04/09/2026
ለአሽከርካሪዎች የግንዛቤ ስልጠና ተሰጠ፣
(ሲቲ ባስ፤ ነሃሴ 29/ 2018 ዓ.ም) አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቴክኒክ ስልጠና ዳይሬክቶሬት ለኮንትራት ሰራተኞች እና ለዜሮ ዓመት ስራ ልምድ ላላቸዉ ባስ ካፒቴኖች ዉጤታማ አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የዕለቱ የክብር እንግዳ የድርጅቱ የቴክኒክ አገልግሎትና ስልጠና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር አዳነ አብደታ በቀጣይ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደዉ ኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅት ደረጃዉን የጠበቀ ትራንስፖርት አገልግሎት ለዕንግዶች እና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ለመስጠት ጨዋና ምስጉን አሽከርካሪ ማብቃት የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ቀዳሚ ተግባሩ በመሆኑ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኃላፊዉ አክለዉም ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) በቀጣይ የምታስተናግድ በመሆኑ ምንግዜም ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸዉ እንደ ተቋምና ሃገር አሽከርካሪዎች አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር እና የትራፊክ አደጋን በመቀነስ የተቋምና የሃገር ንብረትን ከዉድመት መከላከል እንደሚገባ፤ በስነ ምግባሩ የታነጸ እና በጥንቃቄ የማሽከርከር ስነ ባህሪን ጠብቆ አገልግሎትን በመስጠት የተቋም ስም ከፍ እንዲል በመስራት አገልግሎት አሰጣጥን ሁሉን ያማከለ ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
አያይዘዉም አደጋ እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፤ ቀለም፤ሀብታም ወይም ድሃ ብሎ ስለማይመርጥ ሁልጊዜም እንቅስቃሴያችን ከአደጋ የፀዳ እንዲሆን የትራፊክ ህግን ማክበርና ተጠንቅቆ ማሽከርከር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ስልጠናዉን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቴክኒክ ስልጠና ዘርፍ የአሽከርካሪ አሰልጣኝ ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ክብረት ሲሆኑ ተሸከርካሪንና አሽከርካሪን ተቆጣጥሮ ማሽከርከር ላይ ትኩረት ያደረገ፣ አሽከርካሪ ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ ፣ ተሸከርካሪን ለአደጋ የሚያጋልጡ ተፈጥሯዊ እና ሰዉ ሰራሽ አምክንያቶችን ለይቶ ማወቅ ላይ ፣ የመንገድ አጠቃቀምና ሙያዊ ስነ ባህሪን አሟልቶ የተሸከርካሪን ደህንነት አረጋግጦ በመንቀሳቀስ ቀጣዩን 2019 በጀት ዓመት በስኬት ማሽከርከር ላይ ያተኮረ የስልጠናዉ አላማ መሆኑን በስልጠናዉ አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልጣኞች የስልጠናዉን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ በመረዳት ላነሱት ሃሳብ አስተያት አሰልጣኙ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናዉ በመግባባት ተጠናቋል፡፡
https://www.facebook.com/citybus2015
ቴሌግራም:https://t.me/citbus
ዩቱብ:https://youtube.com/-f2t.
ኢሜል: [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected]