቃሽ… ታሪክ ጦማሪ።
ለእምነቱ አጥቢያ… ውቅር አንፆ
ታሪክ ያኖረ… ስሙን ቀርፆ።
አማራ ስልህ…
መንሹ ነጣይ ነው… እንክርዳድ ፈታኝ
ከንፋስ ሲያውል… ገለባ በታኝ።
ፎጣ ለባሽ ነው… ለምዳም ትከሻ
ሊሸምን ሲበጅ ጀምሮ ሚያድር ከመጨረሻ።

አማራ ስልህ…
አርማው ሲነካ
ስሙን ሰንደቅ ላይ… ደርሶ ሚፈልግ
የሚያጉረመርም… እንደ ሃምሌ ወግ።
ጦቢያን ሲነኳት…
ሃሞት ይተፋል… ሃገር ሲደፈር
ይቆማል እንጂ… አይቀመጥም ለመደራደር።
:
አማራ ስልህ………

የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት‼°°°°°°ለሚመለከተው ሁሉ¢ትክክለኛውን የፌስቡክ ገጼን የሚጠይቁኝ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ ሲጨምር ስላስተዋልሁ ይህን ለመጻፍ ተገድጃለሁ።[የኔ ትክክለኛ የፌስቡክ ገ...
20/03/2022

የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት‼
°°°°°°
ለሚመለከተው ሁሉ¢
ትክክለኛውን የፌስቡክ ገጼን የሚጠይቁኝ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ ሲጨምር ስላስተዋልሁ ይህን ለመጻፍ ተገድጃለሁ።
[የኔ ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ይህ ብቻ ነው።ይህም የፌስቡኩን አለም አልፎ አልፎ ገብቼ የማይበት እንጅ አሁን ባለሁበት ሁኔታ የማልጽፍበት ገጽ ነው።የወገኖቼ ጥያቄ ገፍቶኝ ለማረጋገጥ ስሞክር በኔ ስም ብዙ ገጾች መከፈታቸውን አረጋግጫለሁ። አንዳንዶቹ በየቀኑ የሚጻፍባቸውም ናቸው።እጅግ የወረዱና እና ህዝቡን ግራ የሚያጋቡ መልእክቶች ሲተላለፉ መሰንበታቸውንም ታዝቢያለሁ።የተጠና አላማ ይዞ፥እኔንና ትግላችን ደጋፊ መስሎ የሚያምታታ መሰሪ ገጽም አይቻለሁ።.....ከዚህ ገጽ ውጭ ያሉት በሙሉ የተለያዩ ሰዎች ለተለያዬ አላማቸው የከፈቷቸው ገጾች መሆናቸውን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።]
ትክክለኛው 👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100071187470447

21/02/2022

ፎቶ ሱስ ሲሆንብህ ክላልኝ...

ለማንኛውም.....በክልሉ ልዩ ሀይል እጣ ፈንታ ላይ ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር ለረጅም ጊዚያት የተደረገው ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ከቦታው እንዲነሳ ተደርጓል  ...
18/02/2022

ለማንኛውም.....

በክልሉ ልዩ ሀይል እጣ ፈንታ ላይ ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር ለረጅም ጊዚያት የተደረገው ውይይት ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ከቦታው እንዲነሳ ተደርጓል

የክልሉ መስተዳደር ሰጥቻለሁ ያለውን አማካሪነት ቦታ አለመቀበላቸውን አረጋግጫለሁ

በተጨማሪ በፌደራሉም ሆነ በክልሉ ብልፅግና የአቶ ፀጋ አራጌን አስያየት ተከቶሎ ሊደግፉ ይችላሉ የተባሉ ሰወችን የማንሳት ስራ እየተሰራ በመሆኑ ብ/ጀ ተፈራ ማሞም እነሱን ሊደግፍ ይችላል በሚል ጥርጣሪ በጥድፊያ እንዲነሳ ካደረጉት ምክኒያቶች ውስጥ ተጠቅሷል ::

30 ፋኖ በፖሊስ ታፍሶ ታሠረ የሚል ዜና ይደብራል።  #አንድ፦ ራሱን ነፃ ያላወጣ ፋኖ ማንን ነፃ ሊያወጣ ይችላል? ከተሰለፈበት አንፃር በፖሊስ እየተነዳ ወደ ጣቢያ የሚሄድበት አመክንዮ አይታ...
18/02/2022

30 ፋኖ በፖሊስ ታፍሶ ታሠረ የሚል ዜና ይደብራል።

#አንድ፦
ራሱን ነፃ ያላወጣ ፋኖ ማንን ነፃ ሊያወጣ ይችላል? ከተሰለፈበት አንፃር በፖሊስ እየተነዳ ወደ ጣቢያ የሚሄድበት አመክንዮ አይታየኝም፤ ካለም ሆድ አይነፋም።

የመሣሪያ እጥረት እንዳለ ይገባኛል ግን የያዝነውን ይዘን ወደ ዱር/ጫካ/በርሃ እንግባና #እንለማመደው። በዚያውም መልካም አጋጣሚዎችን እንፈጥራለን። ከስልጠና በኋላ ከተማ ውስጥ ምን እንሰራለን? ከስልጠና በኋላ ከተማ ማውደልደል ከጀመርን ሰውነታችንም አስተሳሰባችንም መልሶ ይላሽቃል።

