Documents Authentication and Registration service

Documents  Authentication and Registration service ምንግዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከተቋሙ ሰራተኞቸ ጋር ውይይት ተካሄደነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምየሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አ...
05/09/2026

የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከተቋሙ ሰራተኞቸ ጋር ውይይት ተካሄደ

ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ሠራተኞች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ በሰጡት መልዕክት፣ ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አበረታች አፈጻጸም ማስመዝገቡን ጠቅሰው፣ የተመዘገበው ውጤት ለ2019 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ጠንካራ መሠረት እንደሚሆን ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ለተቋሙ ስኬታማ አፈጻጸም የሠራተኞች አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን በመጥቀስ፣ ሠራተኞችን አመስግነዋል።በውይይቱም የሰነድ ማረጋገጥና ምዝገባ፣ የሕግ ጉዳዮች፣ የሰነድ አስተዳደር እና የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሥራ ክፍሎች በ2018 በጀት ዓመት ያከናወኗቸውን ተግባራትና ያስመዘገቧቸውን ውጤቶች አቅርበዋል።

በተጨማሪም፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመከላከል ተአማኒነቱ የተጠበቀ ሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ፣ በተለያዩ ስልጠናዎች የሠራተኞችን አቅም ማጎልበት እንዲሁም በመሶብ የአንድ አገልግሎት ማዕከላት የሚሠሩ ሠራተኞች የተቋሙን መልካም ስምና ገጽታ በመጠበቅ የተቋሙ አምባሳደሮች ሆነው መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል።

ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገበውን ስኬት በማስቀጠል፣ በ2019 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ደረጃን የበለጠ ለማሻሻል በተሰማሩበት የሥራ መስክ በትጋትና በኃላፊነት እንደሚያገለግሉ ገልጸዋል።

የአገልግሎቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆችና የማኔጅመንት አባላትም በድሬዳዋ ከተማ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል የትብብር ውይይት ተካሄደ::ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ምየሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ ከአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ የ...
04/09/2026

ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል የትብብር ውይይት ተካሄደ::

ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ ከአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ የውጭ ሀገር ወንጀል መርማሪ መኮንን ሚስተር አሮን ክሊንገር ጋር ሀሰተኛ ሰነዶችን በመከላከልና በመለየት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም ሀሰተኛ ሰነዶችን በተሻለ ሁኔታ ለመከላከል፣ በተቋማት መካከል ትብብርን ለማጠናከር እና ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች በመቅሰም የተሻለ አሰራር ለመዘርጋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

አሜሪካ ኤምባሲም በሰነድ ማረጋገጫና ምዝገባ ዘርፍ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ሀሰተኛ ሰነዶችን በቀላሉ መለየት እንዲችሉ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ከመስጠት ባሻገር፣ UV Light ጨምሮ የሰነድ ምርመራ መሳሪያዎችን በመደገፍ በዘርፉ የተቋሙን አቅም ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።

የሀሰተኛ ሰነዶችን መከላከል፣ የሰነዶችን ታማኝነት ማረጋገጥ!

የአገልግሎቱ የማኔጅመንት አባላትና የቅርንጫፍጽህፈት ቤቶች ስራ አስኪያጆች በአመራር ልህቀት ዙሪያ ስልጠና ወሰዱነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ምየአገልግሎቱ የሥራ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስ...
02/09/2026

የአገልግሎቱ የማኔጅመንት አባላትና የቅርንጫፍጽህፈት ቤቶች ስራ አስኪያጆች በአመራር ልህቀት ዙሪያ ስልጠና ወሰዱ

ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የአገልግሎቱ የሥራ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል በተለያዩ የአመራር ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሦስት ቀናት ስልጠና ወሰዱ።

ከነሐሴ 25 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና የአእምሮ ውቅር (Mindset)፣ ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence)፣ የደንበኞች አገልግሎት፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና ዲጂታል መር አመራር (Digital Leadership) በዋናነት ተዳሰዋል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ እንደገለጹት፣ በየቀኑ ከ6,000 በላይ ዜጎችን የሚያስተናግድ ተቋም እንደመሆኑ፣ አመራሮች በየዕለቱ የሚወስኗቸው ውሳኔዎች የዜጎችንና የሀገርን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም በማስከበር ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው።

በመሆኑም የአመራር አባላት እውቀታቸውን፣ ልምዳቸውንና የአመራር ክህሎታቸውን በተከታታይ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ፣ ይህ ስልጠና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።

