Ministry of Education Ethiopia

Ministry of Education  Ethiopia This is FDRE Ministry of Education Official Face Book Page.We are promoting Educational Achievement & Attainment.

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት...
22/08/2026

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ።

በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል።

----------------------------- // -------------------------------

‎(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።


‎ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።


‎በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል።


‎በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ ፤ 583.03 በሴት ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል።


‎ በዚህ ዓመት ተማሪዎችን ካስፈተኑ ት/ቤቶች መካከል 88 ት/ቤቶች 100% ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን እና 565 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ተናግረው ከባለፈው ዓመት ምንም ካላሳለፉ 1232 ት/ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ለፈተና ከተመዘገቡ 563,960 ተማሪዎች ውስጥ 550,210 ተማሪዎች ፈተናቸውን ወስደዋል።


‎በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ እየነተገበሩ ባሉ የሪፎርም እርምጃዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የዘንድሮው ውጤት ማሳያ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
See less

ማስታወቂያበፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉትምህርት ሚኒስቴር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በፌደራል ልዩ አ...
22/08/2026

ማስታወቂያ
በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለመቀጠር የተመዘገባችሁ እና ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ለተካተተ መምህራን የጽሁፍ ፈተናው ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ፈተናው በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀርባችሁን በመምረጥ በአካል በመገኘት እንድትፈተኑ እናሳውቃለን፦
ፈተናው የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች፤
1. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 4. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ 7. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
2. ወሎ ዩኒቨርሲቲ 5. ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ 8. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
3. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 9. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ

ማሳሰቢያ፣


1. ለውድድር የተመዘገባችሁበትን መለያ ቁጥር (Reference Number) በመጠቀም የፈተና መግቢያ መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ማግኘት ትችላላችሁ፤
2. በተጨማሪም መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ለፈተና በምትመጡበት ቀን በየዩኒቨርሲቲዎቹ ከሚመደቡ የፈተና አስተባባሪዎች ዘንድ ማግኘት ይቻላል፤
3. ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው የኮምፒዊተር ኮዲንግ እና አልጎሪዝም ስልጠና ተጠናቀቀ           ------------------------...
21/08/2026

ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው የኮምፒዊተር ኮዲንግ እና አልጎሪዝም ስልጠና ተጠናቀቀ

---------------------------- // ------------------------

(ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ኮደር ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው በኮምፒዊተር ኮዲንግ፣ ፓይተን ፕሮግራሚንግ እና አልጎሪዝም ላይ ያተኮረው የክረምት ሥልጠና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ።

በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ባስተላለፉት መልዕክት ሥልጠናው መንግሥት በሁሉም ዘርፍ ሀገራችንን ለማዘመን እየሰራ ያለውን ጥረት የሚደገፍ ወቅታዊና ተገቢነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ አያይዘውም ሥልጠናው በተግባር የተደገፈ እና ተማሪዎች የማህበረሰብ ችግሮችን አጥንተው እንዲለዩና እንዲፈቱ ክህሎታቸውንና የፈጠራ ብቃታቸውን የሚያሳድግ መሆኑንም አንስተዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል ዕውቀት ዴስክ ሀላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ ሥልጠናው የተሰጠው ለአንድ ወር መሆኑን ጠቅሰው ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ 150 ከ9ኛ-11ኛ ክፍል ያሉ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደተስተፉበት ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ ሰላም መርሃ-ግብሩ ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ አካል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ኮደር ድርጅት መስራችና ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጂላኔ ኒልሰን በበኩላቸው የሥልጠናው ዓላማ በመስኩ ፍላጎትና ተሰጥኦ ያላቸውን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቸ የአልጎሪዝምና ፕሮግራሚንግ እውቀትና ከህሎታቸውን በማሳደግ በቀጣይ ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሥልጠናው በመስኩ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገራት በመጡ አሰልጣኞች የተሰጠ መሆኑንም አንስተዋል።

በማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተሳታፊዎች በንድፈ ሀሳብና በተግባር ባገኙት እውቀትና ክህሎት መሰረት በማድረግ የሰሯቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ለሁሉም ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን ስልጠናውን በላቀ አፈጻጸም ላጠናወቁ ተማሪዎች የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

ማስታወቂያ ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር  የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል። ሆኖም አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ...
21/08/2026

ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል። ሆኖም አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በመልቀቃቸውና በኢንተርኔት ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባው እስከ ነሃሴ 20/2018 ደረስ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 80 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት
✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉 በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነቶች 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች፤

መሆኑን በድጋሚ እያስታወስን በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

21/08/2026
በ2019 የትምህርት ዘመን 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገለጸ፤ወላጆች ልጆቻቸውን በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ...
19/08/2026

በ2019 የትምህርት ዘመን 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገለጸ፤

ወላጆች ልጆቻቸውን በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በማስተማር የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

--------------------------- // --------------------------

(ነሐሴ 2018 ዓ.ም) በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ። የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ትምህርት የሚጀምርባቸውን ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በ9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የሚተዳደሩት እነዚህ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸው፣ ተወዳዳሪ የሆኑ፣ ሥነ-ምግባርን የተላበሱ እንዲሁም ለሀገር የሚበቁ የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት የሚያግዙ ተቋማት መሆናቸውን ፕሮፌሰር ክንደያ አስገንዝበዋል።

ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች በተለየ መልኩ በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የተግባርና የክህሎት ትምህርት ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ተገልጿል። ይህም ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ፣ ቴክኖሎጂን በተግባር እንዲጠቀሙና ለወደፊት የሥራና የትምህርት ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል።

በተጨማሪም፣ ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የቻይንኛ ቋንቋ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንደሚሰጥ ፕሮፌሰር ክንደያ ገልጸዋል።

በመሆኑም ወላጆች፣ መምህራንና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተማሪዎች ይህንን አንደ ዋና የትምህርት እድል አድርገው እንዲጠቀሙበት የማበረታታትና የማስተባበር ሥራ እንዲያከናውኑ ፕሮፌሰር ክንደያ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባለፉት 5 ዓመታት በትምህርት ዘርፉ ከተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለፈው ዓመት ሥራ በጀመሩ 5 የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 1,250 የተሻለ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ዶ/ር ዮሐንስ ገልጸዋል።

በ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ትምህርት በሚጀምርባቸውና ባለፈው ዓመት ትምህርት በተጀመሩባቸው ትምህርት ቤቶች የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን፣ ተማሪዎች ካሉበት ቦታ ሆነው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚችሉም ዶ/ር ዮሐንስ አብራርተዋል።

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ በስፋት እንዲዳረሱ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች 13 ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
See less

Ministry of Education  Explores  Health Sciences Partnership with Apollo Hospitals                               -------...
17/08/2026

Ministry of Education Explores Health Sciences Partnership with Apollo Hospitals

--------------------- // --------------------

Aug. 17, 2026 — The Ministry of Education held discussions with a delegation from Apollo Hospitals International on potential collaboration in medical education, clinical training, and health sciences capacity development.

H.E. Ato Kora Tushune, state minister for higher education, highlighted the potential for collaboration between the Ministry and Apollo Hospitals at the national level, particularly in transferring knowledge and expertise in clinical education and training, hospital leadership, and the development of supporting training facilities. He also emphasized the importance of identifying Ethiopia's capacity gaps in clinical training, medical specialties and super-specialties, as well as biomedical engineering, which he identified as an emerging priority area for specialized training and residency program development.

The Apollo delegation included Dr. Rahul Menon, Senior Vice President of Apollo International; Mr. Abu Bakr Siddique, General Manager of Apollo International Patient Services; and Dr. Zelalem Molla, CEO of Washington Health Care.

Ato Kora noted that discussions with Apollo first began three years ago and cited Ethiopia's existing partnership with nine Indian Institutes of Technology (IITs), under which around 250 PhD students are sent annually to partner universities in India. Building on this experience, he suggested that the two sides begin by identifying areas where Ethiopia's capacity needs to be strengthened.

