Gullele Woreda 6 Communication-ወ6

Gullele Woreda 6 Communication-ወ6 Gullele Wereda 6 Communication (ጉለሌ ወረዳ 6 ኮሙኒኬሽን)

''ጎቤና ሺኖዬ'' የወጣቶች የባህላዊ ጭፈራ መርሃ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  ተካሄደ።በክፍለ  ከተማው  ''ጎቤና ሺኖዬ'' የወጣቶች የባህላዊ ጭፈራ  መርሃ ግብር የባህሉ  ባለቤ...
05/09/2026

''ጎቤና ሺኖዬ'' የወጣቶች የባህላዊ ጭፈራ መርሃ ግብር በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ።

በክፍለ ከተማው ''ጎቤና ሺኖዬ'' የወጣቶች የባህላዊ ጭፈራ መርሃ ግብር የባህሉ ባለቤት የሆኑ ወጣቶች ፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

የክረምቱ ዝናብ አልፎ መሬቱ በአበቦችና በለመለሙ ተክሎች ይሸፈናል። ወጣቶችም ከክረምቱ የሥራ ጊዜ ዕረፍት አግኝተው፣ ተፈጥሮ ይዞት የመጣውን አዲስ ተስፋ ይቀበላሉ።

በዚህም አዲስ ተስፋ፣ ደስታና ብሩህ ፊት ይዘው ወደ ሜዳ በመውጣት በዓል ያከብራሉ። ይህንን ባህላዊ በዓል ጎቤ እና ሺኖዬ ብለው ይጠሩታል።

ጎቤ እና ሺኖዬ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበሩ ሲሆን፤ አከባበራቸውም እንደ የአካባቢው በተለያየ መልኩ ይከናወናል።

በኦሮሞ ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ጎቤ እና ሺኖዬ፣ በተለይም በበልግ ወቅት ወጣቶች ባህላዊ ልብስ በመልበስ፣ በባህላዊ ዘፈንና ጨዋታ በመሳተፍ ደስታቸውንና መልካም ምኞታቸውን የሚገልጹበት ሥርዓት ነው።

እነዚህ ባህላዊ ጨዋታዎች የኦሮሞን ታሪክና ማንነት ለአዲሱ ትውልድ ከማስተላለፍ ባለፈ፤ እየተረሳ የመጣውን ባህል ለመመለስ፣ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የኦሮሚያን የቱሪዝም ማራኪነት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና አላቸው።

ወጣት ወንዶችና ሴቶች የወረሃ መስከረም መጥባትን በምስጋና፣ በልዩ ልዩ ዜማዎችና ዘፈኖች ይቀበላሉ።

ሴቶች ወረሃ መስከረምን በሺኖዬ፣ ወንዶች ደግሞ በጎቤ በመግለጽ፣ ለፈጣሪና ለተፈጥሮ ያላቸውን ምስጋና፣ ተስፋና ደስታ ያሳያሉ።

የጎቤ ሥርዓት ከክረምቱ ዝናብ ወደ ብራ ወቅት የሚደረገውን ሽግግር የሚያመለክት ሲሆን፣ ይህም ከክረምት ወደ በጋ ለሚደረገው ሽግግር ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት ሥርዓት ነው።

የወረዳ 6 ሰላም ሰራዊት  የአካባቢያቸዉን ሰላም ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ:: ጉለሌ ወረዳ 6 ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 29/2018ዓ.ም  የወረዳ 6አስተዳደር  የሰላም ሰራዊት አባላት ለአ...
04/09/2026

የወረዳ 6 ሰላም ሰራዊት የአካባቢያቸዉን ሰላም ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ::

ጉለሌ ወረዳ 6 ኮሙኒኬሽን ነሐሴ 29/2018ዓ.ም

የወረዳ 6አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላት ለአካባቢያቸዉ ሠላም መጠበቅ ግንባር ቀደም በመሆን እንደ ክፍለ ከተማችንም እንደ ወረዳም የሠላሙ ባለቤት መሆናቸዉን በመግለፅ የፀጥታ ስምሪት የአካባቢን ሰላም ከማረጋገጥ አንፃር በከፍተኛ ሚና ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ እና ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገልፀዋል ።

ያናገርናቸው የሰላም ሰራዊት አባላትም በበጎ ፈቃደኝነት በሰላም ሰራዊት በወረዳቸዉ በመደራጀት የተጠናከረ ስምሪት በመዉሠድ ከመደበኛው የፀጥታ አካል ጋር በመሆን አካባቢን በመጠበቅና የተለየ እና የሚያጠራጥሩ እንቅስቃሴ የሚያጠራጥሩ እንቅስቃሴዎች ሲመለከቱ ለፀጥታ አካሉ ፈጣን
መረጃ በመስጠት የክፍለ ከተማው እና የወረዳው ሰላም ከማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና በትጋት እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

