Addis Ketema Woreda 3 Communication

Addis Ketema Woreda 3 Communication W3 press

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

06/09/2026
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ከቦሌ - መገናኛ የቪአይፒ  ኮሪደር ልማት ላይ ቦሌ ብራስ አካባቢ የሚገኝ በመንገድ መሿለኪያ ውስጥ የተፈጠረውን የውሃ መሙላት ችግር አስመልክ...
06/09/2026

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ከቦሌ - መገናኛ የቪአይፒ ኮሪደር ልማት ላይ ቦሌ ብራስ አካባቢ የሚገኝ በመንገድ መሿለኪያ ውስጥ የተፈጠረውን የውሃ መሙላት ችግር አስመልክቶ የሰጣችሁትን ጥቆማ በአክብሮት ተቀብለናል።

የተለያዮ የከተማችን ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚድያና ሌሎች መንገዶች የገለጻችሁት ጥቆማ በእርግጥም ትክክል እና ተገቢነት ያለው ነው። ለከተማችን ያላችሁን የላቀ ተቆርቋሪነት ስለሚያሳይ ከልብ እያመሰገንን።

ይህ ያልተጠናቀቀው የምድር ውስጥ መሿለኪያ ቦታ የውሃ ማቆር ችግር ያጋጠመው፤ ቀደም ሲል ስራውን ይዞት ከነበረው ኮንትራክተር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የውል መቋረጥ በማጋጠሙ እና የግንባታ መጓተት በመከሰቱ ነው።

ይህንን ያልተጠበቀ ችግር በወቅቱ በመረዳት ተቋማችን መፍትሄ ለመስጠት ሲሰራ ቆይቷል። በመሆኑም ያልተጠናቀቀውን የመሿለኪያውን የምድር ውስጥ ስራ ዳግም ለማስጀመር በፍጥነት የአዲስ ኮንትራት ግዢ ጨረታ ወጥቶ ሂደቱ ተጠናቋል።

ስለሆነም ሀሳባችሁን ለገለጻችሁ እና ላጠቆማችሁን የከተማችን ነዋሪዎች በድጋሚ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ይህንን የተጓተተ ስራ ሰርተን በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱን መልሰን ለእናንተው የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

የከተማችንን ልማት ከነዋሪዎቿ ጋር በመሆን በጋራ እናፋጥናለን!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል:: ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።

በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::

‎የእሁድ ሰንበት ገበያ ለነዋሪው የኑሮ ጫናን እንዲያቃልል ግብይቱ ላይ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ በተገቢው መልኩ የታሰበው አላማ ከግብ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። በአዲስ ከተማ ክ/ከ...
05/09/2026

‎የእሁድ ሰንበት ገበያ ለነዋሪው የኑሮ ጫናን እንዲያቃልል ግብይቱ ላይ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ በተገቢው መልኩ የታሰበው አላማ ከግብ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ላይ 3 የሰንበት ገበያዎች በተጨማሪ ገዳመ እየሱስ አካባቢ አንድ የሰንበት ገበያ መጨመሩን ሀላፊውለኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ያለማቋረጥ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም ወተት እየቀረቡ እንደሚገኙ የገለፁት የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ መርጋ ዲንቃ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ግዥፈት ለመቀነስ ከፍተኛ ትግል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‎በዋናነት የሰንበት ገበያ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት፣ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት እንዲሁም በሕገ ወጥ ነጋዴዎች የሚፈጠረውን የንግድ አሻጥር በመቅረፍ ሕጋዊ የግብይት ሥርዓትን በማስፈን ህብረተሰቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱ ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል በማለት ሀላፊወ አክለው ገልፀዋል።

የወረዳ 3 ኮሚኒኬሽን
30/12/2018

ወጣቶች ለጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለሰላም እሴት ግንባታ መሳካት ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ተገለፀ::********************  ነሐሴ 30-2018ዓምበአዲስ ከተማ ክ/...
05/09/2026

ወጣቶች ለጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለሰላም እሴት ግንባታ መሳካት ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑ ተገለፀ::
********************
ነሐሴ 30-2018ዓም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ "የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ሐሳብ ከሁሉም ወረዳዎች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል::

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው ወጣቶች ለጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ እንዲሁም ለሰላም እሴት ግንባታ መሳካት ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ገልፀው በክፍለ ከተማችን የሚገኙ ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ እቅዶች ተነድፈው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል::

የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ወጣቶች በሃገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑ ሃገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ታደሰ ወርቁ በበኩላቸው ወጣት ለሃገር ግንባታም ሆነ ለማህበረሰባዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ ከመንግስትና ህዝብ ጋር ተናቦና ተቀራርቦ መስራት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው ያለችን አንድ ሃገር በመሆኗ ለሃገራችን ሰላምና እድገት መረጋገጥ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈን መስራታችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda 3 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ketema Woreda 3 Communication:

Shortcuts

Share