Twenty-six teaching hospitals currently operating in Ethiopia, the state minister noted the potential for joint programs between Ethiopian and Indian universities to strengthen medical education and specialty training capacity across the sector.

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች የውድድር ምርጫን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያየመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች አሰያየም በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ከ...
17/08/2026

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች የውድድር ምርጫን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች አሰያየም በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ https://sl1nk.com/9npn2w7 ሊንክ በመግባት ሙሉ መመሪያውን ማውረድ ይችላሉ።

ማስታወቂያየትምህርት ሚኒስቴር ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች (Special Boarding Schools) ርዕሰ መምህራን ለመቅጠር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም. በበይነ መረብ (Online) ባወጣው ...
14/08/2026

ማስታወቂያ

የትምህርት ሚኒስቴር ለልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች (Special Boarding Schools) ርዕሰ መምህራን ለመቅጠር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም. በበይነ መረብ (Online) ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሰ አመልካቾች ለፈተና የተመረጣችሁ ስለሆነ ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 በትምህርት ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት አዳራሽ ተገኝታችሁ የጽሑፍ ፈተና እንድትወስዱ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፦ ተወዳዳሪዎች ለፈተና ስትመጡ የሥራ ልምድ መረጃ፣ ዋናውን የትምህርት ማስረጃ (Original) እንዲሁም በቅጥር ማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶች ዋናውንና ኮፒውን (Original & Copy) በተጨማሪም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሰደግ የሚረዳ የኣይሲቲ ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፤          ------...
12/08/2026

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሰደግ የሚረዳ የኣይሲቲ ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፤

---------------------------- // -----------------------------

(ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኔስኮና የጃፓን መንግሥት ጋር በመተባበር የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሰደግ የሚረዳ ተንቀሳቃሽ የኣይሲቲ ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ለሚመለከታቸው ተቋማት አስረክቧል።

በዚሁ ወቅት በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ተ/መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ አሰግድ ምሬሳ ባስተላለፉት መልዕክት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚሰሩ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ለማሰደግ የሚረዳ የኣይ ሲቲ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክትን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች 35 የሚደርሱ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እና በመምህራን ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ያሉ 5 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በሁሉም ዘርፍ ሀገሪቷን ለማዘመን እና የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓትን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየሠራቸው ላሉ ሥራዎች አዎንታዊ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑንም አንስተዋል።

ወ/ሮ አሰግድ አክለውም የተሰጡ የኣይ ሲቲ ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የሚመለከታቸው ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የጃፓን ኤምባሲ አንደኛ ጸሃፊ ሚስ ሳሱኪ ፉካኢ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ እየተከናወነ ያለው የጃፓን መንግሥት እና የዩኔስኮ አለም አቀፍ የአፍሪካ የአቅም ግንባታ ተቋም በ2025 በተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት መሠረት መሆኑን ገልፀዋል።

ሚስ ሳሱኪ አክለውም ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለትግበራ ምዕራፍ መብቃቱ ጃፓን ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ጥረት ለመደገፍ የማያወላውል ቁርጠኝነት እንዳላት ማሳያ መሆኑንም አንስተዋል።

የዩኔስኮ አለም አቀፍ የአፍሪካ አቅም ግንባታ ተቋም ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት ሚስተር ሳሊኡ ደግሞ በዚህ ፕሮጀክት የተገኘው ቴክኖሎጂ ከተለመደው የሥልጠና አሰጣጥ በተለየ ተለማጭ፣ ምቹና መምህራን ለሚያጋጥማቸው ችግሮች ምላሽ የሚስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚስተር ሳሊኡ አያይዘውም ተቋማት ቴክኖሎጂውን በሚገበ መጠቀም እንዲችሉ ከሚመለከታቸው መምህራን ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ ቴክኒካል ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም በተግባር የተደገፈ ሥልጠና የተሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።

Address

Arat Kilo/Patriot Square
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30

Telephone

+251111565529

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Education Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Education Ethiopia:

Shortcuts

Share