ስልጠናው በነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሲጠናቀቅ፣ ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት ተቋሙ አገልግሎቶቹንና አሰራሩን በፍጥነት ወደ ዲጂታል ሥርዓት እያሸጋገረ በመሆኑ፣ የዘመኑን የዲጂታል እውቀትና የሥራ ሥነ-ምግባር ለማዳበር ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀሚድ ኪኒሶ በበኩላቸው፣ ስልጠናው “ዲጂታል 2030” ራዕይን እውን ለማድረግ የሚያግዝ፣ ወቅቱን የጠበቀና ተግባራዊ ጠቀሜታ ያለው ስልጠና መሆኑን ገልጸው፣ ለአፍሪካ አመራር ልህቀት ማዕከል ምስጋና አቅርበዋል።

የ2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዋና የሥራ አፈፃፀም ስኬቶች  በጥቂቱ:-የቀጠለ... ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም 1. ሀገራዊ ወጥ አሰራርና ሀገራዊ የመረጃ ቋት ...
30/08/2026

የ2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዋና የሥራ አፈፃፀም ስኬቶች በጥቂቱ:-

የቀጠለ...

ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

1. ሀገራዊ ወጥ አሰራርና ሀገራዊ የመረጃ ቋት ከመፍጠር አኳያ ክልሎችን በመደገፍና በማስተባበር, የተቋማችንን ዳታ ቤዝ እና የDARS system በነፃ እንዲጠቀሙ በማድረግ እስከ አሁን 9 ክልሎች አሰራራቸውን ዲጅታላይዝ አድርገው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን በክልሎች በተከፈቱ የመሶብ አንድ ማእከል ውስጥም አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል;
2. ከመደበኛ ሥራ ሰዓት ውጭ የምሳ ሰዓት, ምሽትና ቅዳሜ ሙሉ ቀን አገልግሎት ስሰጥ ቆይቷል;
3.ተጋልጋዮች ተገማች በሆነ ሰዓት አገልግሎት እንድያገኙ በኦንላይን የወረፋ ማስያዣ ስርዓት እንዲጠቀሙ በማድረግ የተገልጋይ እንግልት መቀነስ ተችሏል;
4. ፋይዳ መታወቂያ ፣ የደህንነት መለያ ያላቸው ወረቀቶች ( security feature printings) ኤሌክትሮኒክ ማህተም እና የሲስተም ትስስር በመፍጠር የተቋሙ ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖ የቆየውን ሀሰተኛ ሰነዶችን መቀነስ ተችሏል::
5. በUnified MESOB, በመሶብ የባስ ላይ አገልግሎት ቀዳሚ በመሆን አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን SMART MESOB ላይ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
6. በመሶብ አገልግሎት ምክንያት ከነበሩት 17 ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች 5ቱ ታጥፈው ሰራተኞችን ወደ መሶብ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
7. DARIS ሲስተም ላይ ማሻሻያ በማድረግ ወረቀት አልባ አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን አገልግሎቱ ክልሎችንም እንዲያካትት የቋንቋ ብዘሃነትን እንድያስተናግድ ተደርጓል፡፡
8. የመረጃ አገልግሎት ለፌዴራልም ሆነ ለክልል ፍ/ቤቶች፣ ለአቃብያን ህግ፣ ለፖሊስ፣ለደህንነት ተቋማት፣ለሚመለከታቸው የንግድ ድርጅቶች/ ኩባንያዎች/ እና ተገልጋይ ግለሰቦች፣ ለጥናትና ምርምር ተቋማት፣ ለተሞክሮ ለሚፈልጉ ተቋማት በመስጠት ለህግ ማስከበር እና ለፍትህ መረጋገጥ የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል;
9. ከ1938 ዓ.ም ጀምሮ የቆዩ ሰነዶችን የያዘ ተቋም እንደ መሆኑ መጠን እስካን በማድረግ ድጅታላይዝ ለማድረግ ከኢኖቨሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በተገኘ ድጋፍ በቅርቡ ሥራው ተጀምሮ 152, 734 ኮፒ ሰነዶች ዲጂታላይዝ ተደርጓል፡፡ ሥራው ቀጣይነት እንዲኖረው በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
10. የሲስተምና የሰነድ መረጃ ደህንነቱ እንዲጠበቅ INSA በየጊዜው ኦዲት እያደረገና እየተከታተለ የሚገኝ ሲሆን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የ data Storage & Redundancy service ድጋፍ አድርጓል
11.እየተገነባ ያለው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ( 4B+G+M +22) የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ ሲሆን በተያዘው ጊዜ ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡

የ2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዋና የሥራ አፈፃፀም ስኬቶች  በጥቂቱ ነሃሴ 23 ቀን 2018  ዓ.ም1. ወደ 1 ትሪሊየን  የምሆን በገንዘብ የሚገለጹ ውሎችን በማ...
29/08/2026

የ2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዋና የሥራ አፈፃፀም ስኬቶች በጥቂቱ

ነሃሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም

1. ወደ 1 ትሪሊየን የምሆን በገንዘብ የሚገለጹ ውሎችን በማ ጽደቅ በሀገራችን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የጎላ ድርሻ አበርክቷል፡፡