04/09/2026
ለአዲስ ዓመት በቂ  የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸየአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶች...
04/09/2026

ለአዲስ ዓመት በቂ የበዓል የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት፣ መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በቂ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለከተማዋ ነዋሪዎች መቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኮሚሽኑ የገበያ ጥናትን መሠረት በማድረግ በበዓላት ወቅት በገበያ ላይ የሚፈጠረውን ፍላጎት በመለየት በቂ የፍጆታ ምርቶች እንዲቀርቡ በስፋት መስራቱን ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሽታዬ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ ከአምራቾች፣ ከአስመጪዎች፣ ከዩኒየኖችና ከተለያዩ የኀብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመተባበር የምርት ትስስር በመፍጠር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች እንዲሁም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶች በበቂ መጠን መቅረቡን አስረድተዋል።

እነዚህ ምርቶች በከተማው በሚገኙ በዘመኑ 700 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ በአዲስ ዓመት ኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በ154 የኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በስፋት ለሸማቹ እየቀረቡ መሆናቸውን ኮሚሽነሯ ገልጸዋል።

ከነፃ ገበያው ጋር ሲነፃፀር በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡት እነዚህ ምርቶች የከተማዋን ነዋሪዎች የበዓል ፍላጎት በማሟላት የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና ገበያውን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በበዓሉ ወቅት 27/4 የሸማች ኀብረት ሥራ ማህበራት ሉካንዳ ሥጋ ቤቶች ሥጋን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ዝግጅት መደረጉን ወ/ሮ ሽታዬ ገልጸው፤ ይህም በበዓሉ ወቅት የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

ዋና ኮሚሽነሯ በመጨረሻ ህብረተሰቡ ምርቶቹን ከኀብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች፣ ከኤግዚቢሽንና ባዛር ማዕከላት እንዲሁም ከቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በመግዛት ከተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኮሚሽኑም በበዓላት ወቅት የምርት አቅርቦትና የገበያ መረጋጋት ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ መከታተሉን አረጋግጠዋል።

ተገልጋዮች ያለምንም እንግልት ፈጣን አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ገለጹ።ጉለሌ ወረዳረ  6 ኮሙኒኬሽ ጽ/ቤት 29/12/2018 ዓ.ም።በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳው 6 አስተዳደር የሚሰጡ የተለያዩ ...
04/09/2026

ተገልጋዮች ያለምንም እንግልት ፈጣን አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ገለጹ።
ጉለሌ ወረዳረ 6 ኮሙኒኬሽ ጽ/ቤት 29/12/2018 ዓ.ም።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳው 6 አስተዳደር የሚሰጡ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶች ያለምንም እንግልት፣ በፍጥነትና በቀላል አሰራር እያገኙ መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ።

ተገልጋዮቹ አገልግሎቱ በወቅቱ መሰጠቱ ጊዜንና ወጪን እንደቆጠበላቸው ጠቁመው፣ የአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት ይበልጥ ምቹና ቀልጣፋ እንዲሆን የተደረገውን ለውጥም አድንቀዋል።

በተጨማሪም በተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት ግልጽና ተገማች በመሆኑ ተገልጋዮች በእርካታ አገልግሎታቸውን እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥርአዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ  ስራዎች ብቻ ሳይ...
03/09/2026

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥር

አዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ ስራዎች ብቻ ሳይሆን፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ ለማድረግ አጠቃላይ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ማዕከል በሆነው የሰብዓዊ ልማት እና ትውልድን በማነጽ ላይ በሰራችው ስር ነቀል ለውጥ ጭምር ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም”ን በብቃት በመምራታቸው በዓለም አቀፉ “አክት ፎር ኤርሊ ይርስ” (Act For Early Years) ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው ተሸልመዋል። ይህ ትልቅ እውቅና ከተማዋን ለህፃናት የምትመች ከተማ እና ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ መዲና ለማድረግ የሰነቀችውን ራዕይ የሚያንፀባርቅ፣ እንዲሁም ለትውልድ ግንባታ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ያመጣውን ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።

የዚህ ስኬት እና የከተማዋ አስደናቂ እድገት ማሳያ የሆነው ከቁጥር በላይ የሆነው መረጃ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የሕፃናት ማቆያዎች መስፋፋት ነው። 20 የመጫወቻ ስፍራዎች ብቻ የተነሳው የከተማዋ አስተዳደር በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 5 ሺህ 500 ማድረስ ችሏል። በሌላ በኩል 5 ሺህ 3 የሚሆኑት የልጆችን የዕድገት ደረጃና ሥርዓት ታሳቢ ያደረጉ የመጫወቻ ቦታዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም የሕዝብ የሕፃናት ማቆያዎች ከ11 ብቻ ተነስተው በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 100 ደርሰዋል። ይህ በተለያዩ ሞዴሎች የተደራጀው የማቆያ ቁጥር በጥቅሉ 1 ሺህ 155 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሺህ 302 ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ይህ ስኬታማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በመዲናችን የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ሕፃናትን፣ በተለይም 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ታዳጊዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለሙ አምስት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