#ሁለት፦
የሚሠጠው ስልጠና ይዘትና ጥራት ላይ በደንብ መሠራት እንዳለበት አመላካች ነገር ነው። የስልጠናው ይዘት
👉 ሚሊታሪ ሳይንስ እና ጥበብ
👉 ፖለቲካና የፖለቲካ ርዕዮትዓለም
👉 አካላዊ ብቃት ስልጠና
👉 የአማራ ብሔርተኝነት መግፍዔ
👉 ወዘተ
መካተት አለባቸው።

የንድፈ ሃሳቡም ሆነ የተግባር አካላዊ #ስልጠናው በፍፁም ከተማ ውስጥ መሆን የለበትም። ምክንያቱም በነባራዊ ከባቢ (real situation) ሲሆን አእምሯችን ይቀበለዋል፤ ይዋኸደናል፤ አካላችን በጦርነት ወቅት የሚያጋጥመውን አሜኬላ ተፈትኖ ያልፋል። ከተማ ውስጥ የሚሰጥ ስልጠና መተኮስ መቻልና ጂም ቤት ከምንሠራው ስፖርት ብዙም አይደለም። ጧት አንዳፍታ ከተማ ውስጥ ሰለጥነን የቀሰምናትን እውቀት በደንብ ሳናብላላውና ወደውስጣችን ሳናሰርፀው ወዳውኑ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለን በጃምቦ፣ በመንደር አሉባልታ፣ በውስዋስ ወዘተ እናጣፋታለን። ሰውነታችንንም መልሰን በምቾት ውስጥ እናስገባዋለን፤ እናበላሸዋለን፤ እናማርጠዋለን። በምቾት ውስጥ ስንሆን ቁርጠኝነታችን እየተሸረሸረ ይሄዳል፤ የዓላማ ፅናት ይጎድለናል። ስልጠናው ካለቀ በኋላማ ርግፍ አድርጎ የሚተወው (out of track የሚሆነው) ይበዛል።

ወታደራዊ ስልጠና አስቸጋሪና ፈታኝ የአየር ንብረትን (በርሃ፣ ዝናብ፣ ቁር)፣ ዳገትና ቁልቁለት (ጥሻ፣ ወንዝ፣)፣ አራዊት፣ የምድር ላይ ተሳቢዎች፣ ርሃብና ጥማትን ወዘተ ለመቋቋም የሚደረግ ስልጠና ነው። በፈታኝ (hardship) ሁኔታ ውስጥ ስናልፍ አካላዊ ብቃት ብቻ ሳይሆን የዓላማ ፅናትና ቁርጠኝነታችን እየጨመረ ይሄዳል። የምንሞትለት የተቀደሰ ዓላማ እንዳለን በፅኑ እናምናለን፤ ላይናወፅ በውስጣችን ይሠርፃል፤ ነፃነት ወይም ሞትን የእውነት እናውጃለን።

ከስልጠናው ጀምሮ በርሃ ወይም ጫካ ውሰጥ ከሆነ ትክክለኛ ፋኖ እንሆናለን፤ በፋኖነት ፍቅር እንወድቃለን። ከስልጠናው ጎን በጎን መሬት ላይ ብዙ ነገሮችን እናመቻቻለን። ከስልጠና በኋላ በዚያው ነፃ መሬት ይዞ ጠላቶቻችን ቀያችን ድረስ መጥተው እስከሚተነኩሱን ሳንጠብቅ አቅደን እንሠራለን። ወጣቱን ወደጫካ/በርሃ መሳብና ትልቅ ጦር መገንባት እንችላለን። እንኳን በአንዴ 50 ወይም 100 ሰልጥኖ ቀርቶ የ 5 ሰው ቡድን ዱርቤቴ ቢልና ሌሎች እንዲቀላቀሉት ቢሠራ ብዙ ሺህዎችን ያፈራል። የኦነግ ጦር ከኤርትራ ሲገባ 200 አይሞሉም ነበር - ምቹ (fertile) የሆነ ነገር ቢጠብቀውም።

ስለዚህ የስልጠናው ይዘትና ጥራት፣ የስልጠናው ቦታና ከስልጠና በኋላ በወጡበት ዱር ቤቴ ብሎ መቅረት ትክክለኛውን ፋኖነት በአጭር ጊዜ አላብሶ፣ የአማራ ትግል በፍጥነት ግቡን እንዲመታ (ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ሁሉ) ያደርገዋል። ስለሆነም ከምልመላ ጀምሮ እስከ ስልጠናና ከዚያም ባለፈ የምንመራበት ከዘመናዊ የውትድርና ሳይንስ ያጣቀሰ የምልመላ፣ ስልጠናና ፋኖ መመሪያ (guideline) ያስፈልጋል። አሰልጣኞች በየአካባቢው ማዘጋጀት ብትጀምሩ ጨምቆ አንድ ወጥ እንዲሆን እናደርገዋለን።

አንድ ወረዳ ላይ 1000 ፋኖ በከተማ ሰልጥኖ ከተማ ከሚቀመጥ በበርሃ የሰለጠነና በዚያው ዱርቤቴ ያለ 100 ፋኖ ይሻላል፤ በሌላው ወጣትም ላይ በጎ ተፅኖ ያሳድራል፤ የጥንቱ ፋኖነት ከእነ አባቶቻችን መንፈስና ጀግንነት ያስቀጥላል። በየጊዜው አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ብቃታችንም እያደገ እያደገ ይሄዳል። ከዚያም ታሪክ እንሠራለን።

አማራነት = ነፃነት ወይም ሞት!!!

በጠቢቡ አማራ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara popular force APF posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category