2. 1,074,472 የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ጉዳዮችን ለማስተናገድ አቅዶ 1,051,253 ጉዳዮችን አስተናግዷል ;(%)

3. ሰነድ የተረጋገጠላቸው 1,868,741 ተገልጋዮች ያስተናገደ ሲሆን በቀን በአማካይ 6000 ተገልጋዮችን አስተናግዷል;

4. ገቢ 4 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 4.5 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል;። በዚህም የእቅዱን 113.7% አሳክቷል

5. በ መገናኛ ፣ ቦሌ ፣ካዛንቺስ እና ሜክሲኮ በሚገኙት 4 ልዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች 179, 106 ጉዳዮች የተስተናገዱ ሲሆን 1.2 ቢልዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

6. በ13 የመሶብ ማዕከላት ( ፌዴራል 1, አዲስ አበባ መሶብ 11 እና ድሬደዋ 1) 125 ሰራተኞችን በመመደብ 54,768 ጉዳዮችን ለ82,803 ተገልጋዮች ተደራሽ በማድረግ 216,259,668 ብር ገቢ ሰብስቧል ፡፡

7. ዲጂታል አገልግሎት ተደራሽ ለማድርግ በተሰጠው ትኩረት ተገልጋይ በአካል ሳይቀርብ(Virtual by telesign) በተወሰኑ ጉዳዮች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ፡፡

8. ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በDigital MOFA 10,149 ጉዳይ ማስተናገድ ተችሏል ;

9. ከ44 ፋይናንስ እና ልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂ የሲስተም ትስስር በመፍጠር የተቀላጠፈ እና ከማጭበርበር የፀዳ አገልግሎት መስጠት ሚስችል አሰራር ተዘርግቷል፡፡

10. ….ይቀጥላል::

የውክልና ሥልጣን ቀሪ ማድረጊያ አገልግሎት  ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመሁኔታዎች  ነሃሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የውክልና ስልጣን  ቀሪ ማድረግ  ማለት ወካይ የሰጠውን የውክልና ስልጣን ...
28/08/2026

የውክልና ሥልጣን ቀሪ ማድረጊያ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመሁኔታዎች

ነሃሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም

የውክልና ስልጣን ቀሪ ማድረግ ማለት ወካይ የሰጠውን የውክልና ስልጣን ሲሽር ወይም ተወካይ የተሰጠውን የውክልና ሥልጣን ሲተው ነው፡፡

ይህንን የውክልና ሥልጣን ቀሪ ማድረጊያ አገልግሎት ለማግኘት የሚከተሉት ሁኔታዎችና ማስረጃዎች በትክክል መሟላት አለባቸው

ሀ. የመጀመሪያው ዋና የውክልና ሰነድ መቅረቡንና ከተቋሙ የመረጃ ቋት በማጣራት አለመሻሩን፣

ለ. ከብዙ ወካዮች አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ለመሻር ከፈለገ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2228 (2) ድንጋጌ መሠረት ተወካዩን ብቻውን የሚሽርበትን በቂና ትክክለኛ ነው የሚለውን ምክንያት በውክልና ሰነዱ ላይ በማስፈር ያቀረበ መሆኑን፣

ሐ. የውክልና ሥልጣን በመሻርም ሆነ በመተው ጊዜ ሻሪው ወይም ተወካይነቱን የሚተወው ተወካይ የመሻሪያ ወይም የመተው ሰነዱን ለተወካዩ ወይም ለወካዩ የሚያሳውቅ መሆኑን በመሻሪያ ሰነዱ ላይ በትክክል መግለጹን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

27/08/2026
እንኳን ለ1501ኛዉ የመዉሊድ በዓል አደረስዎ። በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንልዎ እንመኛለን። የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣  ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!
25/08/2026

እንኳን ለ1501ኛዉ የመዉሊድ በዓል አደረስዎ። በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣
ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

ከፌደራልና ከአዲስ አበባ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት  አስተባባሪዎችና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዴስክ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ:: ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ምየሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ...
24/08/2026

ከፌደራልና ከአዲስ አበባ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪዎችና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዴስክ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ::

ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የፌደራልና አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አስተባባሪዎች፣ የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰነድ አስተዳደር እንዲሁም የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ዴስክ ኃላፊዎች ጋር የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸምና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዱ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ እንደገለጹት የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ አስተባባሪዎቹም ሆኑ ዴስክ ሀላፊዎቹ ስራውን በቅርበት የሚመሩና ለባለሙያው ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርጉ እንደመሆናቸው ሰነድን አረጋግጦ ከመመዝገብ እንዲሁም ከማስተዳደር አኳያ ተዓማኒነት ያለው አገልግሎት በጥራትና በቅልጥፍና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የስራ አቅጣጫ ለመስጠት መሆኑን አስታወቀዋል፡፡