አዲስ አበባ ዛሬ አለምን ያስገረመችው እና የትኩረት ማዕከል የሆነችው በውብ የኮሪደር ልማቷ፣ በወንዝ ዳርቻዎቿ ውበት፣ ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቿ ብቻ አይደለም። ብሩህ አእምሮ ያለው ጤናማ ትውልድ በማፍራት፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ መሆኗን በተግባር በማሳየትና የዜጎችን በተለይም የሕፃናትን ሕይወት በሚቀይር የሰብዓዊ ልማት ሥራዋ ጭምር ነው። ይህ በሰብዓዊነት እና በትውልድ ላይ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት የመንግስትን የመደመር እሳቤ መሬት ያወረደ፣ ዜጎችን በአንድነት አስተባብሮ ከተማዋን እውነተኛ የብልፅግና ተምሳሌት ያደረጋት ሲሆን፣ ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድትቀዳጅ ያስቻላት ዋነኛ ሚስጥርም ይኸው ነው።

" መሰረታዊ የግብር እና ኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን !! "በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪው የ2019 የአዲስ ዓመት  በዓል ምክንያ...
03/09/2026

" መሰረታዊ የግብር እና ኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን !! "

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪው የ2019 የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚያቀርቡ አንቀሳቃሾችና ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ።

በክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ፣ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ፣ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ፣ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን መጪው የ2019 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የባዛር መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ አምራቾችና ሸማቾች በተገኙበት ተከፍቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸው አምራቾችን በማበረታታት ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንዳለበት ገልጸው በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር በቀል ምርቶችን የሚያገኙበት ስለሆነ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የበዓል ዝግጀት የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በሚቀርበው ባዛሮች በመሄድ ምርቶቹን እንዲሸምቱ ጠቁመዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ኢንተርፕራይዞች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ እና በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመግለጽ የአዲስ ዓመት ባዛርና ኤግዚቢሽን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚያነቃቃ ፣ ነዋሪዎች በንግድ ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ በመገኘት ጥራት ያላቸውን ምርቶችን በተመጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ጥሪ አቅርበዋል።

በኤግዚቢሽን ባዛሩ ላይ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የተሳተፉ ሲሆን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ፣ በንግድ ኢንተርፕራይዝ ፣ በከተማ ግብርና ፣ በኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዞች ፣ በአገልግሎት ዘርፍ አንቀሳቃሾች የሚሳተፉ ሲሆን በርካታ ነዋሪዎች ሰዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በክፍለ ከተማው እየተካሄደ በሚገኘው ኤግዚቢሽን እና ባዛር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን የገበያ ትስስር እንደሚፈጠርላቸው ይጠበቃል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ መሠረታዊ ፍጆታ ምርቶች ፣ የከተማ ግብርና ውጤቶች ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ የእንጨት ምርቶችና የቤት ዕቃዎች የባህል አልባሳት ፣ ባህላዊ መጠጦች እና የሸክላ ውጤት ምርቶች ቀርበው እየተሸጡ ይገኛል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሆኑን ተገልጋዮች ገለፁ።ጉለሌ ወረዳረ  6 ኮሙኒኬሽ ጽ/ቤት 27/12/2018 ዓ.ም።በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር  አገልግሎቱ በ...
02/09/2026

የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሆኑን ተገልጋዮች ገለፁ።

ጉለሌ ወረዳረ 6 ኮሙኒኬሽ ጽ/ቤት 27/12/2018 ዓ.ም።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር አገልግሎቱ በተሻለ ሁኔታ መሰጠቱን፣ የአገልግሎት አሰጣጡም ፈጣንና ተገልጋይን ያማከለ መሆኑን አንዳድ ያነጋገርናቸው አገልግሎት ፈልገው የመጡ ተገልጋዮች ገልጸዋል።

ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች እንደገለፁት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የተገልጋይ እምነትን ለማጠናከር እንደሚያግዝና ጊዜአችንን በአግባቡ እንድንጠቀም አግዞናል ያሉ ሲሆን አሁን ላይ የሚታየውም ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት በቀጣይም እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻልና ተገልጋዮችን በእርካታ ማስተናገድ የተቋማት ተጠቃሚነትና እምነት እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251111221329

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gullele Woreda 6 Communication-ወ6 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share