ተቋሙ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ድሬ መሶብን ጨምሮ በሁሉም የአዲስ መሶብ የአንድ አገልገሎት ማእከል ሰራተኞችን አሟልቶ በመመደብ አስራአምስት ዲጂታል አገልግሎቶችን እየሰጠ ሲሆን በቀጣይ ሁሉንም አገልግሎቶች በማእከሉ ተዳራሽ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሠራ መሆኑ በዉይይቱ ተመላክቷል።

የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ሆነ የ2019 እቅድ ከዚህ ቀደም ለተቋሙ ለካውንስል አባላት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደበት መሆኑ ይታወሳል፡፡

የአክሲዮን ማህበራትን  በተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ  ነጥቦች ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ምከሃምሳ በላይ አባላት ያላቸው የአክስዮን ማህበራት በተቋሙ ቀርበው ድንገተኛ እና መደበኛ የባ...
20/08/2026

የአክሲዮን ማህበራትን በተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች

ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

ከሃምሳ በላይ አባላት ያላቸው የአክስዮን ማህበራት በተቋሙ ቀርበው ድንገተኛ እና መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎችን በተመለከተ፣

1. በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ ጉባኤ ሰነድ፣

2. ስብሰባው በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በህጉ መሠረት መጠራቱን የሚገልጽ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡

3. ቃለጉባኤው የማህበሩ ሙሉ ስም፣ ስብሰባው የተደረገበት ቦታ፣ ስብሰባው የተደረገበት ቀን፣ በስባሰባው ላይ የተገኙ አባላት ዝርዝር፣ በስብሰባው ላይ ያልተገኙ አባላት ዝርዝር፣ የሁሉም አባላት የአክስዮን ድርሻ መጠን፣ የስብሰባው አጀንዳዎች፣ የውሳኔው ይዘት መግለጽ ይኖርበታል፡፡

4. በድንገተኛም ሆነ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተገኙ አባላትን የሚገልጽ የአቴንዳስ ሽት ከቃለ ጉባኤው ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

5. የድንገተኛም ሆነ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ቃለጉባኤዎች በተለያዩ ሰነዶች ተዘጋጅተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. የአባላቱ ቀጥር ከ50 በላይ የሆነ አክሲዮን ማህበር ተቋሙ ሰነድ አረጋጋጭ ባለሞያ እንዲላክለት ሲጠየቅ ከደብዳቤ ጋር ስብሰባውን ማን እንደጠራ፤ የስብሰባውን አይነት ድንገተኛ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ በሚል መለየት፤ ስንተኛ ጥሪ እንደሆነ፤ ጥሪ ያደረገበትን መንገድ እንዲሁም አጀንዳዎቹን አስቀድሞ ከደብዳቤው ጋር ሊገለፅ ይገባል፡፡

7. የአክሲዮን ማህበራት መመስረቻና መተዳደሪያ ደንባቸው ድንገተኛ ወይም መደበኛ ጠቅላላ ጉበኤዎችን የሚጠሩበትን የጥሪ መንገዶች ወስነው ስለመግለጻቸው ማረጋገጥ ይገባል፡፡

8. በአክሲዮን ማህበር ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ከጉባኤው ስልጣን ውጪ መሆን አለመሆናቸውን በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡

9. አክሲዮን በሽያጭ ከማህበሩ አባል ውጭ ለሆነ ሰው ሲዘዋወር በቅድሚያ ከማህበሩ አባላት በቀዳሚነት የመግዛት መብት የነበረባቸው ባለአክሲዮኖች በሰነዱ ላይ በመፈረም የተስማሙ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገባል፡፡

10. በጥሬ ገንዘብ ካፒታልን ካሳደጉ በኋላ ይህንን ለማህበሩ የገባውን ገንዘብ በዓይነት መዋጮ ለመለወጥ የሚቀርብ ቃለጉባኤ የህግ መሰረት ስለሌለው ሊመዘገብ አይገባም፡፡ በዓይነት የገባውንም መዋጮ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥሬ ገንዘብ መለወጥ አይቻልም፡፡

11. የንግድ ማህበራት በቃለ ጉባኤ የሚያደርጓቸው ማሻሻያዎች ሰነዱ ከፀደቀበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት ወር ድረስ ካላስመዘገቡ ተቋሙ አገልግሎት አይሰጥበትም፡፡

12. የንግድ ማህበራት የማፍረስ ውሳኔ ከወሰኑ በኋላ ማህበሩን በነበረበት ለማስቀጠል ከፈለጉ

-ዋና ምዝገባና የንግድ ፈቃድ፣
-ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ማህበሩ ያልተሰረዘ ለመሆኑ፣
-ከገቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ ሊቀርቡ ይገባል፡፡

Address

Addis Ababa
29935

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Documents Authentication and Registration service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Documents Authentication and Registration service:

Share